ማኅበረ ቅዱሳን "ኑ ቸርነትን እናድርግ " በሚል መሪ ቃል የድጋፍ ማሰባሰቢያ መርሐ ግብር አዘጋጀ
በአገራችን በሰው ሠራሽ እና የተፈጥሮ አደጋዎች የተፈናቀሉ ወገኖችን ለመደገፍ የሚያስችል ልዩ መርሐ ግብር በሚሊኒየም አዳራሽ የፊታችን መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም "ኑ ቸርነት እናድርግ " በሚል መሪቃል መዘጋጀቱ ተገልጿል።
ጉባኤውን በማስመልከት በማኅበሩ ጽ/ቤት በተሰጠው ጋዜጣዊ መግለጫ ላይ የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ የሆኑት ሊቀ ትጉኅን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ስዩም እንደገለጹት ማኅበሩ ከሚያከናውናቸው በርካታ ተግባራት መካከል አንዱ የተቸገሩ ወገኖችን መደገፍ እንደሆነ ገልጸው ከችግሩ ስፋት አንጻር ባልድርሻ አካላት ለየብቻ የሚያደርጉት ድጋፍ ውጤት ማምጣት ስለማይችል ማኅበሩ ከምእመናን እና ጉዳዩ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በጋራ እንደሚሠራ አሳውቀዋል።
የማኅበረ ቅዱሳን የሙያ እና ማኅበራዊ አገልግሎት ማስተባበሪያ ም/ኃላፊ የሆኑት ዲ/ን ንጉሤ ባለውጊዜ እንደተናገሩት በተለያዩ የአገራችን ክፍሎች ከቤት ንብረታቸው የተፈናቀሉ ወገኖች እንዲሁም በድርቅ እና በተለያዩ ጊዜያት በሚከሰቱ ግጭቶች ምክንያተ በከፈተኛ ችግር ውስጥ የሚገኙ አድባራት እና ገዳማት እንደሚገኙ ገልጸው ማኅበሩ እስካሁን ድረስ አጋር አካላትን በማስተባበር የተለያዩ ድጋፎችን ሲያደርግ ቆይቷል ብለዋል።
ምክትል ኃላፊው አያይዘው ምእመናን ማኅበሩ በመልሶ ማቋቋም ረገድ እያደረገ ያለውን ድጋፍ እንዲደግፉ ጥሪያቸውን አስተላልፈዋል።
የማኅበሩ ምክትል ዋና ጸሐፊ ዲ/ን አንድነት ተፈራ እንደገለጹት ምእመናን መጋቢት 15 ቀን 2016 ዓ.ም በሚሊኒየም አዳራሽ በሚደረገው መርሐ ግብር ላይ በመገኘት የማኅበሩን አገልግሎት በመደገፍ አጋርነታቸውን እንዲያሳዩ መልእክታቸውን አስተላልፈዋል።

የማኅበረ ቅዱሳን ጥናት እና ምርምር ማእከል ፰ኛውን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት መጽሔት ኅትመት አጠናቀቀ።
በተለያዩ ርእሰ ጉዳዮች ላይ ምሁራንን በማሳተፍ የጥናት መጽሔቶችን በማሳተም የሚታወቀው የማኅበረ ቅዱሳን ጥናት እና ምርምር ማእከል ፰ኛውን የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት መጽሔት ለአንባብያን ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቋል። መጽሔቱ የቤተ ክርስቲያንን ልዩ ልዩ ገጽታዎች ሊያሳዩ የሚችሉ አምስት መጣጥፎችንና አንድ የመጽሐፍ ግምገማን ያካተተ ነው፡፡ ይህም በዘርፉ ያለውን መልከ ብዙ እውቀት በጨረፍታም ቢሆን ለማየት የሚያስችለንን ዕድል የሚሰጥ ነው፡፡
