ፖሊ ግቢ ጉባኤ
3.58K subscribers
1.83K photos
35 videos
102 files
228 links
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖሊ ግቢ ጉባኤ መርሃግብራትና፤ ወቅታዊ የግቢ ጉባኤው መረጃዎች የሚቀርቡበት ቻናል ነው።

ለሃሳብና አስተያየቶቻችሁ
☝️👉 @mkpolybot
ለመድሎተ አሚን ጥያቄዎቻችሁ
☝️👉 @NikiyamkBot
መጻሕፍትን ለማንበብ
☝️👉 @polylibrary
ላይ ያስቀምጡልን።
Download Telegram
ጠቢቡ ንጉሥ “መካሪ የሌለው ሕዝብ ይወድቃል፤ በመካሪዎች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል” ብሎ እንደተናገረው (ምሳሌ 11፥14)
ውድቀት (ኃጢአት) ሳይመጣ በፊት ደኅንነትን (ድልን) ለማግኘት የመካሪ አስፈላጊነትን ይገልጻል። ወጣቶቹ በምክረ ካህን ጥላ ሥር ሲሆኑ ከውድቀት ይጠበቃሉ እንጂ ውድቀትን አይጠብቁም።

ማጠቃለያ
በዓለ ሃምሳን በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ስንመለከተው፣ የክርስቶስ ትንሣኤ ለሰው ልጅ የሰጠው ነጻነት በኃጢአት ባርነት እንድንመላለስ ሳይሆን፣ በጽድቅ ብርሃን እንድንመላለስ መሆኑን እንረዳለን። የግቢ ጉባኤ ወጣቶች ከጾም ማግስት የሚገጥማቸውን መንፈሳዊ ዝለት አሸንፈው፣ ይህን ታላቅ ወቅት በቅድስና ሊኖሩ ይገባቸዋል።

“በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።” ገላትያ ፭፥፩
​ነጻ ያወጣችሁ ጌታ በነጻነቱ ያጽናችሁ፤ በነፍሳችሁ ላይ የታተመው የትንሣኤው ብርሃን ደግሞ በኃጢአት ዝገት እንዳይጠፋ በጸሎትና በምክረ ካህን ጠብቁት።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ሃሳቡ ከተመቻችሁ ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉ!
────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
9
በአንድ ቀን ሁለት ደስታ 🥰

ሰሞኑን በፈተና ምክንያት በጣም ተወጥሬ ተጨንቄ እንቅልፍ አጥቼ ሰነበትኩ።
ግን እኮ እሚገርመው ፈተናው ደግሞ  አይቀናኝም እንደዚያ እንቅልፌን ትቸ !

በዚህ ምክንያት ተናድጄ ባለሁበት ሰዓት  አንድ ነገር ትዝ አለኝ እሱም ምንድን ነው ብትሉኝ ፈተናው ሊያልቅ አንድ ቀን  ቀርቶታል ለካ ። ደስ አይልም ?

በዚያ ተደስቸ ደስታዬን ሳልጨርስ ሌላ አዲስ ደስታ ደግሞ ሹክ  አሉኝ ፣ምንድን ነው አትሉኝም ? ምን ይሆን?

ለየት ያለ ፣መንፈስ አዳሽ የሆነ የበገና ምሽት በፖሊ ግቢ ጉባዔ ዜማና  ኪነ ጥበብ ክፍል የተዘጋጀ ፕሮግራም እንዳለ ነገሩኝ ፣ በዚህ ተደስቼ ያቺ ቀን እስክደርስ ጓጓሁ!

እናም  ጮቤ እረግጨ ያችን ዕለት በደስታ እየተጠባበኩ ነው ፣ የደስታየ ተካፋዮች ሁኑልኝ፣ በዛች ዕለትም ሁላችን ተሰባስበን ይመርብን  🤗

ኑ እግዚአብሔርን በመዝሙር  አብረን እናመስግን !!!

🏛  አቡዬ ግቢ ጉባዔ  አዳራሽ
🕰 11፡00
📅  17/09/2018  ዓ.ም

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
9🎉3
በዕለተ ማክሰኞ ከቀኑ 09:00 ሲል ለምናካሂደው ጠቅላላ ጉባኤያችን ዝግጁ ናችሁ?🤔



11111111
1111111111
1111111111111
111111111111111
111111
111111
111111
111111
111111
111111
111111
111111
111111
111111
1111111111111111111
1111111111111111111
ቀን ቀረው

፩,ማክሰኞ ከቀኑ 09:00 ሲል መርሀግብራችንን እንጀምራለን።

፪, presentation እና defense ያላችሁ ወንድም እህቶቻችን
👉 30 ደቂቃዎች👈 ብቻ


ሁላችን በጉጉት እና በፍቅር ለምንጠብቃት የመርሀግብራችን ዕለት ላይ ሁላችንንም ከቁጥር ሳያጎል በሰላም ያደርሰን ዘንድ ሁላችንም ባለንበት እንጸልይ።

ተመጉ ዘፖሊ

ሰዓቱ ሳይቀድምዎ ፣ ከቦታው ይድረሱ!

