Ministry of Urban and Infrastructure 🇪🇹🇪🇹
9.9K subscribers
18.4K photos
269 videos
16 files
507 links
This is the official Telegram page of Ministry of Urban and Infrastructure
Download Telegram
ለዘርፉ የልማት ስራዎች እያደረገ ያለውን ድጋፍ አጠናክሮ እንደምቀጥል የዓለም ባንክ አስታወቀ

የዓለም ባንክ የመሠረተ ልማት ዘርፍ ሪጂናል ዳይሬክተር ኤሪክ ማግነስ በዘርፍ የልማት ስራዎች ዙሪያ ከሚኒስቴሩ አመራሮች ጋር መክረዋል

አዲስ አባባ፣ ነሐሴ 18 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ) የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር እና የዓለም ባንክ በዘርፉ ፕሮጀክቶች  አሁናዊው ሁኔታ፣ ያጋጠሙ ችግሮች እና በቀጣይም  በቅንጅት መስራት በሚቻልባቸው  ጉዳዮች ዙሪያ  ነው የተወያዩት፡፡

የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን የዓለም ባንክ  በዘሪፉ የልማት ስራዎች እያበረከተ ያለውን ድጋፍ አድንቀው ይሄው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል እምነት እንዳላቸው ገልጸዋል። አሁን ላይ ከተሞች ከመቸውም ጊዜ በላይ በመንግሥት ከፍተኛ ሪብርብ ምቹ
የመኖሪያ እና የመሥሪያ ማዕከላት ለማድረግ እየተሰራ ነው ብለዋል።

በዓለም ባንክ ድጋፍ እየተሰራ ያሉ ፕሮጀክቶች ዝርዝር አፈጻጸም እና ቀጣይ ባንኩ ድጋፍ ማድረግ በሚገባቸው ጉዳዮች ዙሪያ በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ዋና አማካሪ አቶ ተስፋዬ ወ/ሚካኤል በዝርዝር ቀርቦ ውይይት ተደርጓል ፡፡  

በዓለም ባንክ የመሰረተ ልማት ዘርፍ ሪጂናል  ዳይሬክተር  ኤሪክ ማግነስ  ባንኩ በኢትዮጵያ  ትልልቅ የመሰረተ ልማት ግንባታዎች መጠነ ሰፊ ድጋፍ እያደረገ እንደሆነ ገልጸው ይሄው ተጠናክሮ ይቀጥላል ብለዋል። በዝርዝር በቀረበው ሰነድ መሰረት ዘሪፉን ለማገዝ ባንኩ ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል።
የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር አመራሮች አዲስ በጸደቁ ፖሊሲዎች ዙሪያ ውይይት አደረጉ

አዲስ አባባ፣ ነሐሴ 23 ቀን 2018 ዓ/ም (ከመልሚ)  የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር  የከተማ ልማት ፖሊሲ፣ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ እና የቤት ልማት ፖሊሲ መጽደቃቸውን ተከትሎ የጋራ ግንዛቤ እንዲኖር የሚያስችል የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አመራሮች ውይይት አድርገዋል፡፡

ፖሊሲዎቹ በ2030 የኢትዮጵያ ከተሞች ለሀገራዊ እድገትና ብልጽግና ስኬት መሪ ሚና ያላቸው፣ ተወዳዳሪ፣ ዘላቂ፣ ምርታማና ለስራና ለኑሮ ምቹ ሆነው ማየትን ያለሙ ናቸው፡፡

መድረኩን በንግግር ያስጀመሩት የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን የከተሞች እድገት በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ መምጣቱን እና ከላይ እስከታች ያለው አመራር ትኩረት ሰጥቶ ከመደገፉ ጋር ተያይዞ ፖሊሲ ማሻሻልና ማዘጋጀት ውጤታማ ስራ ለመስራት ያስችላል ብለዋል፡፡

የከተማ ልማት ፖሊሲ ዓላማው አገልግሎት አሰጣጥን በማዘመን ከተሞች ውብና ጽዱ፣ ለነዋሪዎቻቸው ምቹ እንዲሆኑ ማድረግ፣ የዜጎችን ኑሮ ለማሻሻልና የስራ እድል የሚፈጥሩ ከመሆኑም ባሻገር ፈጣን እና ተደራሽ አገልግሎት እንዲኖር የሚያደርግ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡

በከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር የፖሊሲና ስትራቴጂ ጥናትና ምርምር  ሾል አስፈጻሚ  አማን አሰፋ(ዶ/ር) አዲሱ የከተማ ልማት ፖሊሲ ዓላማ ከተሞች በፕላን የሚመሩ፣ በመሰረተ ልማት የተቀናጁ፣ ቀልጣፋና ዘላቂ ልማት የሚረጋገጥባቸው አካታች ኢኮኖሚና ማህበራዊ ብልጽግና እንዲኖራቸው ማድረግ ታሳቢ ያደረገ ነው ብለዋል፡፡

በተመሳሳይ የኮንስትራክሽን ኢንዱስትሪ ፖሊሲ እና የቤት ልማት ፖሊሲ በዝርዝር ቀርበው ሰፊ ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡
❤1