Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.62K subscribers
1.33K photos
15 videos
9 files
509 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
🔆🔆 በክረምቱ ቆይታችን የልጆችን ስሜት ላጋራችሁ🔆🔆🔆

🌟⭐️ ቅዳሜ ነሐሴ 28 ግሩም ጊዜ አሳለፍን!!
🌦 በክረምቱ ወቅት ለ 7 ሳምንታት ራስን የማወቅ ክህሎቶችና ተግባራት ላይ ከ 180 በላይ ልጆችን በ 14 የመማሪያ ሰዓታት ድንቅ በሆነ ሁኔታ ልጆች ራሳቸውን አይተዋል፣ ብዙ ክህሎቶችን አዳብረዋል፣ ችግሮቻቸውን በመረዳት ተሸገረዋቸዋል፣ ለቀጣይ የትምህርት ዓመት ራሳቸውን ብቁ እና ንቁ አድርገዋል፡፡

🤩🥰 የየልጆችም ስሜታቸው፣ ልምዳቸው እና እይታቸው በተለያዩ መንገዶች ተገልጸዋል።

🏆 ማይንድ ሞርኒንግም ዓላማውን አሳክቷል፣ ህልሙን ኖሯል፣ ትውልድን አፍርቷል፡፡

🎯🎯 ደስታችንን ተጋሩን!!🥰🥰🥰

🌟 በቀጣይ የበጋ ጊዜም ለልጆች የቅዳሜ ፕሮግራማችን ይቀጥላል፣
⭐️ለአዋቂዎች እንዲሁ ራስን ማወቅ ስልጠናች ይቀጥላል፣
🌟 በተጨማሪም የምክክር አገልግሎታችን በልዩነቱ ይቀጥላል፣
⭐️የሬድዮ ፕሮግራማችን ተደማጭነቱ ይሰፋል፡፡

💫💫ሁሌም ከኛ ጋር ስለሆናች እናመሰግናለን!!🌟⭐️

#mind-morning
👍1
🌼 እንኳን አደረሳችሁ! 🌼
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼

🌼የማይንድ ሞርኒንግ ቤተሰቦች እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም አደረሳችሁ!

🌼 የአርባ ምንጭ ኃይሌ ሪዞርት የአንድ ሳምንት ጥሩ ራስን የማዳመጥ፥ የእረፍትና የአርምሞ ድንቅ በሆነ ተፈጥሮ እና መስተንግዶ ውስጥ እንድናሳልፍ ጊዜ ስለሰጣችሁን እናመሰግናለን🙏🙏

🌼 የማይንድ ሞርኒንግ አጋር በመሆንም ከንጋትና ሕይወት የሬድዮ ፕሮግራም ጋር አብራችሁን ስለሰራችሁ በድጋሜ እናመሰግናለን!
🌼🌼🌼🌼🌼🌼
የማይንድ ሞርኒንግ ቤተሰቦች ዓመቱ በጎ ፍሬዎችን የምናይበት ዓመት ይሁን!!
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
መልካም አዲስ ዓመት
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼
ነሐሴ ወር አምስተኛ ሰኞ እንግዳ
<unknown>
🖍 ነሐሴ ወር- ራስን የመቀበል ወር

4️⃣ አምስተኛ ሰኞ-- እንግዳ

🌟 10 ዓመት የከበደኝን፤ ህመም የፈጠረብኝን ታሪኬን-- የእኔ ታሪክ ነው ብዬ ስቀበለው እረፍት አገኘሁ፤ እንቅልፌን ተኛሁ፤ ሙሉነት ተሰማኝ
🌟 መቀበል ለእኔ እረፍት ነው። እንግዳችን

☀️ ጊዜ ወስደው ያድምጡት! ለሌሎችም ያጋሩት


🌟 መልካም አዲስ አመት!!!


ማይንድ ሞርኒንግ የባህሪ ስልጠና ምርምርና ማማከር ከ ኤፍ ኤም አዲስ 97.1 ጋር በመተባበር  ዘወትር ሰኞ ከ 9-10 ሰዓት በቀጥታ በእድሜዓለም ግዛ ተዘጋጅቶ ይቀርብላችኋል፡፡

https://t.me/mindmorning
http://mind-morning.com
👍1
#2015ዓ.ም
#አዲስ ለ6 ሳምንታት የሚሰጠው ተከታታይ ስልጠናችን ቅዳሜ መስከረም 07/2015 ይጀመራል!!
🔺 ያለን ቦታ ጥቂት ነው!!

🎯🎯ስልጠናው ለአዋቂዎች (For Adults) ነው!

❇️ ከ 60 ዙር በላይ የተሰጠ ስልጠና

👉በእነዚህ 6 ቅዳሜዎች
🔎 ሃሳቦች፣
🔎የውስጥ ስሜቶች፣
🔎 የህይወት ጥያቄዎች፣
🔎ስለ ራሳችን ያሉን ግራ መጋባቶች መልስ ያገኛሉ

💎 ከራስዎ ጋር ዘለግ ያለ ግዜ ይወስዳሉ!።

🔑ቁጣ፣ 🔑ብስጭት፣ 🔑ህመም፣ 🔑ድካም፣ 🔑አለመርካት፣ 🔑አሉታ አስተሳሰብ 📍📍ቦታ ቦታቸውን ያገኛሉ። 📍📍

📕 ራስን ማወቅ ይጀመራል እንጂ የሁል ጊዜ ሂደት ነው!!
📕 ደስታ፣ ስኬት፣ ዓላማን መኖር፣ የተረጋጋ ሰው መሆን፣ ጤነኛ መሆን የሚጀምረው ራስን ከማወቅ ነው!!

🎯ራስን መመልከቻ፣ 🎯ችግሮችዎን መፍቻ፣ 🎯ከራስ ጋር መታረቂያ፣ 🤔 ቆሞ ማሰቢያ ስልጠና!

#mind_Morning