Mizan Institute of Technology - MiT🇪🇹
8.2K subscribers
143 photos
9 videos
2 files
179 links
A multi-national tech company headquartered at Addis Ababa, Ethiopia. The first Full stack (MERN) bootcamp in Ethiopia.

https://www.mizantechinstitute.com
Download Telegram
ሰሪወችንና ተስተናጋጁን መሃል ላይ ሆነው ያገናኙት አስተናጋጆች፤ ፍሮንትኢንድንና ባክኢንድን እንደሚያግባባው እንደ API ናቸው። ተጠቃሚው ድረ-ገጽ ላይ "ግባ" የሚለውን በተን ሲጫን፣ Front-End ያንን ጥያቄ በኤፒአይ በኩል ወደ Back-End ይልካል። Back-End መረጃውን አጣርቶ መልሱን በኤፒአይ በኩል ወደ Front-End ይመልሳል።


❤️ፍል ስታክ ደቨሎፐር (Full Stack Developer) ምን ይሰራል?

ልክ አንድን ህንፃ ከመሰረቱ እስከ ጣሪያው ድረስ እንደሚገነባ መሃንዲስ ነው። የድረ-ገጹን ፊት ለፊት (Front-End)፣ ጀርባ (Back-End)፣ እና የመረጃ ቋት (Database) የመስራት ችሎታ አለው። ሁሉንም ነገር በአንድ ላይ ማስተዳደር ይችላል።

❤️ ፉል ስታክ የሚሰራባቸው የቴክኖሎጂ ምድቦች (Stacks):
ከላይ አንድ ፉል ስታክ የሚባል ድረ ገፅ ሲሰራ Front-end, Back-end & Database አለው ብለናል። Front-endን ለመስራት ብዙ አማራጮች እንዳሉና ብዙ ፍሬምወርኮች መኖራቸውን ተነጋግረናል። Back-endንም፣ ደታቤዝንም ለመስራት ብዙ አማራጭ እንዳሉ አይተናል።
ስለዚህ ሁሉንም እነዚህን ያሟላ ድረ ገፅ ሲገነባ Front-end ላይ ካሉ አማራጮች እነማንን ይዞ፣ Back-end ላይ ካሉ አማራጮችም እነማንን ይዞ፣ ከደታቤዝም እነማንን ይዞ ማንን ከማን በማጣመር አንድ የተሟላ full stack ድረ ገፅ ያበለፅጋል የሚለውን እንመልከት።

ከላይ እንደተጠቀሰው MERN እና MEAN ብቻ አይደሉም:

➡️ MERN Stack: MongoDB, Express.js, React.js, Node.js (ይህ እኛ የምናስተምረው ነው!)
ለFront-end የምንጠቀመው Reactን፣ ለBack-end የምንጠቀመው Express.jsን በNode.js፣ ለደታቤዝ የምንጠቀመው MongoDBን ነው።

➡️ MEAN Stack: MongoDB, Express.js, Angular.js, Node.js (ከReact.js ይልቅ Angular.jsን ይጠቀማል)

➡️ LAMP Stack: Linux (ኦፕሬቲንግ ሲስተም), Apache (ዌብ ሰርቨር), MySQL (የመረጃ ቋት), PHP/Python/Perl (የጀርባ –ባክኢንድ ቋንቋ) - ይህ መንገድ በጣም የቀድሞ እና ታዋቂ ፍልስፍና (የፉል ስታክ አሰራር መንገድ) ነው።

➡️ MEVN Stack: MongoDB, Express.js, Vue.js, Node.js (ከReact.js እና Angular.js ይልቅ Vue.jsን ይጠቀማል)

➡️ Django (Python) + (Frontend Framework): Django (ኃይለኛ የPython የጀርባ Back-end ፍሬምወርክ ነው) ከማንኛውም የፊት ለፊት (Front-end) ፍሬምወርክ (React, Angular, Vue) ጋር አጣምሮ መጠቀም ይቻላል።

➡️ Ruby on Rails+(Frontend Framework): ልክ እንደ Django ሁሉ, ከማንኛውም የፊት ለፊት (Front-end) ፍሬምወርክ ጋር መጠቀም ይቻላል::

➡️ .NET (C#) + (Frontend Framework): .NET ከማንኛውም የፊት ለፊት (Front-end) ፍሬምወርክ ጋር መጠቀም ይቻላል::

✔️ እኛ MiTዎች ለምን MERN Stackን መረጥን?

➡️JavaScript በሁሉም ቦታ!
ሁሉም ቴክኖሎጂዎች (MongoDB, Express.js, React.js, Node.js) JavaScriptን ስለሚጠቀሙ፤ አንድ ቋንቋ ብቻ መማር በቂ ነው። ይህም ሂደቱን በጣም ቀላል እና ፈጣን ያደርገዋል። ጃቫስክሪፕትን ካወቅን ለፍሮንት ኢንድም፣ ለባክኢንድም፣ ለደታቤዝም የምንጠቀማቸው አማራጮች እንደ ፕሮግራሚንግ ላንጉጅ መስታቸው አንድ ስለሆነ ሌላ አድስ ፕሮግራሚንግ ቋንቋ ሲንታክስና ሴማንቲክስ ማወቅ አይጠበቅብንም።

➡️እጅግ በጣም ፈጣን!
React.js የፌስቡክ ኩባንያ ያበረከተው በጣም ፈጣን እና ዘመናዊ የፊት ለፊት (Front-End) ቴክኖሎጂ ነው። ድረ-ገጾችን እና መተግበሪያዎችን በሚገርም ፍጥነት እንዲሰሩ ያደርጋል።

➡️ተለዋዋጭነት!
MongoDB በቀላሉ የሚለዋወጥ (Dynamic የሆነ)የመረጃ ቋት (Database) ነው። አዳዲስ መረጃዎችን በቀላሉ ለማስተናገድ ያስችላል።

➡️ከፍተኛ ተወዳጅነት!
በአሁኑ ጊዜ በአለም ላይ ያሉ ብዙ ታላላቅ ኩባንያዎች MERN Stackን ይጠቀማሉ። ይህም ማለት የስራ እድሉ በጣም ሰፊ ነው።

➡️ዘመናዊነት (Cutting-Edge):
MERN ስታክ በአሁኑ ጊዜ በድረ-ገጽ ልማት አለም ውስጥ ካሉት በጣም ዘመናዊ እና ተፈላጊ ቴክኖሎጂዎች አንዱ ነው። ካሉት ፍልስታክን የመስራት አማራጮች በአለም ላይ ግንባር ቀድም የሆነው ይህ መንገድ ነው።


በMizan Institute of Technology (MiT) የፉል ስታክ (MERN) ስልጠና የምንሸፍናቸው ርዕሶች (በዝርዝር):

📌መሰረታዊ የድረ-ገጽ አሰራር: HTML, CSS, JavaScript (እነዚህን ቋንቋዎች ጠንቅቆ ማወቅ ለማንኛውም የድረ-ገጽ ገንቢ መሰረታዊና የግድ ነው!)
እነዚህን ስናስተምር HTML ውስጥ ከጀማሪ እስከ አድቫንስድ የሚባሉትን ጭምር እንዳስሳለን። CSS ላይ ለresponsive ድረ ገፅ ያግዘንና ስራችንን ያፋጥንልን ዘንድ ካሉ የ CSS ፍሬምወርኮች ቀዳሚ የሆኑትን Tailwindን እና Bootstrapን እናያለን።

📌 Figma: ድረ ገፅ ሲገነባ ቴምፕሌት ኢድት ማድረግ እንደ አማራጭ ቢሆንም ከUI/Ux ድዛይን ይጀምራል። ድዛይኑን በፊግማ ከሰራን በሗላ ወደ ኮድ ይቀየራል።

📌React.js (የፊት ለፊት (Front-end) ማበልፀጊያ): ዘመናዊ እና ተለዋዋጭ ድረ-ገጾችን ለመስራት የሚያስችል ኃይለኛ ቴክኖሎጂ ነው።

📌 Node.js (የጀርባ (Back-end) ልማት): JavaScriptን ከድረ-ገጽ አሳሽ (ብሮውዘር) ውጭ በማስኬድ (run በማድረግ) የድረ-ገጹን ጀርባ ለመስራት የሚያስችል ቴክኖሎጂ ነው።

📌Express.js (ድረ-ገጽን ለማስተዳደር): ከNode.js ጋር በመሆን ድረ-ገጹን በቀላሉ ለማስተዳደር የሚያስችል ፍሬምወርክ።

📌 MongoDB (የመረጃ ቋት): ሁሉንም የድረ-ገጹን መረጃዎች በቀላሉ ለማከማቸት እና ለማስተዳደር የሚያስችል ዘመናዊ የመረጃ ቋት።

📌 API (Front-End እና Back-Endን ለማገናኘት): እነዚህን ሁለት ክፍሎች በማስተሳሰር ድረ-ገጹ በትክክል እንዲሰራ የሚያደርግ ወሳኝ ቴክኖሎጂ።

📌Git and Github: የስራችንን ሂደት ለመቆጣጠር, ከሌሎች ጋር ለመተባበር::

📌 Authentication and Authorization: የተጠቃሚዎችን ደህንነት ለመጠበቅ::

📌 Deployment: ድህረ-ገፃችንን ለህዝብ እይታ (ለተጠቃሚ ይፋ ማድረግ) ክፍት ለማድረግ::

ከንድፈ ሃሳብ ባሻገር፡ እውነተኛ ፕሮጀክቶችን አስደግፈን ለእያንዳንዱ ርእስ እንሰጣለን። (Capstone Projects)!

