💡💡 5ኛ የልጆች የክረምት የአዕምሮ ብልፅግናና የህይወት ብቃት ሥልጠና!!💡💡
🚩 ለሁሉም የእድሜ ክፍል የራሳቸው የሆነ የመማርያ መንገድ አለው!
በቆይታቸው ከሚዳሰሱ ርእሶች ውስጥ በጥቂቱ
✴ ዝግጁነት
✴ ለራስ የሚሰጥ ግምትና በራስ መተማመን
✴ ሚናን መለየትና ሃላፊነት መውሰድ
✴ የግል ጥንካሬና ድክመት
✴ አማራጭ ሃሳብ የማምጣት ክህሎት
✴ የመማርያ ዘዴ ተሰጥዖን ማቅና የጥናት ዘዴ
ሌሎችም ፥ ሌሎችም፥ ሌሎችም ርዕሶች ይነሳሉ፥ ይጠየቃሉ፥ ይጠይቃሉ ይወያያሉ
👉👉 እርስዎም ይወዱታል፤ ልጆችም ይወዱታል ፤ እኛም እንወደዋለን!!👈👈
⭐አንድ ክፍል ጥቂት ልጆች ብቻ ስለምንይዝ ቀድመው ልጆችዎን ያስመዝግቡ!!🌟

✍️✍️ልጆች ሃሳባቸውን መግለፅ እንዳይለምዱ የሚያደርጉ የአስተዳደግ ዘይቤዎች✍️
ልጆች ሃሳባቸውን በነፃነት መግለፅ የሚለምዱት መጀመርያ በቤተሰብ ውስጥ ነው፡፡ ሆኖም ግን ልጆች ሃሳባቸውን ለመግለፅ እንዳይለምዱ ከሚያደርጓቸው ነገሮች ውስጥ ጥቂቶቹ
1. 👂👂👂ሁሌ የኑሮ ሩጫ ላይ ያለ ቤተሰብ፣ ለማረፍና ለመረጋጋት ጊዜ የሌለው፣ ከቤተሰቡ ጋር ጥሩ እና ከሁካታ ነፃ ግዜ ማሳለፍ አለመቻል አንዱ ምክንያት ነው፡፡
በዚህ ምክንያት ልጆች ሲናገሩ ማብራሪያቸውን ጊዜ ወስደን መስማት ስለማንችል ልጆች ቶሎ ቶሎ ነጥብ ነጥቡን ብቻ እንዲነግሩን እንፈልጋለን ከዛም የወላጅ ምላሽ እሺ ከሆነ እሺ እምቢም ከሆነ እምቢ ብቻ ይሆንና ከውይይት ይልቅ ትእዛዝ ተኮር የሆነ የህይወት ዘይቤ ይፈጠራል ማለት ነው፡፡
👉👉በዚህም ምክንያት ልጆች በተረጋጋ ሁኔታ ማስረዳት፣ ሃሳብንና እይታቸውን መግለፅ፣ የውስጣቸውን አውጥተው መናገር፣ ባመኑበትና በገባቸው ነገር ላይ ለመከራከር ወላጅ ለጆሮ የሚሆን ጊዜ ስለሌለው ሃሳባቸውን የማይገልፁና ትዕዛዝ ጠባቂ የሆኑ ልጆች እናፈራለን ማለት ነው፡፡
2. 👂👂👂ወላጅ በችኮላ፣ በስጋት፣ አንዳንዴም ሳያውቀው በልምድ ልጆች መናገር ሲጀምሩ ሃሳባቸውን ሳይጨርሱ ማቋረጥ እና ለእነርሱ እኛ ማብራራት ወይም ከእህት ወይም ከወንድም ማብራሪያ መጠየቅ ልምድ ሲሆንብን ልጆች የእኔ ሃሳብ ተሰሚ አይደለም፣ እኔ ትክክል አደለሁም፤ የኔ ሃሳብ አይጠቅምም የሚል አመለካከት ያዳብሩና ዝምታን ይመርጣሉ፡፡
👉👉በዚህም ምክንያት ልጆች የጉዳዩ አካል ከመሆን ይልቅ በሌሎች ሰዎች ሲሆን፤ ሲከወን፣ ሃሳብ ሲሰጥ ዝም ብለው ማየትን እየተቀበሉት ይሄዳሉ በግል ህይወታቸውም ላይ ሃሳብ ሰጪ ከመሆን ይልቅ “አይቀበሉኝም” በሚል አመለካከትን ሃሳባቸውን ከመግለፅ ተገድበው ሲቸገሩ እናያለን፡፡
3.👂👂👂 ልጆች መናገር ሲጀምሩ ንግግራቸውን ውድቅ እንደምናደርግ ሲያስቡና በተቃውሞ (በአሉታ መንገድ) መስማት ስንጀምር ሃሳባቸወን ከመግለፅ ይልቅ ዝም ብልስ ባልናገርስ በማለት ሃሳባቸውን ይውጡታል ግዴታ ሃሳባቸው መግለፅ ከለባቸውም ደግሞ በልቅሶ መግለፅ ይጀምራሉ ማለት ነው፡፡
💥💥 ስለሆነም ልጆች የራሳቸው ምልከታና ሃሳብ አላቸው ብሎ ካለማሰብና በተለያየ ምክንያት በቤተሰብ ውስጥ የውይይት፣ የክርክርና፣ የጥያቄ እድልን መከልከል የልጆችን እይታ ማጥፋትና ሃሳብን የመግለፅ ልምምዳቸውን ማሳጣት ስለሚሆን ወላጅ የኑሮ ዘይቤውን፣ የአስተዳዳግ ልምዱን፣ ድክመት እና ጥንካሬውን ኦዲት የሚያደርግበት ጊዜ፣ ስልጠናና ውይይት ያስፈልገዋል ፡፡
ወላጅነት በልዩነት
ማይንድ ሞርኒንግ

❤1
