Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.64K subscribers
1.33K photos
15 videos
9 files
508 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
ክትትል

በተለምዶ እንበለው በሳይንስ በማወቅ ዋናው መሪ ነው እንላለን። አሁን አሁን ሁሉም ነገር መሪ እየሆነ መጥቷል። ይህ ደግሞ የሰውን ልጅ ራሱን እንዳይመለከትና ጠባቂ እንዲሆን በሌላ መልኩም እኔ አውቅልሀለሁ የሚሉ መሪ የሚመስሉ ሰዎች እንዲበዙ ምክያት ሆኗል። ወላጅና ተመሪዎችም ሃላፊነትን ከመውሰድ ይልቅ ማሳበብና ሰው መውቀስን ዋና አድርገውታል። አንዳንዴም ምንም ጥሩ መሪ ቢኖር የገባውና ጥሩ ተመሪ ወይንም ተከታይ ያስፈልጋል እንላለን። ይሄም የሚያዋጣ አይደለም። ምክንያቱም ጉዳያችን ጥሩ ተመሪ ከመሆን ጋር ብቻ እይደለምና።

✂️ ይህን ጉዳይ ወደ ልጆችና ወላጆቻቸው ስንወስደው የሁለቱም ግንኙነት ከላይ እንዳብራራነው ተመሳሳይ ነው። ወላጅም የመሪ ሚናው ከብዶታል። ልጆችም ከወላጆች የተነሳ ጥሩ ተከታይ እየሆኑ አይደለም። አንድ ህይወት የምትፈልገው መሪም ተመሪም ቢሆንም ዋናው ነገር ክትትል ነው። መሪም ስያሜውን ያገኘው ከክትትል አቅሙ ነው። ተመሪም ምስጋና የሚቸረው ነገሮችን ከሚከታተልበት አቅሙ የተነሳ ነው። ክትትል ምንድነው?

❗️ትንሽዬ የውሃ ጠብታ ድንጋይ ትሰብራለች እንዲሉ⁉️

🔶ሃላፊነት መውሰድ ፣ በዚህ ብዙ ህዝባችን የሚታማ አይደለም ተማሪን ጨምሮ
🔶ለእያንዳንዱ ሃላፊነት ጊዜ መመደብ ፣ ጊዜ ከመወቅ ጋር ስለሚገናኝ በሀገር ደረጃ ዋና ውድቀታችን ነው።
🔶ሃላፊነታችን እየተወጣን እያለ ያልጠበቅነው ተግዳሮት ሲገጥመን መቋቋም ያልቻልነውም ጊዜ ስለማናውቅና ስለምናሳብብ ነው
🔶ለስሜታችንም ለስራችንም አጋዥ / ተባባሪ/ ደጋፊ ማዘጋጀት ጥሩ ባህልና ማንነታች የነበረ ቢሆንም አሁን አሁን በተለይ በከተሞች ጊዜ ከማጣት የተነሳ ፣ የጋራ ጊዜም ስላጣን አልቻልነውም ፤
🔶ስህተትን መቀበል ፣ ድሮ ድሮ ስህተትን አለማመን ያሳፍራል። አሁን አሁን ያለውን ሁኔታ ለእናንተ ተውሁት
🔶ስህተትን ማወጅ ፣ ይህ ደግሞ ስህተትን ከመቀበል ጋር ስለሚገናን አጉል ጥንካሬን ማወጅ ካልሆነ በስተቀር ስህተትን ማወጅ እጅግ የማይታሰብና የመይታወቅ ጉዳይ እየሆነ ብቻ ሳይሆን ስህተት የሚባል ነገር መሬት ላይ ያለ አይመስልም።
🔶በዓላማ መስራት ፣ ጊዜን የማያውቅና ስህተቱን የማያምን አላማ ስለማይኖረው ከማብራረት ተቆጠብሁ። ሌላውን ለእናንተ ተውሁት ።

ሌጅ ኢትዮጵያ -የወላጅነት አካዳሚ
Village Ethiopia-Parenting Academy
@ Mind Morning
15👍10
🎤🎤🎤🎤🎤
ለ10ኛ ክረምት ለ 7 ሳምንታት ሲሰጥ የቆየው የልጆችና የታዳጊዎች የአቅምና ክህሎት ስልጠና በሚያምር እና በሚናፍቅ መልኩ የመዝጊያ እና የሰርተፊኬት ጊዜ አካሂዷል።
🙋🙋🙋

📖 በንቃት፥ በጉጉት እና በናፍቆት የነበራችሁ ቆይታ ባያልቅ ያሰኛል ያስናፍቃል። 

📖 ምሳሌ የሆናችሁ ወላጆች አርዓያነታችሁ ይቀጥል

🖍ሁሌም ድንቅ ናችሁ🖍

በመጨረሻም
🎉🎉🎉🎉🎉🎉🎉

ለቤተሰብ ለሀገር ፍሬ አፍሩ ብለን መርቀን ተመራርቀን አጠናቀቅን።

በብዙ ማማር፥ ፍቅርና አክብሮት የሞላበት ድንቅ ቆይታ!!!

ለምታስቡልን፥ ለተሳተፋችሁ፥ ላበረታታችሁን፥ ከማይንድ ሞርኒንግ ጎን ለነበራችሁ ሁሉ ምስጋናችን ታላቅ ነው!!🙏🙏🙏

@mindmorning
👍111