Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.7K subscribers
1.33K photos
15 videos
9 files
507 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
🎤🎤🎤🎤🎤
ለ10ኛ ክረምት ለ 7 ሳምንታት ሲሰጥ የቆየው የልጆችና የታዳጊዎች የአቅምና ክህሎት ስልጠና በሚያምር እና በሚናፍቅ መልኩ የመዝጊያ እና የሰርተፊኬት ጊዜ አካሂዷል።
🙋🙋🙋

📖 በንቃት፥ በጉጉት እና በናፍቆት የነበራችሁ ቆይታ ባያልቅ ያሰኛል ያስናፍቃል። 

📖 ምሳሌ የሆናችሁ ወላጆች አርዓያነታችሁ ይቀጥል

🖍ሁሌም ድንቅ ናችሁ🖍

በመጨረሻም
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

ለቤተሰብ ለሀገር ፍሬ አፍሩ ብለን መርቀን ተመራርቀን አጠናቀቅን።

በብዙ ማማር፥ ፍቅርና አክብሮት የሞላበት ድንቅ ቆይታ!!!

ለምታስቡልን፥ ለተሳተፋችሁ፥ ላበረታታችሁን፥ ከማይንድ ሞርኒንግ ጎን ለነበራችሁ ሁሉ ምስጋናችን ታላቅ ነው!!🙏🙏🙏

@mindmorning
👍31👏1
የስልጠናው ርዕስ፣ መዝጊያና መክፈቻ

የፊታችን ቅዳሜ ጳጉሜ 02/2016 ዓ.ም.

መግቢያ ፣ በነጻ -አያምልጥዎ
ቦታው ፣ መገናኛ ስለሺ ስህን ህንጻ፡ ቢሮ ቁጥር ፣ 805
ሰዐት: 8:00-11:00
👍2
መዝጊያና መክፈቻ

አዲስ ዓመት ሲመጣ ትዝ የሚለኝ ነገር ስንቅና ትጥቅ ነው ። ሆኖም ሰንቅም ትጥቅም ምግብ አይደሉም። ማንነትና ዝግጁነት እንጂ። ማንነት መፈተሽ አለበት። ስንቅም ይቋጠርለታልና። መሸከም የሚችለውን ለማለት ነው። የማይችሉትን መሸከምም ሆነ የማይበቃን መታጠቅ የትም አያደርስም። እንኳን አንድ ዓመት ።
🖐 በእርግጥ ልምድ ያላቸው ለአመታት የሚሆን ይሰንቃሉ ።ይታጠቃሉም። ለዚህ ደግሞ ራሳችንን እንድንፈትሽ አዲስ አመት ሁሌ ይመጣል ፡ አይቀርም። አንድ ደንበኛዬ ራስን መፍጠር እንጂ ራስን ወደኋላ መፈተሽ ምን ያደርጋል ያለኝን አልረሳውም። ማንነትን ማወቅ ለስንቅም ፣ለትጥቅም አያስፈልግም እንደማለት።

🖐አንድ ፎቅ ላይ ሌላ ተጨማሪ ወለል ለመጨመር መሸከም የሚችለውን ሳናውቅ ይቻላልን ስለው አሁንም ክርክሩን ቀጠለ። መቸስ ክርክር ይቻላል ህይወት እሆንልንም እንጂ። ይህ የአዲስ አመት የመባቻ ጊዜ ማረፊያችን ነው። በር መዝጊያችን። ብዙ ድርጅቶች ቆጠራ ላይ ነን እንደሚሉት። ከዛም በር እንከፍታለን። አቅማችንን መዝነን። በር መክፈትና መዝጋት ለሚያውቅ አራት ዋና ዋና መርሆች ይኖሩታል ። እንደ ስንቅም ይገለገልባቸዋል።

👍የለውጥ አስተሳሰብ ወይንም የማደግ መርህ የህይወቱ መንገድ ይሰጠዋል።

👍ወድቆ መነሳት የስንቁን መጠን ይወስንለታል ። ትጥቁንም ከፍ ያደርግለታል።
👍ሌሌችን ተጽዕኖ ውስጥ መጣል ብቻ ሳይሆን ማበርከትም ይሆንለታል።

👍ከዛም የሁሌ ተማሪ ስለሚሆን ሙሉነትን ይጎናጸፋል። በር እንዝጋ!! በር እንከፈት !!

ስንቅ የሌለው ህዝብ መድረሻው አይታወቅም!!!
አዲሱ ዓመት የፍሬ ይሁንላችሁ !!!!!ይሁንልን!!!!!


ቪሌጅ ኢትዮጵያ -የወላጅነት አካዳሚ
Village Ethiopia-Parenting Academy
@ Mind Morning
👍161
የዚህ ሳምንት የወላጅነት በልዩነት ስልጠና ርዕስ
ሆን ብሎ መሰጠት
በማይንድ ሞርኒንግ ቢሮ መገናኛ ስለሺ ህንፃ 8ኛ ወለል በ0970414243 መደወል ይችላሉ። ቅዳሜ 04/01/2017 መግቢያ በነፃ ሰዐት ከቀኑ 9:00-12:00
👍21
🎉🎉🎉 እንኳን ደስ አላችሁ!!🎉🎉🎉

