Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.44K subscribers
1.34K photos
16 videos
9 files
510 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
10ኛ መድረክ ወላጅነት በልዩነት!!
🔶 በዚህ ሩጫ በበዛበት ጊዜ ልጅን ቀርፆ፤ ዓላማ አስይዞ፣ በራስ መተማመን ሰርቶ፣ ራሱን መምራት የሚችልና ከማንኛውም ደባል ነገሮች የፀዳ ልጅ ማበርከት አቅም ይጠይቃል።

👉👉 የሚጠይቀው አቅም ደግሞ የገንዘብና የቁስ ሳይሆን 🌟የንቃት፣የጊዜና የውሳኔ ነው።🌟
ስለዚህ እርስዎ ምን አይነት ወላጅ ነዎት?

🔑 እስካሁን በቀጠሮ እየኖሩ ከሆነ አሁን እየወሰኑ ይኑሩ።

🌟 ህዳር 6 ከቀኑ 9:00 ሰዓት ጀምሮ በ ቫምዳስ አዳራሽ ይገኙና ስለ ራስዎ፣ ስለ ልጆችዎ እና ስለ ቤተሰብዎ ያለዎትን እይታ ይጨምሩ!!👏👏

ወላጅነት በልዩነት!!
ማይንድ ሞርኒንግ!
ልጆችዎ ዓመቱን በደስታና በውጤት ያሳልፉ!!

👉 የክረምቱን ሥልጠና ላልወሰዱ ልጆች👈

🌟ማይንድ ሞርኒንግ የክረምቱን ስልጠና ላልወሰዱ ልጆች የበጋ ዋና ዋና የልጆች ተግዳሮቶች ላይ ስልጠና አዘጋጅተናል

🔶 የጥናት ዘዴ
🔶 ዝግጁነት
🔶 በራስ መተማመን
🔶 ራስን መምራት እና ሌሎችም

የስልጠና ጊዜ
👉 ከ 8-11 ዕድሜ ለ 4 ቅዳሜ ከ 3-6 ሰዓት
👉 ከ 12-18 እድሜ ለ 4 እሁድ ከ 3-6 ሰዓት

● ዓመቱን በስኬት ለማሳለፍ ለ 4 ሳምንት ብቻ ውሳኔ ይወስኑ ለውጡንም ውጤቱንም ያዩታል ●

ማይንድ ሞርኒንግ !!
ልጆች የትምህርት መሳሪያዎቻውን ወይም ለግል እቃዎቻቸው ቸልተኛ የሚሆኑትና ረስተው፣ ጥለው እንዲሁም አበላሽተው የሚመጡት ለምንድን ነው ከምንስ ይመነጫል??
☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️☄️

👉አንዳንድ ግዜ ልጆች ለግል እቃዎቻቸው ወይም ለትምህርት መሳሪያዎቻቸው ዝርክርክና ግድ የለሽ ሲሆኑ ይታያሉ በዚህም ምክንያት ወላጆች ያማረራሉ ልጆቻቸውንም ሲወቅሱ ይደመጣሉ፡፡

👂👂 ሆኖም ግን ይህ ተግባርና ባህሪ በዋነኝነት የሚመነጨው
ልጆችን በልጅነታቸው ካለማሰልጠን ነው የሚመጣ ችግር ነው፡፡

ልጆቻችንን እንዳናሰለጥን የሚያደርገንም ዋናው ሃሳብ
👉ልጄ ገና ነው/ ገና ናት
👉አሁን አላደጉም ሲያድጉ ይደርሳል፣ በሚል እሳቤና መዘናጋት
👉እንዲሁም ቤታችን ወስጥ በሚኖሩ ሞግዚቶች ምክንያት
💥 “ነይ አንሳሺው፣ ነይ ውሰጂው” እያልን ልጅ ምንም ሚና ሳይኖረው 🔒 ሁሉ ተነስቶለት፣ 🔒ሁሉ ቀርቦለት፣ 🔒 እየተጎረሰ፣ 🔒 ሳይጠይቅ እየቀረበለት፣ 🔒ሳይቸገር፣ 🔒 ሳይወድቅ ሳይነሳ፣ 🔒እንቅፋት ሳይመታው፣ 🔒መጠንን ሳያውቅ፣ እናሳድግና

ልጃችን ከፍ ሲል ያልዘራነውን ፍሬ ለመልቀም እንሞክራለን

ከዛም ልጃችንን
👉 “ና አንሳው? 👉የት አደረከው? 👉ምንድን ነው የሆነው? 👉ለዕቃዎችህ ጥንቃቄ አድርግ“ እና የመሳሰሉትን ጥያቄዎች ሁሉ መመለስ የማይችል ልጅ ይሆንና

