Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.44K subscribers
1.34K photos
16 videos
9 files
510 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
ከፈለኝ ዘለለው
የሐዋዝ የጥበብ ምሽት አዘጋጅ

ስለ መጀመር ደግሞም ስለመጨረስ
ስለ መንቃት ደግሞም ስለ መትጋት
ስለ በጎነት ደግሞም ስለ ማካፈል
በጥልቅ ቋንቋና ጥበብ ስጦታህን ስላካፈልከን እና ዓይን ስለጨመርክልን
እናመሰግናለን!!
ሁሌም አብረኸን ለመሆን በጎ ፈቃድህ ስለሰጠኸን በድጋሚ አመስግነናል።
3ተኛው መድረክ በዚህ መልክ ተከናውኗል። ሁላችሁም የዚህ ሃሳብ ባለቤት ስለሆናችሁ እናመሠግናለን!!
ልጆች በራሳቸው ምንም ነገር እንዲያደርጉ አለመፍቀድ
        (ይወድቃሉ፣ ይታመማሉ፣ ሲያድጉ፣ አሁን አይችሉትም፣ የሆነ ነገር ቢሆኑስ… የሚል የተሳሳተ በመውደድ የተተካ አስተሳሰብና ሰበብ)
          ይህም ማለት የምናጎርሰው እኛ፣ የምናለብሰው እኛ፣ ሁሉን ነገራቸውን የምናከናውነው እኛ እንሆንና የልጆቹ ድርሻ መተንፈስ ያህል ብቻ ይሆናል ከዛም ልጆቹ ሲያድጉ እጅ ይኖራቸዋል ግን አቅም የሌለው  እጅ፣  እግር ይኖራቸዋል ግን ርቆ የማይራመድና ቶሎ የሚደክመው እግር፣ በአካል ያድጋሉ ግን ትንንሽ እንቅፋትን ማለፍ የሚከብዳቸው፣ እራሳቸውን ችለው መቆም የማይችሉና ጥገኛ፤ እስኪደረግላቸው ጠባቂ ይሆናሉ በዚህም ምክንያት ብዙ ጊዜ የሚሰሩት ነገር ስለሚያጡ (ነፃ ስለሚሆኑ) በቀላሉ ለሱስ የተጋለጡ ይሆናሉ ፡፡ 

ሁሉን ነገር ልጆች ጥያቄ ሳይጠይቁ ማቅረብ (መልስ መስጠት)
       ይህም እኔ ለልጄ አላንስም፣ የኢኮኖሚም የጊዜም ችግር የለብኝም፣ እኔ እንዳደኩት ልጄን አላሳድግም… በሚል አስተሳሰብና ሰበብ የልጆች የወደፊት ህይወት ላይ ትልቅ እንቅፋት የሆነ የአስተዳደግ ዘይቤ ነው፡፡ ይህም ሲሆን ልጆቹ መምረጥ የማይችሉ፣ መወሰን የማይችሉ፣ መብታቸውን የማያውቁ እና የማይጠይቁ፣ ዝም ብሎ ብቻ እንዲሆንላቸው የሚፈልጉ፣ ጠባቂነት (expectation) ያላቸው, ማግኘትን ብቻ እንጂ የማጣትን ትርጉም የማያውቁ፣ የህይወትን ሙሉ ገፅ የማያውቁ ይሆናሉ፡፡ 

በአጠቃላይ የሚያለሙንንና የሚያጠፉንን  በአስተዳደግ ዘይቤዎቻችንን እንቃኝ
ወላጅነት በልዩነት
ማይንድ ሞርኒንግ
4ተኛው የወላጆች መድረክ ይህን ይመስላል ነበር። ሁላችሁንም እናመሰግናለን!
ወዳጆቻችሁ ይህን ሃሳብ መጋራት እንዲችሉ ይህንን link ሼር አድርጓቸው።
@mindmorning