በMiT ስልጠናችን፣ በንድፈ ሃሳብ ብቻ አንወሰንም። የተማራችሁትን በተግባር የምትፈትሹበት፣ እውነተኛ ድረ-ገጾችን እና መተግበሪያዎችን የምትሰሩበት እድል ይኖራችኋል። ከእነዚህ ፕሮጀክቶች (Capstone Projects) መካከል፡

➡️የራሳችሁን ፖርትፎሊዮ ድረ-ገጽ መስራት: የተማራችሁትን ችሎታ የምታሳዩበት፣ ለስራ ስታመለክቱ የምትጠቀሙበት ድረ-ገጽ ይሆናችሁ ዘንድ ገና ከፊግማ ድዛይኑ ጀምሮ ፍሮንት ኢንዱንም፣ ባክኢንዱንም፣ አውተንቲኬሽንና ፎርም ካለው ቫሊዴሽኑን፣ ደታቤዙንም ትሰራላችሁ።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Mizan Institute of Technology - MiT🇪🇹
ሰሪወችንና ተስተናጋጁን መሃል ላይ ሆነው ያገናኙት አስተናጋጆች፤ ፍሮንትኢንድንና ባክኢንድን እንደሚያግባባው እንደ API ናቸው። ተጠቃሚው ድረ-ገጽ ላይ "ግባ" የሚለውን በተን ሲጫን፣ Front-End ያንን ጥያቄ በኤፒአይ በኩል ወደ Back-End ይልካል። Back-End መረጃውን አጣርቶ መልሱን በኤፒአይ በኩል ወደ Front-End ይመልሳል። ❤️ፍል ስታክ ደቨሎፐር (Full Stack Developer)…
➡️የኢ-ኮሜርስ ድረ-ገጽ መስራት: እቃዎችን መሸጥ እና መግዛት የሚቻልበት ድረ-ገጽ በራሳቸው ከፊግማ ድዛይኑ ጀምሮ ትሰራላችሁ። በዚህ ዘርፍ ታዋቂውን የአማዞንን ገፅ ክሎን ታደርጋላችሁ።

➡️የዙም መተግበሪያ መስራት: ሰዎች በቪድዮ የሚገናኙበትንና መልዕክት የሚለዋወጡበት የሆነውን ዙም መተግበሪያን ክሎን ታደርጋላችሁ።

➡️ የአፕልን ዌብሳይት አኒሜሽን፣ jQuery ሳይቀር በመጨመር በየምትማሯቸው ርእሶች ሁሉ ያሉ ሃሳቦችን እየተገበራችሁበት ትሄዳላችሁ።

➡️  ከኮድ ባሻገር እንደ ወርድፕረስና ሾፒፋይ ያሉ  የCMS አማራጮችን ስለምናስተምር በነርሱም ፕሮጀክቶችን ትሰራላችሁ።

➡️ ሲስተሞችን መስራት: የት/ቤት፣ የሆስፒታል፣ የንብረት አስተዳደር፣ የሆቴል፣ የምግብ ቤት፣ የሪልስቴት፣ የንግድ፣ የሽያጭ ማኔጅ ማድረጊያ ሲስተሞችን ትሰራላችሁ።

ሌሎችም! እንደ ፍላጎታችሁ እና ችሎታችሁ የተለያዩ ፕሮጀክቶችን መስራት ትችላላችሁ።

✅ የስራ እድሎች፡ ገደብ የለሽ ነው!
➡️በአገር ውስጥ (ኢትዮጵያ): የቴክኖሎጂው ዘርፍ በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ነው። የፉል ስታክ ደቨሎፐሮች ፍላጎት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ ነው።

➡️በውጭ አገር: በአለም አቀፍ ደረጃ የፉል ስታክ ገንቢዎች በጣም ተፈላጊ ናቸው። ከፍተኛ ደመወዝ እና ጥቅማጥቅሞች ያገኛሉ።

➡️ፍሪላንስ (Freelance): የራስዎ አለቃ መሆን ይችላሉ!
ፕሮጀክቶችን መርጠው፣ በፈለጉት ጊዜ እና ቦታ መስራት ይችላሉ።

➡️የርቀት ስራ (Remote Work): ከቤትዎ ሆነው፣ ለአለም አቀፍ ኩባንያዎች መስራት ይችላሉ። አለምን ሳይዞሩ፣ አለም አቀፍ የስራ ልምድ ማግኘት ይችላሉ!

➡️ግምታዊ ደመወዝ፡ ህልምዎን እውን ለማድረግ!

*️⃣በአገር ውስጥ: እንደ ልምድ፣ ችሎታ፣ እና በሚሰሩበት ኩባንያ የደመወዝ መጠኑ ይለያያል። ነገር ግን፣ ጥሩ ደሞዝ እና ጥቅማጥቅሞች ማግኘት ይቻላል። በአንፃሩ ወርሃዊ ደመወዝ ከ10ሺህ–40 ሺህ ያገኙበታል። እንደየብቃቱና ልምዱ ከዚህም ይበልጣል።

*️⃣በውጭ አገር: በጣም ከፍተኛ ደሞዝ ማግኘት ይቻላል። በአመት በመቶ ሺዎች የሚቆጠር ዶላር ማግኘት የተለመደ ነው።

✔️ታዋቂ ድረ-ገጾች በMERN Stack ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የተሰሩ:
➡️Facebook (አንዳንድ ክፍሎች): የአለማችን ትልቁ የማህበራዊ ሚዲያ መድረክ።

➡️Instagram: ፎቶዎችን እና ቪዲዮዎችን ለማጋራት::

➡️WhatsApp: መልዕክት መለዋወጫ አፕልኬሽን::

➡️Airbnb: መኖሪያ ቦታዎችን ለማከራየት::

➡️Dropbox: ፋይሎችን ለማስቀመጥ::

➡️Uber: ትራንስፖርት አገልግሎት

➡️Paypal: የኦንላየን ክፍያ ለመፈፀም::
እና ሌሎችም!


♾ማጠቃለያ፡
ፉል ስታክ ድረ-ገጽ ማበልፀግ (Full Stack Web Development) መማር በሩን ለብዙ እድሎች ይከፍታል። በMiT ጥራት ያለው ስልጠና፣ እውነተኛ ፕሮጀክቶችን የመስራት ልምድ፣ እና ለስራ ገበያው የሚያዘጋጅዎትን ክህሎት እናቀርብልዎታለን።

ፍላጎቱ ካለዎት አሁኑኑ ይመዝገቡ! የወደፊትዎን ህልም በዲጂታል አለም ይገንቡ!

በMizan Institute of Technology ፉል ስታክ ኮርስ ረዳት ኢንስትራክተር የተዘጋጀ

አሁን ላይ እየተካሄደ ባለው 8ኛ ዙር ምዝገባችን መሳተፍ ከፈለጉ: www.mizantechinstitute.com ላይ ገብተው ይመዝገቡ።

ስለሚመዘገቡት ኮርስ በቂ መረጃ ከሌለዎ: በቴሌግራም ወይም በአካል ቢሯችን በመገኘት ያናግሩን::

✅ቴሌግራም: http://t.me/MizanInstituteOfTechnologyEthio
🗺 በአካል ተገኝተው በቂ ማብራሪያ አግኝተው ለመመዝገብ: ቤተል አፕል ፕላዛ 7ኛ ፎቅ (ቢጫ ፎቅ ፊት ለፊት)





ስሌሎች ኮርሶች ምንነትና ማብራሪያ ለማወቅ ፍላጎቱ ካለዎት ኮመንት ላይ ያሳውቁን።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ስለምንሰጣቸው ኮርሶች ማብራሪያ ✅ ክፍል 2️⃣
ለዛሬ ፓይተን ፕሮግራሚንግን በተመለከተ የተወሰኑ ሃሳቦችን እናካፍላችሁ!

ፓይተን ከፕሮግራሚን ቋንቋዎች መካከል አንዱ ስለሆነ ሃሳቡን እንረዳው ይረዳን ዘንድ ቅድሚያ ስለ ፕሮግራሚንግ ቋንቋ ምንነት ትንሽ እንበል።


በመጀመሪያ ወደ ፕሮግራሚንግ ዓለም እንኳን ደህና መጡ! (Introduction to the World of Programming)

ግን ግን… ከኮምፒውተር ጋር መነጋገር እንደሚችሉ ያውቃሉ? በድምጽዎ ወይም በጽሑፍ መልእክት አይደለም የምትግባቡት! ኮምፒውተሮች የራሳቸው ቋንቋ አላቸው፡ የፕሮግራሚንግ ቋንቋ (Programming Language) ይባላል።

የፕሮግራሚንግ ቋንቋ ምንድን ነው?
ልክ ሰዎች እርስ በእርስ ለመግባባት ቋንቋ እንደሚጠቀሙት (ለምሳሌ፡ አማርኛ፣ ኦሮምኛ፣ እንግሊዝኛ፣ አረብኛ፣ ፈረንሳይኛ...) እንደሚጠቀሙ ሁሉ፣ እኛ ሰዎች ከኮምፒውተር ጋር ለመግባባትም የፕሮግራሚንግ ቋንቋ እንጠቀማለን።

የፕሮግራሚንግ ቋንቋ ለኮምፒውተሩ፤ ምን ማድረግ እንዳለበት፣ እንዴት ማድረግ እንዳለበት እና መቼ ማድረግ እንዳለበት የሚነግሩ ትዕዛዞች (instructions) ስብስብ ነው። እነዚህ ትዕዛዞች በተወሰነ ቅደም ተከተል (syntax) እና ትርጉም (semantics) የተጻፉ ናቸው። ልክ የምግብ አዘገጃጀት መመሪያ (recipe) አንድን ምግብ እንዴት ማዘጋጀት እንደሚቻል ደረጃ በደረጃ እንደሚነግረን ሁሉ፣ የፕሮግራሚንግ ቋንቋም ኮምፒውተሩ አንድን ስራ እንዴት ማከናወን እንዳለበት ይነግረዋል።

✔️የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ጥቅሞች:

👉አውቶሜሽን (Automation): ተደጋጋሚ ስራዎችን በራሳቸው እንዲሰሩ ማድረግ። ለምሳሌ፡- በየቀኑ አንድ አይነት ኢሜይል መላክ ካለብዎት፣ ይህን ስራ በፕሮግራም መስራት ይችላሉ። እርስዎ በየቀኑ ተመሳሳይ ነገር ማኑዋሊ ከመስራት ያንን ስራ የሚሰራ አንድ ፕሮግራም መፃፍ ማለት ነው።

👉ችግር መፍታት (Problem Solving): ውስብስብ ችግሮችን ለመፍታት ኮምፒውተርን መጠቀም እንችላለን። ለምሳሌ፡- የአየር ሁኔታ ትንበያን ለማስላት፣ የህክምና ምስሎችን ለመተንተን።

👉አዲስ ነገር መፍጠር (Innovation): አዳዲስ ሶፍትዌሮችን፣ ድረ-ገጾችን፣ የሞባይል መተግበሪያዎችን፣ ጌሞችን... ለመፍጠር።

👉የመረጃ ትንተና (Data Analysis): ብዙ መረጃዎችን (data) በፍጥነት እና በትክክል ለመተንተን። ማንዋሊ እነ excel ጋ ከመዛዛግ በፕሮግራሚንግ ማፋጠን ይችላል።



✔️የተለመዱ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች (Common Programming Languages):
በአለም ላይ የሰው ልጆች የምንግባባባቸው በሺዎች የሚቆጠሩ ቋንቋዎች እንዳሉ ሁሉ በሺዎች የሚቆጠሩ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች አሉ። አንዳንዶቹ በጣም ተወዳጅ ሲሆኑ፣ አንዳንዶቹ ደግሞ ለተወሰኑ ስራዎች ብቻ ያገለግላሉ። ከታዋቂዎቹ መካከል፡-

⚡️Python: ሁለገብ፣ ለመማር ቀላል፣ ለዳታ ሳይንስ፣ ለማሽን ለርኒንግ፣ ለድረ-ገጽ ልማት... የሚውል። (ስለ ፓይተን ዛሬ ከዚህ ጽሁፍ በታች በዝርዝር እናያለን!)

