Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.44K subscribers
1.34K photos
16 videos
9 files
510 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
፤፤፤፤
እንዳዲስ ተፀንሶ የመወለድ ምስጢር
ፍላጎት ነውና መፈለግን ፈልግ
፤፤፤፤
በጨለማው መንገስ አትፍራ ተራመድ
ህልምን ያዘለ ሰው አጣው አይልም መንገድ
፤፤፤፤
መራመድ ሳትጀምር ከመሮጥህ በፊት
ከራስህ ጋር አውራ ቁጭብለህ ፊት ለፊት
፤፤፤፤
መኖር እንቆቅልሽ ሁሌ ጥያቄ ናት
መልስ መስጠት ሳትችል በፊት የማትኖራት
፤፤፤፤
ከፈለኝ ዘለለው (የሐዋዝ የጥበብ ምሽት አዘጋጅ)
ስለ ውብ ግጥምህና ስለሃሳቦችህ እናመሰግናለን
በሰው ልጅ ህይወት ውስጥ ታላቁ ነገር አለማወቁን ያወቀ ቀን ነው፡፡
ልጆች አሃ ማለት እንዲችሉ መሞከርንና ስህተት መስራትን ፍቀዱላቸው፡፡
ስህተትን ስንከለክል ልጆች ትልቅ ግብ አያስቀምጡም፣ በራስ መተማመን ያጣሉ፣ ስህተትን መደበቅና መዋሸት ይጀምራሉ ፡፡ ስለዚህ ልጆች የራሳቸውን መልስ እራሳቸው እንዲያገኙ ፍቀዱላቸው እናንተም የራሳችሁን መልስ ፈልጉ!
እድሜዓለም ስለ እይታህና ስለዕውቀትህ እናመሰግናለን
ወላጅነት በዚህ ዘመን ቀላልና መልካም አጋጣሚ ነው፡፡ ምክንያቱም የምናነባቸው፣ የምንማራቸው እና የምናደማጣቸው ብዙ አማራጮች ስለሞሉ፡፡
ሆኖም ይህን ለማድረግ ንቁ (Conscious) ወላጅ መሆን አለብን ንቁ ለመሆን ደግሞ መጀመሪያ ንቁ አለመሆናችንን ማወቅ ግዴታ ይሆናል!!
የቤተሰባችን እሴት መነጋገር፣ ስላለን ነገር ማመስገን፣ የራስን ሃላፊነት ራስ መውሰድ ናቸው
ወ/ሮ እመቤት ወልደሔር (ልምድ አካፋይ)
እመቤት ስለ ጎበዝ እናትነትሽና ስላካፈልሽን ልምድሽ እናመሰግናለን
በአጠቃላይ የመጋቢት 7/2011 ኢትዮጵያ ሆቴል የተካሄደው ወላጅት በልዩነት ትምርታዊ መድረክ ይህ ይመስል ነበር
3ተኛው መድረክ
የእርስዎ ልምምድ የትኛው ነው??