MT Tech Ethiopia
1.87K subscribers
651 photos
8 videos
4 files
178 links
Download Telegram
ውጤታቹን ለማየት በመጠበቅ ላይ ያላቹ ውጤታቹን ምታገኙት በነዚህ 3 አማራጮች ነው

1. ዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et
2. ቴሌገራም፡ https://t.me/EAESbot
3.  አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡  6284

GOODLUCK
1
#Udate

ውጤት እንዴት ማየት ይቻላል ?

የ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና ውጤትን ተፈታኞች የሚያገኙበት አድራሻዎች ይፋ ሆነዋል።

የ2017 ትምህርት ዘመን 12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና የተፈተኑ ተፈታኞች በሚከተሉት አድራሻዎች ዛሬ ከሰዓት ጀምሮ ውጤታቸውን ማየት ይችላሉ፡፡

ዌብ ሳይትና ቴሌግራም አድራሻ የሚጠቀሙ ተፈታኞች ጊዜያዊ ሰርቲፊኬታቸውን ወዲያውኑ አውርደው (download አድርገው) መውሰድና መጠቀም ይችላሉ፡፡

አድራሻዎቹ፡
1. ዌብ ሳይት፡ https://result.eaes.et
2. ቴሌገራም፡ https://t.me/EAESbot
3.  አጭር የጽሑፍ መልዕክት (SMS)፡  6284

(የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት)
1
🔫
MT Tech Ethiopia
🔫
12ተኛ ክፍል ያሉበት ሁኔታ
😐3
#ካሊድ_በሽር👏

የዶዶላ ኢፈ ቦሩ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ተማሪ የሆነው ካሊድ በሽር በ12ኛ ክፍል ማጠናቀቂያ ፈተና 591 በማምጣት በሀገር አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ውጤት አስመዝግቧል፡፡

የኦሮሚያ ክልል ትምህርት ቢሮ ይፋ ባደረገው መረጃ ተማሪ ካሊድ በሽር ፦
- እንግሊዘኛ 96፣
- ሒሳብ 100፣
- ፊዚክስ 100
- ኬሚስትሪ 98፣
- ባዮሎጂ 99፣
- አፕቲትዩድ 98 አምጥቷል፡፡

የዶዶላ ኢፈ ቦሩ ልዩ አዳሪ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ርዕሰ መምህር ደቱ ዲቦ " ተማሪ ካሊድ በሽር በትምህርቱ በጣም ጎበዝ፣ ጥሩ ሥነ ምግባር ያለው እና አርአያ የሆነ ተማሪ ነው " ሲሉ ለኤፍ ኤም ሲ ተናግረዋል።

#ኤፍኤምሲ
#Update

ከፊዚክስ ትምህርት ፈተና  ጋር በተያያዘ በውጤት ላይ ተፈጥሮ የነበረው ችግር ተስተካከለ።

በሀገር አቀፉ የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና በሁለተኛው ዙር የፊዚክስ ፈተና ከ60ው ወደ 100 ሳይየቀር በመቀመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው መውረዱን ጠቁመው መፍትሄ እንዲሰጣቸው ጠይቀው ነበር።

የውጤት ችግሩ ዛሬ መስተካከሉን እና ከ100 ተቀይሮ መቀመጡን ተማሪዎቹ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ አሳውቀዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ ችግሩ መስተካከሉን ከክልል ትምህርት ቢሮዎችም ያገኘነው መረጃ ያመለክታል።

በሌላ በኩል ፤ መጀመሪያው ዙር የማሕበራዊ ሳይንስ የኢኮኖሚክስ ፈተና ውጤትም ችግር ያለበት እንደሆነ ተማሪዎች እና ወላጆቻቸው ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ጠቁመዋል።

በርካታ የመጀመሪያ ዙር ተፈታኝ ተማሪዎች የሌሎች ትምህርታቸው ውጤታቸው ከፍተኛ ሆኑ የኢኮኖሚክስ ውጤታቸው እጅግ ዝቅተኛ ሆኖ መቀመጡን ገልጸዋል።

በተመሳሳይ ከመጀመሪያው ዙር የሒሳብ ፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ ችግር እንዳለ ተማሪዎች እና ወላጆች ገልጸዋል። " የሚሰሩ ተማሪዎች ውጤት ሳይቀር እጅግ ወርዶ ተቀምጧል " ያሉ ሲሆን የሒሳብ ውጤትም እንዲታይላቸው እና ተስተካክሎ እንዲቀመጥ አመልክተዋል።

ቲክቫህ ኢትዮጵያ የተማሪዎች እና ወላጆችን ጥያቄ ይዞ የሚመለከታቸው አካላት ጋር ለማድረስ ይሰራል።
#ገነት_መርጋ 👏

ተማሪ ገነት መርጋ በሀገር ደረጃ ከፍተኛ ውጤት ካመጡ ተማሪዎች መካከል አንዷ ናት።

የዶዶላ ኢፋ ቦሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት ተማሪ ስትሆን በተፈጥሮ ሳይንስ 579/600 አምጥታለች።

የሒሳብ እና ፊዚክስ ውጤቶቿም 100/100 ናቸው።
ቅሬታዎን ያስገቡ!

