ፖሊ ግቢ ጉባኤ
3.9K subscribers
1.89K photos
35 videos
103 files
311 links
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖሊ ግቢ ጉባኤ መርሃግብራትና፤ ወቅታዊ የግቢ ጉባኤው መረጃዎች የሚቀርቡበት ቻናል ነው።

ለሃሳብና አስተያየቶቻችሁ
☝️👉 @mkpolybot
ለመድሎተ አሚን ጥያቄዎቻችሁ
☝️👉 @NikiyamkBot
መጻሕፍትን ለማንበብ
☝️👉 @polylibrary
ላይ ያስቀምጡልን።
Download Telegram
ለምን የአብነት ተማሪዎች የደብረታቦር ዕለት ይዘክራሉ ? 🤔

በማቴዎስ ወንጌል ምዕራፍ ፲፯ ከቁጥር ፩-፱ ያለው የእግዚአብሔር ቃል :-

     ከስድስት ቀንም በኋላ ÷ ጌታችን ኢየሱስም ጴጥሮስን፣ ያዕቆብን እና ወንድሙንም ዮሐንስን ይዞ ወደ ረዥም ተራራ ብቻቸውን አወጣቸው። መልኩም በፊታቸው ተለወጠ፤ ፊቱም እንደ ፀሓይ በራ ልብሱም እንደ ብርሃን ነጭ ሆነ። እንሆም ሙሴና ኤልያስ ከርሱ ጋራ ሲነጋገሩ ታዩዋቸው።

ጴጥሮስም መልሶ ጌታችን ኢየሱስን ጌታ ሆይ በዚህ መኾን ለእኛ መልካም ነው ብትወድስ በዚህ ሦስት ዳስ አንዱን ለአንተ አንዱንም ለሙሴ አንዱንም ለኤልያስ እንሥራ አለ።

እርሱም ገና ይህን ሲናገር እንሆ ብሩህ ደመና ጋረዳቸው እንሆም ከደመናው ውስጥም ''በርሱ ደስ የሚለኝ የምወደው ልጄ ይህ ነው ርሱን ስሙት'' የሚል ድምፅ መጣ።

ደቀ መዛሙርቱም ሰምተው በፊታቸው ወደቁ እጅግም ፈርተው ነበር። ጌታችን ኢየሱስም ቀርቦ ዳሰሳቸውና ተነሡ አትፍሩም አላቸው። ዐይናቸውንም አቅንተው ሲያዩ ከጌታችን ከኢየሱስ ብቻ በቀር ማንንም አላዩም። በማለት ይነግረናል።

ይህ ዕለት ከተሰዓቱ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ ሲሆን በዚህ ወቅት ለሐዋርያት የክርስቶስ የባህርይ ልጅነት ከባህርይ አባቱ ተገልጧልና፣ እንዲሁም የባህርይ አምላክነቱን በመግለጥ በልባቸው የነበረውን ጥርጣሬ አስወግዶላቸዋልና፣ በተጨማሪም ነገረ ሥጋዌውን እንዲሁም ምስጢረ ሥላሴን ገልጦላቸዋልና።

የአብነት ተማሪዎችም አቤቱ በዚህ ዘመን ላለን ሐዋርያትን በመምሰል አርድዕተ ሊቃውንት ለሆንን ለእኛም ትምህርታችንን ግለጥልን፣ የራቀውን አቅርብልን የቀረበውንም አራቅልን በማለት በየዓመቱ ነሐሴ ፲፫ የደብረታቦር ዕለት ዝክር ይዘክራሉ።

ይህ ዕለትም በፖሊ ግቢ ጉባዔ አብነት ተማሪዎች በደመቀ እና በአማረ መልኩ ይከበራል ።

ለበዓሉ ማዘጋጃ ድጋፍ ለምታደርጉ :-
ንግድ ባንክ :-1000358173199
ተስፋሁን ገድፍ እሸቴ

እመሰ ረሳይኩኪ ቤተ ጉባዔ ለትርስዓኒ የማንየ
ወይጥጋዕ ልሳንየ በጉርዔየ   መዝ 136÷8

ትርጉም:-
  የአብነት ቤተ ጉባዔ ሆይ ብረሳሽ ቀኘ ትርሳኝ፣
ባላስብሽም ጉረሮየ ከተናጋየ ትጣበቅ።

እርስዎም ድጋፍ በማድረግ ፣ በዕለቱ በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ ❗️

⏰ሰዓት:- ምሽት 11:00
📆ቀን:- ነሃሴ 13/12/2018 ዓ.ም
🏛ቦታ:- አቡዬ ግቢ ጉባዔ አዳራሽ

አዘጋጅ :- ፖሊ ግቢ ጉባዔ አብነት ተማሪዎች

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤‍🔥7❤6⚡1👍1🥰1🙏1🕊1
እኔስ ቤቴ ናፈቀችኝ!!!😢