⚡️JavaScript: በዋናነት ለድረ-ገጽ ልማት (front-end) የሚያገለግል (ከላይ ፉል ስታክ ላይ አይረናል)፣ ግን ደግሞ ለጀርባ (back-end) እና ለሞባይል መተግበሪያ (React Native) ማበልፀግም የሚውል።

⚡️Java: ለትላልቅ ሲስተሞች፣ ለሞባይል መተግበሪያዎች (Android), ለድረ-ገጽ ጀርባ (back-end)... የሚውል።

⚡️C# (C Sharp): በማይክሮሶፍት የተሰራ፣ ለዊንዶውስ መተግበሪያዎች፣ ለጌሞች (Unity), ለድረ-ገጽ ጀርባ... የሚውል።

⚡️C++: ለከፍተኛ አፈጻጸም (high performance) የሚያስፈልጉ ስራዎች፣ ለጌሞች፣ ለኦፕሬቲንግ ሲስተሞች (ዊንደውስ፣ ማክ፣ ላይነክስ... የሚውል።

⚡️PHP: በዋናነት ለድረ-ገጽ ጀርባ (back-end) የሚያገለግል።

⚡️Swift: በ Apple የተሰራ ለ iOS እና macOS.

⚡️Go: በ Google የተሰራ አዲስ ቋንቋ.

⚡️Kotlin: ለ Android (አሁን ላይ በ5 ሚሊዮን ኮደርስ ላይ ቤዚኩ እየተሰጠ ያለው ኮርስ).

⚡️⚡️ Dart:  ይህ ለአንድሮይድና iOS ስልኮች ላይ የሚሰራ ሞባይል አፕ በFlutter ለመስራት ይጠቅማል.



😄የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ግንኙነት እና ተመሳሳይነት:

ምንም እንኳን እያንዳንዱ የፕሮግራሚንግ ቋንቋ የራሱ የሆነ ልዩ ባህሪያት ቢኖረውም፣ ብዙዎቹ ተመሳሳይ መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳቦች (fundamental concepts) አሏቸው። እነዚህም፡-

➡️ (Variables): መረጃዎችን ለማከማቸት የሚያገለግሉ ስያሜዎች ናቸው።

➡️የዳታ አይነቶች (Data Types): ቁጥሮች፣ ጽሑፎች፣ ቡሊያኖች (እውነት ሀሰት)...

➡️ኦፕሬተሮች (Operators): የሂሳብ ስሌቶችን፣ ንፅፅሮችን፣ ሎጂካዊ ኦፕሬሽኖችን ለመስራት።

➡️Control Structures: ሁኔታዊ መግለጫዎች (ይህ ከሆነ ይህ ይሆናል፣ ካልሆነ ግን ሌላኛው ይሆናል) (if/else), ዑደቶች – ድግግሞሽ (for, while, do while))።

➡️ፈንክሽኖች (Functions): ተደጋጋሚ ኮዶችን በአንድ ቦታ ለመሰብሰብ።

አንድ የፕሮግራሚንግ ቋንቋ መማር ሌሎችን ለመማር ቀላል ያደርገዋል፣ ምክንያቱም እነዚህ መሰረታዊ ፅንሰ-ሀሳቦች በብዙ ቋንቋዎች ውስጥ ተመሳሳይ ናቸው።


💎 ፓይተን (Python) ከሌሎች ፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች ለየት የሚያደርገው ምንድን ነው? (Why Python?)

ከላይ ከተዘረዘሩት ታዋቂ ቋንቋዎች መካከል ፓይተን ልዩ ቦታ ይይዛል። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች አሉ፡-

💻 ቀላልነት (Exceptional Simplicity): ፓይተን ለመማር በጣም ቀላል ነው። ኮዱ ግልፅ፣ ለማንበብ ቀላል እና ለመረዳት የማያስቸግር ነው። ወደ እንግሊዝኛ ቋንቋ የቀረበ ነው። ይህ ማለት በፍጥነት መማር እና ወደ ተግባር መግባት ይችላሉ ማለት ነው! ሌሎች ቋንቋዎች ከሚጠይቁት ጊዜ በጣም ባነሰ ጊዜ ውስጥ ፓይተንን መማር ይቻላል።

💻 ሁለገብነት (Incredible Versatility): ፓይተን ልክ እንደ ሁለገብ መሳሪያ (multi-tool) ነው። ለተለያዩ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ያገለግላል። ከድረ-ገጽ እስከ ዳታ ሳይንስ፣ ከማሽን ለርኒንግ እስከ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ... ፓይተን በሁሉም ቦታ አለ!

💻ግዙፍ ማህበረሰብ ከጀርባው መኖር (Huge Community): ፓይተንን ሲማሩ ብቻዎን አይደሉም! በአለም ዙሪያ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ የፓይተን ደቨሎፐሮች (developers) አሉ። ይህ ማለት ማንኛውም ጥያቄ ቢኖርዎት፣ ማንኛውም ችግር ቢያጋጥምዎት፣ እርዳታ ማግኘት በጣም ቀላል ነው! ምናልባትም እርስዎን ያጋጠመዎ ጥያቄ ከእርስዎ በፊት የነበሩ ደቨሎፐሮችን አጋጥሟቸው፣ እነሱ ጠይቀው ተመልሶላቸው፣ አሁን ላይ እርስዎ ያልገባዎትን ሲጠይቁ መልሱ በቀላል የሚገኝ ይሆናል።

💻ብዙ ላይብረሪዎች (Libraries) እና ፍሬምወርኮች (Frameworks): ፓይተን ብዙ ዝግጁ የሆኑ ኮዶች (libraries) እና ፍሬምወርኮች (frameworks) አሉት። ይህ ማለት ብዙ ስራዎችን ከባዶ መፃፍ አያስፈልግዎትም ማለት ነው! ለምሳሌ፡- ድረ-ገጽ ለመስራት Django ወይም Flask, ለዳታ ሳይንስ NumPy, Pandas, Matplotlib, ለማሽን ለርኒንግ Scikit-learn, TensorFlow, Keras... እነዚህ ሁሉ ዝግጁ የሆኑ መሳሪያዎች ናቸው።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
💻ከፍተኛ ተፈላጊነት በስራ ገበያ: በአሁኑ ወቅት ፓይተን በዓለም ላይ ካሉት በጣም ተፈላጊ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች አንዱ ነው።




ስለምንነቱ ትንሽ እናውራ!
ፓይተን ፕሮግራሚንግ (Python Programming) ከድረ-ገጽ ልማት እስከ ዳታ ሳይንስ፣ ከማሽን ለርኒንግ እስከ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ከጨዋታ (ጌም) ስራ እስከ ሳይንሳዊ ምርምር... ፓይተን የሌለበት የቴክኖሎጂ ዘርፍ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ ነው። ይህ ቋንቋ የዘመናዊ ቴክኖሎጂ መሰረት ብቻ ሳይሆን፣ የወደፊትዎንም የሚቀርፅ ቁልፍ ነው።

✅️ፓይተን ምንድን ነው?
ፓይተን ቀላል የሚመስል፣ ግን እጅግ ውስብስብ ስራዎችን መሥራት የሚችል!

ፓይተንን መማር ልክ አዲስ ቋንቋ መማር እንደመጀመር ነው። ቀላል ቃላትን እና አጫጭር ዓረፍተ ነገሮችን በመጠቀም ይጀምራሉ። ኮዱ ግልፅ፣ ለማንበብ ቀላል እና ለመረዳት የማያስቸግር ነው። ይህ ማለት በፍጥነት መማር እና ወደ ተግባር መግባት ይችላሉ ማለት ነው! በሌሎች ቋንቋዎች በደርዘን የሚቆጠሩ መስመሮች የሚፈጀውን ኮድ፣ በፓይተን በጥቂት መስመሮች መፃፍ ይቻላል!

ፓይተን ልክ አንድ ሁለገብ መሳሪያ የተለያዩ ስራዎችን እንደሚሰራ ሁሉ፣ ለተለያዩ የቴክኖሎጂ ዘርፎች ያገለግላል። አንድን ነገር በፓይተን መሥራት አይቻልም ብሎ ማሰብ ይከብዳል! ከድረ-ገጽ እስከ ሞባይል መተግበሪያ፣ ከዳታ ትንተና እስከ ሮቦት ቁጥጥር... ሁሉም በፓይተን ይቻላል!

ከፍተኛ ተወዳጅነት (Popularity) አለው: ፓይተን በአለም ላይ ካሉ በጣም ታዋቂ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች አንዱ ነው። ለምን? ምክንያቱም ይሰራል! ትላልቅ ኩባንያዎች፣ ዩኒቨርሲቲዎች፣ የምርምር ተቋማት... ሁሉም ፓይተንን ይጠቀማሉ። ይህ ማለት የስራ እድልዎ ሰፊ ነው ማለት ነው! Stack Overflow, GitHub, TIOBE Index – እነዚህ ሁሉ የፓይተንን ተወዳጅነት ያረጋግጣሉ።


🌏ፓይተን ለምን ይጠቅማል?

✅ድረ-ገጽ ማበልፀግ (Web Development):
ፓይተን ድረ-ገጾችን ከመሰረቱ ጀምሮ ለመገንባት ያስችልዎታል። ልክ አንድን ቤት ሲሰሩ የተለያዩ ክፍሎች (ሳሎን፣ መኝታ ቤት፣ ወጥ ቤት...) እንደሚያስፈልጉት ሁሉ፣ ድረ-ገጽም የተለያዩ ክፍሎች አሉት። ፓይተን እነዚህን ክፍሎች በቀላሉ እና በፍጥነት ለመስራት ያግዝዎታል።

✅Django እና Flask: እነዚህ በፓይተን የተሰሩ ኃይለኛ ፍሬምወርኮች (frameworks) ናቸው። ልክ አንድን ቤት ለመስራት የሚያገለግሉ ዘመናዊ መሳሪያዎች (ለምሳሌ፡- ኤሌክትሪክ መሰርሰሪያ፣ ሌዘር መቁረጫ...) ስራውን እንደሚያቀላጥፉት ሁሉ፣ Django እና Flaskም የድረ-ገጽ ልማትን በጣም ያቀላጥፉታል።

➡️Django: ለትላልቅ እና ውስብስብ ድረ-ገጾች ተመራጭ ነው። ለምሳሌ፡- Instagram በከፊል የተገነባው በDjango ነው።

➡️Flask: ለአነስተኛ እና መካከለኛ ድረ-ገጾች ተመራጭ ነው። ለመማር ቀላል እና ፈጣን ነው።
ከጀርባ (ከኋላ) ያለው (Back-End): ይህ ከፊት ለፊት የማይታየው፣ ነገር ግን ድረ-ገጹ እንዲሰራ የሚያደርገው ዋናው ክፍል ነው። ለብዙ አገልግሎት የሚውሉ ሎጂኮችን የሚይዝልን! ለምሳሌ ተጠቃሚዎች ፎርም ሲሞሉ፣ መረጃ ሲያስገቡ፣ ክፍያ ሲፈጽሙ... ይህ ሁሉ የሚከናወነው በBack-End ነው።

