የሳይኮሎጂ ምክሮች
4.15K subscribers
96 photos
196 links
🔥ድንቅ አዝናኝና አስተማሪ አባባሎች
🔥የሳይኮሎጂ ምክሮችን ለማግኘት
ይቀላቀሉ
Download Telegram
​“አንድ ብርጭቆ ውኃ ሰጥቼህ፣ በውስጡ መርዝ ብጨምርበት፣ ከዚያም ስኳር ባዋህድበት... ስኳሩ የመርዙን ኃይል አያስወግደውም። ሊያጣፍጠው ይችላል፣ ነገር ግን አሁንም መርዛማ ነው።

​ሰዎች ስለ ስነ-ልቦናዊ ስብራት (trauma) የሚሳሳቱት ልክ እንደዚሁ ነው።

በሕይወትህ ላይ መልካም ነገሮችን ልትጨምር ትችላለህ፤ አዳዲስ ሰዎችን፣ ስኬትን፣ በራስ መተማመንን፣ ገንዘብን፣ ውበትን ወይም አዳዲስ ልማዶችን... ነገር ግን ከእነዚህ መካከል አንዳቸውም በራሳቸው ጊዜ ያልዳነውን ቁስል አያስወግዱትም።

​እግርህ ከተሰበረ፣ የፈለገውን ያህል የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ብታደርግ እግርህን ሊያድነው አይችልም።

አእምሮም በተመሳሳይ መንገድ ነው የሚሰራው። አንዳንድ ጊዜ ህመሙ በየቀኑ አይሰማህም፤ ስለዚህ የጠፋ ይመስለናል። ነገር ግን አልጠፋም፤ ዝም ብሎ ተኝቷል ብቻ።

​ከዚያም አንድ መጥፎ ተሞክሮ፣ አንድ ዝምታ፣ አንድ አለመቀበል (rejection) ወይም አንድ የሚታወቅ ስሜት... መልሶ ይቀሰቅሰዋል። ስነ-ልቦና ይህንን triggers ብሎ ይጠራዋል።

​ይህ አንተ ዝም ብለህ ነገሮችን የምታጋንን ሰው ስለሆንክ አይደለም፤ ይልቁንም ትኩረት የሚሹ አሮጌ ቁስሎች ናቸው።

ስለዚህ መፈወስ ማለት መርዝ ላይ ስኳር መጨመር አይደለም፤ መፈወስ ማለት ከመጀመሪያውም ህመምተኛ ያደረገህን ነገር ማስወገድ ነው።”

የጠቢባን መንገድ

https://t.me/mrtababl

https://t.me/mrtababl
25👍5
አንዲት ቀበሮ ቀን ሙሉ ምግብ ስትፈልግ ውላ አመሻሽ ላይ አንድ የወይን ዛፍ ታያለች። ቀደም ሲል የበሰለ ወይን ቀምሳ ጣዕሙን ታውቀዋለች በጣም አስጎመዥት ወደ ዛፉ ተጠግታ ቀና ስትል አንድ የሚያምር የበሰለ የወይን ፍሬ አየች። ሆኖም ዛፍ መውጣት አትችልም።
....
ፍሬውን ለማግኘት ዘለለች፤ አልቻለችም። እንደገና በኃይል ዘለለች... አሁንም አልደረሰችበትም። ደግማ፣ ደጋግማ ሞከረች... ፍፁም ልትደርስበት አልቻለችም። በመጨረሻም ተስፋ ቆረጣ "እንድያውም ጥሬ ነሽ!" ብላ ትታ ይባላል።
...
ብዙ ሰው የሌለውን ያጣጥላል፤ "ትምህርት ምን ይጠቅማል? ሀብት ምን ፋይዳ አለው? ወይም መፃፍ መቻል ምን ያደርጋል?" እያለ እነሱ ስለሌላቸው እናንተ ስላላችሁ የበታችነታቸውን ለመሸፈን የእናንተን ይዞታ ያቃልላሉ። እንዲህ ሲሆን "የእንዲያውም ጥሬነሽ" ተጠቂ እንደሆኑ ገምቶ ማለፍ ያስፈልጋል። የያዛችሁትን ጠበቅ አድርጉ

source ማዕደ ጥበብ
Join🌼🌼🌼🌼👇
https://t.me/mrtababl
27🔥6👍2
አንዴ ከሄዱ ብትለምኗቸው የማይመለሱ አራት ነገሮች!

