መድሃኒዓለም 1ኛ እና መለስተኛ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት
333 subscribers
934 photos
6 videos
216 files
21 links
ትምህርት በቤቴ
Download Telegram
የመድኃኒዓለም 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት የ2016 ዓ.ም 1ኛው ወሰነ_ትምህርት ፈተና ከጥር 27/05/2016 ጀምሮ በዚህ መልኩ እየተሰጠ ይገኛል።
#ማስታወቂያ

በትምህርት ሚኒስቴር የመምህራንና የትምህርት አመራሮች ልማት መሪ ስራ አስፈጻሚ በ2016 በጀት አመት የሁለተኛ ደረጃ መምህራንን አቅም ለማጎልበት የሚያግዝ ልዩ የስልጠና መረሃግብር ለማዘጋጀት እየሰራ ይገኛል።

በዚሁ መሰረት ስልጠናው የመምህራንን የስልጠና ፍላጎት ታሳቢ ያደረገ እንዲሆን ለማድረግ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍል ከሚገኙ መምህራን መርጃ ለመሰብስብ የሚያስችል የበይነ መረብ መጠይቅ ተዘጋጅቷል።

በመሆኑም በማንኛውም የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት የሒሳብ፣ እንግሊዘኛና የተፈጥሮ ሳይንስ የትምህርት ዓይነቶችን የምታስተምሩ መምህራን
https://forms.office.com/r/B8GAUYUg4H

ላይ በመግባት የተዘጋጀውን መጠይቅ እንድትሞሉና ለሚዘጋጀው ስልጠና ጥራት አስተዋፅኦ እንድታደርጉ ጥሪያችንን እናስተላልፋለን።

የትምህርት ሚኒስቴር!
የ2016 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና የተማሪዎች ምዝገባ ተጀመረ ።

...................................................
የካቲት 7/2016 ዓ.ም (ትሚ) የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት የ2016ዓ/ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና (12ኛ ክፍል) የተፈታኞች ምዝገባን በሚመለከት ለሚዲያ አካላት ማብራሪያ ሰጥቷል፡፡

የአገልግሎቱ ም/ዋና ዳይሬክተር አቶ ተፈራ ፈይሳ የ2016ዓ/ም የኢትዮጵያ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ማጠናቀቂያ ፈተና ተፈታኞች የመመዝገቢያ መስፈርቱን በማሟላት በተቀመጠው የጊዜ ገድብ መመዝገብ እንዳለባዉ አብራርተዋል፡፡

ም/ዋና ዳይሬክተሩ ምዝገባዉ የሚከናወነዉ በበይነመርብ /Online Registration / ሲሆን ከየካቲት 3 -30/2016 ዓ.ም ይሆናል ብለዋል።

በየደርጃዉ የሚገኙ ባለድርሻ አካላት ትኩርት ማድርግ ያለባቸውን ጉዳዮችም እንደሚከተለው አሳስበዋል።

1. በተቀመጠው የጊዜ ገደብ መምዘገብ እንዳለባቸው ከየካቲት 3 -30 /2016 ዓ.ም ብቻ

2. ምንም አይነት ስህትት ማለትም የፆታ ߹የስም ስህተት߹የፎቶ ߹የትምህርት መስክ እና የመሳስሉት ችግሮች እንዳይፈጠሩ በትኩርት መስራት መቻል

3. ከየካቲት 30 /2016 ዓ.ም በኃላ የሚመጣ ምዝገባ ተቀባይነት እንደሌለዉ ማወቅ መቻል

4. የመደበኛና የማታ ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወንው በተማሩበት ት/ቤት እንደሚሆን

5. የግል ߹ የርቀት /የበይነ መርብ /ተፈታኞ ምዝገባ በክፍለ ከተማ ߹በወረዳና ትምህርት ፅ/ቤቶች እንደሚከናወን የየትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መረጃ ያመለክታል።
Forwarded from BEKELE
ለመድኃኒዓለም 1ኛ እና 2ኛ ደረጃ ት/ቤት መ ማህበረሰብ በሙለ :-<እንኳን ደስ አላችሁ> ዛሬ መጋቢት 14 2016 ዓ.ም በድሬዳዋ ከተማ ባሉት 2ኛ  ደረጃ ት/ቤቶች ጋር በተደረገው የታክስና  ጉሙሩክ ክበብ ጥያቄና መልስ ውድድር  ትምርት ቤታችንን ወክላ የተወዳደረችው  ተማሪ አማናዊት ሲሳይ የተጠየቀችውን 7 ጥያቄዎች  በመመለስ የላቀ ፉክክር በማድረግ 1ኛ በመውጣት  ወደ  3ኛ ዙር  አልፋለች ። በቀጣዩ ዙርም አሸናፊ ሆና አገር አቀፍ ውድድር ላይ ተሳታፊ  እንድትሆን ድጋፋችሁ  እንዳይለያት አደራ  እላለሁ። ት/ቤቱ!!!