ለተገዙለት ነገሮቹ ደንታ ቢስ፣ ዋጋ የማይሰጥ ፣ መጣል ብቻ ሳይሆን እንደጣለ እንኳ የማያውቅ፣ ት/ቤት ለመርፈዱም ለደብተሩም እኛ የምናስብለት ልጅ፣ በአጠቃላይ አቅም የሌለውና ሃላፊነትን የማያውቅ ልጅ እናፈራለን ማለት ነው፡፡

💡💡ስለሆነም በትንሽ ትንሹም ቢሆን ልጆችን:-

1. ከልጅነት እድሜያቸው ጀምሮ የራሳቸው ሚናና ሃላፊነት እንዲወስዱ በማድረግ በትዕግስት ማሰልጠንና ማስተማር

2. ለምናደርግላቸው ነገሮች እስኪጠይቁ ድረስ መጠበቅ (ሳይጠይቁ አለማድረግ)

3. ለሚደረግላቸውና ለሚገዙ ነገሮች በምርጫ ሂደቱ ላያ ማሳተፍ (ምርጫ ቢሳሳቱም በትዕግስት እያለፉ በማስተማር)

ሃላፊነት የሚወስዱና ሃላፊነት የሚሰማቸው ልጆች ማፍራት እንችላለን፡፡

ወላጅነት በልዩነት!
ማይንድ ሞርኒነግ
በልጆች ላይ ተነሳሽነት ማጣትና ግድየለሽነት እንዴት ይመጣል ?

👉👉አንዳንድ ጊዜ ልጆች የራሳቸውን ሃላፊነት ለመወጣትም ሆነ የራሳቸውን ግዴታ ለማከናወን ተነሳሽነት ሲያጡ፣ እስከሚታዘዙና ግዴታ ውስጥ እስከሚገቡ ይጠብቃሉ። ◌ መታጠብም ካለባቸው ሳይታጠቡ፣ ◌ ማድረግም ካለባቸው ሳያደርጉ ◌ ብቻ በአጠቃላይ ከተቀመጡበት ሳይነሱ፣ ከሄዱበት ሳይመለሱ ታካች የምንላቸው ልጆች ይሆናሉ👈👈 👉👉👉ይህ ባህሪ እንዴት ይመጣል🔑🔑

1.➻ ልጆችን ከልጅነታቸው እድሜ ጀምሮ ሃላፊነት ሳይሰጡ ማሳደግ ልጆችን ታካች ከማድረጉም በላይ እንደሚደረግላቸው እንጂ ማድረግ እንዳለባቸው እንኳ እንዲያስቡ ልጆች ያደርጋቸዋል፡፡

2. ➻ ትዕዛዝ ተኮር የሆነ የወላጅነት ዓይነት ደግሞ ልጆች ይሳሳታሉ፣ ይጎዳሉ፣ ያለሆነ ተግባር ይፈፅማሉ ብሎ በማሰብ ልጆችን ለትዕዛዝ ጠባቂነት እና ግድ የለሽነት የሚዳርግ የወላጅነት አይነት የሚያመጣው ተፅዕኖ
3. ➻ የወላጆች “እኔ ሳከናውነው ብቻ” የሚል የፍፁምነት (Perfection) አስተሳሰብ ልጆችን በራሳቸው ተነሳስተው እንደ አቅማቸውም ቢሆን ባከናወኗቸው ነገሮች ላይ ትችት ማብዛትና ዋጋ አለመስጠት ልጆች እየቆዩ እየሰለቹና እየታከቱ እንዲሄዱ ያደርጋቸዋል፡፡

ወላጅነት በልዩነት
ማይንድ ሞርኒነግ
1
💡ጀምረው የማይጨርሱ ልጆች 💡

🔒አንድን ነገር ጀምረው መጨረስ የሚያቅታቸው ልጆች ብዙ ጊዜ እራሳቸውን የማይወዱ፣💥 ለራሳቸው ዋጋ የማይሰጡ 💥 ስለራሳቸው የሚሰማቸው ስሜት ዝቅተኛ የሆኑና💥 ስኬት ለእኔ እሩቅ ነው፤ አልችልም ብለው የሚያስቡ ናቸው፡፡ 💥

👂👂ይህ ጀምሮ ያለመጨረስ ባህሪ በተደጋጋሚ እነርሱ ጋር ሲከሰት ወደ ድብርት፤ ተጠራጣሪነትና ስኬት አልባነት ይወስዳቸዋል ማለት ነው፡፡👂👂


