ፖሊ ግቢ ጉባኤ
3.58K subscribers
1.83K photos
35 videos
102 files
228 links
የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን፤ በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ የፖሊ ግቢ ጉባኤ መርሃግብራትና፤ ወቅታዊ የግቢ ጉባኤው መረጃዎች የሚቀርቡበት ቻናል ነው።

ለሃሳብና አስተያየቶቻችሁ
☝️👉 @mkpolybot
ለመድሎተ አሚን ጥያቄዎቻችሁ
☝️👉 @NikiyamkBot
መጻሕፍትን ለማንበብ
☝️👉 @polylibrary
ላይ ያስቀምጡልን።
Download Telegram
7. ይህ ቅዱስ አባት ማን ነው?
መልስዎን በዚህች ቦት ይላኩ ::👇👇
@mkpolyPlayBot

◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆
                 ፖሊ ግቢ ጉባኤ

📥@mkpolybot   ለአስተያየትዎ
@NikiyamkBot  ለጥያቄዎ
📖@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ ማህደር እና ቪዲዮ  ትውስታዎች
📚@polytmhirt   ለኮርስ ይከታተሉን!
◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆

              Telegram|Instagram
41❤‍🔥1🙏1
መልስ
1. ሊቀ ሃዋርያት ቅ/ጴጥሮስ
2. ቅ/ መቅደላዊት ማርያም
3. ቅ/ ባህራን
4. ፍያታዊ ዘይማን/ጥጦስ
5. ቅ/ ክርስቶስ ሰምራ
6. ቅ/ኡራኤል
7. አባ ዮሃንስ ሃጺር

መንፈሳዊ ጥያቄወቹን የተሳተፋችሁ እህት እና ወንድሞቻችን በእግዚያብሔር ስም ከልብ እናመሠግናለን🙏
ያልተሳተፋችሁ ደግሞ ለቀጣይ ሳምንት  እንድትሳተፉ ስንል በፍቅር ቃል እንጠይቃለን።
የሳምንት ሰው ይበለን🙏


ሰላመ እግዚያብሔር ከሁላችን ጋር ይሁን!!🕊🙏
አሸናፊወችን ከተወሰኑ ደቂቃዎች በኋላ እናሳውቃለን 🕊


✍️ ፖሊ ግቢ ጉባኤ ባች እና መርሃ-ግብራት ማስተባበሪያ ክፍል
🔥
◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆
                 ፖሊ ግቢ ጉባኤ

📥@mkpolybot   ለአስተያየትዎ
@NikiyamkBot  ለጥያቄዎ
📖@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ ማህደር እና ቪዲዮ  ትውስታዎች
📚@polytmhirt   ለኮርስ ይከታተሉን!
◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆
              Telegram|Instagram

🕊 የያዕቆብ ሌሊት ያድርግልን 🕊
2❤‍🔥2👍2
ሚያዚያ 23/2018 ዓ.ም

በፖሊ ግቢ ጉባኤ ቴሌግራም ቻናል 
የኤማሁስ መንገደኞች ጨዋታ ትክክለኛ መልስ ቀድመው የመለሡ 3 ተማሪወች:-

የኤማሁስ መንገደኞች  ጨዋታ አሸናፊወች🏅


🥇  Mahder /Software/096518982_
🥈 Melak Asmamaw /IT BED/092727509_
🥉  G/kidan /IT bed/094998456_


▰▰▰▰▰▰◈▰▰▰▰▰▰▰▰
                 ፖሊ ግቢ ጉባኤ

📥@mkpolybot   ለአስተያየትዎ
@NikiyamkBot  ለጥያቄዎ
📖@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ ማህደር እና ቪዲዮ 
📚@polytmhirt   ለኮርስ ይከታተሉን!
▰▰▰▰▰▰◈▰▰▰▰▰▰▰▰

              Telegram|Instagram

✍️ ፖሊ ግቢ ጉባኤ
ባች እና መርሃ-ግብራት ማስተባበሪያ ክፍል


🕊 ሰናይ ሌሊት 🕊
🏆6🎉21🤩1
📢 እንሆ  ቀኑ እኮ ደረሰ   📢


<<ወለኩሉሰ በሥርዓት  ወበተዓቅቦ ይኩን ።>>
    (1ኛ ቆሮንቶስ ፲፬ ÷ ፵ )


ሰላም ውድ የፖሊ ግቢ ጉባዔ አባላት እንዴት ናችሁ 👋  በጉጉት ሲጠበቅ የነበረው የፖሊ ግቢ ጉባዔ ጠቅላላ ጉባዔ በነገው ዕለት ይካሄዳል ። ስለሆነም በዕለቱም

➊  የጽህፈት ቤት  ሪፖርት
➋  የሂሳብ  ሪፖርት
➌  የኦዲት ሪፖርት
❹  የቀጣይ ዓመት ስራ አስፈፃሚዎችን የምናስመርጥበት ዕለት ነው።