ምንጩ ያልታወቀ አንድ ማስታወሻ፡-

በሕይወታችሁ እንደገና ለመመለስ የሚያስቸግሯችሁ አራት ነገሮች፡-

“እድል” - አንዴ ካመለጣችሁ በኋላ!

“ቃል” - አንዴ ከአንደበታችሁ ከወጣ በኋላ!

“ጊዜ” - አንዴ ሳትጠቀሙበት ካለፈ በኋላ!

“አመኔታ” አንዴ ከጎደለ በኋላ ለመመለስ አስቸጋሪ ነው፡፡

1.  “እድል” - በአጋጣሚም ሆነ ጠንክራችሁ በመስራታችሁ የመጣን እድል መለየት፣ ማክበርና በተገቢው ሁኔታ መጠቀም፡፡

2.  “ቃል” - ሁኔታዎች ሲገፋፏችሁም ሆነ እንዲሁ ስለለመደባችሁ በቀላሉ የምትናገሯቸውን ሰው ጎጂ ንግግሮች በሚገባ ማሰብና ራስን መግታት፡፡

3.  “ጊዜ” - በሆነ ባልሆነ የምታባክኑትና አሁን ባላችሁ እድሜ ማድረግ የሚገባችሁን ነገር ባለማድረግ የምታባክኑትን ጊዜ በጥንቃቄ መያዝ

4.  “አመኔታ” - ሰዎች ሲያምኗችሁና ራሳቸውንም ሆነ ነገሮቻቸው በእናንተ ላይ ሲጥሉ እምነት ከማጉደል መጠበቅ፡፡

በሉ እንግዲህ፣ ያለፈው አልፏል፣ የባከነው ባክኗል፡፡ የተራረፈውን እንሰባስበውና ሕይወትን እንደገና በአዲስ መልክ እንጀምር፡፡

ዶ/ር እዮብ ማሞ
35
ኤአይ (AI)ን እንዴት እንጠቀም ?

ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለረጅም ጊዜ እና ያለገደብ መጠቀም የሰዎችን የፈጠራ ብቃት እና ነገሮችን በጥልቀት የመመርመና የማሰብ ክህሎትን አደጋ ላይ ሊጥል እንደሚችል በቅርቡ የወጡ ተከታታይ ጥናቶች አመልክተዋል።

​በዘርፉ የተደረጉ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ሰዎች መረጃዎችን እና ውሳኔዎችን ሙሉ በሙሉ በኤአይ (AI) ላይ ጥገኞች ሆነው ማከናወን ሲጀምሩ " ኮግኒቲቭ ሰረንደር " ወይም የአእምሮን የማሰብ ስራ ለቴክኖሎጂ አሳልፎ የመስጠት ዝንባሌ ይታይባቸዋል።

ይህም አእምሮ በራሱ ጥረት መረጃዎችን የማቀናበር፣ የመተንተን እና አዳዲስ ሀሳቦችን የማመንጨት የተፈጥሮ ብቃቱ እንዲደክም ያደርገዋል።

በተለይ #ወጣቶች እና #ተማሪዎች ለተወሳሰቡ ጥያቄዎች እና ስራዎች ፈጣን ምላሽ ከኤአይ ማግኘት መልመዳቸው የራሳቸውን የአእምሮ አቅም የመጠቀም ተነሳሽነታቸውን እንደሚቀንሰው ተመራማሪዎች ያስጠነቅቃሉ።

ነገር ግን ቴክኖሎጂውን እየተጠቀሙ አእምሮን ሁል ጊዜ ንቁ፣ ብቁ እና ጤናማ አድርጎ ለማቆየት የሚረዱ በርካታ ሳይንሳዊ መንገዶች እንዳሉ ባለሙያዎች ይጠቁማሉ።

የአእምሮን የአስተሳሰብ ብቃት ላለማጣት ምን አይነት ልምዶች ማዳበር ይቻላል ?

