የ2ኛ ዙር የታክስና ጉሙሩክ ክበብ የጥያቄና መልስ ውድድር ተካሄደ
…………………
በገቢዎች ሚኒስቴር የምስራቅ /አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት//የካቲት 28/2018ዓ.ም //
̋ታክስ የልማት ሁሉ መሰረት በመሆኑ ሀገር እንድትገነባ የሚያግዝ ዋና ኃይል የሆነውን የነገ ሀገር ተረካቢ ትውልድን በታክስና በጉሙሩክ ጉዳዮች ዙርያ እውቀት አስጨብጦ መቅረጽ፣ ሀገር ታማኝና ሃላፊነት ያለው ዜጋ እንዲኖራት ያስችላል ፡፡ ̋ //ወ/ሮ ወርቀለም ተሾመ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ//
ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ ይህን ያሉት እንደ ቅርንጫፍ ጽ/ቤትየ2ኛ ዙር የታክስና ጉሙሩክ ክበብ የጥያቄና መልስ ውድድር ላይ ያስተላለፉት መልዕክት ሲሆን የውድድሩም ዓላማ በተማሪዎቹ ውስጥ የታክስና ጉሙሩክ እውቀት ግንዛቤ እንዲያገኙና የሃላፊነት ስሜት እንዲያድግ ነው ብለዋል፡፡
የታክስ ስርዓት ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ አለም ታምራት ውድድሩን ላጠናቀቁ ተማሪዎች በውድድር መንፈስ የታክስ እውቀት መጨበጣቸውና ይህም ለማህበረሰቡ የማስተላለፍ ሃላፊነት እንዳለባቸው በመግለጽ በቀጣይ ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ወክሎ የሚወዳደረውን ተማሪ እንኳን ደስ አለህ በማለት ለቀጣይ ውድድር እራሱን እንዲያዘጋጅ አደራ ጭምር ሰጥተዋል ፡፡
ከዚህም ጋር ተያይዞ ወ/ሮ የሺወርቅ ተጫነ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የሥራ ሂደት አስተባባሪ የውድሩን ሂደት ምን እንደሚመስል ስለቀጣይ የውድድር ሁኔታም ማብራሪያ የሰጡ ሲሆን ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ወክሎ አንደኛ የወጣውን የየካ አባዶ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ኃይለ ልዑል የማነ ለሦስተኛው ዙር ወይም ክላስተር ብሎም በሀገር አቀፍ ለሚኖረው ውድድር ድጋፍ እንደሚደርጉና ትምህርትቤቱና ተማሪው ከወዲሁ በቂ ዝግጅት ማድረግ እንዳለባቸው አቅጣጫ አስቀምጠዋል፡፡
በውድድሩም ከአንድ እስከ ሶስት የወጡ ተማሪዎች የተለዩ ሲሆን ኃይለ ልዑል የማነ የካ አባዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት ፣ናትናኤል ዮናስ ከቦሪ 2ኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እና ረድኤት መሳፍንት ከማጂክ ካርፔት 2ኛ ደረጃ በቅደም ተከተል ከአንድ እስከ ሶስት በመውጣት ለተማሪዎችም ሽልማት ተበርክቶላቸዋል ፡፡
በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በመገኘት የጥያቄና መልስ ውድድር የተሳተፉት ከሶስቱም ክፍለ ከተማዎች (ቦሌ ፣ለሚኩራ እና የካ ) ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች የተወጣጡ 28 ተማሪዎችን በዛሬው እለት በ በአብቂ መምህራን እገዛ በውድድሩ ተሳትፈዋል ፡፡
##ውድድሩን በአንደኛ ደረጃ ያጠናቀቀው ተማሪ ኃይለ ልዑል የማነ የካ አባዶ 2ኛ ደረጃ ት/ቤት በቀጣይ በሚደረገው ውድድር ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱን ወክሎ የሚወዳደር ይሆናል ፡፡
…………..

❤11👍4
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የበላይ ሃላፊዎች ክትትልና ድጋፍ ከመስተንግዶ ጋር
……………..