ቀኑ እየቀረበ ሲሄድ ትዝታዎቸ ተቀሰቀሱብኝ ናፍቆቴ ጨመረ በዕለቱ የሚካሄዱትን ሳስብ ሙልሙል ዳቦው ፣ ጠላው ፣ ቆሎው ፣ መዝሙሩ ፣ ጭውውቱ ኧረ ስንቱ ብቻ  ለመግለጽ ቃል ያጥረኛል ።

ይህን ናፍቆት ልታስታግስ ውድ ግቢ ጉባዔያችን :-
➥ ትምህርት
➥ ቅኔ
➥ መዝሙር
➥ እና ሌሎች ፕሮግራሞችን አዘጋጅታ እኛን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች ።

ይህን ሁሉ ካረገችልን ከእኛ ምን ይጠበቃል ?😊
በባህር ዳር አካባቢ ለምትገኙ በዕለቱ በመገኘት ፣ መገኘት ላልቻላችሁ ደግሞ ለዝክር ማዘጋጃ የሚሆን ከታች ባለው አካውንት የቻሉትን ድጋፍ በማድረግ የበረከቱ ተካፋይ ይሁኑ!!

እመሰ ረሳይኩኪ ቤተ ጉባዔ ለትርስዓኒ የማንየ
ወይጥጋዕ ልሳንየ በጉርዔየ   መዝ 136÷8


💳ንግድ ባንክ:-
1000358173199
ተስፋዬ ገድፍ እሸቴ
Username :- ደብረ ታቦር በዚህ ስምዎትን እና
screen shoot ይላኩልን ።

መልዕክቱን ለጓደኞቻችሁ በማጋራት ይተባበሩን!!

⏱ሰዓት:- ምሽት 11:00
📆ቀን:- 13/12/2018 ዓ.ም
🏛ቦታ :- አቡዬ ግቢ ጉባዔ አዳራሽ

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤‍🔥11❤5🥰1🎉1
በመጨረሻም ደረሰ !!


በየ አመቱ በድምቀት በግቢ ጉባኤያችን ለምናከብረው ከ፱ቱ የጌታችን ዓበይት በዓላት አንዱ ለሆነው መድህን ዓለም ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን ለወዳጆቹ ለሀዋርያት ጴጥሮስ ፣ ዮሀንስ እና ያዕቆብ እንዲሁም  በብሔረ ህያዋን ካሉት ኤለያስን እና ከአለፉት ሙሴን ጠቅሶ ነገረ - መለኮትን ለገለፀበት ትልቁ  የመገለጥ በዓል፤
             ደብረ- ታቦር 
እንኳን በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን
!!!

አቤት ምን ተሠምቷቸው ይሆን ፤ ጌታን በግርማ መለኮቱ ማየት እንዴት ያለ መታደል ነው?...🤔

እኛም የእናንተው ወድሞች እና እህቶች የ2018 ዓ.ም የፖሊ ግቢ ጉባኤ አብነት ትምህርት ከራሚ ተማሪዎች ይህን ከጥንት ከአባቶችችን ሊቃውንት ጀምሮ ሲዋረስ የመጣውን ትውፊታችን ለማስቀጠል እነዚህን :-

              ➥  ትምህርት
              ➥  ቅኔ
              ➥  መዝሙር
              ➥  ጭውውት

እና ሌሎችም አስተማሪ ፕሮግራሞች እያዘጋጀን ሽር ጉድ እያልን እንገኛለን ።

እርስዎም የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ  :-
ለሚኖረው ድምቅ ያለ ቤተሰባዊ መርሃ ግብር ማስኬጃ የሚሆን ፤ 
ፈቃደኛ የሆናችሁ  የቻላችሁትን በዚህ አካውንት በመላክ
ስንል እናሳስባለን ።

Account
CBE:- 1000358173199
ተስፋሁን ገድፍ እሸቴ
Username : ደብረ ታቦር

በዚህ ሙሉ ስማችሁን  እና screen shoot ይላኩልን ይደርሰናል
ለታሪክ ይቀመጣል!!

መልዕክቱን ለሁሉም ወንድሞች እና እህቶች አድርሱልን !!