መጽሔቱ ስድስት የምርምር ውጤቶችን ይዟል። ከእነዚህ መካከል ሦስቱ በአማርኛ ቋንቋ የቀረቡ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ ሦስት የምርምር ውጤቶች ደግሞ በእንግሊዝኛ ቋንቋ የተጻፉ ናቸው፡፡ በአማርኛ ቋንቋ ከቀረቡት መካከል የመጀመሪያው መጣጥፍ፣ በኢትየጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ዘንድ ከጥንት ጀምሮ እየተተገበረ በኖረው፣ በብራና ጥበብ አሠራርና አዘገጃጀት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ የእስቴ ወረዳን በማሳያነት የተጠቀመው ይህ ጥናት፣ የብራና ጥበብ አሠራርና አዘገጃጀትን የሚያቀርብ ብቻ ሳይሆን፣ የሙያውን ሃይማኖታዊና ትውፊታዊ፣ ማኅበራዊና ባህላዊ እንዲሁም ታሪካዊ ገጽታ የሚያሳይ ነው፡፡

ሁለተኛው መጣጥፍ፣ የፎክሎር ጥናት የቤተ ክርስቲያንን ገዳማትና ቅዱሳት ቦታዎች በማስተዋወቅ ረገድ የሚያስተላልፈውን አዎንታዊና ገንቢ ሚና በማሳየት ላይ ያተኮረ ነው፡፡ ጥናቱ፣ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ጉዳዮች ላይ አተኩረው የተሠሩ ቀደምት የፎክሎር ጥናቶችን በመገምገም ባህላዊ ሁነቶችን፣ ንዋያተ ቅድሳትን፣ ገዳማትንና ቅዱሳት ቦታዎችን በጥልቀትና በስፋት ለመረዳት የፎክሎር ጥናቶች ጠቃሚ መሆናቸውን የሚያሳዩ ማስረጃዎችን ያቀረበ ነው፡፡ በዚህ ቅጽ ሥር የተካተተው ሦስተኛው መጣጥፍ ደግሞ ሃይማኖታዊና ታሪካዊ ፋይዳ ያላቸውን ሚኒራሎች ሳይንሳዊ በሆኑ ስሌቶችና ስልቶች ለመተንተን የቻለ ነው፡፡ እነዚህ ሚኒራሎች በዋናነት በቤተ መዘክርና ቤተ መዛግብት ውስጥ የሚገኙ ሲሆኑ፣ አብዛኛዎቹ በቤተ ክርስቲያን ባለቤትነት ሥር ያሉ ናቸው፡፡
አራተኛውና በእንግሊዝኛ ቋንቋ ከቀረቡት መካከል የመጀመሪያ የሆነው መጣጥፍ፣ የኢትዮጵያ ቤተ እምነቶች ካውንስል ከግጭት በኋላ የሚኖረውን ሚና የሚመረምር ነው፡፡ ጥናቱ በተለያዩ ቤተ እምነቶች ውስጥ ያሉ አማኞች ተከባብረው እንዲኖሩ ሃይማኖታዊ ተቋማት ያላቸውን ወደር-የለሽ ድርሻ የሚያስተዋውቅ ነው፡፡ የድጓ መጽሐፍን መነሻ አድርጎ የቀረበው አምስተኛው መጣጥፍ በቅዱስ ያሬድ ጽሑፎች ውስጥ የሚታየውን ስለ ቅድስት ሥላሴ የነገረ ቤተ ክርስቲያን አስተምህሮን (Trinitarian Concept of Ecclesiology) የሚያሳይ ነው፡፡ መጣጥፉ ድጓን፣ መጽሐፍ ቅዱስንና ሃይማኖተ አበውን እንደ ማስረጃ በመጥቀስ የቤተ ክርስቲያንን ዶግማዊ አስተምህሮን የሚመረምር ነው፡፡