✅ዳታ ሳይንስ (Data Science):
በዘመናችን መረጃ (data) እንደ ነዳጅ ነው። ግን ነዳጅ ብቻውን ምንም አይጠቅምም። መኪና ውስጥ ገብቶ መንቀሳቀሻ እስኪሆን ድረስ። ልክ እንደዚሁ፣ መረጃም ተተንትኖ፣ ተቀናጅቶ፣ ትርጉም እስኪያገኝ ድረስ ምንም አይጠቅምም። ፓይተን ይህን ሂደት በጣም ቀላል ያደርገዋል።

✅NumPy, Pandas, Matplotlib: እነዚህ በፓይተን የተሰሩ አስፈላጊ ላይብረሪዎች (libraries) ናቸው። ልክ አንድን ኬክ ለመጋገር የሚያስፈልጉ ግብዓቶች (ዱቄት፣ ስኳር፣ እንቁላል...) እንደሚያስፈልጉት ሁሉ፣ ዳታ ሳይንስንም ለመስራት እነዚህ ላይብረሪዎች ያስፈልጋሉ።

➡️NumPy: ለቁጥራዊ ስሌቶች (numerical computations) ያገለግላል። ለምሳሌ፡- አማካይ (average)፣ መደበኛ መዛባት (standard deviation) ለማስላት።

➡️Pandas: መረጃዎችን ለማቀናጀት እና ለመተንተን ያገለግላል። ለምሳሌ፡- ከExcel ፋይል ላይ መረጃ ለማንበብ፣ ለማጣራት፣ ለመቀየር።

➡️Matplotlib: መረጃዎችን በግራፍ እና በቻርት መልክ ለማሳየት ያገለግላል። ለምሳሌ፡- የሽያጭ መረጃን በጊዜ ሂደት ለማሳየት።

✅ ምሳሌ: አንድ የባንክ ሰራተኛ የደንበኞቹን የብድር ታሪክ ተንትኖ፣ ብድር መክፈል የሚችሉ እና የማይችሉ ደንበኞችን መለየት ቢፈልግ፣ ፓይተንን ይጠቀማል።

✅ማሽን ለርኒንግ (Machine Learning):
ማሽን ለርኒንግ ኮምፒውተሮች ከመረጃዎች (ከዳታ) እንዲማሩ ማድረግ ነው። ልክ አንድን ልጅ ሲያስተምሩ በተደጋጋሚ ምሳሌዎችን እያሳዩ እንደሚያስረዱት ሁሉ፣ ማሽን ለርኒንግም እንዲሁ ነው። ግን ማሽን ለርኒንግ ከልጅ ትምህርት የሚለየው፣ ኮምፒውተሮች በጣም ብዙ መረጃዎችን በአጭር ጊዜ ውስጥ መማር መቻላቸው ነው!

➡️Scikit-learn, TensorFlow, Keras: እነዚህ በፓይተን የተሰሩ ኃይለኛ ላይብረሪዎች ናቸው።

➡️Scikit-learn: ለአብዛኛዎቹ የማሽን ለርኒንግ ስራዎች ተመራጭ ነው። ለምሳሌ፡- ምስሎችን መለየት፣ ጽሑፎችን በተለያዩ ምድቦች መከፋፈል።

➡️TensorFlow እና Keras: ለdeep learning ያገለግላሉ። ለምሳሌ፡- ፊትን መለየት፣ ድምጽን መለየት።

✅ ምሳሌ: አንድ የኢሜይል አገልግሎት አቅራቢ (ለምሳሌ፡- Gmail) "spam" ኢሜይሎችን ለመለየት ፓይተንን ይጠቀማል። ይህ ማሽን ለርኒንግ ነው!  Spam or non-spam ብሎ! ከክላስፊኬሽን (ባይናሪ ክላስፊኬሽን) ይመደባል። ወደዚህ ወደ ውስጥ ከገባን መንገዱ ሰፊ ስለሆነ በራሱ በማሽን ለርኒንግ ርእስ እናየዋለን።


✅አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence - AI):
AI ከማሽን ለርኒንግ ይበልጣል። AI ኮምፒውተሮች እንደ ሰው እንዲያስቡ፣ እንዲወስኑ እና እንዲሰሩ ማድረግ ነው።

➡️PyTorch: ይህ በፓይተን የተሰራ ላይብረሪ ለAI ምርምር እና ሞደሎችን ለመስራት በስፋት ጥቅም ላይ ይውላል።

ምሳሌ: ራሳቸውን የሚያሽከረክሩ ሹፌር አልባ መኪኖች (self-driving cars) በAI ላይ የተመሰረቱ ናቸው። ፓይተን የእነዚህ መኪኖች "አንጎል" (ሞደል) ለመገንባት ያገለግላል።

✅ስክሪፕቲንግ እና አውቶሜሽን (Scripting and Automation):
በኮምፒውተርዎ ላይ ተደጋጋሚ ስራዎችን መስራት አሰልቺ ነው አይደል? ለምሳሌ መቶ ፎቶዎችን በአንድ ጊዜ ስም መቀየር፣ ብዙ ፋይሎችን ከአንድ ፎልደር ወደ ሌላ ፎልደር መገልበጥ... ፓይተን እነዚህን ስራዎች የሆነች ስክሪፕት በመፃፍ በቀላሉ በራሳቸው እንዲሰሩ ማድረግ ይችላል!

ምሳሌ: አንድ የሲስተም አስተዳዳሪ (system administrator) በየቀኑ የኮምፒውተሮችን ሁኔታ ለመፈተሽ እና ችግሮችን ለመፍታት ፓይተን ስክሪፕት ሊጠቀም ይችላል።

በMizan Institute of Technology (MiT) የፓይተን ኮርስ ስልጠና የምንሸፍናቸው ርዕሶች:

✅መሰረታዊ የፓይተን ፕሮግራሚንግ (Python Fundamentals):

➡️ (Variables): መረጃዎችን ለማከማቸት የሚያገለግሉ ስያሜዎች።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Mizan Institute of Technology - MiT🇪🇹
💻ከፍተኛ ተፈላጊነት በስራ ገበያ: በአሁኑ ወቅት ፓይተን በዓለም ላይ ካሉት በጣም ተፈላጊ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች አንዱ ነው። ስለምንነቱ ትንሽ እናውራ! ፓይተን ፕሮግራሚንግ (Python Programming) ከድረ-ገጽ ልማት እስከ ዳታ ሳይንስ፣ ከማሽን ለርኒንግ እስከ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ፣ ከጨዋታ (ጌም) ስራ እስከ ሳይንሳዊ ምርምር... ፓይተን የሌለበት የቴክኖሎጂ ዘርፍ ማግኘት በጣም አስቸጋሪ…
➡️የዳታ አይነቶች (Data Types): ቁጥሮች (integers, floats), ጽሑፎች (strings), ቡሊያኖች (booleans), ዝርዝሮች (lists), መዝገበ-ቃላት (dictionaries)...
እነዚህ በተጨባጩ አለም ያለውን ነገር ሁሉ የምንወክልባቸውና ለኮምፒዩተሩ የምናስተዋውቅባቸው ናቸው።

➡️ኦፕሬተሮች (Operators): የሂሳብ ስሌቶችን (+, -, *, /), ንፅፅሮችን (==, !=, >, <), ሎጂካዊ ኦፕሬሽኖችን (and, or, not) ለመስራት።

➡️የቁጥጥር መዋቅሮች (አንዳንድ ጊዜ ቀጥታ በአማርኛ መተርጎሙ ሴንሱን ያሳጣዋል) (Control Structures): ሁኔታዊ መግለጫዎች (if, elif, else), ዑደቶች (for, while) - ፕሮግራሙ በተወሰነ ቅደም ተከተል እንዲሰራ ለማድረግ።

➡️ፈንክሽኖች (Functions): ተደጋጋሚ ኮዶችን በአንድ ቦታ ለመሰብሰብ እና ስም ለመስጠት። ኮዱን እንደገና መጠቀም (reuse) ያስችላል።

➡️ሞጁሎች እና ፓኬጆች: ከሌሎች የሰሩትን ኮድ ለመጠቀም የሚረዱን።

✅ የፓይተን ፅንሰ-ሀሳቦች (Advanced Python Concepts):

➡️(Object-Oriented Programming - OOP): ኮድን በክፍሎች (classes) እና ነገሮች (objects) መልክ ለማደራጀት ይጠቅማል። ትላልቅ ፕሮግራሞችን ለመስራት በጣም አስፈላጊ ነው።

✅ ሞጁሎች (Modules) እና ፓኬጆች (Packages): የራስዎን ሞጁሎች እና ፓኬጆች መፍጠር።

✅ ፋይል አያያዝ (File Handling): ከፋይሎች ላይ መረጃ ለማንበብ እና ለመፃፍ።
Exceptions handling
Regular expressions
✅ ዌብ ስክራፒንግ

ከላይ የተጠቀሱትን የፓይተን ዘርፎች (Web Development, Data Science, Machine Learning...) በዝርዝር እናስተምራለን።

🔽Django/Flask: ለድረ-ገጽ ማበልፀግ።
🔽NumPy, Pandas, Matplotlib: ለዳታ ሳይንስ።
🔽Scikit-learn, TensorFlow, Keras: ለማሽን ለርኒንግ።

✅ ፕሮጀክቶችን (Capstone Projects): ቲዎሪውን በተግባር ለማዋል ፕሮጀክት ወሳኝ ነው! ከታች ያሉትን እና ሌሎች በርካታ ፕሮጀክቶችን አብረን እንሰራለን።

ፕሮጀክቶችን መስራት (Hands-on Projects):
በMiT ስልጠናችን፣ ቲዎሪ ብቻ አይደለም የምናስተምረው። የተማራችሁትን በተግባር የምትፈትሹበት፣ እውነተኛ ፕሮጀክቶችን የምትሰሩበት እድል ይኖራችኋል። ይህ በጣም አስፈላጊ ነው! ምክንያቱም ፕሮጀክቶችን ስትሰሩ ነው በእውነት የምትማሩት!
የራስዎን ድረ-ገጽ መገንባት: በDjango ወይም Flask በመጠቀም ከባዶ (from scratch) ድረ-ገጽ እንሰራለን። ይህ ድረ-ገጽ የእናንተ ፖርትፎሊዮ (portfolio) ሊሆን ይችላል። ለስራ ሲያመለክቱ የሚያሳዩት! ድረ ገፅ ያልሰራ ሰው የቴሌግራም ቦት፣ የአየር ንብረት ትንታኔ፣ የክሪፕቶ ፕሪዲክሽን… ወዘተ መስራት የሚችል ስራ ይሰራል።

➡️የዳታ ትንተና ፕሮጀክት: ከድረ-ገጽ ላይ መረጃዎችን ሰብስበን (web scraping), አቀናጅተን፣ ተንትነን፣ በግራፍ መልክ እናሳያለን። ለምሳሌ፡- ከኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ድረ-ገጽ ላይ የምንዛሬ ተመንን (exchange rate) መረጃ ወስደን መተንተን።

➡️የማሽን ለርኒንግ ሞዴል መገንባት: ለምሳሌ፡- የእጅ ጽሑፍን (handwritten digits) የሚለይ ሞዴል መገንባት። ይህ ሞዴል የፖስታ ኮዶችን (zip codes) ለማንበብ ሊያገለግል ይችላል።

➡️የአውቶሜሽን ስክሪፕት መፃፍ: ለምሳሌ፡- በኮምፒውተርዎ ላይ ያሉትን ሁሉንም .jpg ፋይሎች ወደ .png የሚቀይር ስክሪፕት መፃፍ።

➡️ጌም መስራት: ለምሳሌ እንደ ፓክ-ማን ያሉ ቀላል ጌሞችን መስራት።

ይህ ከጀማሪ እስከ አድቫንስድ ይወጥላል!

