Minber News - ሚንበር ኸበር
8.23K subscribers
3.51K photos
2 videos
1 file
598 links
Download Telegram
#ምርኩዝ33፡ በሻሸመኔ እየተከናወነ የሚገኘው ምርኩዝ 33 የረመዳን ቀለማት 7 መድረክ በድምቀት እንደቀጠለ ነው። መድረኩ በቀረበበት ጃሎ ሆቴል ለተገኙ ዕድምተኞች የሚንበር መልቲ ሚዲያ ፕሮዳክሽን ዋና ሥራ አስጻሚ አቶ አዩብ አደብ የእንኳን ደህና መጣችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል። በመድረኩ ላይ ለመታደም ከአዲስ አበባ እንዲሁም ከሻሸመኔ አጎራባች ከተሞች በርካቶች ተጉዘዋል።

💡 ህልም... 🏃‍♂️‍➡️ ትጋት... 🏅ስኬት...
ምርኩዝ!

#ምርኩዝ
#ምርኩዝ33
#የረመዳንቀለማት7
11👍6
በሁለት የሕክምና ትምህርት ተቋማት ሥልጠናቸውን ያጠናቀቁ ሐምሳ ሐኪሞች ተመረቁ

በአዲስ አበባ ከሚገኙት ጥቁር አንበሳ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል እና ቅዱስ ጳውሎስ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል ትምህርታቸውን ሲከታተሉ የቆዩ ሐምሳ ዶክተሮች ምርቃት ሥነ ሥርዐት በዛሬው እለት ተከናውኗል። የምርቃት ሥነ ሥርዓቱን ያዘጋጁት በኢትዮጵያ ሙስሊም የጤና ባለሞያዎች ማኅበር አስተባባሪነት የሁለቱ ሆስፒታሎች ተማሪዎች ናቸው።

የምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ዛሬ የካቲት 8/2018 አዲስ አበባ በሚገኘው ስቴይ ኢዚ ፕላስ ሆቴል ተከናውኗል። ከተመራቂዎች መካከል 19 ገደማ ሴት ዶክተሮች እንደሚገኙበት ተገልጿል።

በምርቃት ሥነ ሥርዓቱ ላይ ከተመሠረተ ሁለት ዓመት ገደማ ያስቆጠረው የኢትዮጵያ ሙስሊም የጤና ባለሙያዎች ማሕበር እያከናወናቸው የሚገኙ ተግባራትን በተመለከተ ገለፃ ተደርጓል። በዚህም በርካታ ድጋፍ የሚሹ ወገኖችን በበጎ አድራጎት ስራዎች ተደራሽ አድርጓል ተብሏል። 13 ሺሕ 270 ሙስሊሞች በማሕበሩ አማካኝነት ድጋፍ እንዳገኙ ተገልጿል።

በቀጣይ ማሕበሩ በርካታ ሙስሊሞችን በሕክምና አገልግሎት እና ተዛማጅ የበጎ አድራጎት ሥራዎች መድረስ እንዲችል አባል በመሆን የጀመረውን ጥረት ማገዝ እንደሚገባ ጥሪ ቀርቧል። የኢትዮጵያ ሙስሊም የጤና ባለሞያዎች ማኅበር በአሁኑ ጊዜ ወደ 300 ገደማ አባላት አሉት።

የሙስሊም የጤና ባለሞያዎችን ቁጥር ለማሳደግ የሚደረገው ጥረት አካል ነው በተባለው በዚህ የምርቃት ሥነ ሥርዓት ላይ የኢትዮጵያ ሙስሊም የጤና ባለሞያዎች ማኅበር ተወካዮች፣ የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ተወካይን ጨምሮ የኢትዮጵያ ሙስሊም ወጣቶች ካውንስል ፕሬዝዳንት ኡስታዝ ሀይደር ከድር፣ የተመራቂ ቤተሰቦች እና ሌሎች እንግዶች ተገኝተዋል። (ሚንበር ቲቪ)
11
- ኢትዮጵያ ፍትሕ እና ታማኝነት ድንበር እንደሌላቸው ከ1 ሺሕ 400 ዓመት በፊት ለዓለም አሳይታለች
- በውሃ ሐብታችን ልማትን መሻታችን የማንንም ድርሻ አይቀንስም
- ዐባይ መለኮታዊ ሥጦታ መሆኑን እናምናለን - ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ከሦስት ቀናት በኋላ ለሚጀመረው የተከበረው ለረመዳን ወር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ዛሬ ሰኞ የየካቲት 9/2018 ባስተላለፉት በዐረቢኛ ቋንቋ የተዘጋጀ መልዕክት፤ ከረመዳን መልካም ምኞት ጎን ለጎን ኢትዮጵያ በዘመናት ውስጥ ከእስልምና ታሪክ ጋር ያላትን ቁርኝት አንስተዋል፡፡

