ኢትዮጵያ በከተማና ከትመት፣ በከተማ ፕላንና በቤቶች ልማት ዙሪያ ለናሚቢያ ልምዷን አካፈለች
የከተማና መሠረተ ልማት ሚኒስቴር ሚ/ድኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን የናሚቢያን የከተማና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ልዑክ በጽ/ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ
አዲስ አበባ፣ ነሐሴ 13 ቀን 2018 ዓ.ም (ከመልሚ) የናሚቢያ የከተማና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ክቡር ሳንኳዋሳ ጀምስ የተመራ ልዑካን ቡድኑ ከከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ጋር በከተሜነትና ክትመት፣ በከተማ ፕላን እና በቤት ልማት ዙሪያ የልምድ ልውውጥ አድርገዋል፡፡
ልምድ ልውጡን አስመልክተው የከተማና መሰረተ ልማት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ፈንታ ደጀን እንዳሉት የኢትዮጵያና የናሚቢያ ግንኑነት ታሪካዊ መሆኑን ገልጸው በቅርብ ዓመታት ኢትዮጵያ ዘርፈ ብዙ የትብብር ስራዎችን ከግምት ውስጥ በማስገባት እየሰራች መሆኑን ተናገረዋል።
በተለይ በአየር ትራንስፓርት አገለግሎት የተደረሰው ስምምነት ትለቁና ዋነኛው መሆኑን ገልጸዋል ክቡር ሚኒስትር ድኤታው፡፡
በኢኮኖሚ፣ በግብርና፣ በንግድ፣ በቱሪዝምና በኢንቨሰትመንት እየታያ ያለውን መነቃቃት በማስፋት የሁለትዮሽ የንግድ ለውውጥን ከግምት በማስገባት ለጋራ ብልጽግና መስራት እንደሚገባ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ፈንታ አስገንዝበዋል፡፡
የከተማ የተቀናጀ ፕላንና ተመጣጣኝ የሆነ የቤት ልማት ላይ እየታየ ያለውን ተሰፋ ሰጪ ዕድገት ለናሚቢያ የልዑካን ቡድን አባላት ስናጋራ እጅግ በጣም በደስታ ነው ብለዋል፡፡
የናሚቢያ የከተማና ገጠር ልማት ሚኒስቴር ሚንስትር ክቡር ሳንኳዋሳ ጀምስ በበኩላቸው በኢትዮጵያ በከተማ ፕላንና በቤቶች ልማት ብሎም በከተማ ውበትና ጽዳት ባዩ ት ነገር መደሰታቸውን ገልጸው፣ ለዑካን ቡድናቸው የቀሰሙትን ተሞክሮ በሀገራቸው ላይ ወስደው እንደሚተገብሩት ያላቸውን ተስፋ ገልጸዋል፡፡
ከተሜነትና ክትመት በኢትዮጵያ፣ የከተማ ፕላን እና የቤቶች ልማት ያለበት ነባራዊ ሁኔታ በተሞክሮነት ለናሚቢያ የልዑካን ቡድን አባላት ቀርቧል።