✅የስራ እድሎች፡ ወሰን የለሽ ነው!
ፓይተንን ከተማሩ በኋላ፣ የስራ እድልዎ በጣም ሰፊ ነው።

➡️ በአገር ውስጥ (ኢትዮጵያ): ባንኮች፣ ቴሌኮሙኒኬሽን ኩባንያዎች፣ መንግስታዊ ድርጅቶች፣ ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች... ሁሉም ፓይተን ፕሮግራመሮችን ይፈልጋሉ።

➡️በውጭ አገር: በአለም አቀፍ ደረጃ ፓይተን ፕሮግራመሮች በጣም ተፈላጊ ናቸው። ከፍተኛ ደሞዝ እና ጥቅማጥቅሞች ያገኛሉ።

➡️ፍሪላንስ (Freelance): የራስዎ አለቃ መሆን ይችላሉ! ፕሮጀክቶችን መርጠው፣ በፈለጉት ጊዜ እና ቦታ መስራት ይችላሉ። Upwork, Fiverr, Toptal... እነዚህ ድረ-ገጾች ለፍሪላንስ ፓይተን ፕሮግራመሮች ብዙ እድሎችን ይሰጣሉ።

➡️የርቀት ስራ (Remote Work): ከቤትዎ ሆነው፣ ለአለም አቀፍ ኩባንያዎች መስራት ይችላሉ። ይህ ማለት አለምን ሳይዞሩ፣ አለም አቀፍ የስራ ልምድ ማግኘት ይችላሉ!

✅ግምታዊ ደሞዝ:
በኢትዮጵያ: እንደየልምድና ብቃቱ ይለያያል። ከጀማሪ እስክ ከፍተኛ ልምድ ላላቸው 10,000 - 50,000+ ብር በወር ክፍያ ማግኘት ይቻላል።

➡️በውጪ: በአሜሪካ ለምሳሌ ጀማሪ የፓይተን ፕሮግራመር በዓመት ከ70,000 ዶላር በላይ ሊያገኝ ይችላል። ልምድ ያላቸው ፕሮግራመሮች ደግሞ ከ100,000 - $200,000+ ዶላር በዓመት ያገኛሉ።



✅ታዋቂ ኩባንያዎች ፓይተንን ለምን ይጠቀማሉ?
➡️Google: ለsearch engine, ለዩቲዩብ, ለGmail... ፓይተን በGoogle ውስጥ በጣም ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

➡️Facebook: ለማህበራዊ ሚዲያ መድረካቸው፣ ለInstagram... ፓይተን Facebook በፍጥነት እንዲያድግ ረድቶታል።

NASA, IBM, Dropbox, Reddit, ... እና ሌሎች በጣም ብዙ ኩባንያዎች ፓይተንን ይጠቀማሉ።


ፓይተን መማር ለወደፊትዎ ምርጥ ኢንቨስትመንት ነው! በተለይም በዚህ ከሚጠበቀው በላይ እየተስፈነጠረ ባለው የአርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ አለም ፓይተን የጀርባ አጥንት ነው።
በተቋማችን MiT ጥራት ያለው ስልጠና፣ እውነተኛ ፕሮጀክቶችን የመስራት ልምድ፣ እና ለስራ ገበያው የሚያዘጋጅዎትን ክህሎት እናቀርብልዎታለን። ከቲዎሪ ባለፈ በተግባር ላይ ያተኮረ ስልጠና እንሰጣለን።


አሁንኑ ይመዝገቡ! ጊዜ አይጠብቁ! የወደፊትዎን በቴክኖሎጂው አለም ዛሬ ይገንቡ! በMiT የፓይተን ስልጠና በትክክል ከተማሩት ህይወትዎን ይቀይራል!



በMizan Institute of Technology የፓይተን ኮርስ ረዳት ኢንስትራክተር የተዘጋጀ።


አሁን ላይ እየተካሄደ ባለው 8ኛ ዙር ምዝገባችን መሳተፍ ከፈለጉ:  www.mizantechinstitute.com ላይ ገብተው ይመዝገቡ።
ስለሚመዘገቡት ኮርስ በቂ መረጃ ከሌለዎ: በቴሌግራም ወይም በአካል ቢሯችን በመገኘት ያናግሩን::
✅ቴሌግራም: http://t.me/MizanInstituteOfTechnologyEthio
🗺 በአካል ተገኝተው በቂ ማብራሪያ አግኝተው ለመመዝገብ: ቤተል አፕል ፕላዛ 7ኛ ፎቅ (ቢጫ ፎቅ ፊት ለፊት)



ስሌሎች ኮርሶች ምንነትና ማብራሪያ ለማወቅ ፍላጎቱ ካለዎት ኮመንት ላይ ያሳውቁን።


ቀጣይ ስለ የትኛው ኮርስ ማብራሪያ እንስጥዎት⚡️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2️⃣4️⃣ 🔤🔤🔤🔤🔤 🔠🔠🔠🔠
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ምዝገባ ክፍት ነው👨‍💻

በተቋማችን Mizan Institute of Technology (MiT) በሚከተሉት ኮርሶች ስትማሩ ከምታገኟቸው ጥቆሞች መካከል፦

1⃣ እያንዳንዱ የምንሰጠው ኮርስ በተለመደው የሃገራችን የትምህርት ስርአት መሰረት በተግባር ባልታገዘ ቲዎሪ ላይ ብቻ ያጠነጠነ ሳይሆን ገበያው ላይ ባሉ እውነተኛና ተጨባጭ ፕሮጀክቶች የተደገፈ መሆኑ፣

2⃣ እኛ ጋር በተማራችሗቸው የትምህርት ዘርፎች ጠንክረው የተማሩ ብቁ ተማሪዎችን በዙሪያችን ካሉ መንግስታዊና መንግስታዊ ካልሆኑ ተቋማት ጋር በማገናኘት የስራ እድል እንዲያገኙ ማመቻቸት መቻላችን፣


3⃣ በጣም ምጡቅ የሆኑትን ተማሪዎች እኛው ጋር የምንቀጥር መሆኑ፣


4⃣ ከቅጥር ስራ ባሻገር በግላቸው የራሳቸው ስታርታፕ ከፍተው ለመስራት ፍላጎቱና አቅሙ ላላቸው የበኩላችን ድጋፍ ማድረጋችን፣


5⃣ ተማሪዎቻችን ከኛ ጋር የሚማሩትን ኮርስ ካጠናቀቁ በሗላ የተለያዩ መማሪያ ማቴሪያሎችን በነፃ እንደፈለጉ እንዲጠቀሙ መፍቀዳችን፣

6⃣ ከኢትዮጵያ እስከ አሜሪካ ባሉ ባሉ ድርጅቶች ላይ መስራት የሚችሉ ተማሪዎችን ማብቃታችን፣

7⃣ ምንም አይነት የኮምፒዩተር እና አይቲ ልምድ የሌላቸውን ተማሪዎች ከጀማሪ ደረጃ "ሀ" ብለን አስጀምረን ልምዱ ካላቸው ጋር እኩል እና አንዳንድ ጊዜ የተሻለ ሆነው እንዲበቁ ማድረጋችን፣

8⃣ ኮምፒዩተር ለሌላቸው ተማሪዎች የተሟላ ዘመናዊ የኮምፒዩተር ላብራቶሪ ማመቻቸታችን፣

9⃣ ይህን ላብራቶሪ ከትምህርት ፕሮግራም ባሻገር በማንኛውም በሚመች ሰአት በነፃ እንዲጠቀሙ ክፍት ማድረጋችን፣

🔟 በኦንላይን ለሚማሩ ተማሪዎች የመማሪያ ማቴሪያሎችን በቪድዮ፣ በጽሑፍ፣ በቀጥታ ስርጭትና መሰል አማራጮች ለአጠቃቀም ቀላልና አመች በሆነው ዘመናዊ ድረ ገፃችን ላይ ማቅረባችን፣

1⃣1⃣ በኦንላይን ለሚማሩ ኢንተርኔት ሲቆራረጥ እንዳይቸገሩ የቀጥታ ስርጭት ክላሶችን ሪከርድ አድርገን በሚመቻቸው ሰአት እንደፈለጉ እንዲከታተሉ ማስቻላችን፣

1⃣2⃣ የምንሰጣቸውን ኮርሶች የተወሰነ ክፍላቸውን ብቻ በብዙ ቦታ እንደሚደረገው ከላይ ከላይ ነካ ነካ አድርገን ሳናስተምር፤ በዚያ መስክ ገበያው ላይ አስፈላጊ የሆኑና ጊዜ ያላለፈባቸውን መስኮች መርጠን በብቃት ማስተማር መቻላችን፣

1⃣3⃣ አዲስ አበባና አካባቢው ላሉ በአካል መማር ለሚፈልጉ የበአካል ክላስ መጀመራችን፣ ከሃገር ውጭ ለሆኑና ክፍለ ሃገር ላሉ የኦንላይን ፕሮግራም ማመቻቸታችን፣

1⃣4⃣ በአካል ለሚማሩ regular, weekend እና extension አማራጮችን ማመቻቸታችንና በአሳማኝ ምክንያት ከአንዱ ወደ አንዱ ፕሮግራም መቀየር ለሚፈልጉ በነፃ መፍቀዳችን፣

1⃣5⃣ ለብቃታችን በቀላሉ ከዘመናዊ ድረ ገፃችን ጀምሮ ውጤታማ የቀድሞ ተማሪዎቻችን ምስክር ናቸው::

ዛሬ ነገ ሳይሉ ዛሬውኑ ይመዝገቡና ቴክኖሎጂውን ከነ ቤተሰብዎ ይቀላቀሉ::

ከታዳጊ እስከ ታላላቅ ሰዎች፣ ልምዱ ላላቸውም ለሌላቸው በየደረጃው በሚገባ የተዘጋጁ ኮርሶች አሉን:: ተቀላቀሉን::


ለመመዝገብና ኮርሶቹ በውስጣቸው የሚያካትቱትን ዝርዝር ለማየት: http://www.mizantechinstitute.com

ኮርሶቹን ለማጠናቀቅ ምን ያክል ወር ይፈጃል የሚለውን ለማወቅ ይህን ሊንክ ተጭነው ያንብቡ። https://t.me/MizanInstituteOfTechnology/183