እርስዎም በዕለቱ በመገኘት እናት ግቢ ጉባኤያችን በምን ሁኔታዎች ላይ እንዳለ ጠለቅ ያለ ዕውቅና ይኖርዎታል ።


ሰዓት :- 10:40 -11:50
⛪️  ቦታ :- አቡዬ ግቢ ጉባዔ አዳራሽ
📅  ቀን :-  25/08/2018 ዓ.ም

እናት ግቢ ጉባኤያችንን በአንድነት ተባብረን እናስቀጥል



◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆
                 ፖሊ ግቢ ጉባኤ

📥@mkpolybot   ለአስተያየትዎ
@NikiyamkBot  ለጥያቄዎ
📖@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ ማህደር እና ቪዲዮ  ትውስታዎች
📚@polytmhirt   ለኮርስ ይከታተሉን!
◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆◆

              Telegram|Instagram
❤‍🔥6🥰32😭2💯1
ነገ ነው? 😳 አዎ ነገ ነው።

በአመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚካሄደው በዚህ አመት ውስጥ በግቢ ጉባኤያችን
የተከናወኑ ተግባራትን የምንገመግምበት ጠቅላላ ጉባኤ ነገ ነው! 🎉


በዚህ ዕለትም  ፦

➴ የፅህፈት ቤት ሪፖርት
➴ የሂሳብ ሪፖርት
➴ የኦዲት ሪፖርት ይቀርባል።

እንዲሁም በዚህ አመት ያገለገሉንን ስራ አስፈፃሚዎች አመስግነን እየሸኘን 🥺
እግዚያብሄር ቢፈቅድ እና ለከርሞ ቢያደርሰን ብለን

➴  ተተኪ ስራ አስፈፃሚዎችን እንመርጣለን።

ተጋባዥ እንግዶችም ይኖሩናል

ኑ  አብረን አመቱን እንጨርሰው



  ሰዓት :- 10:40
  📍 ቦታ :- አቡዬ ግቢ ጉባዔ አዳራሽ
 🗓️ ቀን :-  25/08/2018 ዓ.ም

───────── ✦ ───────── 
             ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@mkpolybot   ለአስተያየትዎ
@NikiyamkBot  ለጥያቄዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
───────── ✦ ────────
           Telegram | Instagram
11❤‍🔥2🙏21
በማህበረ ቅዱሳን ማህደር ውስጥ የእርስዎ ፎቶ የለም? 📸🎓


ያሳለፉት አራት እና አምስት ዓመት ድካም ፍሬ አፍርቶ ለምረቃ ሲበቁ፣ ያ የደስታ ቀን በታላቁ የማህበረ ቅዱሳን ማህደር (Digital Magazine) ላይ እንዲሰፍር አላደረጉም?

⚠️ ማሳሰቢያ፦

ምዝገባው ሊዘጋ 3 ቀናት ብቻ ቀርተዋል።

👉ነገ እሁድ የፎቶ ማንሳት ፕሮግራም በጠቅላላ ጉባኤው ምክንያት ቀረጻ አይኖርም።

እንዳያመልጥዎት! አሁኑኑ @walie_21 ላይ በመልዕክት ያነጋግሩን።


"ታሪክዎን ዛሬ ያስቀምጡ፤ ነገ በትውልድ መዝገብ ውስጥ ያገኙታል!"



─────────────── ✦ ───────────────
            
ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@mkpolybot   ለአስተያየትዎ
@NikiyamkBot  ለጥያቄዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
─────────────── ✦ ───────────────
           Telegram | Instagram
6❤‍🔥3
ጠቅላላ ጉባዔው ሊካሄድ ሰዓታት ቀርተውታል ።

በአመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚካሄደው በዚህ አመት ውስጥ በግቢ ጉባኤያችን
የተከናወኑ ተግባራትን የምንገመግምበት ጠቅላላ ጉባኤ ከሰዓታት በሗላ ይካሄዳል! 🎉


በዚህ ዕለትም  ፦

➴ የፅህፈት ቤት ሪፖርት
➴ የሂሳብ ሪፖርት
➴ የኦዲት ሪፖርት ይቀርባል።

እንዲሁም በዚህ አመት ያገለገሉንን ስራ አስፈፃሚዎች አመስግነን እየሸኘን 🥺
እግዚያብሄር ቢፈቅድ እና ለከርሞ ቢያደርሰን ብለን

➴  ተተኪ ስራ አስፈፃሚዎችን እንመርጣለን።

ሌላም አዲስ ነገር አለ !!!


በዚሁ መርሐ ግብር የኤማሁስ መንገደኞች ጨዋታ አሸናፊዎች የማበረታቻ ሽልማት ይሰጣቸዋል ።

ተጋባዥ እንግዶችም ይኖሩናል

ኑ  አብረን አመቱን እንጨርሰው



  ሰዓት :- 10:40
  📍 ቦታ :- አቡዬ ግቢ ጉባዔ አዳራሽ
 🗓️ ቀን :-  25/08/2018 ዓ.ም

────────── ✦ ────────── 
             ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@mkpolybot   ለአስተያየትዎ
@NikiyamkBot  ለጥያቄዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
           Telegram | Instagram
8❤‍🔥1🕊1
መቅረቱንስ ይቅሩ😊... እናት ግቢ ጉባኤዎን ግን በምን ያስታውሷታል

ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።”
መዝሙር 133፥1


ሰላም ለ እናንተ ይሁን👋
ውድ ተመራቂ ተማሪዎቻችን እንሆ እናት ግቢ ግባኤአችን በአይነቱ ልዩ የሆነ መርሃግብር አዘጋጅታ እናንተን በመጠባበቅ ላይ ትገኛለች ::

በዕለቱም አጋፔን ጨምሮ ከግቢ በሗላ ስለሚኖረን ህይወት

ትምህርት ፣
❷ የልምድ ልውውጥ፣
❸ መዝሙሮች፣
❹ አዝናኝ እና ፈታኝ ጨዋታዎች፣
❺ የቡና ሴሪሞኒ፤

❻ Camfireም አለ።

ብሎም ልዩ ልዩ አስተማሪ፣አዝናኝ እንዲሁም በግቢ ቆይታችን መቼም ልንረሳው የማንችለውን ልዩ መርሃ ግብር ተዘጋጅቷል።

ትኬቶቹን0993817650 Fikir
0908011840 Neway
በመደወል ትኬቱን ይቁረጡ ከፕሮግራሙ ይሳተፉ!!!

እርስዎ ሲመጡ ተመራቂ ጓደኛዎን አይርሱ🤔



📆ቀን :- ሚያዝያ 30 2018 ዓ.ም
ሰዓት :- ከምሽቱ 2:00
⛪️ቦታ :- አቡየ ግቢ ጉባዔ አዳራሽ


────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@mkpolybot   ለአስተያየትዎ
@NikiyamkBot  ለጥያቄዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
14🎉1
እያጠቡ መታጠብ!

ፖሊ ሆይ  ታላቅ የበረከት ሥራ ቤትሽ ድረስ መጥቷል 🎉


ይሄ ለየት ያለ ነው! የእኛን የዘወትር ልብሶች እንደማጠብ አይደለም። የእግዚአብሔር ስም የማይለየውን ፣ ከዓለም መዓዛ ሁሉ የሚልቀውን የእጣኑን ሽታ የተሸከመውንና ለባሹን ከመላእክት ወገን የሚያስመስለውን  የተቀደሰ የበረከት ልብስ አብረን ልናጥብ ነው 🤗

የእኛ መገለጫ የሆኑትን
◆ ነጭ አልባሳት፣
◆ ነጠላዎችን እና
◆  የጊቢ ጉባኤያችን አንሶላዎች

እያጠብን፤ በእውኑ የእኛንም የኃጢአት ዕድፍ የምናስወግድበት የማይገኝ ዕድል፣ እያጠቡ መታጠብም ማለት ይሄ አይደል።

🧶 ጠዋት ቀናችንን በምስጋናና በሥራ ስንጀምር ደግሞ ቀኑ እንዴት እንደሚባረክ አስቡት።

ከወንድም እህቶቻችን  ጋር የምናሳልፈው የሳቅና የጨዋታ ጊዜ፣ በመጨረሻም  ንጹህ ነጭ ልብስ ገመድ ላይ ስናይ የሚሰማን እርካታ... ይህንን ትዝታ በፍጹም እንዳናጣው !

🗓 ቀን፦ ነገ ረቡዕ
ሰዓት፦ ማለዳ 12:30
🏛 ቦታ፦ አቡዬ ቤተክርስቲያን

እኔ አጥባለሁ እናንተስ? የምትመጡ comment ላይ እኔም እመጣለሁ እያላችሁ ጻፉልን😊

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@mkpolybot   ለአስተያየትዎ
@NikiyamkBot  ለጥያቄዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
10👏3
ግንቦት ልደታ 🕯

እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ።


ልደታ ለማርያምን እንዴት ልታከብሩ ነው

እኛስ የእናታችንን ልደት በዳግማዊት ግሸን እመቤታችን ቤተክርስቲያን በጋራ እናከብር ዘንድ ጠራናችሁ ።

እናንተ ደግሞ ጥሪያችንን አክብራችሁ ስትገኙ ፦

➺ የፀሎት
➺ የትምህርተ ወንጌል
➺ ልዩ የህብረት ዝማሬ

መርሐግብር ተካፋይ ትሆናላችሁ።

እናት ሆይ ልደትሽ ልደታችን ነው🥹 እያልናት

የእናታችንን ልደት በቤቷ እናክብር


📅 ቀን:- 01/09/2018 ዓ.ም
  ሰዓት :- 11:00
🏛  ቦታ :- ዳግማዊ ግሸን እመቤታችን ቤተ ክርስቲያን

──────── ✦ ─────────
             ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@mkpolybot   ለአስተያየትዎ
@NikiyamkBot  ለጥያቄዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
──────── ✦ ─────────
       Telegram | Instagram
20❤‍🔥3🕊2
ፖሊ ግቢ ጉባኤ
ግንቦት ልደታ 🕯 እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ። ልደታ ለማርያምን እንዴት ልታከብሩ ነው እኛስ የእናታችንን ልደት በዳግማዊት ግሸን እመቤታችን ቤተክርስቲያን በጋራ እናከብር ዘንድ ጠራናችሁ ። እናንተ ደግሞ ጥሪያችንን አክብራችሁ ስትገኙ ፦ ➺ የፀሎት ➺ የትምህርተ ወንጌል ➺ ልዩ የህብረት ዝማሬ መርሐግብር ተካፋይ ትሆናላችሁ። እናት ሆይ ልደትሽ…
በረከቷን ይፈልጋሉን

አወ ! እፈልጋለሁ ። እንኳን ለእመቤታችን ለቅድስት ድንግል ማርያም የልደት በዓል በሰላም አደረሳችሁ አደረሰን ።ዛሬ በግቢ ጉባያችን የእመቤታችንን የልደት ቀን በማስመልከት ጥሬ ይጣዳል ፣ ስለሆነም ግቢ ጉባኤ መጥታችሁ እንድታግዙ !


