Mind Morning/ ማይንድ ሞርኒንግ
6.44K subscribers
1.34K photos
16 videos
9 files
510 links
-ስልጠናዎቹ ህይወት ለዋጭ ናቸው!
-የሬድዮ ፕሮግራሙ ራስን አመልካች ነው!
-ጥናቶቹ ችግር ፈቺ ናቸው!
-ምክክሮቹ አሃ የሚያስብሉ ናቸው!
-ዓላማው ሰዎች የራሳቸውን ታላቅነትና ያላዩትን አቅማቸውን እንዲያዩት ማስቻል ነው!
ቤተሰብ ይሁኑ!
@mindmorning
Download Telegram
4ተኛው የወላጆች መድረክ ይህን ይመስላል ነበር። ሁላችሁንም እናመሰግናለን!
ወዳጆቻችሁ ይህን ሃሳብ መጋራት እንዲችሉ ይህንን link ሼር አድርጓቸው።
@mindmorning
🚩🚩አሁን ላይ ብዙ ግዜ ብዙ ልጆች ምክር አይሰሙም
ይላሉ ---ወላጆችና አሳዳጊዎች።

🚩🚩 በጣም የማልወደው ነገር ምክር ነው
ይላሉ ---ልጆች ሲጠየቁ።
ምክር ያለመስማቱም፤ ምክር የመጥላቱም ዋናው ምንጭ
👉እኛ ያልሆነውን
👉 እኛ ያልቻልነውን
👉 እኛ ያቃተንን
👉 በተግባር ሆነን ማሣየት የተሳነን
በቃላት፣ በንግግርና በምክር ልጆችን መምራት እናስብና ልጆች ከምክራችን ይልቅ ተግባራችንን ያዩብንና ምክራችን እንዳይሰራ ያደርገዋል።
ከዛም
ብመክረው፣ ብመክራት፣ ባስመክረው ባስመክራት አልሰማ አለ፣ አልሰማ አለች ብለን የኛን ድክመት የሌሎች እናደርገዋለን፨

እንዲህ እንደማለት ነው፦

🤔 ሲያነብ አይደለም በእጁ ላይ ጋዜጣ እንኳ ይዞ ልጆቹ አይተውት የማያውቅ ወላጅ ልጆቹን ስለ ንባብ ጥቅም ቢመክር እንደማለት ነው።
እናንተ ደግሞ ሌላ እይታችሁን ጨምሩበት...

ከንግግራችን ተግባራችን ይቅደም!!
💡💡 5ኛ የልጆች የክረምት የአዕምሮ ብልፅግናና የህይወት ብቃት ሥልጠና!!💡💡
🚩 ለሁሉም የእድሜ ክፍል የራሳቸው የሆነ የመማርያ መንገድ አለው!
በቆይታቸው ከሚዳሰሱ ርእሶች ውስጥ በጥቂቱ
ዝግጁነት
ለራስ የሚሰጥ ግምትና በራስ መተማመን
ሚናን መለየትና ሃላፊነት መውሰድ
የግል ጥንካሬና ድክመት
አማራጭ ሃሳብ የማምጣት ክህሎት
የመማርያ ዘዴ ተሰጥዖን ማቅና የጥናት ዘዴ
ሌሎችም ፥ ሌሎችም፥ ሌሎችም ርዕሶች ይነሳሉ፥ ይጠየቃሉ፥ ይጠይቃሉ ይወያያሉ

👉👉 እርስዎም ይወዱታል፤ ልጆችም ይወዱታል ፤ እኛም እንወደዋለን!!👈👈

አንድ ክፍል ጥቂት ልጆች ብቻ ስለምንይዝ ቀድመው ልጆችዎን ያስመዝግቡ!!🌟
✍️✍️ልጆች ሃሳባቸውን መግለፅ እንዳይለምዱ የሚያደርጉ የአስተዳደግ ዘይቤዎች✍️

ልጆች ሃሳባቸውን በነፃነት መግለፅ የሚለምዱት መጀመርያ በቤተሰብ ውስጥ ነው፡፡ ሆኖም ግን ልጆች ሃሳባቸውን ለመግለፅ እንዳይለምዱ ከሚያደርጓቸው ነገሮች ውስጥ ጥቂቶቹ