- ከኤአይ (AI) የተገኙ ምላሾችን ወይም መረጃዎችን በቀጥታ ወስዶ ከመገልበጥ ይልቅ " ይህ መረጃ ትክክል ነው ? ምን ጎደለው ? አመክንዮአዊ ነው ? " በማለት በራስ አእምሮ መርምሮ፣ መዝኖ መጠቀም።

- ማንኛውንም ስራ፣ ጽሑፍ ወይም ፕሮጀክት ከመጀመርዎ በፊት መነሻ ሀሳቦችን እና እቅዶችን በራስ አእምሮ ማመንጨት እና ማስታወሻ መያዝ። ኤአይ ስራውን ለማስጀመር ሳይሆን የተጀመረውን ስራ ለማደራጀት ወይም ለመፈተሽ ብቻ መጠቀም።

- የፈጠራ እና የጥልቅ አስተሳሰብን የሚያነቃቁ እንደ መጽሐፍ ማንበብ፣ ስልታዊ ጨዋታዎችን መጫወት እና አዳዲስ ክህሎቶችን ያለ ቴክኖሎጂ እገዛ ለመማር መሞከር።

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ መረጃዎች/ስራዎችን ለኤአይ ሰጥቶ ያለ ምንም ምርመራ፣ ማስተካከያና ደጋግሞ የማንበብ ጥረት በቀጥታ #በመገልበጥ አንዳንዴም እንደራስ ስራ ማስመሰል እየተለመደ መጥቷል። ይህ በጥልቀት ሳያስቡና ሳይመራመሩ በቴክኖሎጂ ላይ ሙሉ በሙሉ ጥገኛ መሆን አእምሮን የማሰብ ስራውን እንዲተው በማድረግ፣ እውነታን የመተንተን እና የጥልቅ አስተሳሰብ ብቃትን በከፍተኛ ደረጃ እየገደለው ይገኛል ፤ ሰዎች ትንሽ ስራ እንኳን ለመስራት የማይፈልጉ ስልቹና ሰነፍ እያደረጋቸውም ነው።

ባለሙያዎች እንደሚመክሩት ኤአይ (AI) የሰውን ልጅ ሙሉ በሙሉ የሚተካ ሳይሆን እንደ ረዳት መሳሪያ ሆኖ ሊያገለግል የሚገባው ነው። ጥቅም የሚኖረውም የሰው ልጅ የራሱን የአስተሳሰብ ልዕልና ጠብቆ ሲቀጥል ብቻ ነው

Source (TIKVAH)
Join for more
https://t.me/mrtababl
11👍2
16
በሥነ-ልቦናው ዓለም ከሚያስገርሙኝ ኀልዮቶች (Theories) መካከል በሥነ-ሰብዕ ዕድገት ላይ በስፋት የሚታወቀው ጂያን ፒያዤ Cognitive Development theory አንዱ ነው። በዚህ ንድፈ-ሐሳብ እና የጥናት ውጤት መሠረትም ሕፃናት ወደዚህች ዓለም ከመጡ በኃላ ዓለምን፣ ተፈጥሮን (Physical World) የሚረዱበትን፣ እያወቁ የሚመጡበትን መንገድን ዘርዝሯል።

ሕፃናት በለጋነታቸው ምንም ነገር እንደ ስፖንጅ እውቀትን እያዳበሩ አይመጡም፤ ይልቁንስ ሲድሁ፣ ሲነካኩ፣ እሳት ሲፈጃቸው፣ ያንንም-ይሄንንም ሲቀምሱ፣ በሁሉም የስሜት ሕዋሶቻቸው መረጃ ሲቃርሙ ዓለምን የበለጠ እየተረዷት ይመጣሉ። የፅንሰ-ሐሳቡ ባለቤት ፒያዤ ይህ የዕድገት ምዕራፍ እስከ 6 - 8 ዓመት ድረስ ይዘልቃል ይለናል።

የዕድገት ምዕራፎች/ደረጃዎች በሕፃናት

1.  በስሜት ሕዋሶች በኩል ዓለምን መተዋወቅ (The Sensorimotor stage)፡ በዚህ የዕድገት ምዕራፍ ከውልደት እስከ 2 ዓመት ያለውን ያካትታል። ዓለምን በስሜት ሕዋሶቻቸው በኩል ያገኟታል። መንቀሳቀሳቸው ደግሞ ዋነኛው የመረዳታቸው Pillar ነው።

◦ለድንገቴ ተግባራት አረዳዳቸው እያደገ መሄድ ( Reflexes to intentional Actions)

◦በመሞከርና በመሳሳት መማር (Trial and Error Exploration) ልጆች በዚህ ጊዜ ከተለያዩ ዕቃዎች ጋር እየበጠሱ፣ እየሰበሩ፣ እየጣሉ፣ እየገነጠሉ የሚማሩበት ጊዜ ነው።