ቀን :- ዛሬ ግንቦት 1
ሰዓት:- ከ2:30 ጀምሮ
ቦታ :- አቡዬ ግቢ ጉባዔ አዳራሽ (በአብነቱ በኩል )

ከስራው በመገኘት የበረከቱ ተካፋይ እንሁን !


────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@mkpolybot   ለአስተያየትዎ
@NikiyamkBot  ለጥያቄዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
14👍1
ቀኑን  ግን  አስታውሰውታል

እንኳን ለ አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ወርሀዊ መታሰቢያ በዓል በሠላም አደረሳችሁ!

የጻድቅ መታሰቢያ ለበረከት ነው።   ምሳ ፲÷፯


በግቢ ጉባዔያችን በየወሩ ከሚዘጋጀው የአቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ ፅዋ ኑ እንዘክር እንዲሁም እንዘከር።


ስለዚህ ጓደኞቻችሁን በመቀስቀስ እንገናኝ!👬



🏛  አቡነ ገብረ መንፈስ ቅዱስ    ቤተክርስያን    አውደ ምሕረት
🕰 11፡30 ጀምሮ
📅  ዛሬ 05/09/2018  ዓም

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
13🙏2
ሚስጢር ስለሆነ እንዳታነቡት🤫

የትላንትናው  ፈተና እንዳሰብኩት አላስደሰተኝም ነበር ። ከጠዋት እስከ
ሌሊት እንቅልፌን መስዋዕት አድርጌ
ባነብም ፈተናው ላይ ስቀመጥ
ያጠናውት ሁሉ ይጠፋል።

መፍትሔው:-

ፀሎት እንደሆነ ስለማውቅ ፀሎቴን እያደረስኩ  የቀሩትን ፈተናዎች
ተረጋግቼ ለመስራት አስቢያለሁ ፤ ከዚህ ባለፈ  ፈጣሪ ይጨመርበት ።

ደግሞ እኮ...
"እግዚአብሔር የሚወደውን ይፈትናል"

ይባላል ስለዚ በዚህ ደስ ይበላችሁ !

የሆነው ሆኖ ግን ፈተናውን ልንጨርስ ጥቂት ቀናት ብቻ እንደቀሩን ሳስብ ደስ አለኝ። 🤗

ከዚህ ደስታ ሳላበቃ ሚስጢር ነው ተብሎ አንድ ትልቅ የምስራች ተነገረኝ
እኔ ግን አላስችል ስላለኝ
እንደኔ እንድትደሰትቱ በፈተና ለተጨናነከው ወዳጄ ልነግርህ መጣሁ።

ምንድነው? እሺ ልንገርህ...

ግንቦት 17 ፈተና እንጨርሳለን አይደል? ታዲያ በፈተና ውጥረት የተጨናነቀውን አእምሯችንን ሊያድስልን ግቢ ጉባኤያችን ልዩ መርሐ ግብር አዘጋጅቶልናል ።

ምን ምን ? .....

●  የበገና ዝማሬ
● ትምህርት
● የስዕላት ትርጓሜ እና
● የበገና ተማሪዎች ምረቃ 

ደግሞ እኮ...

መርሐ ግብሩ የዓመቱ የመጨረሻ ነው!🥺 ለተወሰኑ ወራት ከአይን ልንራራቅ ስለዚህ

ሚስጢሩን እኔ አንደነገርኳቹ ሳትናገሩ
"እንዳትናገሩ" ብላችሁ ለቅርብ ጓደኛቹህ ተናገሩ !!

📅  ቀን : ግንቦት 17
🕰 ሰዓት: 11:00 (ከሰዓት)
🏛 ቦታ: በግቢ ጉባኤው አዳራሽ

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
44🤣12👍2🙏1🕊1
ወዳጀ ዓመቱ አለቀ እኮ !
🙊 ዛሬ እኮ ዕርገት ነው ።


አዎ ! ዕርገት ነው፣ ውድ የእናት ፖሊ ግቢ ጉባኤ ልጆች እንኳን ለጌታችን ለአምላካችንና ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ዕርገት በሰላም አደረሳችሁ !!!