ኢትዮጵያ የሐቅ ምድር መሆኗን ያጸኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ማንም የማይበደልባት የሐቅ ምድር መሆኗን መናገራቸውን አስታውሰዋል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ ፍትሕ እና ታማኝነት ሀገርም ሆነ ድንበርም እንደሌላቸው ከ1 ሺሕ 400 ዓመት በፍት ለዓለም አሳይታለች ብለዋል። ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ የመጀመርያውን አዛን ያሰማው የቢላል ኢብን ረባህ ሀገር መሆኗንም ጠቅሰዋል፡፡

ከዚህ ታሪካዊ፣ የሥነ ምግባር እና መንፈሣዊ ዳራ ጋር አያይዘው የኢትዮጵያውን የመልማት ጥያቄ አንስተዋል፡፡ ከልማት ጋር የጠቀሷቸው ኢትዮጵያ በዐባይ ወንዝ እና ወደብ ለማግኘት የምታደርገውን ጥረት ነው፡፡ ኢትዮጵያ ይህን ለማሳካት የምታደርገው ጥረት ምድሯ በታሪክ ከሚታወቅበት የሐቀኝነት ሚዛን የሚዛነፍ አቋም አለመያዟን ገልጸዋል፡፡ “የመልማት መብታችንን ለማስከበር የምናደርገው ጥረት የሌሎችን በሕይወት የመኖር መብት ለመንጠቅ እንዳልሆነ” ከ“ሐቀኝነት ምድር” ደጋግመን እናረጋግጣለን ብለዋል፡፡

“በውሃ ሐብታችን ልማትን ማሳደድ የማንንም ድርሻ አይቀንስም” ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ታላቁ ዐባይ የአምላክ ሥጦታ እንደሆነ እናምናለን፤ ወንዙ “አምላክ ከበረከቱ እንድንቋደስ ለሁላችንም የሰጠን ታላቅ መለኮታዊ ማዕድ ነው” ሲሉም አብራርተዋል፡፡ ከዚሁ ጋር አያይዘው ያነሱት ጉዳይ “ኢትዮጵያ ለጎረቤቶቿ ታማኝ ሆና እንደምትቀጥል ነው፡፡ “ግፍን [መፈጸም] አንሻም፤ የማንንም ድርሻ ለማሳነስ ፍላጎት የለንም” ብለዋል፡፡

ሌላኛው የወደብ ጉዳይም ቢሆን “የጎረቤት ሉዓላዊነትን የማይጥስ የአጋርነት ጥሪ” ነው። መነሻውም “የኢትዮጵያ ብልፅግና የመላው ቀጣናው ብልፅግና ነው” ከሚል እምነት የመነጨ ሰላማዊ ጥረት እንደሆነ አረጋግጠዋል፡፡ ለእውነተኛ ልማት የትብብር በሮችን መዝጋት ጠቃሚ አለመሆኑን አጽንኦት ሰጥተዋል፡፡ በረመዳን ወር ይህን ቃል ኪዳናችንን እናድሳለን ብለዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ!
13
#በረመዳን_ዋዜማ፡ የተናፋቂው ረመዳን ዋዜማ ሻዕባን ወር ዛሬ 28ኛ ቀን ላይ ደርሷል፡፡ በዚህ ሥሌት መሠረት ረመዳን ከሁለት ቀናት በኋላ የሚጀምር ይሆናል፡፡ በመላው ዓለም ሀገሮች “በረመዳን ዋዜማ ምን አዲስ ኸበር ተሰማ?” ብለን ስናጣራ ለዛሬ ሰኞ የካቲት 9/2018 ተከታዮቹን አግኝተናል፦
#ኢትዮጵያ፡ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ ለተከበረው ለረመዳን ወር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ ዛሬ ሰኞ የየካቲት 9/2018 ባስተላለፉት መልዕክት፤ ከረመዳን መልካም ምኞት ጎን ለጎን ኢትዮጵያ በዘመናት ውስጥ ከእስልምና ታሪክ ጋር ያላትን ቁርኝት አንስተዋል፡፡ ኢትዮጵያ የሐቅ ምድር መሆኗን ያጸኑት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ፤ ታላቁ ነቢይ ሙሐመድ (ሰ.ዐ.ወ) ማንም የማይበደልባት የሐቅ ምድር መሆኗን መናገራቸውን አስታውሰዋል፡፡ በዚህም ኢትዮጵያ ፍትሕ እና ታማኝነት ሀገርም ሆነ ድንበርም እንደሌላቸው ከ1 ሺሕ 400 ዓመት በፍት ለዓለም አሳይታለች ብለዋል። ኢትዮጵያ በእስልምና ታሪክ ውስጥ የመጀመርያውን አዛን ያሰማው የቢላል ኢብን ረባህ ሀገር መሆኗንም ጠቅሰዋል፡፡ ከዚህ ታሪካዊ፣ የሥነ ምግባር እና መንፈሣዊ ዳራ ጋር አያይዘው የኢትዮጵያውን የመልማት ጥያቄ አንስተዋል፡፡ ለእውነተኛ ልማት የትብብር በሮችን መዝጋት ጠቃሚ አለመሆኑን አጽንኦት የሰጡት ዐቢይ፤ የረመዳን ወር ይህን ቃል ኪዳናችንን የምናድስበት ነው ሲሉ ገልጸዋል፡፡