◦ አንድ ዕቃ ከነበረበት ቦታ ከዓይናቸው ቢሰወርም እንኳን ዕቃው መኖሩን መረዳት ወይም እዛው ነው የሚገኘው ብሎ ማሰብ (Object permanence)

◦ በአዕምሯቸው የተለያዩ ነገሮችን መሳል የሌለን ነገርንም ቢሆን ለምሳሌ፦ ስልክ ሲይዙ እናታቸውን እየወሩ ሲመስላቸው (Mental Representation)

2. The PreOperational Stage

ከ2-7 ዓመት ክልል ውስጥ ለሚገኙ ልጆች ሲኾን ቋንቋን በምልክቶችና ከግዑዝ አካላት ጋር በማያያዝ ወይም በመወከል እየተረዱ ይመጣሉ፤ ምንም እንኳ ያልበሰለ ቢሆንም Abruptly

፩ | ' Symbolic Function ' ሁሉን ነገር በSymbol መወከል፣ መግለፅ ወይም በዐይን የማይታዩ በአካል ያላዩትን በሌላ ዕቃ አስመስሎ መግለፅ። ለምሳሌ፦ በመኪና ፋንታ በማንኛውም ካርቶን ቭቭቭቭቭ.. እያደረጉ በእጅ መንዳት፣ በጎራዴ ቦታ በትንሽ እንጨት መጫወት ወ.ዘ.ተ.

፪ | ' Egocentrism ' ልጆች የሌሎች ሰዎችን ዕይታ/ንቃት (point of view) መረዳት ሲቸገሩ ለምሳሌ፦ የተደበቁ መስሏቸው ወይም አያዩኝም ብለው ፊትለፊት ከሚገኝ ሰው ጀርባ መደበቅ፣ ተደብቄያለሁ ብሎ በማሰብ ፊትን በእጅ መሸፈን..

፫ | ' Animism ' ልጆች ሕይወት የሌላቸው ነገሮችን ማለትም ዕቃዎች፣ ቁሳቁሶች እና ማንኛውም ነገሮችን ሕይወት እንዳላቸው፣ እንደ ሰው ስሜት እንዳላቸው አድርጎ ማሰብ። ለምሳሌ፦ ፀሐይ እየተከተለቻቸው ሲመስላቸው፣ ደመናው እየተከተላቸው ሲመስላቸው፣ ያደናቀፋቸው ዕቃ እንዲቀጣ በመፈለግ ሲመታ (ቱ.. በል ይኸው መታሁልህ ) ሲባሉ የእውነት ሲመስላቸው ወ.ዘ.ተ.

፬ | ' Centration ' ልጆች ትኩረት የሚሠጡት ትኩረት-ለሳባቸው ሲሆን ለምሳሌ፦ በሁለት ብርጭቆ ላይ ተመሣሣይ መጠን ያላቸው ውሃ ቀድተን ብናስቀምጥ አንዱ ብርጭቆ ቁመቱ ረዘም ያለ እና ጠባብ ሌላኛው አጭርና ሰፊ ቢሆን ልጆች ግን ብዙ ውሃ ያለው ረዥሙ ላይ ነው ብለው ማሰብ..

፭ | Lack of conservation ስለመጠን እና ብዛት አለመረዳት

Source ዋኖስ መስፍን |
11
የአንተ ህይወት ዋና ተዋናይ ማነው?

ብዙዎቻችን ህይወታችንን እንዲያስተካክልልን፣ ካለንበት ‘ጭንቅ’ ውስጥ እንዲያወጣን ወይም “ተነስ” ብሎ ፍቃድ እንዲሰጠን የምንጠብቀው አካል አለ። ወላጆቻችን፣ የትዳር አጋራችን፣ አልያም ድንገት የሚመጣ “እድል”።

ሳይኮሎጂ የሚነግረን ግን እውነታው ሌላ መሆኑን ነው።

እውነታው ይህ ነው፦

ማንም መጥቶ ህይወትህን ሊያስተካክልልህ አይችልም። ማንም!

ካለህበት ሁኔታ “ነጻ” ሊያወጣህ የሚችል ምልክት ወይም ሰው አትጠብቅ።

ያንተን ሁኔታ ሊለውጠው የሚችለው አንተ ራስህ ብቻ ነህ።

ዛሬ የምናደንቃቸው እና የደረሱበት ቦታ የደረሱ ሰዎች “ሁሉ ነገሬ ተሟልቷል፣ ዝግጁ ነኝ” ብለው አልጀመሩም።

እንዴት ጀመሩ መሰለህ?