ማር 16:19 " ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ። "




ይህ በዓል ቅድስት ቤተክርስቲያን ከምታከብራቸው ፱ ዓበይት የጌታ በዓላት አንዱ ነው ።

ጌታችን አስቀድሞ በቅዱስ ዳዊት ትንቢትን እንዳስነገረው በምድር ላይ 33 ዘመናትን እየተመላለሰ የድኅነትን ስራ ሁሉ ከፈጸመ በኋላ በመላዕክት  ምስጋና እና እልልታ ከላይ በሰማያት ባለው በአባቱ ክብር ተቀምጧል ።

መዝ 47:5 " አምላክ  በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ። "

ጌታችን ወደ ሰማይ ሲያርግ ሐዋርያትን መንፈስቅዱስን እንደሚልክላቸውና ሁል ጊዜ እስከ ዘለዓለም ከእነርሱ እንደማይለያቸው የተስፋን ቃል እየነገራቸው ወደአባቱ ዐርጓል ።

መላዕክትም ሐዋርያትን እንደነገሯቸው ወደላይ በምስጋና ያረገው ክርስቶስ በሕያዋንና በሙታን ላይ ሊፈርድ በምስጋና እንደሚመጣ ተስፋ እያደረግን
💭 ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሆይ ና ... 💭

እንበል ።



እንኳን አደረሳችሁ እያላችሁ ኮሜንት ላይ ፃፉልን!

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
🙏138👍1🕊1
በአንድ ቀን ሁለት ደስታ 🥰

ሰሞኑን በፈተና ምክንያት በጣም ተወጥሬ ተጨንቄ እንቅልፍ አጥቼ ሰነበትኩ።
ግን እኮ እሚገርመው ፈተናው ደግሞ አይቀናኝም እንደዚያ እንቅልፌን ትቸ !

በዚህ ምክንያት ተናድጄ ባለሁበት ሰዓት  አንድ ነገር ትዝ አለኝ እሱም ምንድን ነው ብትሉኝ ፈተናው ሊያልቅ አንድ ቀን  ቀርቶታል ለካ ። ደስ አይልም ?

በዚያ ተደስቸ ደስታዬን ሳልጨርስ ሌላ አዲስ ደስታ ደግሞ ሹክ አሉኝ ፣ምንድን ነው አትሉኝም ? ምን ይሆን?

ለየት ያለ ፣መንፈስ አዳሽ የሆነ የበገና ምሽት በፖሊ ግቢ ጉባዔ ዜማና  ኪነ ጥበብ ክፍል የተዘጋጀ ፕሮግራም እንዳለ ነገሩኝ ፣ በዚህ ተደስቼ ያቺ ቀን እስክደርስ ጓጓሁ!

እናም ጮቤ እረግጨ ያችን ዕለት በደስታ እየተጠባበኩ ነው ፣ የደስታየ ተካፋዮች ሁኑልኝ፣ በዛች ዕለትም ሁላችን ተሰባስበን ይመርብን 🤗

ኑ እግዚአብሔርን በመዝሙር  አብረን እናመስግን !!!

🏛  አቡዬ ግቢ ጉባዔ አዳራሽ
🕰 11፡00
📅  17/09/2018  ዓ.ም

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
132
በዓለ ሃምሳና ተግዳሮቶቹ


ከመምህር ተፈሪ መንገሻ

ከሁሉ አስቀድመን እንኳን ለጌታችንንና ለመድኃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ ብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ በማለት መንፈሳዊ ሰላምታችንን እናቀርባለን።
አሁን የምንገኝበት ወቅት በዓለ ሃምሳ ነው። ይህ ወቅት የሞት ኃይል የተሰበረበት፣ የሰው ልጅ ነጻነት የታወጀበትና የመቃብር ድንጋይ ተንከባሎ የሕይወት ብርሃን የበራበት ነው።

ሆኖም ግን፣ ለግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ወይም ለክርስቲያን ወጣቶች ይህ ወቅት ሌላ ፈተና ይዞ መጥቷል። ዓቢይ ጾምን በከፍተኛ ተጋድሎ፣ በለቅሶና በጸሎት ያሳለፉ ወጣቶች፤ ዛሬ ጾሙ ሲፈታ መንፈሳዊነታቸው አብሮ የተፈታ ይመስል በስካርና በስንፍና፣ በስውርና በግልጥ ኃጢአት ማዕበል እየተወሰዱ ያሉት በርካቶች ናቸው። በዓለ ኀምሳ የነፍስ ደስታ እንጂ የሥጋ ማድለቢያና የዲያብሎስ ፈቃድ መፈጸሚያ እንዳልሆነ ሊታወቅ ይገባል።

1.1. በዓለ ሃምሳ ምንድ ነው?
​በዓለ ሃምሳ ማለት ከጌታችን ትንሣኤ ጀምሮ እስከ ጰራቅሊጦስ (የመንፈስ ቅዱስ መውረድ) ድረስ ያለው የ፶ ቀናት ታላቅ የደስታ ወቅት ነው። ቤተ ክርስቲያን በዚህ ወቅት አዳም ወደ ቀደመ ክብሩ መመለሱን ለማብሠር እንዲሁም በመንግሥተ ሰማያት ጻር ድካም የለም ስትል ጾምና ስግደት እነዳይኖር አድርጋለች።