#ኢትዮጵያ፡ በርካታ ሻጭ እና ሸማቾችን ያገናኛል የተባለ የረመዳን ኤግዚቢሽንና ባዛር በአዲስ አበባ ኤግዚቢሽን ማዕከል ተከፍቷል። በኒምቤክ ኢቨንትስ አዘጋጅነት የተከፈተው ኤግዚቢሽን፤ የቤት እቃዎች፣ ምግብ፣ አልባሳት እና ሌሎችም ምርቶችን የያዙ ነጋዴዎች ተሳታፊ እንደሆኑበት ተገልጿል፡፡ በዚህ ኤግዚቢሽን ላይ ለሸማቾች ልዩ ሽልማት መዘጋጀቱም በአስተባባሪዎች ተነግሯል። ጉብኚዎች በተዘጋጀው ልዮ የእጣ ሽልማት የዑምራ ጉዞ ትኬቶችና የኤሌክትሪክ ባጃጅ ይበረከትላቸዋል ተብሏል።

#ግብጽ፡ የግብጽ መንግሥት የረመዳን ወር መድረሱን ተከትሎ በዜጎች ላይ የሚፈጠረውን የኢኮኖሚ ጫና ለማቃለል የመንግሥት ሠራተኞች ደመወዝ አስቀድሞ እንዲከፈል ውሳኔ አሳልፏል፡፡ ውሳኔው የመጣው የግብፅ ፕሬዝዳንት ዓብዱልፈታህ አል ሲሲ የረመዳን ወር ከመግባቱ በፊት ዝቅተኛ ገቢ ያላቸውን ዜጎች ለመደገፍ ያለመ ሰፊ የማኅበራዊ ጥበቃ ማዕቀፍ ተግባራዊ እንዲሆን ትእዛዝ ካስተላለፉ በኋላ ነው። በጠቅላይ ሚኒስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ እና በፋይናንስ ሚኒስትር አሕመድ ኪጁክ ይፋ የተደረገው ድጋፉ፤ በአጠቃላይ 40 ነጥብ 3 ቢሊዮን የግብፅ ፓውንድ በጀት ተመድቦለታል። ጠቅላይ ሚኒስትሩ የየካቲት እና የመጋቢት ወራት ደመወዝ መደበኛውን የክፍያ ቀን ሳይጠብቅ ቀድሞ ለሠራተኞች እንዲደርስ እንደሚደረግ ማረጋገጫ ሰጥተዋል፡፡ ውሳኔው በዚህ ሣምንት በሚጀምረው ረመዳን ወር እንዲሁም ለመጪው የዒድ አል ፊጥር በዐል የሚታየውን ከፍተኛ የፍጆታ ፍላጎት እና የኑሮ ውድነት ታሳቢ በማድረግ ዜጎች መሠረታዊ ፍላጎቶቻቸውን እንዲያሟሉ ለማገዝ ያለመ ነው ሲል ዳይሊ ኒውስ ኢጂፕት ዘግቧል።

#እንግሊዝ፡ ሁለት የኢፕስዊች መስጂዶች በረመዳን ሁሉንም ማኅበረሰብ የሚያሳትፍ የማዕድ ማጋራት መርሐ ግብር እንደሚያዘጋጁ አስታውቀዋል፡፡ እነዚህ የከተማው መስጂዶች በቦንድ አውራ ጎዳና የሚገኘው ኢፕስዊች መስጂድ እና ሻህጃላል መስጂድ ናቸው፡፡ በኢፍጣር ሰዐት የሚያቀርቡት ምግብ ለሁሉም ሰው በነጻ እንደሚታደል አስተባባሪዎች ገልጸዋል፡፡ የኢፕስዊች መስጂ ለቢቢሲ ሲናገሩ፤ “የአካባቢው የረመዳን ድባብ አስደናቂ ነው፤ ከሁሉም የኑሮ ደረጃዎች የመጡ ሰዎች አሉን፤ ከሌሎች ቤተ እምነቶችም እንግዶች አሉን፣ ማዕዱ ለሁሉም ሰው ክፍት ነው” ብለዋል። (ሚንበር ቲቪ)