ካሉን ዘመናዊ የቴክኖሎጂ ኮርሶች መካከል፦
☞⇨ ፉል ስታክ ዌብ ዴቨሎፕመንት
☞⇨ ዲጅታል ማርኬቲንግ
☞⇨ ግራፊክ ዲዛይን
☞⇨ የሞባይል መተግበሪያ ማበልፀግ
☞⇨ ፓይተን
☞⇨ ማሽን ለርኒንግና ዲፕ ለርኒንግ
☞⇨ ሮቦቲክስ
☞⇨ የሰው ሠራሽ ልህቀት (አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ)


ክፍያን ጨምሮ ሌሎች ያልገቧችሁ ዝርዝር ነገሮች ካሉ በቴሌግራም በውስጥ @MizanInstituteOfTechnologyEthio ላይ ወይም በኢሜይላችን contact@mizantechinstitute.com ላይ አናግሩን።
ቢሯችን ዛሬ ቅዳሜ እና ነገ እሁድ ሙሉ ቀን ክፍት ነው።

በዚህ በቴሌግራም t.me/MizanInstituteOfTechnologyEthio
ከጠዋት 12:00 እስከ ምሽት 6:00 ሰአት ድረስ ምላሽ እንሰጣለን።

በአካል መጥታችሁ መረጃ ማግኘት የምትፈልጉ ቢሯችን ቤተል አፕል ፕላዛ 7ኛ ፎቅ (ቢጫ ፎቅ ፊት ለፊት)

በአካል መምጣት ለማትችሉ ስልክ 0987143030/0989263030

ወይንም በቴሌግራም t.me/MizanInstituteOfTechnologyEthio ማንኛውንም መረጃ ጠይቁን።

ለመመዝገብ: በአካል ብትመጡም በኦንላይንም ቢሆን ድረ ገፃችን ላይ መመዝገብ ግደታ ነው።

መመዝገቢያ ድረ ገፅ: www.mizantechinstitute.com
Mizan Institute of Technology - MiT🇪🇹
ስለምንሰጣቸው ኮርሶች ማብራሪያ ✅ ክፍል 1️⃣ የፉል ስታክ ድረ-ገጽ ማበልፀግ (Full Stack Web Development)፡ የዲጂታል አለም ቁልፍ! ፉል ስታክ ድረ-ገጽ ማበልፀግ (Full Stack Web Development) መማር ዛሬ ባለንበት የዲጂታል ዘመን ልክ እንደ ወርቅ ቁፋሮ ነው። ለምን? ምክንያቱም ድረ-ገጾች እና የሞባይል መተግበሪያዎች የሁሉም ነገር ማዕከል ሆነዋል። ንግድ፣ ትምህርት፣…
ቀጣይ ስለ የትኛው ኮርሳችን ማብራሪያ ማግኘት ይፈልጋሉ?

እስካሁን ስለ ፉልስታክ ዌብ ደቨሎፕመንት እና ፓይተን ፅፈናል።

1️⃣ ስለ ፉል ስታክ የፃፍነው ከዚህ አስፈንጣሪ ጀምሮይገኛል።
https://t.me/MizanInstituteOfTechnology/381


2️⃣ ስለ ፓይተን የፃፍነው ከዚህ ጀምሮ ይገኛል።

https://t.me/MizanInstituteOfTechnology/385



ቀጣይ 3️⃣ ስለ ማን?
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Live stream scheduled for
1️⃣2️⃣ 🔠🔡🔡🔡🔡 🔤🔤🔤🔤



ሰላም🤝

ምዝገባ የምናጠናቅቀው ዛሬ እሁድ የካቲት 16/2017 ስለሆነ በአካል መምጣት ለምትፈልጉ ቢሯችን ክፍት ነው። ቤተል አፕል ፕላዛ 7ኛ ፎቅ (ቢጫ ፎቅ ፊት ለፊት)

በአካል መምጣት ለማትችሉ 0989263030 ላይ ብቻ ደውላችሁ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
ከስልክ መደወል በተጨማሪ በዚሁ በቴሌግራም t.me/MizanInstituteOfTechnologyEthio ላይ በፅሁፍ በደምፅ ማወቅ የምትፈልጉትን ጠይቁን።

💊
ለመመዝገብ: www.mizantechinstitute.com


በርካታ መረጃወችን በዚሁ ቻነላችን ወደ ሗላ ስትመለሱ ታገኛላችሁ።⭐️
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
በድረ ገጻችን ላይ ስትመዘገቡ በመመዝገቢያ ቅጹ ላይ የሚገኙ ፊልዶች ላይ ስትሞሉ{
☞ Course Categories: በሚለው ላይ የምትመርጡት መማር የምትፈልጉትን አንድ ኮርስ ከሆነ አንዱን ብቻ፥ ሁለት ከሆኑ ሁለት ኮርሶችን check box select ታደርጋላቹህ፣

☞ Select Attendance Mode: በሚለው ላይ መማር የምትችሉበትን አማራጭ(ኦንላይን፣ በአካል ከሆነ regular, extension, weekend) ትመርጣላችሁ፣

☞ Payment Receipt: በሚለው የመመዝገቢያ 500 ብር እና የኮርሱን ወርሃዊ ቅድመ ክፍያ አንድ ላይ በባንክ፣ በሞባይል ባንኪንግ፣ በቴሌብርና በመሳሰሉት አማራጮች ከከፈላችሁ ቡሃላ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ታያይዙታላቹህ።

☞  Transaction ID: በሚለው በከፈላቹህበት ደረሰኝ ላይ የሚገኝ የፊደላትና ቁጥሮች ድብልቅ የክፍያ መለያ ታስገባላችሁ።

☞ Password: በሚለው የራሳችሁን የፈለጋችሁትንና የምታስታውሱትን ቢያንስ አንድ Capital Letter, Small Letter, Number, Special Character ($,%,&,*,#,@) ያካተተና ቢያንስ 8 ርዝመት ያለው መሙላት።


☞ Repeat Password: የሚለው ላይ መጀመሪያ የሞላችሁትን ፓስወርድ ድጋሜ መፃፍ ነው።

☞ Maths Answer: የሚለው የሚመጡላችሁን 2 ቁጥሮች ድምር መሙላት ነው።
}

የእያንዳንዱ ኮርስ ክፍያ ስለሚለያይ እና ሁለት ኮርስ ለሚወስድ ሰው 7% ቅናሽ ስላለን የተቋሙን የባንክ አካውንቶችና የምትማሩትን ኮርስ ክፍያ ለማወቅ በኢሜይላችን contact@mizantechinstitute.com ወይም በቴሌግራም @mizaninstituteoftechnologyEthio ላይ ጠይቁን።
#Update
በውስጥ መስመርና በቀጥታ የስልክ መሾመር በቀረቡልን በርካታ ጥያቄዎች መሠረት የምዝገባ ጊዜ ለአንድ ሳምንት  ተራዝሟል።

በነዚህ ቀናት ውስጥ፦
¶ ተመዝግባችሁ ያልከፈላችሁ ወይም የመመዝገቢያ ክፍያ ብቻ የከፈላችሁ ቀሪ ክፍያችሁን አጠናቁ።

¶ ከፍላችሁ ግን ያልተመዘገባችሁ ምዝገባችሁን አጠናቁ።

¶ ከፍላችሁ ግን የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ያልላካችሁ በአድራሻዎቻችን ላኩ።

¶ ያልተመዘገባችሁና ያልከፈላችሁ ሆናችሁ ኮርሱን መውሰድ የምትፈልጉ ክፍያውን ከፍላችሁ ምዝገባውን በማጠናቀቅ የከፈላችሁበትን ደረሰኝ ላኩ።

በአካል መምጣት ለማትችሉ 0989263030 ላይ ብቻ ደውላችሁ መረጃ ማግኘት ትችላላችሁ።
ከስልክ መደወል በተጨማሪ በዚሁ በቴሌግራም t.me/MizanInstituteOfTechnologyEthio ላይ በፅሁፍ ወይም በድምፅ ማወቅ የምትፈልጉትን ጠይቁን።

💊
ለመመዝገብ: www.mizantechinstitute.com
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🌟 ዲጂታል ማርኬቲንግ - የንግድዎ የወደፊት እድል✔️
የገበያው አየር ቀዝቅዟል⁉️

📱 ዲጂታል ማርኬቲንግ ምንድን ነው❓
ዲጂታል ማርኬቲንግ ማለት ንግድዎን እና አገልግሎትዎን (products & services) በዲጂታል መንገድ (በኢንተርኔት፣ በሶሻል ሚዲያ፣ በኢሜይል፣ በሞባይል አፕሊኬሽኖች፣ በድረ ገፆች፣ በሰርች ኢንጂኖች) እንደ ኮምፒዩተር፣ ላፕቶፕ፣ ስልክ፣ ታብሌትና የመሳሰሉትን ድጅታል መሳሪያወች በመጠቀም ለደንበኞች ማድረስ ነው።

መርካቶ ወይም የሆነ ቦታ ላይ ብቻ ተገድቦ ከሚሸጥና ከሚያከፋፍል ነጋደ ይልቅ መርካቶ ላይ ከመሸጡ ተጨማሪ የሚሸጣቸውን ቁሳቁሶች ሶሻል ሚዲያን ጨምሮ በኢንተርኔቱ አለም ላይ በማስተዋወቅ የሚሸጠው ነጋደ ይበልጣል።

ቤተል ወይም የሆነ ቦታ ላይ ብቻ ተገድቦ ትልቅ ታፔላና ባነር ለጥፎ አገልግሎት ከሚሰጠው ተቋም ይልቅ የሚሰጠውን አገልግሎት ሶሻል ሚዲያን ጨምሮ በኢንተርኔቱ አለም ላይ የሚያስተዋውቀው ሰርቪስ ሰጭ ተቋም የተሻለ የደንበኞች ብዛት አሉት።

እሱ ለሚሰጠው ሰርቪስ የሚሆኑ ደንበኞች ያሉት አድስ አበባ ላይ ብቻ ሆነው ሳለ: በመላው አገር ለሚተላለፍ የቲቪ ወይም የራድዮ ማስታወቂያ ከመክፈል ይልቅ አድስ አበባ ላይ ብቻ ላሉ ሰወች ይህን መልእክት አድርስልኝ ብሎ ማስታወቂያ የሚያሰራ ድርጅት የበለጠ አትራፊ ነው።

💼 በዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተገኘ ውጤት:

1. Nike የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ካደረገ በኋላ:
- የኦንላይን ሽያጭ በ82% ጨምሯል
- በ2023 $5.5 ቢሊዮን ገቢ ከዲጂታል ሽያጭ ብቻ አግኝቷል
- የማርኬቲንግ ወጪው በ30% ቀንሷል

2. Starbucks Digital Strategy:
- 27+ ሚሊዮን የፍጆታ መተግበሪያ ተጠቃሚዎች አግኝቷል
- 40% የሽያጭ መጨመር (በአፕ በኩል) አሳክቷል
- $2.5+ ቢሊዮን ተጨማሪ ገቢ በ2023 አግኝቷል

