Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.44K subscribers
1.34K photos
16 videos
9 files
510 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
ልጆችዎ ከ 9 ነኛ ክፍል በላይ ከሆኑ ህዳር 6 የሚሄደው ፕሮግራም ላይ አብሮ መገኘት ይቻላል!!
ቦታ ቫምዳስ አዳራሽ
ከሰዓት ከ9-12 ሰዓት

ወላጅነት በልዩነት!

ማይንድ ሞርኒንግ
👉👉 ጥያቄ የማይጠይቁ ልጆች!!

🔶 ብዙ ጊዜ ምንም የማይጠይቁ ልጆችን እንደ ፀባየኛ፣ እንደ ማያስቸግር ልጅ፤ የሰጡትን ሁሉ የሚቀበል እና የዋህ የሚል ስያሜ እንሰጣቸዋለን◌

ሆኖም ግን ይህ ባህሪ በልጆች ትምህርት፣ ንቃትና ቀጣይ ህይወት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ያለው ነገር ነው፡፡

➻➻ እንዚህ የማይጠይቁ ልጆችን ቀረብ ብለን ስናያቸው ግን 🔶 ደንታቢስ የሆኑ፤🔶 እንቢ-አልፈልግም ማለት የማይችሉ፣🔶 ለብዙ ነገር የተለየ ስሜትና ጉጉት የሌላቸው መሆናቸውን እንመለከታለን፨

🔷 ይህ ባህሪ ልጆችን እቤት ውስጥ የምንይዝበት መንገድ 👉ጥያቄ መጠየቅን እንዳይለምዱ፣ 👉 እንዲያቆሙ፣ 👉እንዳይማሩ ያደርጋቸዋል ለምሳሌ
❶ ልጆች ለምንም ነገር ፍላጎት ሳያሳዩና ሳይጠይቁ ፍላጎቶቻቸውን ቀድመን ስንሞላው /ስናደርግ
❷ ዝም የሚል ልጅ የሰጡትን የሚቀበል ልጅ ትክክል እንደሆነ እየነገርን ስናሳድግ
❸ ለጥያቄዎቻቸው መልስ እንደማያገኙ ሲያስቡና ምላሻችን ወደ መከልከልና መሰላቸት ሲያዘነብል
❹ ጥያቄዎቻቸውን ስናጣጥልባቸው፣ በጥያቄው ስንስቅባቸው፣ ለመመለስ ያህል ስንመልስላቸው

👉ልጆች ጥያቄ መጠየቅን አይማሩም ወይም ያቆማሉ ማለት ነው👈
🚩 ይህ ሲሆን ደግሞ ልጆችን ከተሳታፊነት፤ ከተማሪነት ወደ ተመልካችነትና ጠባቂነት እንቀይራቸውና መማር እንዲያቆሙ እናደርጋቸዋለን ማለት ነው፡፡

ወላጅነት በልዩነት!

ማይንድ ሞርኒንግ
👍1
👏 ልጆች ሁለቱም ወላጆቻቸው ያስፈልጓቸዋል! 👏

👂👂ሁለቱም ወላጆች የየራሳቸው ሚናና ተግባር አላቸው፡፡

እናት ለልጇ የምትተጋውን ያህል አባት መትጋት ያስፈልገዋል፤ አባት ለልጁ የሚተጋውን ያህልም እናት መትጋት ያስፈልጋታል፡፡

ምክንያቱም ተፈጥሮ ለሁለቱም ወላጆች የለገሰችው የየራሳቸው አቅም ስላላቸው፡፡

ስለሆነም

🔑🔑 በቤተሰብ ውስጥ ልጅን ከማሳደግ አንፃር የአባት ሚናዎች በጥቂቱ

♦️1. ጥበቃና ከለላ በማድረግ ልጅ የደህንነትና የመ’ጠበቅ ስሜት እንዲኖረው ማድረግ (Security)
♦️2. እቅድ በማውጣት በፕሮግራም መመራትን ማስቻል (Planning)
♦️3. ተግዳሮቶችን በማጋፈጥ ልጅ በራስ መተማመን እንዲኖረው ማስቻል (Risk Taking)
♦️4. ስፖርታዊ እንቅስቃሴና ጨዋታዎችን አብሮ በማድረግ ልጅ በአካል ጠንካራ እንዲሆን ማድረግ (Physical Strength)

🔑🔑 በቤተሰብ ውስጥ ልጅን ከማሳደግ አንፃር እናት ሚናዎች በጥቂቱ

🛑 1. በስሜት ቅርብና የተረጋጋች በመሆን ልጅ የስሜት ደህንነት እንዲሰማው ማድረግ (Emotional Stability)
🛑 2. በስሜት በመረጋጋትና በመብሰል የቤተሰቡን አንድነት ማስጠበቅ (Family Connectedness)
🛑 3. በመታገስ፣ በመቀበልና በማለፍ ልጅ ራሱን እንዲቀበል እና ለራሱ ዋጋ እንዲኖረው ማስቻል (Self Acceptance)
🛑 4. ስሜትን በማንበብና በማቀፍ ለልጅና ለቤተሰብ ፍቅርና ምቾትን መስራት (Nurturing & Love)

ልጆች ሁለቱም ወላጆቻቸው ያስፈልጓቸዋል

ወላጅነት በልዩነት!

ማይንድ ሞርኒንግ
🔑🔑 ልጆችን አንድ ነገር ልናደርግላቸው ስንፈልግ የማስመረጥ ጥቅሞች

1. ምክንያታዊነትን እንዲያዳብሩ ይረዳቸዋል
2. ፍላጎታቸውን ለይተው እንዲያውቁና ተነሳሽነት እንዲኖራቸው ያደርጋቸዋል
3. በምርጫው ውስጥ ስለነበሩ ሃላፊነት መውሰድ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል
4. የመግባባትና ሃሳብን የመግለፅ ክህሎታቸው ይዳብራል
5. በራስ መተማመናቸውእንዲጨምር ያደርጋል

ወላጅነት በልዩነት!

ማይንድ ሞርኒንግ