ቅጹ ከእነዚህ አምስት መጣጥፎች በተጨማሪ በብፁዕ አቡነ ሳሙኤል የተጻፈውንና Sodomites and the Wage of Sin በሚል ርእስ የቀረበውን መጽሐፍ የዳሰሰ ግምገማም አካቷል፡፡ ይህ ግምገማ በመጻሕፍት ላይ አተኩረው ትንተና በማድረግ ከቀረቡ ቀዳሚ የመጻሕፍት ግምገማዎች በተለየ መልኩ ትኩረቱን ያደረገው ጸሓፊውን ቃለ መጠይቅ በማድረግ አነሳሽ ምክንያታቸውንና ሐሳባቸውን ለመረዳት በመሞከር ላይ ነው፡፡ ገምጋሚው የተከተሉት ስልት መጽሐፉን ምዕራፍ በምዕራፍ በመዳሰስ የመጽሐፉን አጠቃላይ ጠንካራና ደካማ ጎን ለአንባቢ ማሳየት ነው፡፡
ማኅበረ ቅዱሳን ከሁሉ በፊት የእነዚህን ጥናታዊ ጽሑፎች ባለቤቶች፣ ገምጋሚዎች፣ ተባባሪ አርታዒዎችና የአርትዖት ኮሚቴ አባላት እንዲሁም በዚህ የኅትመት ሂደት ውስጥ የተሳተፉ አገልጋዮችና ባለሙያዎች በሙሉ ይህ ቅጽ አሁን ያለበት ደረጃ እንዲደርስና ፍሬ እንዲያፈራ ላደረጉት ያላሰለሰ ጥረትና እገዛ ምስጋናውን ይገልጻል፡፡
የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ጥናት መጽሔትን ወደፊት የምናሳድገውና ዓላማችንን ከግብ ለማድረስ የምንችለው በሁላችን የጋራ ጥረትና ትብብር ነውና እገዛችሁ ወደፊትም አይለየን ይላል፡፡ ማኅበረ ቅዱሳን ይህ ቅጽ ለተመራማሪዎች፣ ለምሁራን፣ ለተማሪዎችና በቤተ ክርስቲያን ዙሪያ የሚነሡ ጉዳዮችን ለማወቅ ጉጉት ላላቸው ግለሰቦች ጠቃሚ የመረጃ ምንጭ ሆኖ እንደሚያገለግል ተስፋ ያደርጋል፡፡አሁን ዝግጅቱ የተጠናቀቀው ቁጥር ፰ የጥናት መጽሔት የፊታችን ቅዳሜ መጋቢት 14 ቀን 2016 ዓ.ም ይመረቃል።
በመጨረሻም፣ ይህንን መልካም አጋጣሚ በመጠቀም ለቤተ ክርስቲያናችን አባቶች፣ እናቶች፣ ወንድሞችና እኅቶች እንዲሁም ለተመራማሪዎች፣ በልዩ ልዩ ዘርፍ ለተሠማራችሁ መምህራንና ተማሪዎች፣ በቀጣይ ለሚዘጋጀው የጥናት መጽሔት. ቁ.፱ ጥናታዊ ጽሑፎችን በመላክ የበኩላችሁን ምሁራዊና ክርስቲያናዊ አስተዋጽኦ እንድታደርጉ በማኅበረ ቅዱሳን ጥናትና ምርምር ማእከል ስም ጥሪ ያቀርባል፡፡

ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርእሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀ ጳጳስ ዘአኵስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት በኢትዮጵያ የአርመን አምባሳደርን በጽሕፈት ቤታቸው ተቀብለው አነጋገሩ።
በኢትዮጵያ የአርመን አምባሳደር ሆነው የተሾሙት ሰሃክ ሳርግስያን (Sahak Sargsyan ) በዛሬው ዕለት ወደቅዱስነታቸው ቡራኬ የተቀበሉ ሲሆን የኢትዮጵያና የአርመን ግንኙነት፣ ህዝብ እንደ ህዝብ፣ ሀገር እንደ ከሀገር፣ ቤተክርስቲያንም እንደ ቤተክርስቲያ ታሪካዊ እንደሆነ አውስተው ይህቺ ዕለት ለእርሳቸው የተቀደሰች መሆኗን እንዲሁም በቅዱሱ የጾም ወር ቅዱሱን ፓትርያርክ በማግኘት መቀደሳቸውን ገልጸዋል።