🎤 💥ልጆቻችንን እንደምንወዳቸው የሚያውቁትና የሚያረጋግጡት ለእነርሱ በምናደርገው ነገር ብዛት ሳይሆን አብረናቸው በምናደርገው ነገር ነው!! 💥🎤
ከልጆቻችን ጋር በተለያየ መንገድ አብረን የምናሳልፋቸው ጊዜያት ለልጆቹ ስብዕና እና የሥነ-ልቦና ጥንካሬ ያለው ድርሻ ከምንም በላይ ነው፡፡ ከልጆቻችን ጋር
👉በአንድነት መብላት
👉አንዳንዴም ሁሉም ቤተሰብ በአንድነት መተኛት
👉በአንድነት መንፈሳዊ ስፍራዎች ላይ መገኘት
👉በአንድነት ስፖርታዊ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ….
እነዚህና የመሳሰሉት የአንድነት ጊዜዎች በልጆች ስብዕና ላይ ከፍተኛ ለውጥ ያመጣል
💥🥁 1. ልጆች በቤተሰቡ ውስጥ አስፈላጊ እንደሆኑ፣ ዋጋ እንዳላቸው እና ተወዳጅ ልጆች እንደሆኑ የሚሰማቸውና የሚማሩት በዚህ ሁኔታ ውስጥ ነው
💥🥁2. ልጆች ሚስጢር እንዳይደብቁን እና በቀላሉ ለማጋራት ስለምንቀላቸው ምስጢራቸውን በቀላሉ እንዲያካፍሉን እድል ያገኛሉ
💥🥁 3. ልጆች በቤተሰባቸው ውስጥ ሚና እና ድርሻ እንዳላቸው እንዲሰማቸው ከማድረጉም በላይ እያደጉ እንደሆኑ ማረጋገጫ የሚያገኙበት አጋጣሚ ነው፡፡
💥🥁 4. ልጆች በቤተሰባቸው ውስጥ የእነርሱን እድሜ ሃላፊነቶች ለምሳሌ ካልሲያቸውን ማጠብ፣ ልብሳቸውን ማጣጠፍ መኝታ ክፍላቸውን ማስተካከል እና ሌሎችም ሌላ ሰው ሲወጣላቸው እነሱ ሃላፊነት አልባ ይሆኑና የሃላፊነት ትርጉም አይገባቸውም፣ የነገሮችን ዋጋ አያውቁልንም፣ ንቃታቸውም አያድግም፣ መረጋጋትና ትኩረት የማድረግ አቅማቸው ይቀንስብናል ስለዚህ ይህን ለማምጣት የአብሮነት ሚና ወሳኝ ነው፡፡
💥🥁 5. ልጆች ወላጆቻቸውን እንደ አርዓያ ለመውሰድ፣ ቤተሰባቸውን ለመውደድና ለማመን እንዲሁም የውጪና የአከባቢ ተፅዕኖ ለመቋቋም መልካም አጋጣሚን ይሰራላቸዋል፡፡
በአጠቃላይ ልጆቻችንን እንደምንወዳቸው የሚያውቁትና የሚያረጋግጡት ለእነርሱ በምናደርገው ነገር ብዛት ሳይሆን አብረናቸው በምናደርገው ነገር ነው፡፡
ወላጅት በልዩነት

👉👉በልጆች ዘንድ የፈተና ውጤት እራስን ለመጥላት አንዱ ምክንያት ነው!👈👈
ከትምህርት ውጤት ጋር ተያይዞ ብዙ ልጆች ፈተና ሲጀመር ውጤት ሲሰጥ የሚፈሩበትና የሚጨነቁበት ጊዜ ነው፡፡
🚩 ወላጅ አውቆትም ይሁን ሳያውቀው የራሱንም ሆነ የልጁን ባህሪ ሳይረዳ በልጆች ላይ የውጤት ጫና ያደርጋል።
ብዙ ጊዜም ወላጆች "ልጄ አቅም አለው፣ የሚያውቀውን ጥያቄ ስህተት ይሆናል፣ አጥንቷል ግን..." የሚሉ የወላጅ አስተያየቶች ይቀርባሉ፡፡
🚩 በልጆች በኩል ግን በውጤት ማምጣትና አለማምጣት፣ እንደማያመጡትም በማሰብ ጭንቀት ውስጥ ሆነው ስለሚፈተኑ የሚያውቁት ይጠፋቸዋል ውጤትም ይቀንሳል፡፡
ከዚህ የተነሳ ወላጅ "እኔ ለእናንተ ብዬ፣ እንደዚህ እየሆንኩ፣ እንዲህ እያደረኩ..." የሚሉ ክስና ወቀሳ ልጆች ላይ ያመጣል ፡፡
በዚህም ወቀሳና የበዛ ምክር ምክንያት ልጆቹ እንደዚህ እየተደረገልኝ፣ እንደዚህ እያጠናሁ… የሚሉ ራስን የመውቀስ ሃሳቦችን ይጀምርና "በቃ እኔ አልረባም፣ አልጠቅምም፣ አላስፈልግም" ወደሚል እራስን መውቀስ ውስጥ ይገባሉ፡፡
✴ከዚህ ሃሳብ መደጋገም የተነሳ እራሳቸውን ይጠላሉ፣ ትምህርት ይጠላሉ፣ ቤተሰብ ይጠላሉ በመጨረሻም መኖርን ይጠላሉ። ይህ ችግር ሳይፈታ ሲቆይ ትኩረታቸውና ፍላጎታቸው ሁሉ ወደ ሌሎች አላስፈላጊ ነገሮች ያዘነብላሉ ማለት ነው፡፡
ወላጅነት በልዩነት!

