Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.65K subscribers
1.33K photos
15 videos
9 files
509 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
🙏ለዚህም እስካሁን ላሳያችሁን ፍቅር እና ድጋፍ እያመሰገንን በሁሉም ድረ ገፅ አብረዉን እንዲሆኑ ሌሎቹንም ቤተሰብ እንዲያረጉ እንጋብዛለን ።

እንንቃ ........ ብቁ እንሁን ........ሌሎችን እናንቃ ...... ሌሎችን እናብቃ

Tiktok : Mind Morning

Linkdin : Mind morning BTRC
https:www.Linkedin.com/company/mind-morning/
3
🎉ተጀመረ🎉

በማይንድ ሞርኒንግ 11ኛ ዙር የልጆች የክረምት ስልጠና ዛሬ ተጀመረ።

ሰልጠናው ልጆች ስለራሳቸው ፣ ስለትምህርታቸው እና ስለህይወት የተለያዩ ክህሎቶችን የሚያውቁበት እና የሚማሩበት ሲሆን በዚህ መሰረት ዛሬ ከ8-11 ዓመት እና ከ12-14 ባሉ ልጆች ተጀምሯል።
6👏6👍3
ልጆች በዚህ መልክ መማርን ጀምረዋል

አሁን ተራው የወላጆች ነው !!

የፊታችን ቅዳሜ ሐምሌ 12 ልጆቻችሁ የክረምት ስልጠናውን እየወሰዱ ላሉ ወላጆች የሚሰጠው የወላጆች ስልጠና የሚጀመር ይሆናል።

9:00 ሰዓት
📍መገናኛ ስለሺ ሕንፃ
👍52👌2
📆ዛሬ ሐምሌ 13
5:00-6:00
📻በኢትዮ ኤፍ ኤም 107.8 “በጤናማ ህይወት” ከአቢጊያ ጋር

በቀጥታ ስርጭት ይከታተሉን ጥያቄዎትን ያቅርቡልን
8👏1
ፍቅር ሳይሆን ስራ

ልጆች የሚፈልጉትን እና የሚስፈልጋቸውን ማሳጣት ፣ ሁሉንም መከልከል ወይም ለጥያቄዎቻቸው ሁሉ እምቢታን ማሰማት የተሳሳተ ሆኖ ሳለ ሁሉንም እሺ እሺ ማለትም በልጆች ላይ ትልቅ ተጽእኖ ይኖረዋል።
ይህም ሁሉንም እሺ እየተባሉ የመጡ ህጻናት
🙁ሁሉን ነገር እሺ እንድንላቸው ያለቅሳሉ
😕ስሜታዊ ናቸው
😕በጨዋታ መሀል ያኮርፋሉ
😕አንድን ነገር ለመስራት ጉቦ ይጠይቁናል...…… የመሳሰሉትን ባህሪ ያሳያሉ
ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም በትክክል የመጣ ማንነትም አይደለም።
ስለዚህ ለእነዚህ ልጆች የሚያስፈልገው ፍቅር ሳይሆን ሥራ ነው።
Standard እያስቀመጡ በዛ ውስጥ ማምጣት ነው። እነዚህ ልጆች ስራን የለመዱ ባለመሆናቸው የመጀመሪያዎች ጊዜን አስቸጋሪ ያደርገዋል ስለሆነም ቀስ በቀስ ለ1 ደቂቃም ይሁን ሚሰራ ነገር በመስጠት ቀስ በቀስ ሰዓቱን እያረዘሙ መምጣት ትክክለኛው መፍትሔ ይሆናል ማለት ነው።
8
‼️ልጆቻችሁ በማይንድ ሞርኒንግ የክረምት ስልጠና እየወሰዱ የሚገኙ ወላጆችን ይመከታል📢

💫ሰላም እንደምን ናችሁ 👋🏽

📌እንደሚታወቀው በክረምት በማይንድ ሞርኒንግ በመሰልጠን ላይ ለሚገኙ ልጆች ወላጆች ዘወትር ቅዳሜ ስልጠና በመስጠት እንገኛለን ።

ሆኖም ከባለፈው ቅዳሜ ጀምሮ ስልጠናውን በልጆቻችሁ እድሜ ከፍለን መስጠት እንደጀመርን ይታወቃል ስለዚህ የፊታችን ቅዳሜ ነሀሴ 3 የሚኖረን የወላጆች ስልጠና ልጆቻችሁ ከ12-14 ዕድሜ ውስጥ ለሚገኙ ወላጆች ይሆናል።

