Forwarded from Mind Morning
🌧ከዝናቡ ይልቅ ቆርቆሮው ይጮሀል🔊
ዝናቡና ቆርቆሮው ድብድብን እንዲወክሉ ሆነው የቀረቡ ናቸው።ደብዳቢና ተደብዳቢ ልዩነታቸው አንዱ ብትር አሳራፊ ሌላው በትር ተቀባይ ስለሆኑ እንጂ ሁለቱም ተማተዋል ።ተመተዋልም። ቆርቆሮው የሚጮኀው የተደበደበውን ያክልና እርሱም የመቋቋም የቻለውን ያክል ነው።ጩኀት ለምን?🤔 ሰንል የተደበደበውን ያክል፣ አንዳንድ ተማሪዎችም ሌሎች ተማሪዎችን በመደባደብ ይታወቃሉ፡፡ልክ እንድ ወንጭፍ እንዳለው እህል ጠባቂ አይነት፣ ወንጭፍ ወደሗላ የተጎተተውን ያክል ወደፊት ይማታል፡፡ አንድ ተማሪም የተመታውን ያክል ይማታል፡፡ የሚገርመው ነገር ደግሞ አንድ ወላጅ የልጁን ጉዳት ሳያይና ጊዜ እንዳጣ ዘንግቶ ተመትተህ እንዳትመጣ የሚሉት ባህል በጣም ያሳዝነኛል። ይህ ለልጆች የበለጠ ጉዳት እንጂ ጥቅም አይሆንምና ፡፡
❓ለምን ቢሉ
‼️አንድ ተማሪ ሌሎች ተማሪዎችን የሚደባደበው እሱ የተደበደበውንና ያጠራቀመውን ያክል ስለሆነ ነው።‼️
በሌላ መንገድ ተደባዳቢው ልጅ ባለበት ያኔ በተደበደበ ጊዜ እንደቆመ መማርም እንዳልጀመረ ስላልገባን ነው።በባህሪ ተደባዳቢ ተማሪዎችን ብንገልጽ
😣ተነጫቻጭ -የሰማቸው ስለሌለ
😔 የአእምሮ እድገታቸው የቀጨጨ - መትፋት እንጂ መቀበል ስለሚቸገሩ
🚶 ብቸኛ -ማህበራዊ አብሮነት ስለሌላቸው
በዚህ የተነሳ ልጆቹ ድብርት፣ ስጋት፣ ያጠራቸው ሲሆኑ መማር አይችሉም፡፡ይልቁን የሀገራችን አባባል የሆነውን "የመጣን መቀበል የሄደን መሸኘት" ብንረዳው ከሁሉ ያተርፈናል።
✅የመጣን መቀበል ማለት መስማትና መማርን እንረዳለን።
✅የሄደን መሸኘት ከሚለው ደግሞ ሰውን በግድ ያለፍላጎቱ መያዝ ይጎዳዋል እንጂ አይጠቅምም የሚለውን እናገኛለን።
✨ለማንኛውም ተደባደብ ለተባለው ልጅ መፍትሄው መስማት ፣ጊዜ መስጠት፣መረዳት፣ራሱን እንዲገልጽ እድል ማመቻቸት ያስፈልጋል።✨
🙏ቸር እንሰንብት 👋

👍4❤1