በ12ኛ ክፍል ውጤትዎ ላይ ያለዎትን ቅሬታ በኦንላይን በቀጥታ ያስገቡ!

https://result.eaes.et ላይ ይግቡ፣
➫ የአድሚሽን ቁጥርዎን ያስገቡ፣
➫ የመጀመሪያ ስምዎን ያስገቡ፣
➫ ውጤትዎን ይመልከቱ፣
➫ እዛው ገፅ ላይ ወደታች ስክሮል ያድርጉ፣
➫ 'Submit Complaint' የሚለውን ይጫኑ፣
➫ 'My Complaints' የሚለውን ይጫኑ፣
➫ ቅሬታዎን ከማስገባትዎ በፊት ከዚህ በፊት ቅሬታ አስገብተው ከነበረና ምላሽ ከተሰጠዎ ይመልከቱ፣
➫ የተሰጠዎን ምላሽ ይመልከቱ። #EAES

📚ለፍሬሽማን ተማሪዎች የሚያግዛችሁን የንባብ ማቴሪያሎች በዚህ ሊንክ ገብተዉ ያውርዱ 👇

https://t.me/+CYz0QrgaSo43ZTZk
1
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አገልግሎቶች ለምን ይቋረጣሉ ?

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ እሁድ በርካታ አገልግሎቶቹ እንደሚቋረጡ ገልጾልናል።

ባንኩ " ከሲስተም ማሻሻያ ሥራ ጋር በተገናኘ እሁድ መስከረም 11 ቀን 2018 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት እስከ ለሊቱ 9፡30 ሰዓት ድረስ ከሲቢኢ ብር አገልግሎቶች በስተቀር ሁሉም የባንካችን ዲጂታል የክፍያ አማራጮች በጊዜያዊነት ይቋረጣሉ " ብሏል።

የሚቋረጡት አገልግሎቶች ፦
- የሞባይል ባንኪንግ፣
- ኢንተርኔት ባንኪንግ፣
- ኤቲኤም ማሽኖች
- የፖስ ማሽኖች እና በኮር ባንኪንግ የሚሰጡ አገልግሎቶች (Core Banking Services) እንደሆኑ አሳውዋል።

ባንኩ ደንበኞቹ ከወዲሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንዲያደርጉ ጠይቋል።

#CBE
1
#MoE

በ2017 ትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል ማጠቃለያ አገር አቀፍ ፈተና ወስደው የዩኒቨርስቲ መግቢያ ውጤት ያመጡና ለትምህርት ሚኒስቴር ተጠሪ በሆኑ የመንግስት ዩኒቨርስቲዎች በወጪ መጋራት (ስኮላርሽፕ) ለመማር ፍላጎት ያላቸው ተማሪዎች የዩኒቨርሲቲ እና የትምህርት መስክ ምርጫቸውን በየትምህርት ቤታቸው በተወከሉ መምህራን በኩል እስከ መስከረም 14/2018 ዓ.ም ድረስ ማስተካከል እንደሚችሉ ትምህርት ሚኒስቴር ገልጿል።

የኢትዮጵያ ሲቪል ሰርቪስ ዩኒቨርሲቲ ከ2018 ዓ.ም የትምህርት ዘመን ጀምሮ በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች ተማሪዎችን ስሚቀበል ምርጫቸው ውስጥ ማካተት የሚችሉ መሆኑን አሳውቋቃ።

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ምርጫ ውስጥ የማይካተቱ መሆኑን አስገንዝቧል።

#MoE
የፈረንሳይ ንጉስ ፣ የፒኤስጂ ኮከብ ኦስማን ዴንቤሌ ባሳየው ድንቅ ብቃት በእግርኳስ ትልቁን የባሎንዶር ሽልማት የግሉ ማድረግ ችሏል። 🔥🏆
1
የ ቴሌብር እዳ ያለባችው  እየከፈላችሁ
ክስ ሊመሰርቱ ነው
1
#MoE

300 ነጥብ የነበረው የየኒቨርሲቲ መግቢያ ወደ 297 ተጠጋጋ 📣


በ2017 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ መልቀቂያ ፈተና ወስደው በአማካይ ውጤታቸው 49.50 - 49.99 በመቶ ያመጡ ተማሪዎች ውጤታቸው ወደ 50 በመቶ የሚጠጋጋ መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

በዚህም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች፥ ዝቅተኛውን 50 በመቶ የማለፊያ ነጥብ ያሟሉ ሆኖ የተወሰነ መሆኑን በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በቀን መስከረም 20/2018 ዓ.ም ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከ ደብዳቤ ያሳያል።

በመሆኑም 49.50 እና በላይ አማካይ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎች ወደ ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመግባት መማር እንደሚችሉ ሚኒስተሩ ገልፀዋል።

ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ የደብዳቤውን ትክክለኛነት ያረጋገጠ ሲሆን፤ በዚህ ውሳኔ መሠረት 300 ነጥብ የነበረው የየኒቨርሲቲ መግቢያ ወደ 297 የተጠጋጋ መሆኑን ተረድተናል።
መልካም የኢሬቻ በዓል!