Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.44K subscribers
1.34K photos
16 videos
9 files
510 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
በማይንድ ሞርኒንግ የባህሪ ጥናት ባለሙያና አማካሪ
እድሜዓለም ግዛ
ኃላፊነት መውሰድ የሙሉነት መገለጫ ነው!

ልጆች ማድረግን ሲማሩ ማመስገን ይችላሉ፤ ማመስገንን ሲማሩ መመስከር ይችላሉ፤ መመስከር ሲችሉ ሚናን መቀበል ይችላሉ፤ ሚናን መቀበል ከቻሉ በመጨረሻ ኃላፊነት መውሰድ ይችላሉ። ስለዚህ ልጆች ይህን መማር እንዲችሉ ወላጆች ሚና የልጅን ጥያቄ መሸከም፥ እኩያ መሆን፥ አብሮ ማድረግና መፍቀድ ጥቂቶቹ ናቸው።
አቶ ሃይሉ ወ/የስ
የዕለቱ ልምድ አካፋይ
የሁለት ልጆች አባት ከልጆቹ ጋር ጓደኛ መሆን የቻለ
"ልጆቼን እንዲህ አድርጉ ብዬ ተናግሬ አላውቅም እኔ ግን ማድረግ ያለብኝን አደርጋለሁ ከዛ እነሱ ተከትለውኝ ያደርጋሉ"
ስላሳየኸን ሆኖ ማሳየት እናመሰግናለን!!
አቶ ብርሃኑ ራቦ
በ ሞሽን ኮንሰልተንሲ አሰልጣኝና አማካሪ

የማያድግ ልጅነት ብለህ የወላጅነትን ሌኤኤኤላ ክፍል አበራህልን! ልጅን ለመረዳት ልጅነታችንን አለመተው፤ልጆቻችን ውስጥ ልጅነታችንን እንይ ብለህ ውስጣችንን ነካኸው!
እናመሠግናለን !!
ፀምረ መዘምር
የመድረኩ ድልድይ

የመማርና የመጠቀም አቅማችን በምንወስደው ነገርና በምርጫችን ላይ ይወሰናል። ያ ደግም የንቃታችንን መጠን ያሳያል። ከዚህ መድረክ በፈለጋችሁት መጠን መውሰድ የናንተ ድርሻ ነው።
ከፈለኝ ዘለለው
የሐዋዝ የጥበብ ምሽት አዘጋጅ

ስለ መጀመር ደግሞም ስለመጨረስ
ስለ መንቃት ደግሞም ስለ መትጋት
ስለ በጎነት ደግሞም ስለ ማካፈል
በጥልቅ ቋንቋና ጥበብ ስጦታህን ስላካፈልከን እና ዓይን ስለጨመርክልን
እናመሰግናለን!!
ሁሌም አብረኸን ለመሆን በጎ ፈቃድህ ስለሰጠኸን በድጋሚ አመስግነናል።
3ተኛው መድረክ በዚህ መልክ ተከናውኗል። ሁላችሁም የዚህ ሃሳብ ባለቤት ስለሆናችሁ እናመሠግናለን!!