ነገር ግን ይህ ደስታ “መንፈሳዊ” መሆኑን አንርሳ። ሐዋርያት በዚህ ወቅት በፍርሃት ተቆልፎባቸው ከነበረበት ቤት ወጥተው፣ ትንሣኤውን እያደነቁ በጸሎትና በምስጋና ይተጉ ነበር። በዓለ ሃምሳ የመንግሥተ ሰማያት ምሳሌ ነው። በመንግሥተ ሰማያት ደግሞ ቅድስና እንጂ ርኩሰት የለም። ነገር ግን “ጾም የለም” በሚል ሰበብ ነፍሳቸውን ለሰይጣን አሳልፈው እየሰጡ ያሉ ወጣቶች ጥቂቶች አለመሆናቸውን የሁላችንም ልባችን የሚያውቀው እውነት ነው።

መንፈሳዊ በዓላት መንፈሳዊነታችንን የምናጣባቸው ሊሆን ይገባ ነበርን?!
“ወንድሞች ሆይ፥ እናንተ ለአርነት ተጠርታችኋልና፤ ብቻ አርነታችሁ/ነጻነታችሁ ለሥጋ ምክንያትን አይስጥ፥ …. ” እንዲል ቅዱስ ጳውሎስ። (ገላ ፭፥፲፫)

1.2. በዓለ ሃምሳን እንዴት ማሳለፍ ይኖርብናል?
1.2.1. እንደማንኛውም ጊዜ ቤተ ክርስቲያን መሔድን በማዘውተር
​ወጣቶች ሆይ! ጾም ሲኖር ብቻ ደጅ የምትጠኑ፣ ጾም ሲፈታ ግን ቤተ ክርስቲያንን እንደ ባዕድ አገር የምትረሱ “ወቅታዊ ክርስቲያኖች” አትሁኑ።

“ወደ እግዚአብሔር ቤት እንሂድ ባሉኝ ጊዜ ደስ አለኝ” (መዝ. ፻፳፩፥፩)
​ያለውን የዳዊትን ቃል ትታችሁ፣ “ወደ መዝናኛ ካፌ፣ ወደ ፊልም ቤት፣ ወደ ጫት ቤት እንሂድ ወዘተ” ሲሏችሁ ደስ የሚላችሁ ከሆነ፣ እናንተ ገና የትንሣኤው ብርሃን አልተገለጸላችሁም።
ጌታችን በመጽሐፍ ቅዱስ “እስከ መጨረሻው የሚጸና እርሱ ይድናል” (ማቴ. ፲፥፳፪) እንዳለ፣ ጽናት በጾም ብቻ ሳይሆን ከጾም ውጭም ይፈተናል።

1.2.2. በቤተ ክርስቲያን አገልግሎት ጽሙድ በመሆን
በጾመ ዓርባ ወቅት የግቢ ጉባኤ መድረኮች በአገልጋዮች ተጨናንቀው፣ መዝሙሩ ፣ ጥናቱ …. ተጠናክሮ እናያለን። ትንሣኤው ሲበሠር ግን አገልጋዩ እንደ ጢስ በኖ፣ እንደ ጉም ተኖ ይጠፋል።

​በግቢ ጉባኤያችሁ ውስጥ ያላችሁ አገልግሎት በትንሣኤ ማግስት መዝለፍለፍ የለበትም። በጾም ወቅት መዘምራንና አገልጋዮች ሞልተው፣ አሁን ግን ዐውደ ምሕረቱ የሚቀዘቅዝ ከሆነ አገልግሎታችሁ ለወቅታዊ ስሜት እንጂ ለዘላለማዊው ለክርስቶስ እንዳልሆነ ማረጋገጫ ነው።

ለሥራ ከመትጋት አትለግሙ፤ በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ፤ ለጌታ ተገዙ” (ሮሜ ፲፪፥፲፩)
​የሚለውን የጳውሎስን ቃል መመሪያችሁ አድርጉ። አገልግሎት በወቅትና በጊዜ አይገደብምና።
የአገልግሎት ጽሙድነት ማለት በምቾትም በችግርም፣ በጾምም በበዓልም የማይናወጥ ጽናት ማለት ነው። “በጊዜውም አለጊዜውም ጽና” እንዲል ጳውሎስ። ፪ኛ ጢሞ ፬፥፪።
ቅዱስ እስጢፋኖስ ድንጋይ እየወረደበትም አገልግሎቱን/ ምስክርነቱን አልተወም (ሐዋ. 7)። እኛ ግን ድንጋይ ቀርቶ ለምግቡ፣ ለመጠጡ ለምቾቱ ወዘተ” ስንል አገልግሎታችንን የምንረሳ ከሆነ፣ የቆምንበት መሠረት ምንኛ የላላ ነው!
አንድ ወታደር ጦርነቱ ካበቃ በኋላ የሚዘናጋ ከሆነና ጸንቶ ካልቆመ፣ ጠላት በድል በዓሉ መሐል መጥቶ ይገድለዋል።

​እኛም በጾም ሰይጣንን ድል አድርገን፣ በበዓለ ሃምሳ ብንሰንፍ፣ ሰይጣን በደስታችን መሐል መጥቶ ነፍሳችንን ይማርካታል። ከዚህ ይጠብቀን።
ስለዚህ ወጣቶች ትንሣኤው በሥራ ይገለጥ! በመንፈስ የጀመራችሁትን በዝለት አታበላሹት። (ገላ. ፫፥፫)።

