Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.44K subscribers
1.34K photos
16 videos
9 files
510 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
ለውጥ ያለው በማወቅ ውስጥ ነው።
ማወቅ ያለው በመጠየቅ ውስጥ ነው።
መጠየቅ ያለው በንቃት ውስጥ ነው።

ቅዳሜ ነሃሴ 4 ከቀኑ 9:00 ሰዓት በ ቫምዳስ አዳራሽ ከባለቤትዎ ጋር ተገኝተው ስለ ልጅዎ፣ ስለ ራስዎ እና ስለ ቤተሰብዎ ዕውቀት ይሸምቱ።

ከትዳር አጋርዎ ጋር አብረው ሲማሩ አብረው ማደግ ይችላሉ። የሚጣላና የሚጣፋ ሃሳብ ሳይሆን አብሮ የሚያድግና የሚገነባ ሃሳብ ይኖራል።

👉 ሁሌ መማርና ማወቅ ነፃ ያደርጋል!

ወላጅነት በልዩነት!
ማይንድ ሞርኒንግ
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
ሰኔ 20/2011 የተጀምረው 5ተኛው ዙር የክረምት የልጆች የአእምሮ ብልፅግና ስልጠና በ 7 ምድብና በ 4 የዕድሜ ክፍፍል በሚያመር ሁኔታ ተካሂዶ በዚህ መልኩ ተጠናቋል፡፡

🌠በስልጠናው ውስጥም የሚገርም አቅም ያላቸውን ልጆች ያየንበት፣ ለለውጥና ራስን ለማሻሻል ቅርብ የሆኑ ልጆች ያሉበት፣ ያላዩትን አቅማቸውን ያዩበት፣ በሚገርም ሁኔታ መነቃቃት ያሳዩበትና ለውጥ ያመጡበት እኛንም ቤተሳቸውንም የስደመሙበት ስልጠና ነሐሴ 20 ተጠናቀቀ፡፡ 👏👏👏

ቤተሰብ ሲታከም ሃገር ይድናል!

ማይንድ ሞርኒነግ
2011 ዓ.ም
🌻🌻እንኳን አደረሳችሁ !! 🌻🌻
ስለ ቤተሰብዎ የአዲስ አመት እቅድዎ ምን ይላል?

ጤናማ ቤተሰብ የእድል ሳይሆን የስራ ውጤት ነው!

🚩 በ 2012 በቤተሰብዎ ጉዳይ ከእናንተ ጋር ነን!

8ኛው ወላጅነት በልዩነት መስከረም 10 ቅዳሜ ከቀኑ 9:00-12:00 በቫምዳስ አዳራሽ ይካሄዳል።
👉 ከአጋርዎ ጋር በመገኘት አብሮነታችሁንና ንቃታችሁን መጨመሪያ ጊዜ አድርጉት!!

ማይንድ ሞርኒንግ
ወላጅነት በልዩነት!!
ባማ ጫማ በእናቶች ስም እናመሰግናለን !!
አዲሱ ዓመት የአንደበት መፍቻ ወይስ የእጅ መፍቻ? በእድሜዓለም ግዛ።
ሐዋዝ የጥበብ ምሽት ላይ የቀረበ።
🌻🌻🌻🌻 እንኳን አደረሳችሁ!!🌻🌻🌻🌻
💡💡💡 ዝግጁነትና ህይወት 💡💡💡

👉 ዝግጁነትና ሰው
👉 ዝግጁነትና ቤተሰብ
👉 ዝግጁነትና ትዳር
👉 ዝግጁነትና ወላጅነት

🚩 ህይወታቸውን ሁሌ በዝግጁነትና በዕቅድ የሚመሩ ሰዎች ስኬታቸው የሚታይ፣ የሚቆጠር፣ የሚነበብ፣ የሚያስተምር ይሆናል፡፡

🚩ከዝግጁነት በተቃራኒው ደግሞ ህይወታቸውን በአጋጣሚ፣ በሁኔታና፣ በሌሎች የሚመሩ ሰዎች ህይወታቸው “እንደክማለን፣ እንጥራለን፣ እንለፋለን ጠብ የሚል ነገር የለ” በሚል ማንቦጫረቅ ዐረፍተነገር የተሞላ ይሆንና መልሳቸው ሁሉ “እኔ እንጃ አላውቀውም፣ አጋጣሚ ነው…” የሚል ይሆናል ማለት ነው፡፡

ሆኖም ግን ቢለምድብንም ባይለምድብንም
አድርገነው ብናቅም ባናቅም

የህይወታችንን ደስታ፣ ስኬትና መነቃቃት 80% ድርሻ የሚይዝ
የህይወታችንን ችግሩንም መፍትሔውንም በራሱ ውስጥ የያዘ
ጆሮአችን በጣም የለመድው እጃችንና እግራችን ግን የሚቸገረው እቅድ የሚባለው ነገር ነው፡፡

እስኪ ከዓመቱ ካሉት ቀናቶች ዛሬን እንውሰድና እንዚህን ሁለት ቀላል መንደርደሪያ ጥያቄዎች ራሳችንን እንጠይቅ
🚩1. ከባለፈው ዓመት ከራሴ፣ ከቤተሰቤ ቢስተካከል፣ ባይኖር ብዬ ያሰብኩትና የጠላሁት ነገር ምንድን ነበር? ብለን እናስብና እንዘርዝራቸው::
🚩2. ከራሴና ከቤተሰቤ አንፃር ማድረግ ኖሮብኝ ያላደረኩት ነገር ምንድን ነው? ብለን ራሳችንን እንጠይቅ

ከዛም ይሄ 12 ወራትን ሙሉ የያዘውን ዓመት
👉 መሆን የምንፈልገውን ራሳችንን፣
👉 እዲሆን የምንፈልገውን ቤተሰባችንን እናቅድበት ከዛም ያ
የሚቆጠር፣ የሚነበብ፣ የሚነገር፣ የሚያስተምር ቤተሰብ እያየነው እየሰራነው እያደገ ይመጣል ማለት ነው፡፡

ማይንድ ሞርኒንግ !
ወላጅነት በልዩነት!
መስከረም 10
ቫምዳስ አዳራሽ
ከቀኑ 9:00 ሰዓት ይገኙና አብረን እናብስለው!!
👍1