3. የአማዞን ዲጂታል ስትራቴጂ:
- 300+ ሚሊዮን አባላት በአለም አቀፍ ደረጃ አግኝቷል
- $514 ቢሊዮን ዓመታዊ ገቢ


📊 አዳዲስ Case Studies:

1. Ethiopian Airlines Digital Success:
- 85% የቲኬት ሽያጭ በዲጂታል ፕላትፎርም ለማድረግ እየሰራ ነው
- 2.5 ሚሊዮን የመተግበሪያ ተጠቃሚዎች
- በቢሊዮን+ ዓመታዊ ገቢ

2. Local Success: Ride App
- 500,000+ ተጠቃሚዎች በአዲስ አበባ
- 1000+ የስራ እድል ፈጥሯል



🌍 የዲጂታል ማርኬቲንግ አሃዞች:

በአለም አቀፍ ደረጃ:
- $400+ ቢሊዮን የገበያ መጠን
- 17% የዓመታዊ እድገት
- 90% ንግዶች ዲጂታል ማርኬቲንግ ለመጠቀም በስራ ላይ ናቸው።

በኢትዮጵያ:
- 25+ ሚሊዮን የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች አሉ ተብሎ ይገመታል
- 6.8+ ሚሊዮን የፌስቡክ ተጠቃሚዎች
- በርካታ % ዓመታዊ የዲጂታል ንግድ እድገት እየታየ ነው።

💡 ለምን አሁን መማር አስፈላጊ ሆነ?⭐️

1. የገበያው እድል:
- 98% የኢትዮጵያ ንግዶችና ድርጅቶች ዲጂታል ማርኬቲንግ አያውቁም
- በቀጣይ 5 ዓመታት 500,000+ የስራ እድል ይፈጠራል ተብሎ ይገመታል
- $50+ ሚሊዮን የሃገር ውስጥ የገበያ እድል ይኖራል ተብሎ ይገመታል

2. የወደፊት እድገት:
- 90% የንግዶች ወደ ዲጂታል እየተሸጋገሩ ነው
- የዲጂታል ማርኬቲንግ ባለሙያዎች ፍላጎት እየጨመረ ነው
- ከፍተኛ የደሞዝ መጠን በቅጥርም ሆነ በግል ስራ ወይም በፍሪላንስ አለ

3. ዓለም አቀፍ እድል:
- Freelancing በUpwork እና Fiverr እንድሁም በሌሎች የፍሪላንስ ፕላትፎርሞች
- Remote Jobs በዓለም አቀፍ ኩባንያዎች
- ማርኬቲንግ Agency ለመክፈት እድል ይፈጥራል

📈 ROI (Return on Investment) Case Studies:

1. Coca-Cola Digital Campaign:
ኢንቨስትመንት ያደረገው: $1,000,000
ውጤት:
- $4,500,000 ገቢ ያገኘው
- 350% ROI
- 10 ሚሊዮን+ reach



🎯 በMiT የሚማሯቸው ዋና ዋና ክህሎቶች:

1. Data-Driven Marketing:
- Google Analytics
- Facebook Insights
- SEO Tools
- Market Research

2. Content Creation:
- Video Marketing
- Copywriting
- Graphic Design
- Social Media Content

3. Digital Advertising:
- Facebook Ads
- Google Ads
- Instagram Ads
- LinkedIn Ads

4. Technical Skills:
- Website Development
- Email Marketing 
- Mobile Marketing & ORM
- Marketing Automation
- CRM Systems

💰 የገቢ እድሎች (በወር):

1. Junior Digital Marketer:
- Local: 15,000 - 25,000 ETB
- International: $800 - $1,500

2. Mid-Level Marketer:
- Local: 30,000 - 50,000 ETB
- International: $2,000 - $4,000

3. Senior Level:
- Local: 60,000+ ETB
- International: $5,000+

4. Freelancing:
- Project Based: $200 - $2,000
- Monthly Retainer: $500 - $3,000

🎁 ልዩ ጥቅማጥቅሞች በMiT:

1. Real Projects:
- እውነተኛ ከሆኑ ንግዶች ጋር መስራት
- Portfolio መገንባት
- የስራ ልምድ ማግኘት

2. Mentorship:
- ከተሳካላቸው ባለሙያዎች መማር
- One-on-One Coaching
- Lifetime Support

3. Tools & Resources:
- Tools Access
- Updated Materials
- Case Studies

4. Job Support:
- CV Writing
- Interview Preparation
- Job Placement


📞 ለመመዝገብ:
ይደውሉ: +251-989-26-30-30
ቴሌግራም: @MizanInstituteOfTechnologyEthio
ድረ-ገጽ: www.mizantechinstitute.com

አድራሻ: Apple Plaza, 7ኛ ፎቅ፣ በቤቴል፣ አዲስ አበባ

"The best time to start was yesterday. The next best time is NOW!"

ለመጀመር የተሻለው ጊዜ ትናንት ነበር። ቀጣዩ የተሻለ ጊዜ ዛሬ ነው።

🎓 Early Bird Special Offer:

- Certification

አሁኑኑ ይመዝገቡ እና የዲጂታል ዘመኑ አካል ይሁኑ!

ለበለጠ መረጃ ድረ ገፃችንን ይጎብኙ:
https://mizantechinstitute.com/course-category/digital-marketing/
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
🎨 ግራፊክ ዲዛይን - የፈጠራ ኢንዱስትሪው መነሻ

📱 ግራፊክ ዲዛይን ምንድን ነው?
ግራፊክ ዲዛይን ማለት የእይታ ኮሙዩኒኬሽን ሙያ ሲሆን፣ በዋናነት ኮምፒውተርን (ስማርት ስልኮችን) በመጠቀም የንግድ ምልክቶችን (ሎጎ)፣ ፖስተሮችን፣ ብሮሸሮችን፣ የማስታወቂያ ቁሳቁሶችን፣ የድረ ገጽ ንድፎችን እና ሌሎች የእይታ ይዘቶችን የመፍጠር ሙያ ነው።

አብዛኛወቹ የእኛ ሃገር ድርጅቶችና ታላላቅ ተቋማት ጭምር ደረጃውን የጠበቀ ብራንድ የላቸውም:: ስለ ከለር ብራንድ ብዙወች አይጨነቁም። ቋሚ የሆነ የተቋም ብራንድ በሁሉም ጊዜና ቦታ የሚጠቀሙ ውስን ናቸው። ልክ የሆኑ ከለሮችና የሆነ ሎጎ ስናይ ይህ የእገሌ ተቋም ነው ብለን መናገር የምንችላቸው ውስን ናቸው! ብዙ ተቋም ደረጃውንና ብራንዱን የጠበቀ ዘመናዊና ቀለል ያለ፣ ውስብስብ ያልሆነ፣ ሳቢና ትርጉም ያለው፣ በቀላሉ ተመልካች አዕምሮ ላይ ተቀርፆ የሚቀር ሎጎ የለውም። የለም ማለት በርካታ የስራ እድል እንዳለ አመላካች ነው። ስራውን መስራት ለኚህ አይነት ተቋማት ስለ ብራንድ ጥቅም ግንዛቤ ከመፍጠር ይጀምራል።

የህትመት ቤቶችን ጨምሮ በርካታ ቦታወች፣ የሚዲያ ተቋማትና ኤጀንሲወች ላይ ግራፊክ ድዛይነር ያስፈልጋል። አብዛኛው ተቋም ስራ ሲጀምር ታፔላ መለጠፍ፣ የማስታወቂያ ባነር፣ ብሮሸር፣ ቢዝነስ ካርድ፣ ሎጎ ይፈልጋል። ይህ መስክ ከሃገር ውስጥ ስራወች በተጨማሪ ከሃገር ውጭም ፍሪላንሰር ሆኖ ያሰራል።

💼 በዓለም አቀፍ ድርጅቶች የተገኘ ውጤት:

1. Apple Design Team:
- $2+ ቢሊዮን በዲዛይን ገቢ አግኝቷል
- 5000+ ዲዛይን ፓተንቶች አሉት
- በዓመት $50+ ሚሊዮን በዲዛይን ብቻ ቆጥበዋል

2. Nike Graphics:
- 30% የሽያጭ እድገት በአዲስ ዲዛይኖች አግኝቷል
- $500+ ሚሊዮን

📊 በMiT የሚሰጡ የግራፊክ ዲዛይን ኮርሶች:

1. Adobe Creative Suite:
- Photoshop
- Illustrator
- InDesign


2. UI/UX Design:
- Figma
- Adobe XD
- Sketch

3. Brand Design:
- Logo Design
- Brand Identity
- Marketing Materials

🌍 የግራፊክ ዲዛይን አሃዞች:

በአለም አቀፍ ደረጃ:
- $45+ ቢሊዮን የገበያ መጠን አለው
- 12% የዓመታዊ እድገት አሳይቷል
- 3.8+ ሚሊዮን የስራ እድሎች አሉ


💰 የገቢ እድሎች (በወር):

1. Junior Designer:
- Local: 10,000 - 20,000 ETB
- Freelance: $300 - $800

2. Mid-Level Designer:
- Local: 25,000 - 40,000 ETB
- Freelance: $1,000 - $3,000

3. Senior Designer:
- Local: 45,000+ ETB
- Freelance: $3,000 - $8,000

🎯 የሚሰሩባቸው መስኮች:

1. Brand Design:
- Logo Design
- Business Cards
- Branding Materials

2. Marketing Materials:
- Social Media Posts
- Flyers & Brochures
- Billboard Designs

3. Digital Design:
- Website Design
- App Design
- UI/UX Design

4. Print Design:
- Magazine Layouts
- Book Covers
- Packaging Design


🎁 በMizan MiT የሚያገኟቸው ጥቅማጥቅሞች:

1. Industry Tools:
- Templates & Assets

2. Practical Training:
- Real Client Projects
- Portfolio Development
- Industry Mentorship

3. Career Support:
- Job Placement for high achievers
- Freelance Guidance
- Business Setup Support

📞 ለመመዝገብ:
ይደውሉ: +251-989-26-30-30
ቴሌግራም: @MizanInstituteOfTechnologyEthio
ድረ-ገጽ: www.mizantechinstitute.com

አድራሻ: Apple Plaza, 7ኛ ፎቅ፣ በቤቴል፣ አዲስ አበባ

🎓 Early Bird Special Offer:
- Certification

ወደ ዲዛይን ዓለም እንኳን በደህና መጡ!