ልጆች ጀምረው ከማይጨርሱባቸው ምክንያቶች ውስጥ ጥቂቶቹ

👉1. ልጆችን በተጣበበ ፕሮግራም መምራት፤- ይህም ሰዓት ጨርሰናል፣ ሌላ ጊዜ እናደርገዋን፣ ብለን የራሳችን የተጣበብ ጊዜ ውስጥ ከተናቸው የተሳተፉበትን ነገር
ውጤት ሳያዩ በቃ በቃ ሌላ ጊዜ እንጨርሰዋለን በማለት ማቋረጥ ምንም እንዳልሆነ ማስተማር

👉2. ትኩ ረትና ማጣትና ልጆች ለሰሯቸውን ነገሮች ዋጋ አለመስጠት፡- ልጆች የቤተሰቦቻቸውን ትኩረትና አድናቆት ለማግኘት ሲሉ የተለያዩ ነገሮችን ያደርጋሉ፣ ይሞክራሉ ሆኖም ግን ላደረጉት ነገር ዋጋ ሳንሰጥላቸው ስንቀር ቤተሰቦቼ አልተደሰቱም ማለት ነው ብለው ሌላ ነገር ይሞክራሉ ያንንም እንዲሁ ከዛም እንደገና ይሞካረሉ ፤ እንደገና፤ እንደገና፡፡ በዚህ ሂደት ውስጥ ልጆች የመጨረስን ዋጋ ሳያዩ ይድጉና ኋላ ላይ በአጠቃላይ ፍላጎትና ተነሳሽነት የሌላቸው ልጆች ይሆናሉ

👉3.የሚሳተፉበት ነገር አሰልቺ ሲሆንን እና ድግግሞሹ የበዛ ተግባር ውስጥ ያለ ፍላጎታቸው ስነከታቸው መጨረስን ሳይሆን ማቋረጥን በቀላሉ ይለምዳሉ፡፡

ወላጅነት በልዩነት!

ማይንድ ሞርንኒግ
ልጆችዎ ከ 9 ነኛ ክፍል በላይ ከሆኑ ህዳር 6 የሚሄደው ፕሮግራም ላይ አብሮ መገኘት ይቻላል!!
ቦታ ቫምዳስ አዳራሽ
ከሰዓት ከ9-12 ሰዓት

ወላጅነት በልዩነት!

ማይንድ ሞርኒንግ
👉👉 ጥያቄ የማይጠይቁ ልጆች!!

🔶 ብዙ ጊዜ ምንም የማይጠይቁ ልጆችን እንደ ፀባየኛ፣ እንደ ማያስቸግር ልጅ፤ የሰጡትን ሁሉ የሚቀበል እና የዋህ የሚል ስያሜ እንሰጣቸዋለን◌

ሆኖም ግን ይህ ባህሪ በልጆች ትምህርት፣ ንቃትና ቀጣይ ህይወት ላይ ትልቅ ተፅዕኖ ያለው ነገር ነው፡፡

➻➻ እንዚህ የማይጠይቁ ልጆችን ቀረብ ብለን ስናያቸው ግን 🔶 ደንታቢስ የሆኑ፤🔶 እንቢ-አልፈልግም ማለት የማይችሉ፣🔶 ለብዙ ነገር የተለየ ስሜትና ጉጉት የሌላቸው መሆናቸውን እንመለከታለን፨

🔷 ይህ ባህሪ ልጆችን እቤት ውስጥ የምንይዝበት መንገድ 👉ጥያቄ መጠየቅን እንዳይለምዱ፣ 👉 እንዲያቆሙ፣ 👉እንዳይማሩ ያደርጋቸዋል ለምሳሌ
❶ ልጆች ለምንም ነገር ፍላጎት ሳያሳዩና ሳይጠይቁ ፍላጎቶቻቸውን ቀድመን ስንሞላው /ስናደርግ
❷ ዝም የሚል ልጅ የሰጡትን የሚቀበል ልጅ ትክክል እንደሆነ እየነገርን ስናሳድግ
❸ ለጥያቄዎቻቸው መልስ እንደማያገኙ ሲያስቡና ምላሻችን ወደ መከልከልና መሰላቸት ሲያዘነብል
❹ ጥያቄዎቻቸውን ስናጣጥልባቸው፣ በጥያቄው ስንስቅባቸው፣ ለመመለስ ያህል ስንመልስላቸው

👉ልጆች ጥያቄ መጠየቅን አይማሩም ወይም ያቆማሉ ማለት ነው👈
🚩 ይህ ሲሆን ደግሞ ልጆችን ከተሳታፊነት፤ ከተማሪነት ወደ ተመልካችነትና ጠባቂነት እንቀይራቸውና መማር እንዲያቆሙ እናደርጋቸዋለን ማለት ነው፡፡

ወላጅነት በልዩነት!

ማይንድ ሞርኒንግ
👍1