1. 👂👂👂ሁሌ የኑሮ ሩጫ ላይ ያለ ቤተሰብ፣ ለማረፍና ለመረጋጋት ጊዜ የሌለው፣ ከቤተሰቡ ጋር ጥሩ እና ከሁካታ ነፃ ግዜ ማሳለፍ አለመቻል አንዱ ምክንያት ነው፡፡
በዚህ ምክንያት ልጆች ሲናገሩ ማብራሪያቸውን ጊዜ ወስደን መስማት ስለማንችል ልጆች ቶሎ ቶሎ ነጥብ ነጥቡን ብቻ እንዲነግሩን እንፈልጋለን ከዛም የወላጅ ምላሽ እሺ ከሆነ እሺ እምቢም ከሆነ እምቢ ብቻ ይሆንና ከውይይት ይልቅ ትእዛዝ ተኮር የሆነ የህይወት ዘይቤ ይፈጠራል ማለት ነው፡፡
👉👉በዚህም ምክንያት ልጆች በተረጋጋ ሁኔታ ማስረዳት፣ ሃሳብንና እይታቸውን መግለፅ፣ የውስጣቸውን አውጥተው መናገር፣ ባመኑበትና በገባቸው ነገር ላይ ለመከራከር ወላጅ ለጆሮ የሚሆን ጊዜ ስለሌለው ሃሳባቸውን የማይገልፁና ትዕዛዝ ጠባቂ የሆኑ ልጆች እናፈራለን ማለት ነው፡፡

2. 👂👂👂ወላጅ በችኮላ፣ በስጋት፣ አንዳንዴም ሳያውቀው በልምድ ልጆች መናገር ሲጀምሩ ሃሳባቸውን ሳይጨርሱ ማቋረጥ እና ለእነርሱ እኛ ማብራራት ወይም ከእህት ወይም ከወንድም ማብራሪያ መጠየቅ ልምድ ሲሆንብን ልጆች የእኔ ሃሳብ ተሰሚ አይደለም፣ እኔ ትክክል አደለሁም፤ የኔ ሃሳብ አይጠቅምም የሚል አመለካከት ያዳብሩና ዝምታን ይመርጣሉ፡፡
👉👉በዚህም ምክንያት ልጆች የጉዳዩ አካል ከመሆን ይልቅ በሌሎች ሰዎች ሲሆን፤ ሲከወን፣ ሃሳብ ሲሰጥ ዝም ብለው ማየትን እየተቀበሉት ይሄዳሉ በግል ህይወታቸውም ላይ ሃሳብ ሰጪ ከመሆን ይልቅ “አይቀበሉኝም” በሚል አመለካከትን ሃሳባቸውን ከመግለፅ ተገድበው ሲቸገሩ እናያለን፡፡
3.👂👂👂 ልጆች መናገር ሲጀምሩ ንግግራቸውን ውድቅ እንደምናደርግ ሲያስቡና በተቃውሞ (በአሉታ መንገድ) መስማት ስንጀምር ሃሳባቸወን ከመግለፅ ይልቅ ዝም ብልስ ባልናገርስ በማለት ሃሳባቸውን ይውጡታል ግዴታ ሃሳባቸው መግለፅ ከለባቸውም ደግሞ በልቅሶ መግለፅ ይጀምራሉ ማለት ነው፡፡
💥💥 ስለሆነም ልጆች የራሳቸው ምልከታና ሃሳብ አላቸው ብሎ ካለማሰብና በተለያየ ምክንያት በቤተሰብ ውስጥ የውይይት፣ የክርክርና፣ የጥያቄ እድልን መከልከል የልጆችን እይታ ማጥፋትና ሃሳብን የመግለፅ ልምምዳቸውን ማሳጣት ስለሚሆን ወላጅ የኑሮ ዘይቤውን፣ የአስተዳዳግ ልምዱን፣ ድክመት እና ጥንካሬውን ኦዲት የሚያደርግበት ጊዜ፣ ስልጠናና ውይይት ያስፈልገዋል ፡፡

ወላጅነት በልዩነት
ማይንድ ሞርኒንግ
1