Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.44K subscribers
1.34K photos
16 videos
9 files
510 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
ልጆች በየራሳቸው እድሜ የሚያድጉ የሰውነት ክፍሎችና የሚዳብሩ የአእምሮ ክፍሎች እንዳሏቸው ይታወቃል፡፡

በዚህም ምክንያት ልጆችን የምንይዝበትና የምናሳድግበት መንገድ በልጆች ማንነትና ባህሪ ላይ ትልቅ አስተዋፅዖ አለው ከዚህም የተነሳ የልጆች ብስለት እና የአስተሳሰብ አድማስ በወላጆቹ ወይም በቅርብ በተገኙ ሰዎች ይወስናል፡፡

ስለሆነም ከ 8-11 ያሉ ልጆች ከአስተሳሰብ አንፃር የሚዳብረው የአእምሮ ክፍላቸው፡-

🚩 ምክንያታዊነታቸው የሚሰራበትና የሚዳብርበት ጊዜ
🚩 የማስታወስ አቅማቸው የሚሰራበት ጊዜ
🚩 እራሳቸውንም ሌሎችንም ማነፃጸር የሚጀምሩበት ጊዜ
🚩 የቋንቋ አቅማቸው የሚያድግበትና ብዙ ቃላትን የሚያውቁበት ጊዜ
🚩 ስሜትን መግለፅ የሚለምዱበት ጊዜ
🚩 ፍትሃዊ አስተሳሰብ የሚዳብርበት ጊዜ
🚩 ፍላጎታቸው፣ ምርጫቸው እና ባህሪያቸው በብዛት አጠገባቸው ወደሚገኝና ወደሚወዱት ሰው የሚያዘነብልበት ጊዜ ነው

👉 👉በመሆኑም ንቁ ወላጅ ያላቸው ልጆች እነዚህ ነገሮች ታሳቢ በማድረግ ልጆቻቸው ላይ አዕምሮአዊ ስራ በትጋት ይሰራሉ
👉👉ንቁ ያልሆነ ወላጅ ያላቸው ልጆች ደግሞ ልጆቹ ካደጉ በኋላ ይነቁና የኔ ልጅ ለምን እንዲህ ሆነ? እንደዚህ አይችልም፣ እንደዚህ አልሆነም፣ ምናምን በሚል ያለመቻል የባህሪ መገለጫዎች ልጆቻቸውን ሲያነሱ ይታያሉ፡፡
እንደ ልጆቻችን እድሜ ተግተን ብንሠራ መልካሙን ፍሬ ለማየት ጊዜ አይወስድም!!

ወላጅነት በልዩነት!
ነሐሴ 4
ማይንድ ሞርኒነግ
ለውጥ ያለው በማወቅ ውስጥ ነው።
ማወቅ ያለው በመጠየቅ ውስጥ ነው።
መጠየቅ ያለው በንቃት ውስጥ ነው።

ቅዳሜ ነሃሴ 4 ከቀኑ 9:00 ሰዓት በ ቫምዳስ አዳራሽ ከባለቤትዎ ጋር ተገኝተው ስለ ልጅዎ፣ ስለ ራስዎ እና ስለ ቤተሰብዎ ዕውቀት ይሸምቱ።

ከትዳር አጋርዎ ጋር አብረው ሲማሩ አብረው ማደግ ይችላሉ። የሚጣላና የሚጣፋ ሃሳብ ሳይሆን አብሮ የሚያድግና የሚገነባ ሃሳብ ይኖራል።

👉 ሁሌ መማርና ማወቅ ነፃ ያደርጋል!

ወላጅነት በልዩነት!
ማይንድ ሞርኒንግ
🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟🌟
ሰኔ 20/2011 የተጀምረው 5ተኛው ዙር የክረምት የልጆች የአእምሮ ብልፅግና ስልጠና በ 7 ምድብና በ 4 የዕድሜ ክፍፍል በሚያመር ሁኔታ ተካሂዶ በዚህ መልኩ ተጠናቋል፡፡

🌠በስልጠናው ውስጥም የሚገርም አቅም ያላቸውን ልጆች ያየንበት፣ ለለውጥና ራስን ለማሻሻል ቅርብ የሆኑ ልጆች ያሉበት፣ ያላዩትን አቅማቸውን ያዩበት፣ በሚገርም ሁኔታ መነቃቃት ያሳዩበትና ለውጥ ያመጡበት እኛንም ቤተሳቸውንም የስደመሙበት ስልጠና ነሐሴ 20 ተጠናቀቀ፡፡ 👏👏👏

ቤተሰብ ሲታከም ሃገር ይድናል!

ማይንድ ሞርኒነግ
2011 ዓ.ም
🌻🌻እንኳን አደረሳችሁ !! 🌻🌻
ስለ ቤተሰብዎ የአዲስ አመት እቅድዎ ምን ይላል?

ጤናማ ቤተሰብ የእድል ሳይሆን የስራ ውጤት ነው!

🚩 በ 2012 በቤተሰብዎ ጉዳይ ከእናንተ ጋር ነን!

8ኛው ወላጅነት በልዩነት መስከረም 10 ቅዳሜ ከቀኑ 9:00-12:00 በቫምዳስ አዳራሽ ይካሄዳል።
👉 ከአጋርዎ ጋር በመገኘት አብሮነታችሁንና ንቃታችሁን መጨመሪያ ጊዜ አድርጉት!!

ማይንድ ሞርኒንግ
ወላጅነት በልዩነት!!
ባማ ጫማ በእናቶች ስም እናመሰግናለን !!
አዲሱ ዓመት የአንደበት መፍቻ ወይስ የእጅ መፍቻ? በእድሜዓለም ግዛ።
ሐዋዝ የጥበብ ምሽት ላይ የቀረበ።