👍1
🚩ብዙ ጊዜ ወላጆች የምኖረው ለልጄ ነው፣ የምሰራው ለእነርሱ ነው፣ እንደ አቅሜ ለልጄ አላንስም፤ በሚል አስተሳሰብና የኑሮ ዘይቤ
👉 የልጆች መሰረታዊ ፍላጎቶች ላይ👈
✴ ልጆች ፍላጎት ሳያሳዩ እኛ ፈልገንላቸው፣
✴ ጥያቄ ሳይጠይቁ ሁሉን ነገር አቅርበንላቸው፣
✴ እነሱ እንደሚያስፈልግ ሳያውቁ እኛ አስፈላጊ ነው ብለንላቸው፤
🚩🚩 እኛ አስበን ሁሉ ነገር ቅድሚያ ገዝተንላቸው፣
🚩🚩ሁሉ ነገር አልቆ ተጠናቆ ብቻ እያዩ ሲያድጉ ልጆች ላይ ያለው 10 ከፍተኛ የሆነ የባህሪ፣ የመማርና የአስተሳሰብ ተፅዕኖ
👉1. የመጠየቅ ክህሎት ያጣሉ
ምክንያቱም ሳይጠይቁ ሁሉ ስለተደረገ
👉2. መወሰን አይችሉም - በጉዳዩ ላይ ድምፅና ተሳትፎ ስለማይኖራቸው
👉3. መምረጥ አይችሉም- የተለያዩ ፍላጎቶቻቸውን በስሜት ስለማያውቋቸው
👉4. ለነገሮች ዋጋ መስጠት አይችሉም-- ድካሙንና የሃሳቡን መጠን ስላላዩትና ማጣትን ስለማያውቁት
👉5. ለምንም ነገር ደንታ ቢስ ይሆናሉ-- ተሳስተውም ልክ ሆነውም አይተውት ስለማያውቁ
👉6. ለሚያደርጓቸው ነገሮች ሁሉ የእኔነት ስሜት አይኖራቸውም-- የጉዳዩ ባለቤት እንዳልሆኑ ስለሚያውቁ
👉7.. እስኪደረግላቸው ይጠብቃሉ- እየተደረገላቸው ብቻ ስለመጡ
👉8. ማመስገን አይችሉም -- ሂደቱን ስለማያውቁት
👉9. ሃላፊነት መውሰድ አይችሉም-- የነሱ ስሜትና ሃሳብ በጉዳዩ ላይ ስለሌለ
👉10. ልጆች የተነቃቁ አይሆኑም ለድብርትና ለሱስ ይጋለጣሉ-- ምክንያቱም ሚናቸውንና ትርጉማቸውን ስለማያውቁት
🚩
እነዚህ የባህሪ ተፅዕኖዎች በልጆች ላይ እናመጣለን ከዛም ልጆች በራስ መተማመን ያጣሉ፣ ለትምህርት ግድ አይኖራቸውም፣ የመኖርን ጣዕም አያውቁትም፣ ሰነፍ ይሆናሉ…እነ ሌሎችም ብዙ ጉዳቶች በልጆች ህይወት ላይ እናደርሳለን፡፡ ስለሆነም በሚደረጉ ነገሮች ላይ ልጆች እንዲጠይቁ፣ ሃሳብ፣ ምርጫና፣ ውሳኔ እንዲኖራቸው በማድረግ በእነርሱ ጉዳዮች ላይ እኔ አውቅልሃለሁ/ አውቅልሻለሁ ከሚል አመለካከት ወጥተን የልጆችን ድምፅ ብንሰማ ልጆችን ማትረፍ እንችላለን፡፡