​1.2.3. በምክረ ካህን በፈቃደ ካህን በመጓዝ
መሪ የሌለው መርከብ ወዴት ይጓዛል?
!
የግቢ ጉባኤ ወጣቶች በዚህ በበዓለ ሃምሳ ወቅት ሊዘነጉት የማይገባ ታላቅ መመሪያ ቢኖር በምክረ ካህንና በፈቃደ ካህን የመመላለስ መንፈሳዊ ጥበብ ነው። የዩኒቨርሲቲ:የኮሌጅ ሕይወት በዕውቀት ባሕር ላይ እንደመጓዝ ቢሆንም፣ ያንን ባሕር ያለ መሪ (ካህን) ለመሻገር መሞከር ግን ነፍስን ለጽኑ ማዕበል አሳልፎ መስጠት ነው።
ፈቃደ/ምክረ ካህን ማለት ለአንድ ክርስቲያን ወጣት የጥበቃ አጥር ነው። አጥር ያለው ተክል እንስሳት እንደማይጎዱት ሁሉ፣ በፈቃደ ካህን የሚኖር ወጣትም የዚህ ዓለም ክፉ ፈተናዎች አያሸንፉትም። የትንሣኤው ደስታ ትርጉም የሚኖረው በካህኑ ቡራኬና መመሪያ ሲቃኝ ነው።

በጾም ወቅት ብቻ “ቀኖና ስጡኝ” እያሉ ደጅ የጠኑ፣ ዛሬ ግን ጾሙ ሲፈታ ፊታቸውን ከካህኑ አዙረው ወደ ሥጋዊ ፈቃዳቸው የሮጡ ወጣቶች፤ ሳያስተውሉት ነፍሳቸውን ለተኩላ አሳልፈው የሰጡ በጎች ናቸው!
በበዓለ ሃምሳ ወቅት “ጾም የለም” ብለው የልባቸውን ክፋት ሁሉ ሲፈጽሙ፣ ያለካህኑ ምክር ሲኖሩ፤ ጌታችን “እናንተን የሚሰማ እኔን ይሰማል፤ እናንተንም የጣለ እኔን ይጥላል” (ሉቃ. ፲፥፲፮) ብሎ የተናገረውን ቃል ራሳቸው ላይ እየፈረዱበት ነው።

በበዓለ ሃምሳ ወቅት “ጾም አበቃ” በሚል ስሜት ከካህን መራቅ ሳይሆን፣ ይልቁንም ያገኙትን መንፈሳዊ ድል ለማጽናት ወደ ካህኑ ይበልጥ መቅረብ ይኖርባቸዋል። በፈቃደ ካህን የሚጓዝ ወጣት በዓለ ሃምሳን በቅድስና የማሳለፍ ልዩ ጸጋ ይታደላል።
እነዚህ የቤተ ክርስቲያን አለኝታዎች የሆኑ ወጣቶች፣ የካህናትን ምክር እንደ ኋላ ቀርነት ሳይሆን እንደ ሰማያዊ ጥበብ ሊመለከቱት ይገባል።

ስለዚህ ወጣቶች ሆይ በዚህ የደስታ ወቅት ከሰይጣን ወጥመድ የምታመልጡት በካህን ምክር ስትጓዙ ብቻ ነው። ካህኑን መፈለግ ያለባችሁ ኃጢአት ስትሠሩ ብቻ ሳይሆን፣ ቅድስናችሁ እንዳይጎድል ጭምር መሆን አለበት።
መረሳት የሌለበት ነገር በግቢ ጉባኤ ተማሪዎች ዘንድ የሚታየው አንዱ ትልቅ ተግዳሮት “ምክረ ካህንን” ከ “ንስሓ” (ከኃጢአት መታጠብና ከቀኖና) ጋር ብቻ አያይዞ መመልከት ነው።

ንስሓ ውድቀት ከተከሠተ በኋላ ነፍስን የምታክም መድኃኒት ብትሆንም፣ ምክረ ካህን ግን ውድቀት ሳይመጣ፣ ኃጢአት ሳይሠሩ፣ ነፍስ እንዳትቆስል የሚደረግ “መከላከያና ቅድመ ጥንቃቄ” ነው። ወጣቶቹ ኃጢአት ሲሠሩ ብቻ ወደ ካህን የሚሮጡ ከሆነ፣ መንፈሳዊ ሕይወታቸው ሁልጊዜ በውድቀትና በጸጸት የተሞላ ይሆናል።

እንደ ግቢ ጉባኤ ተማሪነታቸው በትምህርት፣ በጓደኝነትና በወደፊት የሕይወት አቅጣጫቸው ላይ የካህን ምክር ያስፈልጋቸዋል። ካህናት “መንፈሳዊ አባቶች” ናቸው። አባት ደግሞ ልጁ ሲበድል ብቻ ሳይሆን፣ ልጁ ትክክለኛውን መንገድ ይዞ እንዲያድግ ሁልጊዜ ምክር ይለግሰዋል።
3
ጠቢቡ ንጉሥ “መካሪ የሌለው ሕዝብ ይወድቃል፤ በመካሪዎች ብዛት ግን ደኅንነት ይሆናል” ብሎ እንደተናገረው (ምሳሌ 11፥14)
ውድቀት (ኃጢአት) ሳይመጣ በፊት ደኅንነትን (ድልን) ለማግኘት የመካሪ አስፈላጊነትን ይገልጻል። ወጣቶቹ በምክረ ካህን ጥላ ሥር ሲሆኑ ከውድቀት ይጠበቃሉ እንጂ ውድቀትን አይጠብቁም።