ቅዱስነታቸውም ለክቡር አምባሳደሩ ባደረጉት የእንኳን ደህና መጡ ንግግር፡―"አርመን ታሪካዊት ሀገር ናት። የአርመን አምባሳደር ሆነው በመምጣትዎና የመጀመሪያው አምባሳደርም በመሆንዎ እንኳን ደስ አለዎት" ካሉ በኋላ የአርመኒያ ኦርቶዶክስ መሪ ወንድማቸውን ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ካረኪን 2ኛ የመላዋ አርሜኒያ ካቶሊኮስና የዓለም አብያተክርስቲያናት ፕሬዝዳንት ጤንነት፣ በአርመን የምትገኘዋ ቤተክርስቲያን ሰላም እና የክርስቲያኖችን ሕይወት ደህንነት ጠይቀዋቸዋል።

"የአርመን ኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን ከአኃት አብያተ ክርስቲያናት አንዷ በመሆኗ እርስዎም የአርመንን ህዝብ እና መንግሥት ወክለው በመገኘትዎ ወደ ሀገርዎና ወደ ህዝብዎ እንደመጡ ይቁጥሩት" በማለት አበረታተዋቸዋል። ቅዱስነታቸው አክለውም "የህዝብ ለህዝብ፣ ክርስቲያናዊ ግንኙነታችን በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ የተወጠነ/የተጀመረ ሲሆን በበለጠ በሦስቱን ዓለም አቀፍ ጉባዔያት ሃይማኖታዊና ቀኖናዊ ውሳኔዎች በመቀበል አንድ ቤተሰብ ሆነን እስከ ዚህ ዘመን እኅት ማማች (አኀት) ሆነን ቆይተናል። የአርመን ህዝብ በኦተማን ቱርክ ችግር ሲደርስበት ለጥቂቶቹም ቢሆን ኢትዮጵያ መጠለያ ሆናለች።" በማለት በሌሎችም መንፈሳዊ፣ ማኅበራዊ እና ልማታዊ ጉዳዮች ዙሪያ ውይይት አድርገዋል።
ምንጭ፡― የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት
ምንጭ፡― የብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ ልዩ ጽሕፈት ቤት
ሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት
አመራሮች ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር በወቅታዊ
የቤተክርስቲያን ጉዳይ ዙሪያ ተወያዩ
****
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን በሰንበት ትምህርት ማደራጃ መምሪያ ሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት አመራሮች በቤተክርስቲያናችን መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮች ዙሪያ ከቋሚ ሲኖዶስ ጋር ውይይት አደረጉ።
በውይይቱ ወቅት የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነቱ አመራሮች የቤተክርስቲያናችንን መንፈሳዊና አስተዳደራዊ ጉዳዮችን በተመለከተ ጥቅል ጥናታዊ ሰነድ ከመፍትሔ አቅጣጫ ጭምር ያቀረቡ ሲሆን ያቀረቡት ሰነድ በዝርዝር ተዘጋጅቶ፣
በማስረጃና በመረጃ ዳብሮ ችግሮቹን ደረጃ በደረጃ መፍታት በሚያስችል አግባብ እንዲቀርብ ቋሚ ሲኖዶስ አቅጣጫ ሰጥቷል።
ሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት አመራሮቹም ለቋሚ ሲኖዶስ ያቀረቡት ሰነድ ሁኔታዎችን ለማመላከት እንጂ ያለቀለት ሰነድ እንዳልሆነ ገልጸው ዝርዝር ጥናቱን፣የጥፋቱን መጠን፣ባለቤቱንና የመፍትሔ አቅጣጫዎቹን የሚያመለክት ዝርዝር ሰነድ በማዘጋጀት እንደሚያቀርቡ ገልጸዋል።
በውይይቱ ወቅትም ከቋሚ ሲኖዶስ አባላት ጥያቄና አስተያየት ተሰጥቶ ከሀገር አቀፍ የሰንበት ትምህርት ቤት አንድነት አመራሮቹ ምላሽ ተሰጥቶበታል።
ምንጭ: የ/ኢ/ኦ/ተ/ቤተክርስቲያን ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ

ምኵራብ፡- የዐቢይ ጾም ሦስተኛ ሳምንት
“ቦአ ኢየሱስ ምኵራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት፤ ወይቤሎሙ ምጽዋተ አበድር እመሥዋዕት፤ አነ ውእቱ እግዚኣ ለሰንበት ወአቡሃ ለምሕረት፤ እግዚኣ ውእቱ ለሰንበት ወልደ እጓለ እመሕያው፤ ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኵራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤ ከመሥዋዕት ይልቅ ምሕረትን እወዳለሁ፤ የሰንበት ጌታዋ የምሕረት አባቷም እኔ ነኝ፤ የሰው ልጅም የሰንበት ጌታዋ ነው።” (ጾመ ድጓ)
በኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ሦስተኛውን የዐቢይ ጾም ሳምንት “ምኵራብ” ይባላል። ቀጥተኛ ፍቺው “ኮረብታ፣ ተራራ የሚያህል ታላቅ ሕንጻ፣ ሰቀላ መሰል አዳራሽ” ሲሆን፣ የአይሁድ መካነ ጸሎት ወይም ቤተ መቅደስ በመሆን ያገለግል ነበር። በብሉይ ኪዳን አይሁድ ቤተ መቅደስ ነበራቸው፡፡
ናቡከደነጾር ኢየሩሳሌምን በወረረ ጊዜ ግን ቤተ መቅደሱን አፈረሰ፤ ሕዝቡን ወደ ባቢሎን አፈለሰ፤(፪ኛነገ.፳፬-፳፭፣ኤር.፬፥፯:፣፴፱፥፩-፲፣፶፪፥፩-፴) ከዚህ ጊዜ ጀምሮ አይሁድ በሚኖሩባቸው ሥፍራዎች ሁሉ ለጸሎት ቤት ይሠሩ ነበር፡፡ በዚያን ዘመን ቢያንስ ዐሥር አባ ወራዎች/የቤተ ሰብ ኃላፊዎች/ በቦታው ከተገኙ እነዚህን ምኵራቦችን ለመሥራት ይፈቀድላቸው ነበር፡፡ (Talmud Mishnah, Responsa literature, Jewish Encyclopedia, Academic Scholarly Works.) ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በኢየሩሳሌም እየተዘዋወረ በሚያስተምርበት ጊዜ ግን ብዙ ምኵራቦች ነበሩ፡፡ በሐዲስ ኪዳንም ለሐዋርያት በብዛት የስብከት ዓውደ ምሕረቶች ሆነው አገልግለዋል።

ምኵራበ አይሁድ በውስጡ የብራና የሕግ እና የነቢያት መጻሐፍት ይገኛሉ፡፡ ምእመኑ እንዲሰማቸው ከፍ ባለ መድረክ ላይ በመሆን መምህራንና ካህናት ቆመው መጻሕፍትን ያነባሉ፤ ቃለ እግዚአብሔርንም ያስተምሩ ነበር። የምኵራብ ሹማምንት አለቆች ጥፋተኛ ሰው ሊቀጡ ሥልጣን ነበራቸው፡፡ አገልጋይ ወይም የሚራዱ ወጣቶችም ልጆችን በማስተማር፣ በማቅረብ በተጨማሪ የአለቆችን ትእዛዝ በመፈጸም ያገለግላሉ፡፡