        

🏛ቦታ ፡   አቡዬ ግቢ ጉባኤ አዳራሽ
📅ቀን:    13/12/2018 ዓ.ም
🕰 ሰዓት ፡  10፡30 - 12፡30 AM
          
────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊግቢ ጉባኤ
❤10❤‍🔥1🆒1
ተኩሳችሁት የማታውቁትን ጅራፍ ለማጮህ ዝግጁ ናችሁ? 💥

በዕለቱ ኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ መለኮቱን በደብረ ታቦር ተራራ ሲገልጥ፣ ልጆቻቸው ወደ ኋላ የቀሩባቸው የተጨነቁ ወላጆች ሙልሙል ና ችቦ ይዘው በዚያ በሌሊት ሊፈልጓቸው ወጥተው ነበር።

እኛም ዛሬ በፖሊ ግቢ ጉባኤ የአብነት ትምህርት ለመማር ግቢ የቀረነው እህትና ወንድሞቻችሁ፣ በዓሉን ለማክበር ወደ እኛ ለሚመጡ ተማሪዎችና ኦርቶዶክሳውያን የሚሆን፡

◉ የትምህርት

◉ የቅኔ

◉ የመዝሙር እና

◉  የጭውውት ..........ሙልሙላችንን በኮባ እንደተጠቀለለ ትኩሱን ይዘንላችሁ ለመቅረብ ዝግጅታችንን ጨርሰናል!

እናንተም በቤታችሁ ሆናችሁ በረከቱ እንዳያልፋቹ ለዚህ ታላቅ የዝክር ዝግጅት ማካሄጃ የሚሆን የተወሰነ ገንዘብ ስለሚያስፈልገን
የእገዛ ጅራፋችሁን እንድታጮሁ እንፈልጋለን።

ተኩሳቹት የማታውቁትን ጅራፍ ለማጮህ ዝግጁ ናችሁ ?

እንግዲያውስ ከታች👇 ያለውን አካውንት  እየተጫናችሁ

💳 CBE :
1000358173199
👤 ተስፋሁን ገድፍ እሸቴ

📲 Telegram :- ደብረ ታቦር  (ስምዎን እና የላኩበትን Screen Shot እዚህ ይላኩልን)
የላካችሁትን የብር መጠን የሚያሳይ screenshot ስትልኩልን አካውንታችን "ጣጣጣጣ!" ብሎ እንዲጮህ አድርጉት! ድምፅ የሌለው ጅራፍ እኮ ጅራፍ አይደለም!😉



📍 ቦታ፡ አቡዬ ግቢ ጉባኤ አዳራሽ

📅 ቀን፡ ነሐሴ 13 / 2018 ዓ.ም

⏰ ሰዓት፡ ከምሽቱ 10:30 ጀምሮ

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባዔ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤9⚡4❤‍🔥1✍1🆒1
💥ደብረ ታቦር💥

"አሐደ ለከ ወአሐደ ለሙሴ ወአሐደ ለኤልያስ ንግበር ማኅደረ"

                                    ማቴ ፲፯፥፬

እንኳን ለታላቁ በዓል ለበዓለ ደብረ ታቦር በሰላም አደረሳችሁ!!

እነሆ የፖሊ ግቢ ጉባኤ ይህንን ከዘጠኙ ዐበይት በዓላት መካከል አንዱ የሆነውን የደብረ ታቦር በዓል በታላቅ ድምቀት ያከብራል። ስለሆነም ሁላችሁ በግቢያችን እና ባህር ዳር አካባቢ ያላችሁ ኦርቶዶክሳዊያን ተማሪዎች በዓሉን አብረን በአንድነት እናክብር ስንል በክርስቶስ ፍቅር ጠርተናችኋል።

"ታቦር ወአርሞንኤም በስመ ዚአከ ይትፌሥሁ"  መዝ ፹፱፥፲፪

እርስዎ ሲመጡ ፣ ጓደኛዎን ኩሽ ይበሉት : በአንድነት በዓሉን እናክብር !!!

⏰ ሰዓት፡ ከምሽቱ 10:30 ጀምሮ

📅 ቀን፡ ዛሬ ነሐሴ 13 / 2018 ዓ.ም

⛪️ ቦታ፡ አቡዬ ግቢ ጉባኤ አዳራሽ

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤6❤‍🔥1
ሞት በጥር በነሀሴ መቃብር እነዴት ይሆናል ቢሉ?🤔


ቅዱሳን ሐዋርያት የእመቤታችንን የከበረ ሥጋዋን ገንዘውና ከፍነው ለማሳረፍ ወደ ጌቴሴማኒ መካነ ዕረፍት  ይዘው ሲሄዱ አይሁድ በቅንአት መንፈስ ተነሣሥተው

ቀድሞ ልጇን በሦስተኛው ቀን ከሙታን ተነሣ፤ በዐርባኛው ቀን ወደ ሰማይ ዐረገ እንደገናም ተመልሶ ይህን ዓለም ለማሳለፍ ይመጣል እያሉ ሲያውኩን ይኖራሉ፡፡ አሁን ደግሞ እርሷንም እንደ ልጇ ተነሣች፣ ዐረገች እያሉ ሲያውኩን ሊኖሩ አይደለምን?


