Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.44K subscribers
1.34K photos
16 videos
9 files
510 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
🎯🧩 ከ 4 -11 ዕድሜ እድሜ ላሉ ልጆች ማድረግ የምንችላቸው ነገሮች

🖍 ለልጆች በየእድሜያቸው የተዘጋጁ በቀለማት የሚያሳምሯቸው የተለያዩ አርቶች አሉ ለምሳሌ ማንዳላ “Mandala” አንዱ ልጆች ማድረግ የሚወዱት ተግባር ነው ይህም የትኩረት መጠናቸውን ይጨምራል፣ ፈጠራ አቅማቸውን ያወጡበታል፣በየእድሜያቸው ከተለያየ ዲዛይን ጋር ስላለ ራሳቸወን ይፈትኑበታል፤ ትጋን ይማሩበታል፣ እና ውጤቱን እየሰሩት እዛው ላይ ያዩበታል፡፡ ስለሆነም ይህን ሊንክ ተጠቅመው እነዚህን ማናዳላዎች በማውረድ ፕሪነት አድርገው ሊሰጧቸው ይችላሉ፡፡
https://www.free-mandalas.net/difficulty-level/easy-children/
https://www.woojr.com/mandala-coloring-pages-for-kids-adults/
http://www.supercoloring.com/coloring-pages/arts-culture/mandala/simple-mandalas

🚩 ከሚወዱት የሳይንስ ትምህርት ውስጥ ጊዜ እየወሰዱ እንዲሞክሩ Experiment እንዲያደርጉ ይፍቀዱላቸው፡፡
🚩 የተለያዩ ቀላማትንና ከለሮችን በማዘጋጀት የተለያዩ ስዕሎች እንዲስሉ ነፃ አድረጎ መልቀቅ (አቆሸሻችሁ፣ ቀደዳችሁ፣ አበላሻችሁ) ከሚሉ ጭቅጭቆች ውጪ ሃላፊነት እንዲወስዱ ማድረግ
🚩 ተጠቅመን የምንጥላቸውን የፕላስቲክ መጠጫዎች ለብዙ ዓይነት ለልጆች መጫወቻነት ያገለግላሉ ለምሳሌ 4 የፕላስቲክ መጠጫውችን ደርድሮ ትንንሽ የቴኒስ ኳሶችን አልሞ ማስገባት፣ መጠጫዎች በውሃ ሞልቶ ከ አንዱ መጠጫ ወደሌላው በትንፋሽ ማሻገር
🚩 ተረቶችን በራሳቸው ፈጥረው እንዲፅፉ ማድረግ እንዚህ የፃፏቸውን ተረቶች ለቤተስብ እዲያነቡ ማድረግ፣ የኛ የቴልግራም ገፅ ላይም ቢልኩልን አሰባስበን እንሻልማለን፣ የመታተም እድልም እንዲያገኙ እናደርጋን
🚩 የተቆራረጡ ወረቀቶችን በመሰብሰብ ወረቀቶቹን አቡክተው የተለያየ ቅርፃቅርፅ እንዲሰሩ ማድረግ
http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
🎯🧩 ከ 12 ዓመት እድሜ በላይ ላሉ ልጆች ማድረግ የሚችሏቸው ነገሮች

🚩የራሳቸውን ታሪክ በድራማ ታሪክ አፃፃፍ መሰረት እንዲፅፉ ማድረግ
🚩ለቤተሰቡ አባላት በሙሉ አንድ በአንድ ደብዳቤ መፃፍ
🚩 የሚያስደስቷቸውን የምግብ አይነት ሰርተው መመገብ
🚩 የሚወዷቸውን መዝሙሮች ወይም ሙዚቃዎች ግጥማቸውን መፃፍ
🚩 በቤታቸው ወይም በክፍላቸው ያሉትን የቤት እቃዎች ቦታ በማቀያየር አዲስ ነገር መፍጠር
🚩 የራሳቸውን ፎቶ እንዲስሉ ማድረግ
🚩 የልጆች ማንዳላ በየእድሜው ስላለ እሱንም መጠቀም ከ4-11 እድሜን ይመልከቱና ሊኒኩን ይከተሉ

http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
📣 ከተመቸዎት፣ ከሞከሩት፣ ከተገበሩት 🔶 ይንገሩን ያጋሩን 🔶 ሌሎችንም እያሰባሰብን እንጨምርበታለን
ፈጣሪ ሃገራችንን ይጠብቅልን!!
🏮 በተለያየ ጊዜ የተለያዩ በሽታዎችና ወረርሽኞች በዓለም ላይ ይከሰታሉ፡፡

👉 በዚህም ምክንያት ✏️መንፈሳዊ፣ ✏️ሥነ-ልቦናዊ፣ ✏️ማህበራዊና ✏️ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶች በሰዎች ላይ ይከሰታሉ፡፡ የዚህም ማሳያ አሁን ላይ የተከሰተው የኮረና ቫይረስ ወረርሽኝ ዓለምን ምን ያህል እያስጨነቃት እንደሆነ በየእለቱ የምንሰማው ነገር ሆኗል፡፡

📍በዚህም ምክንያት ብዙ ሰዎች የተለያዩ የስነ-ልቦና ጫና ውስጥ ስለሚገቡ ማይንድ ሞርኒንግ ማህበራዊ ሃላፊነቱን ለመወጣት ከክፍያ ነፃ የሆነ የማማከር አገልግሎት ያዘጋጀ መሆኑን እየገለፅን፡፡
🔖ዘወትር ማክሰኞ ከሰዓት ከ 8-11 ሰዓት አገልግሎቱን የሚያገኙ ሲሆን ቀጠሮ ለመያዝ 0912 333020 መጠቀም ይችላሉ
ፈጣሪ ሃገራችንን ይጠብቅልን!!
http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
☂️ የወቅቱ የማሰቢያ መርሆዎች

🎯 ዓላማችን አንድ ይሁን 👉 ኮረናን ለመከላከል
🎯 እንጠይቅ እንስማ 👉 ከታመኑ ምንጮች
🎯 ከጉዳትና ከግድየለሽነት እንማር 👉 ሌሎችን በማየት
🎯 እንፍጠር እናካፍል 👉 ከራሳችን በመማር
🎯 የመረጃ መስተጋብር ይኑረን 👉 ከውስጥና ከውጭ
🎯 እንተሳሰብ እንናበብ 👉 ከቅንና ለጋስ ሰዎች በመማር
🎯 እውነተኛ እንሁን 👉 ከመታመን አንፃር

ማይንድ ሞርኒንግ

http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
👏👏 ውድ የወላጅነት በልዩነት ቤተሰቦች እንደሚታወቀው አሁን ባለው የሃገራችን ነባራዊ ሁኔታ ሚያዝያ 3 ፕሮግራማችን እንደማይካሄድ ይታወቃል፡፡ 🔹🔹ስለሆነም ቤተሰቦቻችሁ ጋር ስትሆኑ እንዚህንም ሃሳቦች ፕሮግራሞቻችሁ ውስጥ ብታከቷቸው መልካም ግብዓቶች ስለሚሆኑ 💡ራሳችሁን 💡 ትዳራችሁን 💡 ልጆቻችሁን እና 💡 መላ ቤተሰባችሁን የምትመለከቱበት ጊዜ እንዲሆንላችሁ እንመኛለን፡፡

ወላጅነት በልዩነት!

ማይንድ ሞርኒንግ
http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
1
🛎 በትንሹ ላለፈው አንድ ወር ራሳችሁን እንዲሁም ቤተሰባችሁን ከተለያዩ እንቅስቃሴዎች ገድባችሁ የቆያችሁ በእነዚህ ጊዜያት ውስጥ ▪️▪️▪️
🛑 ልጆች እቤት በመዋል ምክንያት በመሰላቸት ምን አይነት ባህሪ ሊያሳዩ ይችላሉ?

🌟 ስንፍና 🌟 ከተቀመጡበት መነሳት አለመፈለግ 🌟የግል ንፅህናን አለመጠበቅ ለምሳሌ ጥርስ አለመታጠብ🌟 በተኙበት ልብስ መዋል 🌟መነጫነጭ 🌟አብዝቶ መመገብ ወይም የምግብ ፍላጎት ማጣት 🌟 እርስ በእርስ መጣላት እንዲሁም ክስ ማብዛት ጥቂቶቹ ናቸው፡፡

👉👉በዚህም ምክንያት ጭቅጭቅ ይበዛል፣ እረፍ፣ ተይ፣ ዋ…የሚሉ ቃላት በቤቱ ውስጥ ይበዙና መደማመጥ ይጠፋል፡፡

💢 በእርግጥ እነዚህን ባህሪያት ልጆች ላይ ብቻ ሳይሆን እቤት የሚውሉ ትልልቅ ሰዎችም ሊያሳዩት ይችላሉ ምክንያም ያልተገለፁ ቢገለፁም ያልተሰሙ ስሜቶች ስለሚኖሩ ማለት ነው፡፡

♻️ ሆኖም ግን ረዘም ላለ ጊዜ በቤታችን በመሆናችን ምክንያት የሚመጡት የተለያዩ ባህሪያት እና የስሜት መለዋወጦችን አካላችን የሚሰራበትን ህግ ስለሚቀይሩት ጉዳዩን ማወቅና መቀበል አስፈላጊ ነው።

👉👉 ስለሆነም መሰላቸትን ለመቀነስ በጥቂቱ እነዚህን እናድርግ

🌀 እንቅልፍ ከጨረስን በኋላም ሆነ አርፍዶ አልጋ ላይ አለመቆየት 💠 የእንቅልፍ ስርዓት ሲዛባ ሰውነታችን የሚሰራበትን ህግ በእጅጉ ይቀይረዋል እንዲሁም ሆርሞኖች ላይ የተለያዩ ለውጦች ስለሚያመጣ በሽታ የመከላከልም ሆነ የሰውነታችንን አቅም ይቀንሰዋል
🌀 በተለያዩ ምክንያቶች ሶፋ ላይ የምንቆይባቸውን ጊዜያቶች ማሳጠር 💠ሶፋ ላይ ለረጅም ሰዓት መቀመጥ ትክክል ላልሆነ አቀማመጥ ስለሚዳርገን ለወገብ ህመም ያጋልጣል
🌀 በድርጊት በተለያዩ ተግባራትና አዳዲስ ነገሮችን በመፍጠር ማሳለፍ 💠ከዚህ በፊት መስራት ፈልገን ጊዜ ያጣንባቸውን ነገሮች ማከናወን፣ ለልጆች ጆሮ መስጠት፣ መማማር…
🌀በኤሌክትሮኒክስ ነገሮች እና ካልተመጠነ መረጃ ራስን መቆጠብ 💠 ሰውነታችንም ሆነ አዕምሮችን የተመጠኑ እና ወጥነት ያላቸውን ነገሮች ይፈልጋሉ፡፡ ስለሆነም መረጃችንና ትንታኔያችን ሲበዛ ለተለያዩ የሥነ-ልቦና ጫና ስለሚዳርገን ራስን መቆጠብ አስፈላጊ ነው
🌀የቤተሰብ ፕሮግራም በማውጣት በዚያ ፕሮግራም መትጋት 💠 ከላይ እንደጠቀስነው ሰውነታችን ወጥነት ያለው ነገር የተሻለ እንዲሰራና ውጤታማ እንዲሆን ስለሚረዳው በቤተሰቡ ውስጥ የጋራ የሆነ ፕሮግራም በአንድ ላይ በማውጣት መተግበር
🌀 በቤት ውስጥ መቀበል ያለብንን “ችግር” ያልናቸውን ነገሮች ለይተን በማወቅ መቀበል፡፡ 💠ብዙ ጊዜ ሁሉም ነገር ትክክልና ቀጥ ያለ እንዲሆን ስንፈልግ አጠገባችን ያሉትን ሰዎች ስሜትና ፍላጎት ለመስማት እድል እናጣለን ስለሆነም በቤታችን ውስጥ እንደ ችግርና ያለመግባባት መንስዔ የሆኑ ነገሮች ላይ ጊዜ በመስጠት መቀበል ሚገባንን ነገሮች ሁሉ መቀበል ህይወትን ለማቅለል አንዱ መንገድ ነው፡፡

🔆 የዝምታና ራስን የመመልከት ጊዜ ይሁንልን!!

ማይንድ ሞርኒንግ
https://t.me/mindmorning
http://mind-morning.com
👍1
👏Congratulations!👏
👌ማይንድ ሞርኒንግን በሌላ አማራጭ👌
🎯ኤፍ ኤም 97.1 ላይ
🎯ዘወትር ሰኞ ከቀኑ 9-10 ያገኙናል!
🔆ንጋትና ሕይወት🔆
የፕሮግራሙ አዘጋጅና አቅራቢ እድሜዓለም ግዛ እና ፀምረ መዘምር
Mind Morning:
🎬📟📻
🌅 ንጋትና ህይወት የሬድዮ ፕሮግራም
📯 አዘጋጅ፡ ማይንድ ሞርኒንግ
💡 የዕለቱ ባለሙያና አቅራቢ፡
እድሜዓለም ግዛ
በየሳምንቱ ሰኞ ከ 9፡00-10፡ 00
📡 ኤፍ ኤም አዲስ 97.1
🎤 የዕለቱ ርዕስ ፡ ደጅ የበላቸው ማንነቶች 🛠 የርዕስ ይዘት፡ ሥነ-ልቦና፣ የህይወት ዘይቤ፣ ትርጉም፣ ልማድ፣ባህሪ፣ ማንነት
📍 ያዳምጡን፣ ይሳተፉ፣ ይጠይቁ፣ አስተያየት ይስጡ
☎️ 0935 545452

ንጋትና ህይወት የሬድዮ ፕሮግራም!
ማይንድ ሞርኒንግ!

https://t.me/mindmorning
http://mind-morning.com
🌅 ንጋትና ህይወት የሬድዮ ፕሮግራም
የዕለቱ ባለሙያና አቅራቢ፡
እድሜዓለም ግዛ
በየሳምንቱ ሰኞ ከ 9፡00-10፡ 00
📡 ኤፍ ኤም አዲስ 97.1

🎤 የዕለቱ ርዕስ ፡ ስሜትና መገለጫዎቹ 🛠 የርዕስ ይዘት፡ ሃሳብ፣ ስሜት፣ ውጤት፣ የኑሮ ዘይቤ
📍 ያዳምጡን፣ ይሳተፉ፣ ይጠይቁ፣ አስተያየት ይስጡ
☎️ 0935 545452

ንጋትና ህይወት የሬድዮ ፕሮግራም!
ማይንድ ሞርኒንግ!

https://t.me/mindmorning
http://mind-morning.com
Audio
ርዕስ፡ የእናት ፍቅር
እርዝማኔ፡ 1 ደቂቃ ከ48 ሰከንድ
ተረቱ፡
• ልጆች ከወላጆች ጋር የሚወያዩበት
• ከስምንት ዓመት በታች ለሆኑ ልጆች ወላጆች ሰምተው የሚተረኩላቸው
3
Forwarded from መልካም ተረት
መልካም ተረት ለመልካም እድገት!
የተረት ቻናላችን በቤተሰቦች በኩል ለህፃናትና ታዳጊዎች የሚደርስ ሲሆን፡-
 ቤተሰብን ያወያያል፤ ያቀራርባል
 ህፃናትና ታዳጊዎች ከተረት ሊያገኙት የሚችሉትን ከፍተኛ ጥቅም እንዲያገኙ ይረዳል::
የመልካም ተረት ይዘት፡-
 በድምፅ የተቀረፁ ተረቶች
 የተለያዩ የእንግሊዘኛ የልጆች መፃህፍት
 የሚያወያዩ ቪዲዮዎች
 በመረጃ ላይ የተመሰረቱ መልዕክቶችን ለወላጆች ያቀርባል
ስሜትና መገለጫዎቹ ክፍለ 1 እና ክፍል 2
👍3