ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ ለአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ሰራተኞች በሙያ ስነ-ምግባር ተያያዥ ስልጠናዎችን ሰጠ ፡፡
………..
የካቲት 20/2018 ምስራቅ አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ከአዲስ አበባ ገቢዎች ቢሮ የአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ሥነ-ምግባርና ፀረ-ሙስና የስራ ሂደት ጋር በመተባበር ለአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት አመራሮችና ሰራተኞች በሙያ ስነ-ምግባር፣ እና የሀብት ምዝገባ ህጎች ጋር በተያያዘ በሁለት ዙር ስልጠናውን ሰጥቷል ፡፡
ስልጠናውንም በቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ተቋማዊ ስጋት ሥራ አመራርና ሥነ-ምግባር ቡድን ሙያተኞች በሆኑት አቶ አዲሱ ኡርጌሳ እና አቶ ጌታሰው አሰፋ ተሰጥቷል ፡፡
በእለቱም የአዲስ አበባ ቁጥር 2 መካከለኛ ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት ስራ አስኪያጅ ዘቧ ኃይሌ በመገኘት ስልጠናው ለስራ ያለው ጠቀሜታ ከፍተኛ መሆኑን በመግለጽ ይህን መሰል የትብብር ስራ ሊጠናከር ይገባል ሲሉ ስልጠናው ለሰጠው የምስራቅ /አ/አ/አነ/ግ/ከ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት አመስግነዋል ፡፡

❤7👏1
ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በገቢ አስተዋጽዖ ከፍ ላሉ የቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ ግብር ከፋዮች ጋር ውይይና በመሰረታዊ የታክስ መርሆች (የታክስ ሞራል) ዙሪያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥቷል ፡፡
…………………
የካቲት 21/2018/ ምስራቅ አ/አ/አነ/ግ/ከ/ቅ/ጽ/ቤት/
"ግብር መክፈል የህግ ግዴታ ብቻ አይደለም፤የዜግነት ክብር እና የሀገር ፍቅር ምልክት ነው !"
ወ/ሮ ወርቃለም ተሾመ የቅርንጫፉ ስራ አስኪያጅ የውይቱንና የስልጠናውን መድረክ ሲከፈቱ ያስተላለፉት መልዕክት ሲሆን አያዘውም እኛ እንደ አሰተዳዳሪዎች በቁርጠኝነት የግብር አገልግሎቱን ቀላል ፈጣንና ፍትሃዊ እንዲሆን ዲጂታል ሥርዓቶችን በማስፋፋት፣የአገልግሎት ጥራትን በማሻሻል፣የስራ ሂደቶችን እንዲቀላጠፉ አስፈላጊውን እገዛ እናደርጋለን ፤እናንተን ውድ ግብር ከፋዮቻችን እንደ ባለቤትነታችሁና ቤተሰብነታችሁ እናገለግላችኋለን ብለዋል ፡፡
በእለቱም ወ/ሮ የሺወርቅ ተጫነ የታክስ ከፋዮች ትምህርትና መረጃ አቅርቦት የስራ ሂደት አስተባባሪ በመሰረታዊ የታክስ መርሆች (ሞራል) ዙርያ የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ሰጥተዋል ፡፡
በቀረበው ስልጠና መነሻነት ውይይት የተካሄደ ሲሆን ግብር ከፋዮቹም መድረኩ መዘጋጀቱ ተቀራርቦ ከመስራት ባሻገር ችግሮቹን በጊዜው ለመቅረፍ ያስችላል በማለት በአገልግሎት አሰጣጥና በግብር አከፋፈሉ ሂደት ይስተዋላሉ ያሉትን ችግሮች አንስተዋል ፡፡
በተነሱት ሀሳብና አስተያየትም ወ/ሮ አለም ታምሩ የታክስ ስርዓት ም/ሥራ አስኪያጅ እና የሚመለከታቸው የስራ ሂደት አስተባባሪዎች ከስራቸው አንፃር ምላሽ ሰጥተዋል፡፡
በመጨረሻም ወ/ሮ ወርቅአለም ተሾመ የአገር ኢኮኖሚውን የምናሳካው ኢኮኖሚ የሚያመነጨው ግብር በመክፈል፣እናንተ ከእኛ ጋር ስትሆኑና ለሀገርር ዕድገት ግብራችሁን በወቅቱ በማሳወቅ ስትከፍሉ ነው ብለዋል አያይዘውም ከግብር ከፋዩ ይጠበቃል ያሉትን መሰረታዊ የታክስ ግዴታዎች ጠቁመው ቅርንጫፍ ጽ/ቤቱ በሚጠቀማቸው የሶሻል ሚዲያ ልዪ ልዩ መረጃዎችን ከማግኘት በተጨማሪ ትምህርቶቹን በአካል በመገኘት መማር ለማይችሉ አማራጭ እንደሆነ ጠቁመው ለውጦችን በወቅቱ ማሳወቅ እና ከሐሰተኛ ደረሰኝ ጋር ተያይዞ ከሚመጣ ወንጀል እራስን መጠበቅ ያስፈልጋል ብለዋል ፡፡
በቀጣይም ይህን መሰለ ስልጠናና የምክክር መድረክ በየደረጃው እንደሚካሄድ ተገልጿል፡፡

❤9