በሰንበት ሕዝብ ሁሉ በምኵራብ ተሰብስቦ ከሕግና ከነቢያት ንባብ፣ ስብከትና ቡራኬ በመቀበል አምልኮታቸውን ይፈጽሙ ነበር፡፡ ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዚህ ምኵራብ ተገኝቶ ሕዝቡን አስተምሯል፡፡ ቅዱስ ሉቃስ በወንጌሉ ”ወዳደገበትም ወደ ናዝሬት መጣ፤ እንደ ልማዱም በሰንበት ቀን ምኵራብ ገባ ሊያነብም ተነሣ” እንዳለ ቅዱሳት መጻሕፍትን ማንበብ፣ መማር፣ መመርመር፣መተርጎም፣ጉባኤ መሥራት አዘውትረው የሚፈጽሙት ተግባር እንደነበር ያስረዳል።(ሉቃ.፬፡፥፲፮)
ነገር ግን በምኵራብ ሰዎች ለተለያየ ዓላማ ይሰበሰቡ ነበር፡፡
፩. አማናዊ እረኛ ነው ብለው፦ ወልድ ዋሕድ ብለው ሲጠብቁት የነበረው ተስፋ “ደረሰልን፤ ወረደ፤ ተወለደ፤ የዓለም መድኃኒት እርሱ ነው” ብለው አዳኝነቱን አምነው ይከተሉታል። “ነዋ በግዑ ለእግዚብሔር ዘያአትት ወያሴስል ኃጢአተ ዓለም፤ የዓለሙን ኃጢአት የሚያስተሰርይ የእግዚብሔር በግ መሆኑን አውቀው የሚከተሉት አሉ። ”በጎቹም ድምፁን ያውቃሉና ይከተሉታል” እንዲል። (ዮሐ.፲፥፬)
፪. የቃሉን ትምህርት የእጁን ተአምራት ሽተው፦ ከደዌ ለመፈወስ ይሰበሰባሉ፤ ልብሱን ዳሰው፣ ወድቀው ሰግደው፣ ጥላውን ተጋርደው፣ በእጁ ተዳሰው የሚፈወሱ ነበሩ። (ማር. ፭፥፳፪ እስከ ፍጻሜ)። ጌታችን በዕለተ ሰንበት ሕዝብ በተሰበሰበበት በምኵራብ እንደሚያስተምር ያስረዳናል፤ ”ሰንበትም በሆነ ጊዜ በምኵራብ ያስተምር ጀመር፤…ወደ ምኩራባቸውም ገብቶ ዝም ይሉ ዘንድ ገሠፃቸው፤ እነርሱም ትምህርቱን፣ የቃሉን ግርማ፣ የአነጋገሩን ጣዕምና፣ የአንደበቱን ቅልጥፍና አደነቁ፡፡” (ማር.፮፥፩) “ወደ ገዛ አገሩም መጥቶ እስኪገረሙ ድረስ በሚገባቸው ያስተምራቸው ነበር።” (ማቴ.፲፫፥፶፬)
፫. ምግበ-ሥጋ ፈልገው ደም ግባቱን አይተው:- ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ከምኵራብ ጉባኤ ትምህርት በኋላ ጥቂቱን አበርክቶ እልፉን ይመግብ ስለነበር ጉባኤውን ይታደማሉ። ክርስቲያኖች እግዚአብሔርን የምናመልከው ምግበ ሥጋ ስለሰጠን አይደለም። እርሱንማ ለሕዝብም ለአሕዛብም ሳይሰስት የሚመግብ መጋቤ ዓለማት ነው። ክርስቲያን በመብል አይገመትም። “እንግዲህ በመብልም ቢሆን÷ በመጠጥም ቢሆን÷ በልዩ ልዩ በዓላትም ቢሆን÷ በመባቻም ቢሆን÷ በሰንበትም ቢሆን የሚነቅፋችሁ እንዳይኖር ተጠንቀቁ፡፡” እንዲል፡፡ (ቆላ. ፪፥፲፮ እስከ ፍጻሜ)
፬. ለክስ የሚቀርቡ አሉ፦ ከቃሉ ግድፈት ከትምህርቱ ስሕተት የሚፈልጉ ሰቃለያን አይሁድ፣ ሊቃነ ካህናት አምላክነቱን የሚጠራጠሩ አይሁድ የሸንጎውን ጌታ ለሸንጎ ፍርድ ሊያቀርቡት ከግር በግር ይከተሉት ነበር። “ወጸቢሖ ተጋብኡ ሊቃነ ካህናት ወጸሐፍት ወሊቃናተ ሕዝብ ወወሰድዎ ውስተ ዐውዶሙ። ወይቤልዎ እመ አንተሁ ክርስቶስ ንግረነ ገሃደ ወይቤሎሙ እመኒ አይዳእኩክሙ ኢተአምኑኒ፡፡ በነጋም ጊዜ፥ የካህናት አለቆች፥ ጻፎችና የሕዝቡ ሽማግሌዎች ተሰብስበው ወደ ሸንጎአቸው ወሰዱት፡፡ “አንተ ክርስቶስ እንደ ሆንህ በግልጥ ንገረን” አሉት፡፡እርሱም እንዲህ አላቸው፥ “ብነግራችሁም አታምኑኝም” እንዲል፡፡ (ሉቃ. ፳፪፥፷፮፣ ማቴ.፳፮፥፶፱)