እየፈሩ፣ እርግጠኛ ሳይሆኑ፣ ባዶ እጃቸውን እያሉ፣ እና በራሳቸው እየተጠራጠሩም ቢሆን ያኔ ባላቸው አቅም መጓዝ ጀመሩ።

ዛሬ አንተም መወሰን አለብህ፦ ዝግጁ እስክትሆን መጠበቅ ትፈልጋለህ ወይስ በጥርጣሬ ውስጥ ሆነህ እርምጃ መውሰድ?

ምርጫው ያንተው ነው!

Source psych addis
12🔥4
Promotion time
2
እጅግ በጣም የሚያማምሩ እና ጥራት ያላቸው አገልግል መሶብ
ይዘዙን ባሉበት ቦታ እናደርሳለን
ለአዲሱ አመት በልዮ ቅናሽ

Dm: @maranathadinku
0986359283
https://t.me/habeshamary
4🔥1
የህይወት ግቦች (goals) ማስቀመጥ የሚሰጠው ጥቅም!

በሕይወታችን የት መድረስ እንደምንፈልግ ማወቁ አስፈላጊ ሲሆን፣ ለምን መድረስ እንደፈለግን በውል ማወቅ የበለጠ አስፈላጊ ነው። አንዳንዶቹ ይህን መድረስ ከምንፈልግበት በስተጀርባ ያለውን ምክንያት እውነተኛው ግብ እያሉ ይጠሩታል። የሕይወት አጭር ወይም ረጅም ግብ (goal) ማዘጋጀት ለምን እንደሚጠቅም ባለሙያዎች እንደሚከተለው ያብራራሉ።

1. ፍላጎታችን እና ምኞታችን ይሟላል፦

በሕይወታችን አንድ ነገር ላይ መድረስ ለምን እንደምንፈልግ አስቀምጠን ስንቃኝ፣ ያስቀመጥነው ግብ በእውነትም ያንን ውጤት ሊያመጣልን እንደሚችልና እንደማይችል መመርመር እንችላለን። ስለሆነም በስሜታችን፣ በደስታችን እና በማንነታችን ላይ ለውጥ የሚያመጡ ነገሮች ላይ ብቻ አተኩረን እንድንሰራ ይረዳናል።

2. በሕይወታችን ምን እንደሚያነሳሱን ብሎም እራሳችንን የበለጠ እንድናውቅ ይረዳናል፦

ግቡን አስቀምጠን የሚያመጣልንን ደስታ እና ትርፍ ስናመዛዝን በዚያ ሂደት ከሕይወታችን ምን ማግኘት እንደምንፈልግ ብሎም ደስታችን በምን ላይ የተመሰረተ እንደሆነ የበለጠ እናውቃለን። ይህም ለበለጠ የእራስ ማስተዋል እና ግምገማ ጥሩ ዕድል ይፈጥርልናል። ወደ ጥሩ የሕይወት አላማም ለመጉዋዝ ማስተካካያወች እንድናደርግ ይረዳናል።

3. ለአእምሯችን ጤንነት ትልቅ አስተዋፅኦ ያበረክታል፦

የሕይወት ግቦችን ማስቀመጥ እና እንደምንደርስባቸው ለራስ መንገር ለአምሯችን ሰላም መሰማት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው። አእምሮአችን፣ ወደ ግባችን ለመድረስ ስንሰራ ደስታን ያገኛል፣ በዚህም የተነሳ ስለወደፊት ሕይወታችን ያለን አመለካከት ከፍ እያለ ይመጣል። በዚህም ትልቅ የአእምሮ ሰላም እናገኛለን። 

Join for more👇👇

https://t.me/mrtababl
👍63
🥸​በፖም እና በፒሪም ፍራፍሬዎች ውስጥ ትሎች በቀላሉ ሲገቡ አይቻለሁ፤ በሎሚ ውስጥ ግን ትል ገብቶ አያውቅም።
:
​ስለዚህ አንተም ከተሳሳቱና አላስፈላጊ ከሆኑ ሰዎች ጋር ከልክ በላይ ለስላሳና ጣፋጭ ለመሆን አትሞክር።!

....

Source የጠቢባን መንገድ

https://t.me/mrtababl
👍6👏1