ማጠቃለያ
በዓለ ሃምሳን በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ መሠረት ስንመለከተው፣ የክርስቶስ ትንሣኤ ለሰው ልጅ የሰጠው ነጻነት በኃጢአት ባርነት እንድንመላለስ ሳይሆን፣ በጽድቅ ብርሃን እንድንመላለስ መሆኑን እንረዳለን። የግቢ ጉባኤ ወጣቶች ከጾም ማግስት የሚገጥማቸውን መንፈሳዊ ዝለት አሸንፈው፣ ይህን ታላቅ ወቅት በቅድስና ሊኖሩ ይገባቸዋል።

“በነጻነት ልንኖር ክርስቶስ ነጻነት አወጣን፤ እንግዲህ ጸንታችሁ ቁሙ እንደ ገናም በባርነት ቀንበር አትያዙ።” ገላትያ ፭፥፩
​ነጻ ያወጣችሁ ጌታ በነጻነቱ ያጽናችሁ፤ በነፍሳችሁ ላይ የታተመው የትንሣኤው ብርሃን ደግሞ በኃጢአት ዝገት እንዳይጠፋ በጸሎትና በምክረ ካህን ጠብቁት።
ወስብሐት ለእግዚአብሔር!

ሃሳቡ ከተመቻችሁ ለጓደኞቻችሁ ሼር አድርጉ!
────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
9
በአንድ ቀን ሁለት ደስታ 🥰

ሰሞኑን በፈተና ምክንያት በጣም ተወጥሬ ተጨንቄ እንቅልፍ አጥቼ ሰነበትኩ።
ግን እኮ እሚገርመው ፈተናው ደግሞ  አይቀናኝም እንደዚያ እንቅልፌን ትቸ !

በዚህ ምክንያት ተናድጄ ባለሁበት ሰዓት  አንድ ነገር ትዝ አለኝ እሱም ምንድን ነው ብትሉኝ ፈተናው ሊያልቅ አንድ ቀን  ቀርቶታል ለካ ። ደስ አይልም ?

በዚያ ተደስቸ ደስታዬን ሳልጨርስ ሌላ አዲስ ደስታ ደግሞ ሹክ  አሉኝ ፣ምንድን ነው አትሉኝም ? ምን ይሆን?

ለየት ያለ ፣መንፈስ አዳሽ የሆነ የበገና ምሽት በፖሊ ግቢ ጉባዔ ዜማና  ኪነ ጥበብ ክፍል የተዘጋጀ ፕሮግራም እንዳለ ነገሩኝ ፣ በዚህ ተደስቼ ያቺ ቀን እስክደርስ ጓጓሁ!

እናም  ጮቤ እረግጨ ያችን ዕለት በደስታ እየተጠባበኩ ነው ፣ የደስታየ ተካፋዮች ሁኑልኝ፣ በዛች ዕለትም ሁላችን ተሰባስበን ይመርብን  🤗

ኑ እግዚአብሔርን በመዝሙር  አብረን እናመስግን !!!

🏛  አቡዬ ግቢ ጉባዔ  አዳራሽ
🕰 11፡00
📅  17/09/2018  ዓ.ም

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
@polytmhirt   ለኮርስ
@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
9🎉3
በዕለተ ማክሰኞ ከቀኑ 09:00 ሲል ለምናካሂደው ጠቅላላ ጉባኤያችን ዝግጁ ናችሁ?🤔



11111111
1111111111
1111111111111
111111111111111
111111
111111
111111
111111
111111
111111
111111
111111
111111
111111
1111111111111111111
1111111111111111111
ቀን ቀረው

፩,ማክሰኞ ከቀኑ 09:00 ሲል መርሀግብራችንን እንጀምራለን።

፪, presentation እና defense ያላችሁ ወንድም እህቶቻችን
👉 30 ደቂቃዎች👈 ብቻ


ሁላችን በጉጉት እና በፍቅር ለምንጠብቃት የመርሀግብራችን ዕለት ላይ ሁላችንንም ከቁጥር ሳያጎል በሰላም ያደርሰን ዘንድ ሁላችንም ባለንበት እንጸልይ።

ተመጉ ዘፖሊ

ሰዓቱ ሳይቀድምዎ ፣ ከቦታው ይድረሱ!

────────── ✦ ────────── 
                      ፖሊ ግቢ ጉባኤ
📩@polygbigubaecommentbox ለሃሳብ አስተያየትዎ
📚@polylibrary   መፅሐፍትን ለማንበብ
📖@polytmhirt   ለኮርስ
📷@mkpoly_gallery  የፎቶ እና ቪዲዮ ማኅደር
────────── ✦ ────────── 
             Telegram | Instagram
8❤‍🔥1👍1🥰1