ኑ ተሰብሰቡና ሥጋዋን በእሳት እናቃጥላት ብለው ተማክረው መጡ፡፡ ታውፋንያ የሚባል አይሁዳዊ የከበረ ሥጋዋን የተሸከሙበትን የአልጋ ሸንኮር በድፍረት ያዘ፡፡

የእግዚአብሔር መልአክ በእሳት ሰይፍ ሁለት እጆቹን ቆረጣቸው፡፡ እጆቹ ተንጠልጥለው ከቆዩ በኋላ በእውነት የአምላክ እናት ናት በማለት ስለ አመነ እጆቹ ተመልሰው እንደነበሩ ሆነውለታል፡፡ ከዚህ በኋላ መልአከ እግዚአብሔር የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ ከሐዋርያው ዮሐንስ ጋር ነጥቆ ወስዶ በገነት ከዕፀ ሕይወት ሥር አስቀመጠው፡፡

ቅዱስ ዮሐንስም ከጥቂት ጊዜ በኋላ ወደ ሐዋርያት ሲመጣ የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ በገነት መኖሩን ነገራቸው፡፡ ሐዋርያትም የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ አግኝተው ለመቅበር በነበራቸው ምኞትና ጉጉት ዮሐንስ አይቶ እኛ እንዴት ሳናይ እንቀራለን ብንጠየቅስ ምን እንመልሳለን በማለት በነሐሴ አንድ ቀን ሱባኤ ጀምረው ሲጾሙና ሲጸልዩ ከሰነበቱ በኋላ በ14 ቀን ጌታችን የእመቤታችንን ትኩስ የከበረ ሥጋ አምጥቶ ስለሰጣቸው በታላቅ ዝማሬ፣ በውዳሴ ወስደው ቀድሞ በተዘጋጀው መካነ ዕረፍት በጌቴሴማኒ ቀበሯት፡፡

የእመቤታችን የቀብር ሥነ ሥርዐት በተፈጸመ ጊዜ ከ12ቱ ሐዋርያት አንዱ የሆነው ቅዱስ ቶማስ አልነበረም፡፡ ከሀገረ ስብከቱ በደመና ተጭኖ ወደ ኢየሩሳሌም ሲመጣ፣ እመቤታችን በተቀበረች በሦስተኛው ቀን እንደ ልጇ ትንሣኤ ተነሥታ ስታርግ ያገኛታል፡፡

ቀድሞ የልጅሽን አሁን ደግሞ የአንቺን ትንሣኤ ሳላይ ቀረሁ ብሎ ቢያዝን እመቤታችን ከእርሱ በቀር ሌሎች ሐዋርያት ትንሣኤዋን እንዳላዩ ነግራው ቅዱስ ቶማስን አጽናናችው፡፡ ሄዶም ለሐዋርያት የሆነውን ሁሉ እንዲነግራቸው አዝዛው ለምልክት ይሆነው ዘንድ የተገነዘችበትን ሰበኗን ሰጥታው ወደ ሰማይ ዐርጋለች፡፡

  ቅዱስ ቶማስም ሐዋርያት ወደ አሉበት ኢየሩሳሌም በደረሰ ጊዜ የእመቤታችን ነገር እነዴት ሆነ? ብሎ ቢጠይቃቸው፤ እመቤታችንን እኮ ቀበርናት ብለው ነገሩት፡፡ እርሱም ዐውቆ ምስጢሩን ደብቆ
አይደረግም ሞት በጥር በነሐሴ መቃብር እንደምን ይሆናል?»


አላቸው፡፡ ቅዱስ ጴጥሮስ አንተ መጠራጠር ልማድህ ነው፡፡ ቀድሞ የጌታን ትንሣኤ ተጠራጠርክ አሁንም አታምንም ብሎ የእመቤታችን መካነ መቃብር ሊያሳዩት ይዘውት ሔዱ፡፡ መቃብሩን ቢከፍቱ የእመቤታችንን የከበረ ሥጋ አጡት፤ ደነገጡም፡፡

በዚህ ጊዜ ቅዱስ ቶማስ አታምኑኝም ብዬ ነው እንጂ እመቤታችንስ ተነሥታ ዐርጋለች ብሎ የሆነውን ሁሉ ተረከላቸው፡፡ ከዚያም ምልክት እንዲሆን የሰጠችውን ሰበኗን አሳያቸው፡፡ እነርሱም ማረጓን አምነው ሰበኗን ለበረከት ከተከፋፈሉ በኋላ ወደየአህጉረ ስብከታቸው ሄዱ፡፡

ከተመችዎ ለጓደኞችዎ ሸር ያድርጉ !

