Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.44K subscribers
1.34K photos
16 videos
9 files
510 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
🛎 በትንሹ ላለፈው አንድ ወር ራሳችሁን እንዲሁም ቤተሰባችሁን ከተለያዩ እንቅስቃሴዎች ገድባችሁ የቆያችሁ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ ▪️▪️▪️
🛑 ልጆች እቤት በመዋል ምክንያት በመሰላቸት ምን አይነት ባህሪ ሊያሳዩ ይችላሉ?

🌟 ስንፍና 🌟 ከተቀመጡበት መነሳት አለመፈለግ 🌟የግል ንፅህናን አለመጠበቅ ለምሳሌ ጥርስ አለመታጠብ🌟 በተኙበት ልብስ መዋል 🌟መነጫነጭ 🌟አብዝቶ መመገብ ወይም የምግብ ፍላጎት ማጣት 🌟 እርስ በእርስ መጣላት እንዲሁም ክስ ማብዛት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

👉👉በዚህም ምክንያት ጭቅጭቅ ይበዛል፣ እረፍ፣ ተይ፣ ዋ…የሚሉ ቃላት በቤቱ ውስጥ ይበዙና መደማመጥ ይጠፋል፡፡

💢 በእርግጥ እነዚህን ባህሪያት ልጆች ላይ ብቻ ሳይሆን እቤት የሚውሉ ትልልቅ ሰዎችም ሊያሳዩት ይችላሉ ምክንያም ያልተገለፁ ቢገለፁም ያልተሰሙ ስሜቶች ስለሚኖሩ ማለት ነው፡፡

♻️ ሆኖም ግን ረዘም ላለ ጊዜ በቤታችን በመሆናችን ምክንያት የሚመጡት የተለያዩ ባህሪያት እና የስሜት መለዋወጦችን አካላችን የሚሰራበትን ህግ ስለሚቀይሩት ጉዳዩን ማወቅና መቀበል አስፈላጊ ነው።

👉👉 ስለሆነም መሰላቸትን ለመቀነስ በጥቂቱ እነዚህን እናድርግ

🌀 እንቅልፍ ከጨረስን በኋላም ሆነ አርፍዶ አልጋ ላይ አለመቆየት 💠 የእንቅልፍ ስርዓት ሲዛባ ሰውነታችን የሚሰራበትን ህግ በእጅጉ ይቀይረዋል እንዲሁም ሆርሞኖች ላይ የተለያዩ ለውጦች ስለሚያመጣ በሽታ የመከላከልም ሆነ የሰውነታችንን አቅም ይቀንሰዋል
🌀 በተለያዩ ምክንያቶች ሶፋ ላይ የምንቆይባቸውን ጊዜያቶች ማሳጠር 💠ሶፋ ላይ ለረጅም ሰዓት መቀመጥ ትክክል ላልሆነ አቀማመጥ ስለሚዳርገን ለወገብ ህመም ያጋልጣል
🌀 በድርጊት በተለያዩ ተግባራትና አዳዲስ ነገሮችን በመፍጠር ማሳለፍ 💠ከዚህ በፊት መስራት ፈልገን ጊዜ ያጣንባቸውን ነገሮች ማከናወን፣ ለልጆች ጆሮ መስጠት፣ መማማር…
🌀በኤሌክትሮኒክስ ነገሮች እና ካልተመጠነ መረጃ ራስን መቆጠብ 💠 ሰውነታችንም ሆነ አዕምሮችን የተመጠኑ እና ወጥነት ያላቸውን ነገሮች ይፈልጋሉ፡፡ ስለሆነም መረጃችንና ትንታኔያችን ሲበዛ ለተለያዩ የሥነ-ልቦና ጫና ስለሚዳርገን ራስን መቆጠብ አስፈላጊ ነው
🌀የቤተሰብ ፕሮግራም በማውጣት በዚያ ፕሮግራም መትጋት 💠 ከላይ እንደጠቀስነው ሰውነታችን ወጥነት ያለው ነገር የተሻለ እንዲሰራና ውጤታማ እንዲሆን ስለሚረዳው በቤተሰቡ ውስጥ የጋራ የሆነ ፕሮግራም በአንድ ላይ በማውጣት መተግበር
🌀 በቤት ውስጥ መቀበል ያለብንን “ችግር” ያልናቸውን ነገሮች ለይተን በማወቅ መቀበል፡፡ 💠ብዙ ጊዜ ሁሉም ነገር ትክክልና ቀጥ ያለ እንዲሆን ስንፈልግ አጠገባችን ያሉትን ሰዎች ስሜትና ፍላጎት ለመስማት እድል እናጣለን ስለሆነም በቤታችን ውስጥ እንደ ችግርና ያለመግባባት መንስዔ የሆኑ ነገሮች ላይ ጊዜ በመስጠት መቀበል ሚገባንን ነገሮች ሁሉ መቀበል ህይወትን ለማቅለል አንዱ መንገድ ነው፡፡

🔆 የዝምታና ራስን የመመልከት ጊዜ ይሁንልን!!