ዛሬም በአማናዊቷ ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ሥጋዊ ነገር ብቻ ገዝፎባቸው ቤተ መቅደሱን ለንግድ፣ ንዋያተ ቅድሳትን ለትርፍ ብቻ አሳልፈው የሚሸጡ፣ የሚለውጡ፣ ለክስ የሚፋጠኑ ከምኵራብ ያልወጡ የበጎችን እረኛ አሳልፈው የሚሰጡ አዋልደ ይሁዳ እንዳሉ ግልጽ ነው። “ወረከበ በምኵራብ እለ ይሠይጡ አልህምተ ወአባግዐ ወአርጋበ …፤ በመቅደስም በሬዎችን፣ ላሞችን፣ በጎችን፣ ርግቦችን፣ የሚሸጡትን አገኘ …፤ “ኢትግበሩ ቤተ አቡየ ቤተ ምስያጥ ቤትየሰ ቤተ ጸሎት ይሰመይ፤ የአባቴን ቤት የንግድ ቦታ አታድርጉት፤ እናንተ ግን የሌቦች ዋሻ አደረጋችሁት፤ ቤቴስ የጸሎት ቤት ይባላል” እያለም የሃይማኖትን ቃል አስተማራቸው፡፡ (ዮሐ.፪፥፲፮፣ማቴ.፳፩፥፲፫)
በምኵራብ ይሸጡ፣ ይለውጡ የነበሩትን የገሠፀበት፣ ቤተ መቅደስን የከብት መንጃ የወርቅ መነገጃ ያደረጉ ሰዎችን ከእነ ሸቀጣቸው ከቤተ መቅደስ ያስወጣበት፣ ቤተ መቅደስ የእግዚአብሔር ማደሪያ፣ የመሥዋዕቱ መክበሪያ፣ የጸሎት ሥፍራ ምስካበ ቅዱሳን መሆኗን ያስተማረበት ዕለት ነው። ቃሉ በዚያን ዘመን ተነግሮ ብቻ ያለፈ አይደለም፤ ለእኛ የተነገረን መሆኑን አውቀን የባለቤቱ ጅራፍ ሳይገርፈን ልንመለስ ይገባል። “የገመድም ጅራፍ አበጅቶ ሁሉን በጎችንም በሬዎችንም ከመቅደስ አወጣቸው፥ የለዋጮችንም ገንዘብ አፈሰሰ ገበታዎቻቸውንም ገለበጠ፡፡” (ዮሐ.፪፥፲፬)
ከሚመጣው ጅራፍ ለመዳን እምነት ከተግባር ይዞ መገኘት ያስፈልጋል።” ወንድሞቻችን ሆይ÷ እምነት አለኝ፤ ምግባር ግን የለኝም የሚል ሰው ቢኖር÷ ምን ይጠቅመዋል? በውኑ እምነቱ ልታድነው ትችላለችን? ከወንድሞቻችን÷ ወይም ከእኅቶቻችን÷ የታረዙ ወይም የዕለት ምግብ ያጡ ቢኖሩ÷ ከእናንተም አንዱ …እንደዚሁም ሥራ የሌለው እምነት ቢኖር በራሱ የሞተ ነው።” እንዳለ። (ያዕ.፪፥፲፬ እስከ ፍጻሜ)
የዕለቱ መዝሙር (ከጾመ ድጓ)፦ ቦአ ኢየሱስ ምኩራበ አይሁድ ወመሐረ ቃለ ሃይማኖት፤ጌታችን ኢየሱስ ወደ አይሁድ ምኩራብ ገባ፤ የሃይማኖት ቃልን አስተማረ፤
መልእክታት፦(ቆላ.፪፥፲፮ እስከ ፍጻሜ) (ያዕ.፪፥፲፬ እስከ ፍጻሜ)
ወንጌል፦ (ዮሐ.፪፥፲፪-እስከ ፍጻሜ)
(የሐዋ.፲፥፩-፰)
ምስባክ፦ “እስመ ቅንዐተ ቤትከ በልዐኒ፡፡ ትዕይርቶሙ ለእለ ይትዔየሩከ ወድቀ ላዕሌየ፡፡ወቀጻዕክዋ በጾም ለነፍስየ፡፡” ትርጉም “የቤትህ ቅንዓት በልቶኛልና፥ የሚሰድቡህም ስድብ በለዬ ወድቆአልና፡፡ ሰውነቴን በጾም አደከምኋት፡፡ (መዝ.፷፰፥፱)
በምሕረቱ ይታደገን፤ ለእግዚአብሔር ምስጋና ይሁን፤ አሜን!!!