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባዔ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤24❤‍🔥4🌭1
እንኳን አደረሳችሁ 🙏

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ነሐሴ ሃያ አንድ በዚች ቀን አምላክን በሥጋ የወለደች የእመቤታችን ድንግል ማርያም የበዓሏ መታሰቢያ ነው :: እርሷ ስለእኛ ሁልጊዜ ትማልዳለችና ::

ለእግዚአብሔርም ምስጋና ይሁን የሕይወትና የድኅነት ወደብ ትሆነን ዘንድ እርሷን እናቱን ስለሰጠን በረከቷም በሁላችን የክርስቲያን ወገኖች ላይ ይደር ለዘላለሙ አሜን ::

ሰላም ለኪ ለዘእምኔኪ ወጽአ :: ዘያድኅን እግዚእ እንስሳ ወሰብአ :: በቍስለ ኃጢአት ሥጋየ አመ በኁበኁ ወጽአ::ኢረከብኩ ማርያም እንበሌኪ አሐደ ባቃዐ::አመ ኢገበርኪ ሊተ ሐዲሰ መልክዐ ::

ስንክሳር ዘወርኀ ነሐሴ ፳፩

መፅሐፍትን በማንበብ መንፈሳዊ ዕውቀትዎን ያሳድጉ!!!

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤12
አይ መታደላችን

ሰላም ውድ የፖሊ ግቢ ጉባዔ አባላት እንዴት ናችሁ 👋  እነሆ ክረምቱ አልፎ  መስከረም ሲመጣ አንድ ነገር ያጓጓናል እርሱም ጌታችን መድሀኒታችን እዮሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ ላይ የተሰቀለበት የመስቀል በዓል ነው ። እርሱንም ምክንያት በማድረግ እናት ግቢ ጉባዔ ለእናንተ በሚመች መልኩ በዓሉን ለማክበር ዝግጅቷን ከዛሬው እንዲሁ ትጀምራለች ።

እንዴት ?

➥ለበዓሉ የሚሆኑ መዝሙሮችን በመምረጥ
➥ የመዝሙር ጥናቶችን በ Online በመጀመር

እናታችን እንዲህ ከተዘጋጀች እኛ ደግሞ በተባለው ሰዓት እና ቦታ በመገኘት መዝሙሩን እናጥና ፣ እግዚአብሔርን እናመስግን !!!

⏰ሰዓት:- ማታ ከ3:00 እስከ 4:15 pm
📆ቀን:- ማክሰኞ እና እሁድ ከ 26 ጀምሮ
⛪️ቦታ :- በOnline ዜማ ክፍል Channel

እርስዎ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ፣ጓደኛዎን አይርሱ!!👬

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤8
አይ መታደላችን

ሰላም ውድ የፖሊ ግቢ ጉባዔ አባላት እንዴት ናችሁ 👋  እነሆ ክረምቱ አልፎ  መስከረም ሲመጣ አንድ ነገር ያጓጓናል እርሱም ጌታችን መድሀኒታችን እዮሱስ ክርስቶስ በቀራንዮ ላይ የተሰቀለበት የመስቀል በዓል ነው ። እርሱንም ምክንያት በማድረግ እናት ግቢ ጉባዔ ለእናንተ በሚመች መልኩ በዓሉን ለማክበር ዝግጅቷን ከዛሬው እንዲሁ ትጀምራለች ።

እንዴት ?

➥ለበዓሉ የሚሆኑ መዝሙሮችን በመምረጥ
➥ የመዝሙር ጥናቶችን በ Online  በመጀመር

እናታችን እንዲህ ከተዘጋጀች  እኛ ደግሞ  በተባለው ሰዓት እና ቦታ በመገኘት መዝሙሩን  እናጥና  ፣ እግዚአብሔርን እናመስግን !!!

⏰ሰዓት:- ማታ ከ3:00  እስከ  4:15 pm
📆ቀን:- ማክሰኞ እና እሁድ ከ 26 ጀምሮ
⛪️ቦታ :- በOnline ዜማ ክፍል Channel

እርስዎ እግዚአብሔርን ሲያመሰግኑ፣ጓደኛዎን አይርሱ!!👬

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤‍🔥5
❤5👏4❤‍🔥2☃1
ሰዓታት ቀሩት!

⏰ሰዓት : - ምሽት 3:00 - 4:15 pm
📲ቦታ:- በOnline Telegram ላይ

መዝሙር ለማጥናት ተዘጋጅተናል እያላችሁ በኮሜንት ፃፉልን!!!