🙏🏽እናመሰግናለን
3
በቀጥታ ባላችሁበት ከእናንተ ከቤተሰቦቻችን ጋር መገናኘት እንደጀመርን ምን ያህሎቻችሁ ታውቃላችሁ😳🤔

📌በዚህ ዓመት ማይንድ ሞርኒንግ ቲክቶክን በመቀላቀል የተለያዩ ጠቃሚ ሃሳቦችን በይበልጥም ልጆች ባህሪ እና ወላጅነትን በተመለከተ ባለሞያዊ እውቀትን እያጋራን እንገኛለን በዛም ወደ 80k የሚጠጉ ቤተሰቦች አፍርተናል 🎉 ለዚህም ሁላችሁንም እያመሰገንን🙏🏽

አሁን ደግሞ በሳምንት 2 ቀናትን LIVE በመግባት ጥያቄዎቻችሁን ቀጥታ እየመለስን በብዙዎቻችሁ ጥያቄ መሰረት ተደራሽነታችንን በማስፋት እንገኛለን

⭕️TikTok LIVE
ርዕስ: የልጆች ስሜትና ሃላፊነት
📆 ዛሬ ቅዳሜ ነሀሴ 3
ምሽት 2 ሰዓት
👤እንግዳም ይኖረናል

ጥያቄዎቻችሁን ሃሳባችሁን ይዛችሁ እንገናኝ
ሌሎችም በተለይ ወላጆች በብዙ ያተርፋ ዘንድ ይህን እናጋራቸው እንጋብዛቸው🥰

https://www.tiktok.com/@mind_morning_?_t=ZM-8yj49Hf8Owf&_r=1
Forwarded from Mind Morning
🌧ከዝናቡ ይልቅ ቆርቆሮው ይጮሀል🔊

ዝናቡና ቆርቆሮው ድብድብን እንዲወክሉ ሆነው የቀረቡ ናቸው።ደብዳቢና ተደብዳቢ ልዩነታቸው አንዱ ብትር አሳራፊ ሌላው በትር ተቀባይ ስለሆኑ እንጂ ሁለቱም ተማተዋል ።ተመተዋልም። ቆርቆሮው የሚጮኀው የተደበደበውን ያክልና እርሱም የመቋቋም የቻለውን ያክል ነው።ጩኀት ለምን?🤔 ሰንል የተደበደበውን ያክል፣ አንዳንድ ተማሪዎችም ሌሎች ተማሪዎችን በመደባደብ ይታወቃሉ፡፡ልክ እንድ ወንጭፍ እንዳለው እህል ጠባቂ አይነት፣ ወንጭፍ ወደሗላ የተጎተተውን ያክል ወደፊት ይማታል፡፡ አንድ ተማሪም የተመታውን ያክል ይማታል፡፡ የሚገርመው ነገር ደግሞ አንድ ወላጅ የልጁን ጉዳት ሳያይና ጊዜ እንዳጣ ዘንግቶ ተመትተህ እንዳትመጣ የሚሉት ባህል በጣም ያሳዝነኛል። ይህ ለልጆች የበለጠ ጉዳት እንጂ ጥቅም አይሆንምና ፡፡

ለምን ቢሉ
‼️አንድ ተማሪ ሌሎች ተማሪዎችን የሚደባደበው እሱ የተደበደበውንና ያጠራቀመውን ያክል ስለሆነ ነው።‼️

በሌላ መንገድ ተደባዳቢው ልጅ ባለበት ያኔ በተደበደበ ጊዜ እንደቆመ መማርም እንዳልጀመረ ስላልገባን ነው።በባህሪ ተደባዳቢ ተማሪዎችን ብንገልጽ
😣ተነጫቻጭ -የሰማቸው ስለሌለ
😔 የአእምሮ እድገታቸው የቀጨጨ - መትፋት እንጂ መቀበል ስለሚቸገሩ
🚶 ብቸኛ -ማህበራዊ አብሮነት ስለሌላቸው
በዚህ የተነሳ ልጆቹ ድብርት፣ ስጋት፣ ያጠራቸው ሲሆኑ መማር አይችሉም፡፡ይልቁን የሀገራችን አባባል የሆነውን "የመጣን መቀበል የሄደን መሸኘት" ብንረዳው ከሁሉ ያተርፈናል።
የመጣን መቀበል ማለት መስማትና መማርን እንረዳለን።
የሄደን መሸኘት ከሚለው ደግሞ ሰውን በግድ ያለፍላጎቱ መያዝ ይጎዳዋል እንጂ አይጠቅምም የሚለውን እናገኛለን።

ለማንኛውም ተደባደብ ለተባለው ልጅ መፍትሄው መስማት ፣ጊዜ መስጠት፣መረዳት፣ራሱን እንዲገልጽ እድል ማመቻቸት ያስፈልጋል።

🙏ቸር እንሰንብት 👋
👍51