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
8❤‍🔥1👍1🥰1
ፈተና አልቋል ብየ ሳላይ አሳለፍኩት!

ፈተናውን ጨርሸ ከግቢ ለመውጣት ክሊራንስ በማስፈረም ላይ እያለሁ፣ሁለት ወንድሞች ዛሬ ግን ቤተክርስቲያን አንሄድም እንሄዳለን እየተበባሉ ሲነጋገሩ ሰማኋቸው ።

ከመሀል አንደኛው ግን ምን አለ ? ብሎ ይጠይቀዋል፣ ወንድሜ እንዴት ቴሌግራም አልገባህም ዛሬ ? አዎ አልገባሁም አለው ።ዛሬማ የመጨረሻው የስንብት መርሐ ግብር በአብነት ተማሪዎች አዘጋጅነት ተዘጋጅቷል ።

በመርሐ ግብሩም :-
➊ መመዝሙር
❷ ስነ ፅሑፍ
❸ ትምህርት እና
❹ የፀሎተ ማርያም መርሐ ግብር ያካትታል አለው ።

ከዚያም መለስ ብዬ ወደ ቴሌግራም ገብቸ ሳይ ግን አሳልፌዋለሁ ። አይ አልኩኝ በራሴ ......

የእግዚአብሔር ቸርነት የእመቤታችን አማላጅነት የቅዱሳን መላእክት ተራዳኝነት አይለየን።

ማሳሰቢያ: ዲያቆናት ቀደም ብላችሁ ዳዊት እየያዛችሁ እንድትገኙ።

እኔ እንዳሳለፍኩት ፣ ጓደኛዎን አይለፉ! 👬

ምሽት 11:00
📆 18/09/018 ዓም
🏛 ቤተ ያሬድ /ግቢ ጉባዔው አዳራሽ
────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
21😭2
ደረሰ  ደረሰ ደረሰ 🤔

ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችኹ መዝ 117÷26



ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የ2018 ተመራቂ ተማሪዎቻችን!

🔶ሁላችንም በጉጉት ስንጠብቀው የነበረው የተመራቂ ተማሪዎች የወረብ ዝማሬ ጥናት ሊጀመር ነው ፤ ማንኛውም ተመራቂ ማጥናት ስለሚችል ተቀሳቅሰን በሰአት እንድንገኝ ይሁን።


                          ብቻን መምጣት አይቻልም

ኑ! አብረን አጥንተን በምርቃታችን ዕለት ለአምላካችን በዝማሬ ምስጋናን እናቅርብ🤲

ሰዓት: 11:00
📅ቀን: ቅዳሜ  ግንቦት 29-2018 ዓ.ም
⛪️ቦታ: ግቢ ጉባኤው አዳራሽ

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
7❤‍🔥21
የማይረሳ ትዝታ በ450 ብር ብቻ 🙏

ውድ ተመራቂዎቻችን እንዴት አላችሁ ? በጉጉት የምንጠብቀው የGC የጋራ ማዕድ መርሐ ግብር በታዋቂው ከራዲዮን ሆቴል በድምቀት ተዛጋጅቷል።

በዕለቱም
➊ ትምህርት
➋ መዝሙር
❸ አዝናኝ ጨዋታዎች
❹ የተለያዩ ሽልማቶች
➎ የፎቶ መርሐ ግብር
➏ የልምድ ልውውጥ
እነዚህን የመሰሉ የማይረሱ ትዝታዎች የሚፈጥሩ አዕምሮ  የሚያድሱ ልዩ ልዩ መርሐ ግብር ተዘጋጅተዋል።

ይህ እንደዚህ ከተዘጋጀ ከእኛ ፣ከዕርስዎ ምን ይጠበቃል ?

ከተጠቀሱት ቀናት በፊት ብር በመላክ የፕሮግራሙ ተሳተፊ ይሁኑ !

📅 ቀን:- እስከ 09/10/2018 ዓ.ም
🏛 ቦታ:- ከራዲዮን ሆቴል

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
8❤‍🔥3👍2👏1
እንዴት ናችሁ ውድ ተመራቂያን 👋

ቀጣይ የወረብ ጥናቱ መቼ ይሁን?
Anonymous Poll
52%
ሰኞ ምሽት 11፡00
9%
ሰኞ ምሽት 10፡00
24%
ማክሰኞ ምሽት 11፡00
15%
ማክሰኞ ምሽት 10፡00
ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የ2018 ተመራቂ ተማሪዎቻችን!

ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችኹ መዝ 117÷26


🔶እንደሚታወቀው የተመራቂ ተማሪዎች የወረብ ዝማሬ ጥናት ተጀመሯል ስለሆነም ነገ ሰኞ ስለሚቀጥል ትናንት ቅዳሜ የተገኛችሁም ሌሎች ሳይመቻችሁ ያልመጣችሁም በሙሉ ተቀሳቅሰን በሰአት እንድንገኝ ይሁን።


ኑ! አብረን አጥንተን በምርቃታችን ዕለት ለአምላካችን በዝማሬ ምስጋናን እናቅርብ🤲

ሰዓት: 11:00
📅ቀን: ሰኞ ሰኔ 1-2018 ዓ.ም
⛪️ቦታ: ግቢ ጉባኤው አዳራሽ

────────── ✦ ────────── 
                   ፖሊ ግቢ ጉባኤ
8
የአሻራችን መዝጊያ፣ የትዝታችን መጀመሪያ!

እሰይ! አመቱ እየተገባደደ ነው። የዘራነውን ፍሬ ልናይ፣ ከኖርነው ማህደር ዘግነን ትውስታን ልንቸረችር፣ መልካሙን ጊዜ በሀሴት ልናወሳ፣ የሚያልፉ የማይመስሉ ቀናቶችን አንስተንም ፈገግ ልንል፤ ከምንም በላይ ሁሉን በቸርነቱ ያሳለፈንን ልዑል እግዚአብሔርን እናመሰግነው ዘንድ አመቱ እያለቀ ነው። ተመስገን 🙏

የተጀመረ ሁሉ ፍጻሜ አለውና፣ በግቢያችን ያላቸውን ቆይታ የጨረሱ ውድ ወንድሞቻችንንና እህቶቻችንን ከቤቱ መርቀን ለመሰናበት ቀጠሮ ይዘናል 🥹

ለፖሊ ግቢ ጉባኤ 2026 ተመራቂዎች የተዘጋጀ ልዩ የGC እራት
ይህ ድግስ ለእናንተ ለ2018 ዓ.ም ተመራቂዎቻችን ነው! አመታችንን ላደመቃችኋት፣ ላሳመራችሁልን፣ ሙሉ ግቢ ጉባኤውን በፍቅር ላስተዳደራችሁ፣ ደከመን ሳትሉ እርስ በርስ ለተደጋገፋችሁ፣ እስከ መጨረሻው አሻራችሁን ጥላችሁ ለሄዳችሁ ሁሉ።

በዛች ልዩ ምሽት:-
🔷ትምህርት
🔹መዝሙር
🔸አዝናኝ ጨዋታዎች
🔸የተለያዩ ሽልማቶች
🔹የፎቶ መርሐ ግብር
🔷የልምድ ልውውጥ

Dress Code፦
ለወንድሞች፦ ሱፍ
ለእህቶች፦ የሀበሻ ቀሚስ

🗓ቀን፦ ሰኔ 14 (እሁድ አመሻሽ)
🕦 ሰዓት፦ ከምሽቱ 9:30 ጀምሮ
🏛 ቦታ፦ ከራድዮን ሆቴል (Keradion Hotel)
🎟️ የመግቢያ ዋጋ፦ 450 ብር


📞 0908011840 (ንዋይ)
📞 0973438584 (እህተ ሙሴ)

ትኬቱን እስከ ሰኔ 9 ድረስ በመቁረጥ የፕሮግራሙ ተካፋይ ይሁኑ!
────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📷@mkpoly_gallery  ፎቶዎቻችን
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
6❤‍🔥1
እንዴት ቆያችሁ ተመራቂያን 👋

ቀጣይ የወረብ ልምምድ መቼ ይሁን?
Anonymous Poll
42%
ሃሙስ ምሽት 10፡30
46%
እሁድ ምሽት 10፡30
25%
እሁድ ጠዋት 4፡00
2
ሰላም ለእናንተ ይሁን ውድ የ2018 ተመራቂ ተማሪዎቻችን!

ከእግዚአብሔር ቤት መረቅናችኹ መዝ 117÷26


🔶የወረብ ዝማሬ ጥናታችን ሃሙስ ስለሚቀጥል የተለቀቁትን ዜማዎች አዳጠን ሁላችንም ተመራቂ ተማሪዎች ተቀሳቅሰን በሰአት እንድንገኝ ይሁን።


ኑ! አብረን አጥንተን በምርቃታችን ዕለት ለአምላካችን በዝማሬ ምስጋናን እናቅርብ🤲

ሰዓት: 10:30
📅ቀን: ሃሙስ 4 - 2018 ዓ.ም
⛪️ቦታ: ግቢ ጉባኤው አዳራሽ


────────── ✦ ────────── 
                   ፖሊ ግቢ ጉባኤ
3