────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
ወንድማችን እንዲህ አለን!


ዛሬ ጧት ከጓደኞቼ ጋር ቤተክርስቲያን ሂደን ስንመለስ ቁርስ እንብላ ብለን ወደ አንድ ካፌ አመራን።  ከደረስንም በኋላ ምግብ አዘዝን ምግባችን እስኪደርስ አንዳንድ ወጎዎችን እያዎጋን እያለ ከመሀላችን አንድ ወንድማችን ነገ ግን መዝሙር እናጠናለን አይደል? አለን ።

ማለት!  የት ነው የምናጠናው ግቢ ጉባዔ እንደሁ ሁሉም ወደ ቤተሰብ እንደሄዱ አልተመለሱም ነው  አንተ ያዘጋጀኸው ቦታ አለህ ? ብለን በጥያቄ ስንዘው ።

እንዴ!  አልሰማችሁም የመስቀል መዝሙር ጥናት እኮ በቴሌግራም ተጀምሯል  ብሎ ክው አደረገን እላችኋለሁ!

👉ግን መቼ መቼ እና በየትኛው ግሩፕ ነው ? ብለን ስንጠይቀው በዚህ የፖሊ ግቢ ጉባዔ መዝሙር ጥናት በቴሌግራም  በሚለው ነው  ፧ እንዲያውም ነገ ሁለተኛ ቀን ነው ብሎ ነገረን ።

ከዚያም ያዘዝነው ምግባችን ደረሰልን ምግባችንን ተመግበን ከጨረስን በሗላ ነገ ማታ የመስቀል መዝሙር ልናጠና ተነጋግረን "ሰላመ እግዚአብሔር አይለየህ ፣አይለየን " ተባብለን ተለያየን ።


⏰ሰዓት : - ምሽት 3:00 - 4:15 pm
📲ቦታ:- በOnline Telegram ላይ

ኑ ምስጉን እግዚአብሔርን በአንድነት እናመስግን !!!

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤10❤‍🔥2⚡1🕊1
ከማስታወቂያዎች ሁሉ የተለየች ማስታወቂያ ✍️


ስራ ፈላጊ ነኝ ከተመረኩ ብዙ ወራቶች አለፉ እኔም ከዛሬ ነገ ስራ አገኛለሁ እያልኩኝ ማስታወቂያ በተለጠፈበት ሁሉ ስዞር እውላለሁ ። ዛሬ ግን ያልጠበቁት አዲስ ነገር ገጠመኝ ።

ማስታወቂያውም እንዲህ ይላል :-
ውድ ኦርቶዶክሳውያን እንኳን ለአዲሱ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ ፣አደረሰን እያልን መስከረም 17 ለምናከብረው የመስቀል በዓል የሚሆን መዝሙር ጥናት በOnline ጀምረናል። ስለሆነም የእጅ ስልክዎን እና Internet በመጠቀም አብረን እድናጠና ስንል በእግዚአብሔር ስም እናስባለን ።

ይላል እኔም ሳየው ቢያንስ ዛሬ አዕምሮዬ ተረጋግቶ ያመሻል ብዬ በሰዓት ተገኝቼ ለማጥናት ወሰንኩ እላችኋለሁ ። ግን እንዴት ነው አብረን አናጠናም? ....

⏰ሰዓት : - ምሽት 3:00 - 4:15 pm
📆 ቀን :- ዘወትር ማክሰኞ እና እሁድ
📲ቦታ:- በOnline Telegram ላይ


በሰዓቱ Online በመገኘት እግዚአብሔርን እናመስግን !!!

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤12❤‍🔥2
ተመላሾች ሆይ! 😁👋

እንኳን ለ2019 ዓ.ም አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ!
ለመሆኑ አንድ ነገር አስተውላችኋል? ከጣት ጣት ይበልጣል ከአመትም አመት ይበልጣል ኋኗል ነገሩ ... ! ይሄ ዛሬ የምንቀበለው አዲስ ዓመታችን (2019) የምስራች አብሳሪው የቅዱስ ገብርኤልን ቁጥር (፩፱) የያዘ መሆኑን? . . . ይሄው እኛ  እናስታወስናችሁ! 🤗

እንደ መልአኩ የምስራች ቃል፣ መጪው ዓመት ያማረ፣ የሰመረና በበረከት የተሞላ ውብ ዓመት እንዲሆንልን ተመኘንላችሁ።

🏵️🏵️🏵️ መልካም አዲስ ዓመት! 🏵️🏵️🏵️

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
🙏32❤13❤‍🔥3
አዋጅ አዋጅ ህዝቤ ሆይ
ማርቆስ ተሽሮ ፣ ሉቃስ ነግሷል !