ማይንድ ሞርኒንግ
https://t.me/mindmorning
http://mind-morning.com
👍1
👏Congratulations!👏
👌ማይንድ ሞርኒንግን በሌላ አማራጭ👌
🎯ኤፍ ኤም 97.1 ላይ
🎯ዘወትር ሰኞ ከቀኑ 9-10 ያገኙናል!
🔆ንጋትና ሕይወት🔆
የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ እድሜዓለም ግዛ እና ፀምረ መዘምር
Mind Morning:
🎬📟📻
🌅 ንጋትና ህይወት የሬድዮ ፕሮግራም
📯 አዘጋጅ፡ ማይንድ ሞርኒንግ
💡 የዕለቱ ባለሙያና አቅራቢ፡
እድሜዓለም ግዛ
በየሳምንቱ ሰኞ ከ 9፡00-10፡ 00
📡 ኤፍ ኤም አዲስ 97.1
🎤 የዕለቱ ርዕስ ፡ ደጅ የበላቸው ማንነቶች 🛠 የርዕስ ይዘት፡ ሥነ-ልቦና፣ የህይወት ዘይቤ፣ ትርጉም፣ ልማድ፣ባህሪ፣ ማንነት
📍 ያዳምጡን፣ ይሳተፉ፣ ይጠይቁ፣ አስተያየት ይስጡ
☎️ 0935 545452

ንጋትና ህይወት የሬድዮ ፕሮግራም!
ማይንድ ሞርኒንግ!

https://t.me/mindmorning
http://mind-morning.com
🌅 ንጋትና ህይወት የሬድዮ ፕሮግራም
የዕለቱ ባለሙያና አቅራቢ፡
እድሜዓለም ግዛ
በየሳምንቱ ሰኞ ከ 9፡00-10፡ 00
📡 ኤፍ ኤም አዲስ 97.1

🎤 የዕለቱ ርዕስ ፡ ስሜትና መገለጫዎቹ 🛠 የርዕስ ይዘት፡ ሃሳብ፣ ስሜት፣ ውጤት፣ የኑሮ ዘይቤ
📍 ያዳምጡን፣ ይሳተፉ፣ ይጠይቁ፣ አስተያየት ይስጡ
☎️ 0935 545452

ንጋትና ህይወት የሬድዮ ፕሮግራም!
ማይንድ ሞርኒንግ!

https://t.me/mindmorning
http://mind-morning.com
Audio
ርዕስ፡ የእናት ፍቅር
እርዝማኔ፡ 1 ደቂቃ ከ48 ሰከንድ
ተረቱ፡
• ልጆች ከወላጆች ጋር የሚወያዩበት
• ከስምንት ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች ወላጆች ሰምተው የሚተረኩላቸው
3
Forwarded from መልካም ተረት
መልካም ተረት ለመልካም እድገት!
የተረት ቻናላችን በቤተሰቦች በኩል ለህፃናትና ታዳጊዎች የሚደርስ ሲሆን፡-
 ቤተሰብን ያወያያል፤ ያቀራርባል
 ህፃናትና ታዳጊዎች ከተረት ሊያገኙት የሚችሉትን ከፍተኛ ጥቅም እንዲያገኙ ይረዳል::
የመልካም ተረት ይዘት፡-
 በድምፅ የተቀረፁ ተረቶች
 የተለያዩ የእንግሊዘኛ የልጆች መፃህፍት
 የሚያወያዩ ቪዲዮዎች
 በመረጃ ላይ የተመሰረቱ መልዕክቶችን ለወላጆች ያቀርባል
ስሜትና መገለጫዎቹ ክፍለ 1 እና ክፍል 2
👍3
በማይንድ ሞርኒንግ የባህሪ ስልጠና ምርምርና ማማከር ከ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በመተባበር የሚያዘጋጀው የሬድዮ ፕሮግራም ዘወትረ ሰኞ ከ 9-10 ሰዓት በቀጥታ ይከታተሉን በእድሜዓለም ግዛ ተዘጋጅቶ ይቀርብላችኋል፡፡
👌1
👏የአሁኑን ክረምት ልጆችዎ በዚህ መንገድ ቢያሳልፉስ?👏

📍ላለፉት 5 ክረምቶች ልጆች ራስን ማወቅና ማበልፀግ ላይ የተለያዩ ስልጠናዎችን ለ 2 ወራት ሲወስዱ ነበር፡፡🔶
🛎አሁን ደግሞ ካለው ተግዳሮት አንፃር ልጆችዎ በቤታቸው በ On line (ZOOM) በመጠቀም እንዲማሩ፣ እንዲሰለጥኑ፣ ጊዜያቸውን በመነቃቃት እንዲያሳልፉ የሚረዱ ስልጠናዎችን በሚገባ ተሰናድተን እየጠበቅንዎ እንገኛለን፡፡ 🎯

📒ያለን ቦታ ጥቂት ስለሆነ ደውለው ማስመዝገብ ይችላሉ
👉0935 545452
👉0912 333020

https://t.me/mindmorning
http://mind-morning.com
👍1