@MizanInstituteOfTechnology
የሞባይል መተግበሪያ ማበልጸግ (Mobile App Development)

📱 መግቢያ:
የሞባይል አፕሊኬሽን ማበልጸግ ማለት ለስማርት ፎኖች፣ ታብሌቶች እና ሌሎች የሞባይል መሳሪያዎች አፕሊኬሽኖችን የመፍጠር ስራ ነው። እነዚህ መተግበሪያወች ለተለያዩ አላማወች የተሰሩ ናቸው።

ከበርካታ አይነቶቻቸው መካከል
1) ከተግባር አንፃር:
→ የማህበራዊ ትስስር አፖች:
ምሳሌ: ፌስቡክ፣ ኢንስታግራም፣ ሊንክድኢን፣ ዋትስአፕ
→ ለፕሮዳክቲቪቲ የሚውሉ እንደ ጎግል ድራይቭና ማይክሮ ሶፍት ኦፊስ አይነት አፖች
→ ለመዝናኛነት የሚውሉ እንደ ዩ ቲዩብአ ቲክቶክና ስፖቲፋይ
→ የኢኮመርስ አፖች እንደ አሊባባ፣ አማዞን፣ ሾፒፋይና ኢባይ
→ ለመገልገያነት የሚውሉ እንደ ፍላሽ ላይት፣ ካልኩሌተር፣ QR ስካነር
→ ለስፖርትና ለጤና የሚውሉ እንደ ማይፊትነስና ሄድስፔስ
→ ለትምህርት የሚውሉ እንደ ኻን አካዳሚ፣ ዩደሚና ኮርሴሪያ
→ ለገንዘብ ዝውውር የሚውሉ እንደ ፔይፓልና ቬንሞ
2) ከደቨሎፕመንት ሂደት አንፃር:
የሞባይል ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች በዋናነት ገበያውን የተቆጣጠሩት የጎግሉ አንድሮይድ እና የአፕሉ አይኦኤስ ናቸው:: ከነዚህ በተጨማሪ የቻይናው ሁዋዌ የጀመረው ሃርሞኒ ኦኤስ አለ። አንድ የሞባይል መተግበሪያ አበልፃጊ በዋናነት ታሳቢ የሚያደርገው ኦፕሬቲንግ ሲስተማቸው አንድሮይድ እና አይኦኤስ ለሆኑ ስልኮች ነው። ይህ ኔቲቭ አፖች ይባላሉ። ለአንዱ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ብቻ እንዲሰራ ተደርጎ የተሰራ አፕ ኔቲቭ አፕ ነው።
ስለዚህ ከማበልፀግ ሂደት አንፃር:
→ ኒቲቭ የሆኑ አሉ! ምሳሌ WhatsApp (iOS), Google Maps (Android).
→ የተዳቀሉ (ሃይብሪድ) አሉ! ምሳሌ ኢንስታግራምና ትዊተር አይነት
→ ዌብ አፖች አሉ! ምሳሌ ጎግል ዶክስ እና ፍሊፕቦርድ
→ ፕሮግረሲቭ ዌብ አፖች አሉ! ምሳሌ ስታርባክና ፒንተረስት
3) ከኢንዱስትሪና ዶሜይን አንፃር:
→ እንደ ዙምና ሴልስፎርስ ያሉ ቢዝነስ አፖች አሉ
→ እንደ ካንዲክረሽ ያሉ ጌም አፖች
→ እንደ ጎግል ማፕስ፣ ኡበር፣ ራይድ፣ ፈረስ፣ ያንጎና ኤየር ቢኤንቢ ያሉ የመጓጓዣና ናቪጌሽን አፖች
→ እንደ ቢቢሲ ኒውስ ያሉ የዜናና መረጃ ሰጪ አፖች አሉ።



💻 ዋና የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች:

1. Android አፖችን ለመስራት:
- Java
- Kotlin
- Android Studio IDE ገበያው ላይ ይታወቃሉ!

2. iOS አፖችን ለመስራት:
- Swift
- Objective-C
- Xcode IDE

3. Cross-Platform (በሁለቱም ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ላይ የሚሰራ አንድ አፕ ለመስራት):
- Flutter (Dart)
- React Native (JavaScript)
- Ionic (Angular/React)

አሁን ላይ ተፈላጊ የሆነው  ይህ 3ኛው ነው። ምክኛቱም ለምሳሌ ራይድና ፈረስ ሞባይል አፓቸውን ለማሰራት የግድ ሳምሰንግና መሰል ኦኤሳቸው አንድሮይድ የሆኑ ስልክ ያላቸው ደንበኞቻቸው የሚጠቀሙት አንድሮይድ አፕ ይፈልጋሉ፣ የሆነ ደንበኛቸው ደሞ አፕል ስልክ ሊኖረው ይችላል። ስለዚህ ለሁሉም ደንበኞቻቸው ተደራሽ እንዲሆኑ ሁለት አፕ ያስፈልጋቸዋል፣ ለሁለቱም ሁለት የተለያየ ባለሙያ አፕ ሰሪ ሊያፈልጋቸው ነው። ከዚህ ይልቅ ሁለቱም ሲስተሞች ላይ የሚሰራ አንድ ባለሙያ ቢቀጥሩ ከክፍያም አንፃር አዋጭ ነው:: አንድሮይድ አፕ ለሚሰራላቸው 100 ሺ ብር፣ አይኦኤስ አፕ ለሚሰራላቸው 100 ሺህ ብር ከመክፈል፣ ለሁለቱም የሚሰራ አንድ አፕ በ150 ሺ ብር ማሰራት ይበልጣል::

በኛ ተቋም 3ቱም ይሰጣሉ፣ ግን በዋናነት ገበያው ላይ ወደፊት ተፈላጊ የሆነው Flutter ይሰጣል!

📊 የገበያ እድሎች:

በአለም አቀፍ ደረጃ:
- $206.7 ቢሊዮን የገበያ መጠን (2024)
- 18.4% የዓመታዊ እድገት
- 6.3 ቢሊዮን የሞባይል ተጠቃሚዎች

በኢትዮጵያ:
- 25+ ሚሊዮን የስማርትፎን ተጠቃሚዎች
- 200% የዓመታዊ የዲጂታል ኢኮኖሚ እድገት
- እያደገ ያለ የፊንቴክ ዘርፍ

💰 የገቢ እድሎች (በወር):

1. Junior Developer:
- የአካባቢ: 15,000 - 25,000 ብር
- ዓለም አቀፍ: $800 - $2,000

2. Mid-Level Developer:
- የአካባቢ: 30,000 - 70,000 ብር
- ዓለም አቀፍ: $2,500 - $5,000

3. Senior Developer:
- የአካባቢ: 70,000+ ብር
- ዓለም አቀፍ: $6,000+

4. Freelancing:
- በፕሮጀክት: $500 - $5,000
- ወርሃዊ ኮንትራት: $1,000 - $4,000

🎯 የሚሰሩ አፕሊኬሽኖች:

1. ፊንቴክ:
- የክፍያ አፕሊኬሽኖች
- የባንክ አፕሊኬሽኖች
- የዋሌት አፕሊኬሽኖች

2. ኢ-ኮመርስ:
- የሽያጭ መደብሮች
- የማድረስ (ዴሊቨሪ) አገልግሎቶች
- የእቃ መከታተያ

3. ማህበራዊ ሚዲያ:
- የመልእክት መላላኪያዎች
- የይዘት መጋሪያዎች
- የኔትወርኪንግ መድረኮች

📚 የስልጠና ይዘቶች:

1. መሰረታዊ ክህሎቶች:
- Programming Fundamentals
- UI/UX Design
- Database Management
- API Integration

2. የልማት ሂደቶች:
- Agile Development
- Version Control (Git)
- Testing & Debugging
- App Store Deployment

3. የንግድ ክህሎቶች:
- Project Management
- Client Communication
- App Monetization
- Marketing Basics


📱 የገበያ ፍላጎት:

1. የአካባቢ (የሎካል ማርኬት) ፍላጎቶች:
- የባንክ አፕሊኬሽኖች
- የትራንስፖርት አፕሊኬሽኖች
- የድርድር መድረኮች

2. ዓለም አቀፍ እድሎች:
- Freelance Platforms
- Remote Jobs
- Startup Opportunities

🎁 በMiT የሚያገኙት ጥቅሞች:

1. ተግባራዊ ልምምድ:
- እውነተኛ ፕሮጀክቶች
- የግል ፖርትፎሊዮ
- የስራ ልምድ

2. የባለሙያ ድጋፍ:
- የግል አሰልጣኝ
- ቴክኒካል መድረክ
- የስራ ምደባ

3. ሪሶርሶች:
- ዘመናዊ ሶፍትዌሮች
- የመማሪያ ቁሳቁሶች
- የተሳኩ ፕሮጀክቶች

📞 ለመመዝገብ:
ይደውሉ: +2519-89-26-30-30
ቴሌግራም: @MizanInstituteOfTechnologyEthio
ድረ-ገጽ: www.mizantechinstitute.com

አድራሻ: Apple Plaza, 7ኛ ፎቅ፣ በቤቴል፣ አዲስ አበባ


"ዛሬ ጀምረው ነገ የሞባይል አፕ ገንቢ ይሁኑ!"



ለበለጠ:

https://mizantechinstitute.com/course-category/mobile-app-development/


https://t.me/MizanInstituteOfTechnology
📱 🔠🔠🔠🔠3️⃣ 🔤🔤🔤🔤🔠🔠🔠🔠🔡

🔗 www.mizantechinstitute.com

📞0️⃣9️⃣8️⃣9️⃣2️⃣6️⃣ 3️⃣0️⃣ 3️⃣0️⃣


📱 t.me/MizanInstituteOfTechnologyEthio
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
የምዝገባ መርሃ ግብራቹህን ያጠናቀቃቹ ሆናቹ ወደ ዋናው የክላስ ግሩፕ add ያልተደረጋቹ ካላቹ ወይም ከፍላቹ ያልተመዘገባቹህ ካላቹህ በውስጥ አናግሩንና add እናድርጋቹህ።

ተመዝግባቹ ወርሀዊ ክፍያ እና የመመዝገቢያ የከፈላቹበትን ደረሰኝ ያላካቹ በቴሌግራም @MizanInstituteOfTechnologyEthio ላይ ላኩልን።
📱 🔠🔠🔠🔠⚡️ 🔤🔤🔤🔤🔠🔠🔠🔠🔡

🔗 www.mizantechinstitute.com

📞0️⃣9️⃣8️⃣7️⃣1️⃣4️⃣3️⃣0️⃣3️⃣0️⃣ 🔤 0️⃣9️⃣8️⃣9️⃣2️⃣6️⃣ 3️⃣0️⃣ 3️⃣0️⃣



📱 t.me/MizanInstituteOfTechnologyEthio
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ዛሬ እሁድ ቢሯችን ክፍት ነው።



📱 🔠🔠🔠🔠⚡️⚡️ 🔤🔤🔤🔤🔤🔠🔠🔠🔠🔡

🔗 www.mizantechinstitute.com

📞0️⃣9️⃣8️⃣7️⃣1️⃣4️⃣3️⃣0️⃣3️⃣0️⃣ 🔤 0️⃣9️⃣8️⃣9️⃣2️⃣6️⃣ 3️⃣0️⃣ 3️⃣0️⃣



📱 t.me/MizanInstituteOfTechnologyEthio
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM