Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.44K subscribers
1.34K photos
16 videos
9 files
510 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
💡“ሁሌ ከመቆንጠጥ አንድ ቀን መፈንከት”!!💡

👉መቆንጠጥ ከውጭ ለሚጎተት ላም እንደ ማነቃቂያ የምንጠቀመው ጨው፤
👉ፍንከታን ደግሞ መልካም ፈቃድን የሚነካ ውስጥን የሚያነሳሳ ከባድ ጥያቄ አድርገን ብንወስድ፤

🔹🔹ልጅን ሁሌ አየቆነጠጡ መቸገር እየተንቦራቹ በማንቦራቸት ባለህበት ሂድ እንደማለት ይወሰዳል፡፡
💎💎💎 ሆኖም ግን የልጅን መልካም ፈቃድ ጠብቆ እረፍት የሚነሳ ጥያቄ ማሸከም ባርነት ሳይሆን ለልጁ ማየት የሚችሉ ዓይኖችን መፍጠር ነው፡፡

ጊዜ እንግዛ፤ እንነጋገር፤ ማየት የሚችሉ ዓይኖችን በጋራ እንፍጠር!!

ወላጅነት በልዩነት!

ማይንድ ሞርኒንግ
http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
🏹 14ኛው ወላጅነት በልዩነት ትምህርታዊ መድረክ ብዙዎችን አንቅቷል፤ ብዙዎችን ቀይሯል፤ ተደራሽነቱን እያሰፋ ይገኛል። እስካሁን ይሄን ቤተሰብ ካልተቀላቀሉ በጣም ዘግይተዋል ሆኖም ግን አሁንም አልረፈደም፤ ቢፈልጉ አዲስ አበባ፤ ቢፈልጉ አዳማ እርሶም ይምጡ፤ ለወዳጅ ዘመድዎ ይጠቁሙ ከዛም ንቃትዎን ይጨምሩ።

🎯 ነገሮቸ የሚገቡን የነቃነውን ያህል ነው🎯

የካቲት 28 አዳማ
መጋቢት 5 አዲስ አበባ

ማይንድ ሞርኒንግ

http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
እነዚህን ጥያቄዎች ይመልሱና ራስዎን ያርሙ📌

ወላጅነት በልዩነት!

ማይንድ ሞርኒንግ
http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
📍📍ወላጅነት በልዩነት ከ አንድ ቀን በኋላ ቅዳሜ የካቲት 28 ከቀኑ 8 ሰዓት ጀምሮ አዳማ ከተማ ላይ ይከ’ትማል!! 🎈

ህይወት እውቀትን ስታገኝ ትበራለች፤ ህይወት ስትበራ ወደምንፈልገው ለመሄድ መንገዱን እናየዋን፤ መንገዱን ስናገኘው ከእረፍት መንደር እንቀላቀላለን!! ስለዚህ ሁሌ ከማወቅና ከመማር ወደኋላ የማይሉ ሰዎች ህይታቸው ውስጥ ብርሃን እንዳለ ይታያል!!

👏ፕሮግራሙ ላይ የምትገኙ ተካፋዮች ራሳችሁን ለማበልፀግ እውቀትን ለመሸመት ጊዜ ስለምትመድቡ በቅድሚያ እናመሰግናል! 👏
👏አዳማ ለሚገኙ ወዳጅ ዘመዶቻችሁ ለምታገሩ ቤተሰቦቻችንም እንዲሁ ምስጋናችን የላቀ ነው!👏

ወላጅት በልዩነት!

ማይንድ ሞርኒንግ
http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
📍አዳማ ከተማ የካቲት 28 የተካሄደው የመጀመሪያው ወላጅነት በልዩነት ትምህርታዊ መድረክ በዚህ መልኩ ተካሂዶ አልፏል፡፡ 💎

🤭🤭ብዙ ጊዜ አዳማ የተለያዩ ስልጠናዎች የሚካሄዱባት ከተማ እንደሆነች ይታወቃል አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ ስልጠናዎች ሲሰጡ የምናውቀው ለሰልጣኞች አበል ተከፍሎ፣ ሻይ ሰዓት ተብሎ፣ ምሳ ወጪ ተሸፍኖ፣ ቦርሳውና ማስታወሻ ደብተሩ ተሰጥቶ እየተፎረፈ ስልጠና በሚካሄድበት ከተማ፡፡ 🛎

🔑🔑ወላጅነት በልዩነት መድረክ ላይ ግን ወላጆች፣ መምህራን፣ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ገንዘባቸውን ከፍለው ገብተው፣ ለ 3ሰዓት ሙሉ ንቅንቅ ሳይሉ፣ በሚገርም ንቃትና ማድመጥ በደስታና በልዩ ተሳትፎ በዚህ መልኩ ተካሂዶ ውሏል፡፡ 👏

👌ለሁለተኛ ጊዜም እንዲካሄድ ተሳታፊዎች ጥያቄያቸውን አቅርበው ማይንድ ሞርኒነግም የቤት ስራውን ይዞ መጥቷል፡፡👍

👏መድረኩ ላይ ለተካፈላችሁ ሁሉ፣ 👏ለመሳካቱ ላገዛችሁን ሁሉ፣ 👏 ሌሎች ይህን ጠቃሚ መድረክ እንዲካፈሉ ለጋበዛችሁ ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡

ወላጅት በልዩነት!

ማይንድ ሞርኒንግ
http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
📍አዳማ ከተማ የካቲት 28 የተካሄደው የመጀመሪያው ወላጅነት በልዩነት ትምህርታዊ መድረክ በዚህ መልኩ ተካሂዶ አልፏል፡፡ 💎

🤭🤭ብዙ ጊዜ አዳማ የተለያዩ ስልጠናዎች የሚካሄዱባት ከተማ እንደሆነች ይታወቃል አብዛኛውን ጊዜ ደግሞ ስልጠናዎች ሲሰጡ የምናውቀው ለሰልጣኞች አበል ተከፍሎ፣ ሻይ ሰዓት ተብሎ፣ ምሳ ወጪ ተሸፍኖ፣ ቦርሳውና ማስታወሻ ደብተሩ ተሰጥቶ እየተፎረፈ ስልጠና በሚካሄድበት ከተማ፡፡ 🛎

🔑🔑ወላጅነት በልዩነት መድረክ ላይ ግን ወላጆች፣ መምህራን፣ የሚመለከታቸው አካላት ሁሉ ገንዘባቸውን ከፍለው ገብተው፣ ለ 3ሰዓት ሙሉ ንቅንቅ ሳይሉ፣ በሚገርም ንቃትና ማድመጥ በደስታና በልዩ ተሳትፎ በዚህ መልኩ ተካሂዶ ውሏል፡፡ 👏

👌ለሁለተኛ ጊዜም እንዲካሄድ ተሳታፊዎች ጥያቄያቸውን አቅርበው ማይንድ ሞርኒነግም የቤት ስራውን ይዞ መጥቷል፡፡👍

👏መድረኩ ላይ ለተካፈላችሁ ሁሉ፣ 👏ለመሳካቱ ላገዛችሁን ሁሉ፣ 👏 ሌሎች ይህን ጠቃሚ መድረክ እንዲካፈሉ ለጋበዛችሁ ሁሉ ምስጋናችን የላቀ ነው፡፡

ወላጅት በልዩነት!

ማይንድ ሞርኒንግ
http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
🛎 “የልጆች የእድሜ ቅደምተከተሎችና የባህሪ ትርጉሞቻቸው”

🔑🔑 በሀገራችን ተረት “የእናት ሆድ ዥንጉርጉር ነው” ይባላል 🌟ምን እንደሆነ? 🌟 ለምንስ እንደ ሆነ አስበውት ያውቃሉ?

🔑 በልጆችዎ የባህሪ መለያየት ተገርመው፣ 🔹 እንደ ልዩነታቸው ለመያዝ ተቸግረው፣ 🔹 መፍትሄ አጥተውለት፤ 🔹የመጀመሪያ ልጅ ሌላ፣🔹 ሁለተኛው ልጅ ሌላ፣ 🔹 ወንዱ ሌላ፣ ሴቷ ሌላ፣🔹 ሲሆኑብዎት በቃ እንግዲህ የእናት ሆድ … ብለው ተረቱን ብቻ ተርተው እያለፉት ከሆነ ተሸውደዋል፡፡👏
🛎 በስነ-ልቦነው ሙያ ይህ የሆነበት ምክንያት፣ የባህሪ ትርጉምና አያያዙ መጋቢት 5 ዋና ርዕሳችን ስለሆነ በፍፁም እንዳይቀሩ፡፡ 👉ሲመጡ ደግሞ ያለዎትን ጥያቄ ሁሉ ይዘው እንዲመጡ ተጋብዘዋል፡፡
👉ልጆችን እንደ አወላለድ ቅደም ተከተላቸው ሳንቸገር እንዴት መያዝ እንችላለን 👉በልዩነታቸው ውስጥስ ልጆችን እንዴት ደስተኛና ውጤታማ ማድረግ ይቻላል የሚሉ ጥያቄዎችው ይመለሳሉ !


ወላጅት በልዩነት!

ማይንድ ሞርኒንግ
http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
🏮 የፍርሃት ስሜቴና ጥያቄዬ

📒 ብዙ ጊዜ የፍርሀት ስሜቴና ጥያቄዬ እኔነቴ ይመስሉኛል፡፡ ምክንያቱም በእኔ ላይ በመፈራረቅ የሁሌ ጓደኞቼ ስለሆኑ፡፡ ልጅ ሆኜ ጥላዬን አምነው ነበር፤ ሰዓት መቁጠሪያዬም ጓደኛየም እርሱው ነበር፤ ነገር ግን በዕድሜዬ ከፍ ስል የጠዋት ጥላ ከሰዓት ያጥራል፡፡ ታማኝ ጓደኛም አለመሆኑን ተመለከትሁ፡፡ ስሜትና ጥያቄዬ ግን ይታመኑኛል፡፡ ስሜቴ ቀድሞ የፈለግሁት ቦታ ያደርሰኛል፡፡ ጥያቄዬም ጠዋት ይቀሰቅሰኛል፤ ቀን ይመራኛል፤ ማታም ያስተኛኛል፡፡

✂️ ነገር ግን ገጣሚን (ስሜትን) ተመራማሪ (ጥያቄን) አይቀድመውም ይላሉ፡፡ ይህም ስሜት ከጥያቄ ወይንም ከዕውቀት ቀድሞ ይደርሳል እንደማለት ነው፡፡ለዚህም ነው በኮረና ቫይረስ ስሜታችን ቀድሞ የተነካውና እውቀት አልባ የመሰልነው፡፡

🔧 ምን ጥያቄ ብናነሳ፤ ምን እውቀት ቢኖረን፤ ስሜት ቀድሞ ስለሚነካ ፍርሀት ቢሰማን አይገርምም፡፡ የዕውቀታችን ጫማ የሆነው ጥያቄያችን ማገናዘብን ተከትሎ ቀስ ብሎ ሲመጣ መረጋጋትና ዘላቂ መፍትሄን ይለግሰናል፡፡

🦠 ኮረናን እንቀበለው እውነት ስለሆነ፤
💡 እንረዳው እውቀት ስለሚሻ ፤
🛠 እንቀይረው ማሸነፍ ስላለብን ፡፡
🔑 ይህ ሁሉ የሚሆነው በጥያቄ ስለሆነ
ጓደኛዬ ጥያቄን Like ያድርጉ፡፡

ማይንድ ሞርኒንግ
http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
👉 ለልጆች ከተግባር ውጪ ሆኖ ማሳለፍ ማለት ለእነሱ ከባድ ቅጣት እንደማለት ነው፡፡

⚖️ 🔑 ስለሆነም ልጆች ከተግባር ውጪ መሆን ስለማይችሉ ብዙ ጊዜ ቤተሰቦቻቸው “ረበሻችሁ” የሚል ወቀሳ ሲያነሱ ይደመጣሉ ከዚህ በተጨማሪም ልጆችም ወላጆችም እንደመጨረሻ አማራጭ ለልጆች ምንም ማሰብ የማያስፈልገውን የዝግጅት ዋጋ የማያስከፍለውን ኤሌክትሮኒክስ ነገሮችን መፍቀድና በቴሌቭዥን ውስጥ ማሳለፍ እንደ መጨረሻ አማራጭ ሲወስዱት እናያለን በዚህም ምክንያት ልጆች ኤሌክትሮኒክስ ነገሮች ውስጥ በመመሰጥ ለሱስ ይዳረጋሉ፡፡
🌞 ሆኖም ግን ልጆቻቸን ለመጫወት፣ ተግባር አልባ ከመሆን ለመታደግ ትንሽ የማሰቢያ ጊዜ፣ ፍላጎትና፣ ቁርጠኝነት ይፈልጋል ስለሆነም ልጆች በዚህ ከትምህርት ውጪ በሚሆኑበት ጊዜ በቤታችን ውስጥ ማድረግ ከምንችላቸው ነገሮች ውስጥ ትቂቱን እናካፍልዎ፡፡ 👇👇👇👇
🎯🧩 ከ 4 -11 ዕድሜ እድሜ ላሉ ልጆች ማድረግ የምንችላቸው ነገሮች

🖍 ለልጆች በየእድሜያቸው የተዘጋጁ በቀለማት የሚያሳምሯቸው የተለያዩ አርቶች አሉ ለምሳሌ ማንዳላ “Mandala” አንዱ ልጆች ማድረግ የሚወዱት ተግባር ነው ይህም የትኩረት መጠናቸውን ይጨምራል፣ ፈጠራ አቅማቸውን ያወጡበታል፣በየእድሜያቸው ከተለያየ ዲዛይን ጋር ስላለ ራሳቸወን ይፈትኑበታል፤ ትጋን ይማሩበታል፣ እና ውጤቱን እየሰሩት እዛው ላይ ያዩበታል፡፡ ስለሆነም ይህን ሊንክ ተጠቅመው እነዚህን ማናዳላዎች በማውረድ ፕሪነት አድርገው ሊሰጧቸው ይችላሉ፡፡
https://www.free-mandalas.net/difficulty-level/easy-children/
https://www.woojr.com/mandala-coloring-pages-for-kids-adults/
http://www.supercoloring.com/coloring-pages/arts-culture/mandala/simple-mandalas

🚩 ከሚወዱት የሳይንስ ትምህርት ውስጥ ጊዜ እየወሰዱ እንዲሞክሩ Experiment እንዲያደርጉ ይፍቀዱላቸው፡፡
🚩 የተለያዩ ቀላማትንና ከለሮችን በማዘጋጀት የተለያዩ ስዕሎች እንዲስሉ ነፃ አድረጎ መልቀቅ (አቆሸሻችሁ፣ ቀደዳችሁ፣ አበላሻችሁ) ከሚሉ ጭቅጭቆች ውጪ ሃላፊነት እንዲወስዱ ማድረግ
🚩 ተጠቅመን የምንጥላቸውን የፕላስቲክ መጠጫዎች ለብዙ ዓይነት ለልጆች መጫወቻነት ያገለግላሉ ለምሳሌ 4 የፕላስቲክ መጠጫውችን ደርድሮ ትንንሽ የቴኒስ ኳሶችን አልሞ ማስገባት፣ መጠጫዎች በውሃ ሞልቶ ከ አንዱ መጠጫ ወደሌላው በትንፋሽ ማሻገር
🚩 ተረቶችን በራሳቸው ፈጥረው እንዲፅፉ ማድረግ እንዚህ የፃፏቸውን ተረቶች ለቤተስብ እዲያነቡ ማድረግ፣ የኛ የቴልግራም ገፅ ላይም ቢልኩልን አሰባስበን እንሻልማለን፣ የመታተም እድልም እንዲያገኙ እናደርጋን
🚩 የተቆራረጡ ወረቀቶችን በመሰብሰብ ወረቀቶቹን አቡክተው የተለያየ ቅርፃቅርፅ እንዲሰሩ ማድረግ
http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning
🎯🧩 ከ 12 ዓመት እድሜ በላይ ላሉ ልጆች ማድረግ የሚችሏቸው ነገሮች

🚩የራሳቸውን ታሪክ በድራማ ታሪክ አፃፃፍ መሰረት እንዲፅፉ ማድረግ
🚩ለቤተሰቡ አባላት በሙሉ አንድ በአንድ ደብዳቤ መፃፍ
🚩 የሚያስደስቷቸውን የምግብ አይነት ሰርተው መመገብ
🚩 የሚወዷቸውን መዝሙሮች ወይም ሙዚቃዎች ግጥማቸውን መፃፍ
🚩 በቤታቸው ወይም በክፍላቸው ያሉትን የቤት እቃዎች ቦታ በማቀያየር አዲስ ነገር መፍጠር
🚩 የራሳቸውን ፎቶ እንዲስሉ ማድረግ
🚩 የልጆች ማንዳላ በየእድሜው ስላለ እሱንም መጠቀም ከ4-11 እድሜን ይመልከቱና ሊኒኩን ይከተሉ

http://mind-morning.com
https://t.me/mindmorning