የካቲት 30/2018 //የምስራቅ አነስተኛ ግብር ከፋዮች ቅርንጫፍ ጽ/ቤት//
በፌደራል የገቢ ግብር/ ማሻሻያ / አዋጅ ቁጥር 1395/2017 መሰረት ከተያዘዉ የግብር ዓመት በፊት በነበረዉ ግብር 25% (ሀያ አምስት በመቶ) ቅድመ ግብር ክፍያ ሰኔ 30 የሚዘጉ ግብር ከፋዮች የ2017 የግብር ዘመን እና Dec.31 የሚዘጉ ግብር ከፋዮች የ2024 የግብር ዘመን የከፈሉትን 25% የመክፈያ ጊዜ ከየካቲት 1 እስከ የካቲት 30/2018 ድረስ መሆኑን ተከትሎ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አሰኪያጅ ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ ጨምሮ በየደረጃው የሚገኙ የስራ ሀላፊዎች በቅርበት በመሆን የግብር አከፋፈል ሂደቱና የአገልግሎት አሰጣጡ የተሳለጠ አንዲሆን ድጋፍና ክትትል ሲደርጉ ቆይተዋል ፡፡
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱም ከሰኞ እስከ አርብ ባሉት ቀናትም እሰከ ምሽቱ 12 ሰዓት ቅዳሜ የሙሉ ቀን አገልግሎት በመስጠት ግብር ከፋዩም ግብሩን ሲከፍል እንደነበር ለማወቅ ተችሏል ፡፡
በዛሬውም እለት ክትትልና ድጋፉ ከሻይ ቡና መስተንግዶ ጋር ቀጥሏል ፡፡

❤13👍3😁1
መጋቢት 01/07/2018ዓ.ም//የምስራቅ አ/አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ቀን //
እንኳን ደሰ አለን እንኳን ደስ አላችሁ!!
ስኬታችን የተባበረ የጥረታችን ውጤት ነው!
“የየካቲት ወር ዕቅድ ለቅ/ጽ/ቤቱ አዲስ ምዕራፍ የሆነ ብር 2.06 ቢሊዮን ታቅዶ ብር 2.13 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ አፈፃፀሙ 103.03 % ያሳካ ሲሆን ይህም ከባለፈው በጀት አመት ተማሳሳይ ወር ጋር ሲነጻጸር በብር 1.46 በቢሊዮን (220%) ብልጫ ያሳየ ሲሆን የገቢ ግባችንን በቁርጠኝነት፣ በትጋት፣ በቡድን መንፈስ እና ለግብር ከፋዮች በታማኝነት በሰጠነው አገልግሎት እና ማሳካታችን እጅግ የሚያኮራ ነው ።
ይህ ስኬት የተባበረ ጥረታችን ውጤት ነው፤ ወደፊትም በተመሳሳይ ቁርጠኝነት ለሀገራችን ልማት እንቀጥላለን።
ለዚህ ስኬት ታላቅ አስተዋፅኦ ያደረጉትን መላው አመራሮች ፣ ሰራተኞች እና ታማኝ ግብር ከፋዮቻችንን ላሳያችሁን ትብብርና ለሰጣችሁን ፍቅር ከልብ እናመሰግናለን።
እንኳን ደስ አለን!!
ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ

❤29👎7👍6
income tax.pptx
501.3 KB
part 1
❤4
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በየካቲት ወር ብር 2.13 ቢሊዮን መሰብሰቡንበመግለጽ ለእቅዱ መሳካት አስተዋጽዖ ለነበራቸው በየደረጃው ለሚገኙ የስራ ሃላፊዎች እውቅና ሰጠ
………………………………………..
መጋቢት 8/2018 / የምስ/አ/አ/አ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት/
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ̋ወደ መጋቢት ወር የምናሻግረው እዳ አይኖርም ̏ በሚል ሞቶ የየካቲትን ወር የእቅድና ፊዚካል ስራዎች ሲያከናውን መቆየቱ ይታወሳል ፤ይህንንም ተከትሎ የየካቲት ወር እቅድ አፈጻጸም የገቢ አሰባሰብና ሂደት የተሳካ በመሆን አፈፃፀሙ 103.03 በመቶኛ አፈጻጸም ተመዝግቧል ፤ይህንንም ተከትሎ በእቅዱ አፈጻጸምና ፊዚካል ስራዎች ውይይት በማድረግ ለእቅድ አፈጻጸም ስኬት ጉልህ ሚና ለነበራቸው የስራ ሃላፊዎች እና የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ሰራተኞች በሙሉ እቅዱን ለማሳካት ላደረጉት አስተዋጽዖ፣የስራ ተነሳሽነት፣ ለነበረው ቅንጅት እንዲሁም የአገልግሎት አሰጣጥ በስራ ሀላፊዎቻቸው አማካኝነት የእውቅና ሰርተፊኬት ተበርክቶላቸዋል ፡፡
የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ የየካቲት ወር ዕቅድ ለቅ/ጽ/ቤቱ አዲስ ምዕራፍ ከፍተኛ ከመሆኑም ባሻገር የከፈተና በገቢ አሰባሰቡ ብር 2.06 ቢሊዮን ታቅዶ ብር 2.13 ቢሊዮን ብር በመሰብሰብ አፈፃፀሙ 103.03 % የተሳካበት ወር ከመሆኑም ባሻገር በተሻሻለው አዋጅ መሰረት 25% (ሀያ አምስት በመቶ) ቅድመ ግብር ክፍያ በወሩ በስኬት የተሰበሰበበት ጊዜ እንደነበር ጠቅሰዋል ፡፡የገቢ እቅድ አፈጻጸም በዋና መሰሪያ ቤቱ ይደረግ የነበረው የቅርብ ክትትልና ድጋፍ ለገቢው መሳካት ጉልህ ሚና እንደነበረው በመግለጽ በቁርጠኝነት፣ በትጋት፣ በቡድን መንፈስ እና ለግብር ከፋዮች በታማኝነት በተሰጠ አገልግሎት መሳካቱን አንስተው ለገቢው ስኬት የድርሻቸውን ለተወጡ ግብር ከፋዮችና ሰራተኞች ልባዊ ምስጋናቸውን አቅርበዋል ፡፡
አያይዘውም ወደቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በቅርብ ጊዜ በታክስ ኦፕሬሽን ምክትል ስራ አስኪያጅ ሆነው የተሾሙት አቶ ማቲያስ አየለ እና የታክስ ስርዓት ምክትል ስራ አስኪያጅ ወ/ሮ ዓለም ታምራትን እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት አቀባበል በማድረግ መልካም የስራ ዘመን እንዲሆንላቸው ተመኝተውላቸዋል ፡፡
አቶ ገንዘብ መካሻ የዕቅድና በጀት አፈፃፀም ክትትል ቡድን አስተባባሪ የየካቲት ወር የስራ አፈፃፀም ሲያቀርቡ ቅ/ጽ/ቤቱ ከቀጥታ ታክሶች፤ ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እና ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች በአጠቃላይ 2.05 ቢልዮን ብር ለመሰብሰብ አቅዶ ብር 2.13 ቢልዮን በመሰብሰብ አፈፃፀሙ 103.13 በመቶኛ መሳካቱን በሪፖርታቸው አመላክተዋል፡፡
በየካቲት ወር ከተሰበሰበው አጠቃላይ ገቢ ብር 2.06 ቢልዮን መካከል ብር 1.32 ቢልየን ከቀጥታ ታክሶች፣ብር 804.81 ሚልዮን ቀጥታ ካልሆኑ ታክሶች እንዲሁም ብር 3.18 ሚሊዮን ታክስ ካልሆኑ ገቢዎች የተሰበሰበ መሆኑ ተገልጿል።
አቶ ቢንያም ገ/ማርያም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ የስጋትና የህግ ተገዢነት እስትራቴጂ የስራ ሂደት አስተባባሪ የአማራጭ አነስተኛ ግብር ክፍያ (2.5 %) በቅርንጫፍ ጽ/ቤት በግብር አሰባሰቡ ላይ ያደረገው አስተዋጽዖ በሚል በማቅርብ ምክረ ሀሳባቸውን ሰጥተዋል ፡፡
በእለቱም አቶ ለማ ደገፋ የ AYSOL ማኔጅመንት አማካሪ ዋና ሥራ አስፈጻሚ፣ የአመራር አመራር አሰልጣኝና ደራሲ በመገኘት አመራሩ ማንን ይመስላል በሚል ሀሳብ በመያዝ አንቂና አትጊ ሀሳቦችን በማንሳት ለአመራሩ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል ፡፡
ስራ አስኪያጇ ስልጠናውን ለሰጡት አሰልጣኝ በማመስገን ስልጠናው የተዘጋጀበት ዓላማ ሲገልጹ እቅድን እንዲያሳካ ለሚጠበቅ አመራር ሁልጊዜ እራሱን በእውቀት ማደስ የሚያስፈልግና ለተነሳሽነትም አቅም እንዲሆን ታስቦ የተሰጠ የማነቃቂያ ስልጠና መሆኑን ተናግረዋል ፡፡ ይህን መሰል ስልጠናም ቀጣይቱን አረጋግጠዋል ፡፡
በመጨረሻም ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ በየካቲት ወር የነበረን የአገልግሎት አሰጣጥ ሆነ ቅንጅታዊነት በመጋቢት ወርና በበቀሩት ወራት በማጠናከር የመጋቢት ወር የገቢና የፊዚካል እቅድ አንዲሳካ ያስችላል ያሏቸውን ሀሳቦች በማስቀመጥ የስራ አቅጣጫ ሰጥተዋል ፡፡
በውይይቱም ላይ የሶስቱም ዘርፍ ምክትል ስራ አስኪያጆች ከዘርፋቸው አንጻር ለተነሱ የተለያዩ ጥያቄዎችና አስተያየቶች ምላሽ ሰጥተዋል፣ በቀረበውም ጥናት ያላቸውን ሀሳብ በመስጠት፣ስልጠናው በስራቸው ላይ ተጨማሪ አቅም እንደሚሆናቸው ሲገልጹ የመጋቢትን ወር ሆነ የዓመቱን እቅድ ለማሳካት ያላቸውን ቁርጠኝነት ገልጸዋል ፡፡
………

❤20