ሰላም ውድ የፓሊ ግቢ ጉባዔ አባላት በሙሉ እንኳን ለ2019 አዲስ ዓመት በሰላም አደረሳችሁ 🤗ዓመቱ የሰላም፣ የፍቅር ፣ የመተሳሰብ ፣የአንድነት እና የንስሐ ዘመን ያድርግላችሁ ፣ ያድርግልን ።

ዘወትር ማክሰኞ እና እሁድ የሚካሄደው የOnline መዝሙር ጥናት እንደቀጠለ ነው ።


⏱ሰዓት : - ምሽት 3:00 - 4:15 pm
📲ቦታ:- በOnline Telegram ላይ

በሰዓት በመገኘት መዝሙሩን እናጥና ፣ እንማር !!

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤8🤗4❤‍🔥2
ኑ እየጠበኳችሁ ነው!!!

ኢየዐቁር እክለ ገብረ መንፈስ ቅዱስ መሥነቅት ፤
አኮኑ ተሠጠ በመንፈስ ቅዱስ መጥባሕት ።

ትርጉም ፥

ገብረ መንፈስ ቅዱስ/አቅማዳ እህልን አይቋጥርም ፤
በመንፈስ ቅዱስ/ካራ ተቀዷልና ።

ሰላም ውዶች እንዴት ናችሁ 👋 እንኳን ለጻድቁ አባታችን ለአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወርኃዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ ።

ከጻድቁ አባታችን ከአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ረድኤት በረከት ያሳትፈን ።

እንኳን አደረሳችሁ እያላችሁ በኮሜንት ይጻፉልን !

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
🙏7❤‍🔥2
🎉 የምስራች! 🎉

የ2019 የትምህርት ዘመንን አብረን ለመጀመር ዝግጁ ናችሁ?

አዎ! ከሆነ መልሳችሁ... እኛም የግቢ ጉባኤ እህትና ወንድሞቻችሁ ከግቢው ጋር በመተባበር እናንተን በፍቅር ለመቀበል ዝግጅታችንን ጨርሰናል!

እውነት ለመናገር ቢቻለን እያንዳንዳችሁን ከየቤታችሁ ደጃፍ pick ብናደርጋችሁ ደስ ባለን ነበር 😉፤ ነገር ግን ከተለያዩ ክፍለ ሀገራትና ከተሞች የምትመጡ ተማሪዎችን ከመናኸሪያና ከኤርፖርት ምንም መንገላታት ሳያጋጥማችሁ እንደ እንቁላል ተንከባክቦ ግቢ ለማድረስ መኪኖችን አዘጋጅተናል።
ስለሆነም ከሃሙስ መስከረም 7 እስከ መስከረም 8 ድረስ በሚከተሉት ቦታዎች እንጠብቃችኋለን፡

📍 አዲሱ መናኸሪያ

📍አሮጌው መናኸሪያ

📍 ኤርፖርት

⏰ የትራንስፖርት ሰዓት:

አገልግሎቱ ጠዋት 2:00 ሰዓት ላይ የሚጀምር ሲሆን፣ በየ 4 ሰዓት ልዩነት ይመላለሳል! (ምሳሌ፡ ጠዋት 2:00፣ ቀትር 6:00፣ ከሰዓት 10:00...)

ስለዚህ በተጠቀሱት ቀናት ከተገለጹት ቦታዎች በአንዱ ተገኝታችሁ አገልግሎቱን ተጠቀሙ።

እግዚያብሔር አምላክ በሰላም ያገናኘን! 🕊️🌿

ይህ መረጃ ለሌሎች ተማሪዎች እንዲደርስ Share ማድረጋችሁን እንዳትረሱ!

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤17❤‍🔥1👍1
የመስቀል መዝሙር ጥናት ጥሪ!


እነሆ በOnline ሲካሄድ የነበረው የመስቀል መዝሙር ጥናት በግቢ ጉባዔያችን መሰጠት ጀመረ ። ስለሆነም ሁላችንም በአንድነት ተገኝተን አምላካችንን  በምስጋና እናስብ ።

   ኑ እግዚአብሔርን እናመስግን !!!

🕰ሰዓት 11:15 -12:30Pm
📆ቀን:- ቅዳሜ መስከረም 9/01/2019 ዓ.ም
🏛ቦታ:- አቡዬ ግቢ ጉባዔ አዳራሽ

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤7⚡1
❌ ማንበብ ክልል ነው!!!

