M.O.R East Addis Ababa Branch
23.1K subscribers
5.73K photos
15 videos
505 files
360 links
East Addis Ababa Small Tax Payer Branch Office is one of many branches of Ministry of Revenues at Addis Ababa. Which are responsible for collecting revenue from customs duties and domestic taxes.
Download Telegram
👍7🙏5❤1
መጋቢት 01/07/2018ዓ.ም//የምስራቅ አ/አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ቀን //
እንኳን ደሰ አለን እንኳን ደስ አላችሁ!!
ስኬታችን የተባበረ የጥረታችን ውጤት ነው!
“የየካቲት ወር ዕቅድ ለቅ/ጽ/ቤቱ አዲስ ምዕራፍ የሆነ ብር 2.06 ቢሊዮን ታቅዶ ብር 2.13 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ አፈፃፀሙ 103.03 % ያሳካ ሲሆን ይህም ከባለፈው በጀት አመት ተማሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር በብር 1.46 በቢሊዮን (220%) ብልጫ ያሳየ ሲሆን የገቢ ግባችንን በቁርጠኝነት፣ በትጋት፣ በቡድን መንፈስ እና ለግብር ከፋዮች በታማኝነት በሰጠነው አገልግሎት እና ማሳካታችን እጅግ የሚያኮራ ነው ።
ይህ ስኬት የተባበረ ጥረታችን ውጤት ነው፤ ወደፊትም በተመሳሳይ ቁርጠኝነት ለሀገራችን ልማት እንቀጥላለን።
ለዚህ ስኬት ታላቅ አስተዋፅኦ ያደረጉትን መላው አመራሮች ፣ ሰራተኞች እና ታማኝ ግብር ከፋዮቻችንን ላሳያችሁን ትብብርና ለሰጣችሁን ፍቅር ከልብ እናመሰግናለን።
እንኳን ደስ አለን!!
ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ
❤29👎7👍6
❤4👍4
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በየካቲት ወር ብር 2.13 ቢሊዮን መሰብሰቡንበመግለጽ ለእቅዱ መሳካት አስተዋጽዖ ለነበራቸው በየደረጃው ለሚገኙ የስራ ሃላፊዎች እውቅና ሰጠ
………………………………………..
መጋቢት 8/2018 / የምስ/አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት/
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ̋ወደ መጋቢት ወር የምናሻግረው እዳ አይኖርም ̏ በሚል ሞቶ የየካቲትን ወር የእቅድና ፊዚካል ስራዎች ሲያከናውን መቆየቱ ይታወሳል ፤ይህንንም ተከትሎ የየካቲት ወር እቅድ አፈጻጸም የገቢ አሰባሰብና ሂደት የተሳካ በመሆን አፈፃፀሙ 103.03 በመቶኛ አፈጻጸም ተመዝግቧል ፤ይህንንም ተከትሎ በእቅዱ አፈጻጸምና ፊዚካል ስራዎች ውይይት በማድረግ ለእቅድ አፈጻጸም ስኬት ጉልህ ሚና ለነበራቸው የስራ ሃላፊዎች እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች በሙሉ እቅዱን ለማሳካት ላደረጉት አስተዋጽዖ፣የስራ ተነሳሽነት፣ ለነበረው ቅንጅት እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ በስራ ሀላፊዎቻቸው አማካኝነት የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል ፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ የየካቲት ወር ዕቅድ ለቅ/ጽ/ቤቱ አዲስ ምዕራፍ ከፍተኛ ከመሆኑም ባሻገር የከፈተና በገቢ አሰባሰቡ ብር 2.06 ቢሊዮን ታቅዶ ብር 2.13 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ አፈፃፀሙ 103.03 % የተሳካበት ወር ከመሆኑም ባሻገር በተሻሻለው አዋጅ መሰረት 25% (ሀያ አምስት በመቶ) ቅድመ ግብር ክፍያ በወሩ በስኬት የተሰበሰበበት ጊዜ እንደነበር ጠቅሰዋል ፡፡የገቢ እቅድ አፈጻጸም በዋና መሰሪያ ቤቱ ይደረግ የነበረው የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ለገቢው መሳካት ጉልህ ሚና እንደነበረው በመግለጽ በቁርጠኝነት፣ በትጋት፣ በቡድን መንፈስ እና ለግብር ከፋዮች በታማኝነት በተሰጠ አገልግሎት መሳካቱን አንስተው ለገቢው ስኬት የድርሻቸውን ለተወጡ ግብር ከፋዮችና ሰራተኞች ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡
አያይዘውም ወደቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በቅርብ ጊዜ በታክስ ኦፕሬሽን ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆነው የተሾሙት አቶ ማቲያስ አየለ እና የታክስ ስርዓት ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዓለም ታምራትን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አቀባበል በማድረግ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተውላቸዋል ፡፡
አቶ ገንዘብ መካሻ የዕቅድና በጀት አፈፃፀም ክትትል ቡድን አስተባባሪ የየካቲት ወር የስራ አፈፃፀም ሲያቀርቡ ቅ/ጽ/ቤቱ ከቀጥታ ታክሶች፤ ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች በአጠቃላይ 2.05 ቢልዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 2.13 ቢልዮን በመሰብሰብ አፈፃፀሙ 103.13 በመቶኛ መሳካቱን በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡
በየካቲት ወር ከተሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ ብር 2.06 ቢልዮን መካከል ብር 1.32 ቢልየን ከቀጥታ ታክሶች፣ብር 804.81 ሚልዮን ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እንዲሁም ብር 3.18 ሚሊዮን ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል።
አቶ ቢንያም ገ/ማርያም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የስጋትና የህግ ተገዢነት እስትራቴጂ የስራ ሂደት አስተባባሪ የአማራጭ አነስተኛ ግብር ክፍያ (2.5 %) በቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግብር አሰባሰቡ ላይ ያደረገው አስተዋጽዖ በሚል በማቅርብ ምክረ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል ፡፡
በእለቱም አቶ ለማ ደገፋ የ AYSOL ማኔጅመንት አማካሪ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ የአመራር አመራር አሰልጣኝና ደራሲ በመገኘት አመራሩ ማንን ይመስላል በሚል ሀሳብ በመያዝ አንቂና አትጊ ሀሳቦችን በማንሳት ለአመራሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል ፡፡

ስራ አስኪያጇ ስልጠናውን ለሰጡት አሰልጣኝ በማመስገን ስልጠናው የተዘጋጀበት ዓላማ ሲገልጹ እቅድን እንዲያሳካ ለሚጠበቅ አመራር ሁልጊዜ እራሱን በእውቀት ማደስ የሚያስፈልግና ለተነሳሽነትም አቅም እንዲሆን ታስቦ የተሰጠ የማነቃቂያ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ ይህን መሰል ስልጠናም ቀጣይቱን አረጋግጠዋል ፡፡
በመጨረሻም ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ በየካቲት ወር የነበረን የአገልግሎት አሰጣጥ ሆነ ቅንጅታዊነት በመጋቢት ወርና በበቀሩት ወራት በማጠናከር የመጋቢት ወር የገቢና የፊዚካል እቅድ አንዲሳካ ያስችላል ያሏቸውን ሀሳቦች በማስቀመጥ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል ፡፡
በውይይቱም ላይ የሶስቱም ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጆች ከዘርፋቸው አንጻር ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል፣ በቀረበውም ጥናት ያላቸውን ሀሳብ በመስጠት፣ስልጠናው በስራቸው ላይ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆናቸው ሲገልጹ የመጋቢትን ወር ሆነ የዓመቱን እቅድ ለማሳካት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል ፡፡
………
❤20