2017 መልካም የትምህርት ዘመን እንዲሆንላችሁ እንመኛለን!!😍🌞😍🌞😍🌞😍🌞

ማይንድ ሞርኒንግ
9👍5👌1
የተወደዳችሁ ደንበኞቻችን ለዛሬ ቅዳሜ መስከረም 18/2017 ዓ.ም የወላጅነት ስልጠና የማይኖር መሆኑን በአክብሮት እገልፃለሁ። መልካም የመስቀል በዓል!!
👍1
ለደንበኞቻችን ሁሉ አሁንም በኢሬቻ ምክንያት ለነገ ቅዳሜ አገልግሎት የማንሰጥ መሆኑን ማሳወቅ እንወዳለን። መልካም በዐል
ጀምሮ የማቋረጥን፣ 🙈 የመሰላቸትን፣ 😳ያለመጨረስን ችግር የሚፈታ

👍 የልጆችዎን ንቃትና ስኬት የሚያስቀጥል የበጋ ስልጠና!!

ምዝገባ ጀምረናል!! በማይንድ ሞርኒንግ!

👐 የልጆች (የተማሪዎች) የመስከረም መነቃቃት፣ ትጋትና ፍላጎት አመቱን ሙሉ ቢዘልቅ የማይወድ አለን?
👌 ልጆችዎን በተለያየ መንገድ ማብቃት ይህን ውጤት ያመጣዋል!!

🖐 ማይንድ ሞርኒንግ ደግሞ ልጆችን በማብቃት እና የተለያዩ ክህሎቶችን በማስታጠቅ ብዙ ልምድ አለው፣ ፍሬም አፍርቷል፡፡
✍️ ስለሆነም ልጆችዎ ሳይጨናነቁ፣ ሳይሰላቹ፣ ውጤታማ ሆነው፣ በዚሁ መጀመሩበት ንቃት እንዲቀጥሉ ማይንድ ሞርኒነግ ባዘጋጀው ስልጠና ከጎንዎ ነን!!

🫵 ይደውሉ መረጃ ይውሰዱ፣ ያስመዝግቡ፣ ቦታ ይያዙ
👊 ልጆችዎ በህይወት ገጻቸው እና በትምህርታቸው ብቁ የሚሆኑበት ስልጠና!!

🤙 0912 33 30 20
🤙 0970 41 42 43

መገናኛ ስለሺ ስህን ህንፃ 8ኛ ፎቅ

@mindmorning
👍9
ቅዳሜ ጥቅምት 23/2017 3:00 ሰዓት ላይ
👉 ልጆች በበጋው ወቅት ለሚማሯቸው ትምህርቶችም ሆነ ለህይወታቸው ስኬት የተለያዩ ክህሎቶችን መማር፣ማወቅ፣ ማዳበር ወሳኝነቱ አያጠያይቅም!!

😍 የብዙ ክህሎቶች ባለቤት የሆኑ ልጆች ጉዳዮቻቸውን የሚያዩበት መንገድ ይስተካከላል፣ እንዴትና ምን ማድረግ እንዳለባቸው በቀላሉ መረዳት ይችላሉ፣ አቅማቸውን አውጥተው መጠቀም ይችላሉ፡፡

ልጆች የተለያዩ ክህሎቶች ከሌሏቸው ትምህርትም አድካሚ፣ ህይወትም አሰልቺ ይሆንባቸዋል፡፡

🤲 መፍትሄው አሁን በወላጆቻቸው እጅ ነው!!

👉 በተለይ በለጋ እድሜያቸው የተዘራባቸው ዘር የህይወት ስንቅ ሆኖ ይቀጥላል ለዚህም ምስክር አያስፈልገውም፡፡
👉 ንቁ ወላጅ ደግሞ ቀድሞ መልካም ዘር ይዘራል፣ ኋላም ያርፋል!!
👉ህይወት ብዙ ገፅ አላት በዚህም ምክንያት ሚዛን ትፈልጋለች፣ ይህ ደግሞ ብስለትን ይጠይቃል!!

ማይንድ ሞርኒንግ!!
👉 ልጆች በበጋው ወቅት ለሚማሯቸው ትምህርቶችም ሆነ ለህይወታቸው ስኬት የተለያዩ ክህሎቶችን መማር፣ማወቅ፣ ማዳበር ወሳኝነቱ አያጠያይቅም!!

😍 የብዙ ክህሎቶች ባለቤት የሆኑ ልጆች ጉዳዮቻቸውን የሚያዩበት መንገድ ይስተካከላል፣ እንዴትና ምን ማድረግ እንዳለባቸው በቀላሉ መረዳት ይችላሉ፣ አቅማቸውን አውጥተው መጠቀም ይችላሉ፡፡

ልጆች የተለያዩ ክህሎቶች ከሌሏቸው ትምህርትም አድካሚ፣ ህይወትም አሰልቺ ይሆንባቸዋል፡፡

🤲 መፍትሄው አሁን በወላጆቻቸው እጅ ነው!!

👉 በተለይ በለጋ እድሜያቸው የተዘራባቸው ዘር የህይወት ስንቅ ሆኖ ይቀጥላል ለዚህም ምስክር አያስፈልገውም፡፡
👉 ንቁ ወላጅ ደግሞ ቀድሞ መልካም ዘር ይዘራል፣ ኋላም ያርፋል!!
👉ህይወት ብዙ ገፅ አላት በዚህም ምክንያት ሚዛን ትፈልጋለች፣ ይህ ደግሞ ብስለትን ይጠይቃል!!

ማይንድ ሞርኒንግ!!
7