ውድ የፖሊ ግቢ ጉባዔ አባላት እንኳን ደህና መጣችሁ ? እነሆ ልዩ የሆነ ፕሮግራም ከኤትዝም እስከ ክርስትና በሚል ርዕስ :-

❶ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምህሮ
   ➥የዶግማ ፣የስርዓትና የታሪክ መሰረቶች
   ➥የተዋህዶ እምነት መገለጫዎች

❷ የኦርቶዶክስ ተዋህዶ አስተምህሮ ከሌሎች ዕምነቶች አንፃር :
  ➥ከካቶሊክ እና ፕሮቴስታንት አንፃር ፣
           ◇የታሪክ ፣የዶግማ እና የስርዓት ልዩነቶች
  ➥ከቅብዓት አስተምህሮ አንፃር ፣
         ◇የታሪካዊ እና የነገረ ክርስቶስ ማብራሪያ
  ➥ከእስልምና አንፃር ፣
        ◇የነገረ መለኮትና የሀይማኖት መሠረቶች ንፅፅር
  ➥ከኤትዝም አንፃር ፣
       ◇የፈጣሪ ህልውና ፣የዓለም አመጣጥ

እነዚህን በመሳሰሉት አጓጊ እና መሰረታዊ በሆኑ የሃይማኖት ትምህርቶች በእንቁ መምህሮቻችን ለየት ባለ መልኩ ይሰጣል ። ታዲያ እርስዎስ ምን ያስባሉ ? መቼስ ነው ፕሮግራሙ ?

ኑ አብረን እንማር ፣ ሃይማኖታችንን እንዎቅ !!!

⏰ሰዓት:- ምሽት 11:20Am - 1:00Pm
📆 ቀን :- ለተከታታይ 4 ቀናት ከሰኞ - ሃሙስ (11- 14/01/2019 ዓ.ም)
🏛ቦታ:-  አቡዬ ግቢ ጉባዔ አዳራሽ

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤14☃1🕊1
ማርያም አታማልድም! ⁉️❔


... አትደንግጡ!

እኔም የመጀመሪያው ቀን ይህንን ስሰማ ልክ እንዳሁኑ ክው ብዬ ነበር። አሁን ግን ነገሩን በጥልቀት ስላወቅኩት እና ስለ እናንተም ስለማስብ፤ አንድም ሳላስቀር ልነግራችሁ መጣሁ።


በየመንገዱ "ወንድሜ/እህቴ ኢየሱስ ይወድሃል... ጌታን ተቀበል" እያሉ ጆሯችንን የሚያደሙ ሰዎች ከመጡ ዓመታት ተቆጥረዋል።


አሁን ደግሞ መልካቸውን ቀይረው የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎችን ድክመት እንደ መልካም አጋጣሚ በመጠቀም በየዶርሙ ከሌሎች እምነት ተከታይ እህትና ወንድሞቻችን የሚሰነዘሩ ጥያቄዎች እና ሀሳቦች ግራ ማጋባታቸውን ቀጥለዋል።


ስለዚህ ለነዚህ ጥያቄዎች ሁሉ ግልጽ መልስ የምናገኝበት እና እምነታችንን በዕውቀት የምንረዳበት ልዩ የመንፈሳዊ ትምህርት መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል!

✨በትምህርቱ የምንዳስሳቸው ዋና ዋና ርዕሰ ጉዳዮች፡

1️⃣ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ
●የዶግማ ፣የስርዓት  እና የታሪክ መሰረቶች

●የተዋህዶ እምነት መገለጫዎች
2️⃣ የኦርቶዶክስ ተዋሕዶ አስተምህሮ ከሌሎች እምነቶች አንጻር


●ከካቶሊክ እና ፕሮቴስታንት አንጻር፡ የታሪክ እና የሥርዓት ልዩነቶች

● ከቅብአት አስተምህሮ አንጻር፡ የታሪካዊ እና የነገረ-ክርስቶስ ማብራሪያ

● እስልምና አንጻር፡ የነገረ-መለኮት እና የሃይማኖት መሠረቶች ንፅፅር

● ኤቲይዝም (Atheism) አንጻር ፡ የፈጣሪ ህልውና እና የዓለም አመጣጥ ጥልቀት ያለው ማብራሪ



ይሄን ከተማራችሁ  በኋላ

ማርያም አማላጅ እንደሆነች በደንብ ይገባችኋል  :)

🗓 ቀን፡ መስከረም 11 - 14 (ለተከታታይ 4 ቀናት

⏰ ሰዓት፡ ከምሽቱ 11:20 - 12:50

📍 ቦታ፡ ፖሊ ግቢ ጉባኤ አዳራሽ

አሁኑኑ ቀኑን ማስታወሻ ላይ ያዙ፤ ለዶርም ጓደኛዎም share በማድረግ ጋብዟቸው!
────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
❤15👏2🆒2☃1❤‍🔥1✍1🤔1