የኢትዮጵያ የመንገድ መሠረተ ልማት እመርታና የመፃኢ እድገት አቅጣጫ
የአንድ ሀገር የኢኮኖሚ ዕድገት፣ የማህበራዊ ትስስር እና የለውጥ ደረጃ ከሚለካባቸው ዋነኛ መስፈርቶች አንዱ የመንገድ መሠረተ ልማት ዝርጋታ፣ ስርጭትና ጥራት ነው።
መንገድ የሀገር የደም ስር ነው ሲባል ማጋነን አይደለም፤ ያለ መንገድ ቀጣይነት ያለው ኢኮኖሚ፣ ልማትና ዕድገት ሊታሰብ አይችልም።
የመንገድ መሠረተ ልማት በጥራትና በብዛት መኖር የዜጎችን እንቀስቃሴ ከማቀላጠፉ ባሻገር፣ ምርቶችና ጥሬ ዕቃዎች በፍጥነት ወደ ማምረቻዎችና ገበያዎች እንዲደርሱ በማድረግ ረገድ ቁልፍ ሚና ይጫወታል።
ኢትዮጵያ ላለፉት አስርት ዓመታት፣ በተለይም ባለፉት ስምንት ዓመታት፣ ለመንገድ መሠረተ ልማት ልዩ ትኩረት በመስጠት ክልሎችን እርስ በርስ፣ ዋና ከተማውን ከክልሎች እንዲሁም ዞኖችን ከዞኖች የሚያስተሳስሩ መጠነ ሰፊ ሥራዎችን ስታከናውን ቆይታለች።
በ2010 ዓ.ም የነበረው የ126 ሺህ 773 ኪሎ ሜትር አጠቃላይ የመንገድ ሽፋን በ2018 ዓ.ም አጋማሽ ወደ 180 ሺህ 232 ኪሎ ሜትር አድጓል። ይህም ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ብቻ ከ53 ሺህ ኪሎ ሜትር በላይ አዳዲስ መንገዶች መገንባታቸውን ያሳያል።
በቀጣዮቹ አምስት ዓመታት ደግሞ ይህንን አኃዝ ወደ 245 ሺህ ኪሎ ሜትር ለማድረስ በዕቅድ እየተሰራ ይገኛል። በ2010 ዓ.ም ከ30 ቢሊየን ብር በታች የነበረው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር በጀት በ2019 ዓ.ም ወደ 121 ነጥብ 8 ቢሊየን ብር በማደግ ከአራት እጥፍ በላይ ጭማሪ አሳይቷል።
ተቋሙ በየዓመቱ ከሀገሪቱ አጠቃላይ የካፒታል በጀት 21 ነጥብ 4 በመቶ ድርሻ በመውሰድ ቀዳሚው የመሠረተ ልማት ተጠቃሚ ለመሆን ችሏል።
የ75 ዓመት ዕድሜ ባለጸጋው የኢትዮጵያ መንገዶች አስተዳደር፣ ሀገራዊ የንግድ ኮሪደሮችን የሚያጠናክር ጠንካራ የፌዴራል የመንገድ መረብ በመዘርጋት ላይ ይገኛል። ባለፉት ስምንት ዓመታት ውስጥ ብቻ 182 ፕሮጀክቶች ወደ ግንባታ የገቡ ሲሆን፣ 71 ግዙፍ ፕሮጀክቶች ግንባታቸው ተጠናቆ ለትራፊክ ክፍት ሆነዋል።
የሀገሪቱን የንግድና የኢንዱስትሪ ማዕከላት የሚያገናኙ እንደ አዲስ አበባ-አዳማ፣ ሞጆ-መቂ-ባቱ-አርሲ ነገሌ እና ድሬዳዋ-ደዋሌ ያሉ የፍጥነት መንገዶች ተገንብተው አገልግሎት እየሰጡ ይገኛሉ።
ከለውጡ በፊት የነበረው የፍጥነት መንገድ ሽፋን 84 ነጥብ 7 ኪ.ሜ ብቻ የነበረ ሲሆን÷ በአሁኑ ወቅት ተጨማሪ የፍጥነት መንገዶች ተጠናቅቀው ለአገልግሎት በቅተዋል።
በቀጣይም ከአዲስ አበባ ወደ ደሴ፣ ጅማ፣ ደብረ ማርቆስ እና ነቀምቴ የሚዘልቁ አራት አዳዲስ የፍጥነት መንገዶችን ለመገንባት የአዋጭነት ጥናት ተጠናቅቋል።
በሚቀጥሉት 10 ዓመታት የሀገሪቱን የፍጥነት መንገዶች ርዝመት ወደ 1 ሺህ 600 ኪሎ ሜትር ለማድረስ ታቅዷል። ከዚህ በተጨማሪ ኢትዮጵያን ከጎረቤት ሀገራት ጋር የሚያገናኙ እና ቀጣናዊ ትስስርን የሚያጠናክሩ ግዙፍ የመንገድ ፕሮጀክቶች ተገንብተው ለኢኮኖሚው ከፍተኛ አገልግሎት በመስጠት ላይ ናቸው።
አዳዲስ መንገዶችን ከመገንባት ባሻገር የነበሩትን ደረጃ ማሻሻል፣ መጠገን እና የዕድሜ ዘመናቸውን ማራዘም የመንገድ አስተዳደሩ ዋነኛ ትኩረት ነው።
በተለይም የከባድ ተሽከርካሪዎችን የጭነት መጠን ለመቆጣጠር የሚያስችሉ የሚዛን ጣቢያዎች ተስፋፍተዋል፤ ያሉትም ዲጂታላይዝ ተደርገዋል። ይህ አሰራር የተሽከርካሪዎችን ክብደት ከሰው እጅ ንክኪ ነፃ በሆነ መንገድ በመመዝገብ፣ የአሰራር ግልጽነትን ለማስፈንና በከባድ ጭነት ምክንያት የሚደርስ የመንገድ ብልሽትን በመቀነስ ረገድ ከፍተኛ አስተዋጽኦ አበርክቷል።
በጥቅሉ፣ የገጠርና የከተማ ትስስርን በማጠናከር፣ የኢኮኖሚ ኮሪደሮችን በማሳደግና ሀገር አቀፍ ልማትን በማፋጠን ረገድ የመንገድ መሠረተ ልማት ዝርጋታው ኢትዮጵያን ወደ ተሻለ የዕድገትና የብልጽግና ምዕራፍ እየመራት ይገኛል።

የገጠር ልማት መለካት ያለበት በሚገነቡት መሠረተ ልማቶች ብቻ ሳይሆን፣ ተከትሎ በሚመጣው የሰዎች ሕይወት ለውጥ መሆን አለበት።
በመሆኑም የገጠር ኮሪደር ልማት ውጥን ተግባራዊና ሰውን ማዕከል ያደረገ አካሄድን በመከተል ላይ ይገኛል። ይህም ትስስርን ማሻሻል፣ ምቹ የኑሮ ሁኔታዎችን መፍጠር እና በገጠር ማሕበረሰብ ውስጥ የኢኮኖሚ ዕድሎችን ማስፋፋት ነው።
የዚህ ዐበይት ግብ የተበታተነና የተቆራረጠ ሐብትን በማስተካከል አምራች፣ እርስ በርስ የተሳሰሩ፣ ዘላቂ ልማት ያላቸው እንዲሁም ለመኖርና ለመሥራት ማራኪ የሆኑ የገጠር አካባቢዎችን መገንባት ነው።
Rural development must be measured not only by what is built, but by how people’s lives change as a result.
The rural corridors initiative is therefore taking a practical, people-centered approach: improving connectivity, creating better living conditions, and unlocking economic opportunities within rural communities.
The goal is to move beyond fragmented interventions and build rural areas that are productive, connected, resilient, and attractive places to live and work.
#PMOEthiopia #EthiopiaDelivers

❤1