እርስዎ የት ነው የሚኖሩት? በአካባቢዎ የተለየ የረመዳን ዝግጅት አለ? እንግዲያውስ መረጃውን በቴሌግራም @minbertv1 ያድርሱን
5
የረመዳንን ወር ስንቀበል የተቸገሩትን በመርዳት እና አንድነታችን በማጠናከር ሊሆን ይገባል - ጠቅላይ ምክር ቤቱ

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ከሁለት ቀን በኋላ የሚጀመረውን የዘንድሮውን 1447 ዓ.ሂ የረመዳን ወር አስመልክቶ ለመላው ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል።

የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክቱን ያስተላለፉት የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ፕሬዝዳንት ሸይኽ ሐጅ ኢብራሂም ቱፋ፣ የረመዳን ወር ማኅበራዊ ሕይወታችን በማስተካከልና በማሳመር በኩል የደግነት፣ የርህራሄ እና የመረዳዳት በመሆኑ ለመልካም ሥራዎች ሁሉ የተመቻቸ ዕድል የሚፈጥር መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

የዘንድሮውን የረመዳን ወር ስንቀበል ከወንጀል በመራቅ፣ አንድነትን በማጠናከር፣ ተፈናቅለው በተለያዩ ችግሮች ውስጥ የሚገኙ ወገኖችን በመርዳት ሊሆን እንደሚገባ ጠቅላይ ምክር ቤቱ ጥሪ አቅርበዋል፡፡

በተመሳሳይ በኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ምክትል ፕሬዝዳንት እና የአስተዳደር ጉዳዮችና ተቋማዊ ልሕቀት ኃላፊ ኡስታዝ ተምኪን ዓብዱላሂ የፌዴራል ጠቅላይ ሸሪዓ ፍርድ ቤት የ1447ኛውን ታላቁን የረመዳን ወር የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፈዋል፡፡ በወሩ ዘካና ሰደቃ በማውጣት የተቸገሩ ወገኖችን መደገፍና መርዳት ትኩረት የምንሰጠው ጉዳይ ሊሆን ይገባል ብለዋል። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ!
8
#በረመዳን_ዋዜማ፡ የእንግሊዝ ከፍተኛው ሊግ አስተዳዳሪ ፕሪሚየር ሊግ እና ኢንግሊሽ ፉትቦል ሊግ በረመዳን ወቅት በቀደመው ጊዜ ሲያደርጉ እንደነበረው ለኢፍጣር የአፍታ ረፍት እንደሚኖር አሳውቀዋል። የኢፍጣር ረፍቱን ለመውሰድ የክለብ አምበሎች ከአርቢትሮች ጋር በመሆን ሙስሊም ተጫዋቾች የሚያፈጥሩበትን አጋጣሚ ይመርጣሉ። ጨዋታው የሚቋረጠው ግጥሚያዎች እየተከናወነ ባለበት ሊኖር በሚችል ረፍት ነው። በዚህም ጨዋታው ፍሰቱን እንደጠበቀ የመልስ ምት፣ የቅጣት ምት አልያም የእጅ ውርወራ ላይ በሚሆንበት ጊዜ እንዲያርፍ ይደረጋል። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #MinberTV
12👍3
#በረመዳን_ዋዜማ፡ በመዲና በሚገኘው መስጂድ አን ነበዊ ውስጥ በረመዳን ኢዕቲካፍ ለሚገቡ ምዕመናን ልዩ ድንኳን ተዘጋጅቷል። በድንኳኑ የሚቆዩ ሁሉም ምዕመናን በመስጂዱ አስተዳደር መመዝገብ ይኖርባቸዋል። የሳዑዲ ዜግነት ያልያዙ ምዕመናን ከስፖንሰሮቻቸው ፍቃድ ያስፈልጋቸዋል። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #MinberTV
15🥰4
#በረመዳን_ዋዜማ፡ የተናፋቂው ረመዳን ዋዜማ ሻዕባን ወር ዛሬ 29ኛ ቀን ላይ ደርሷል፡፡ በመላው ዓለም ሀገሮች “በረመዳን ዋዜማ ምን አዲስ ኸበር ተሰማ?” ብለን ስናጣራ ለዛሬ ማክሰኞ የካቲት 10/2018 ተከታዮቹን አግኝተናል፦
በዘንድሮ ዓመት ረመዳን እንደተለመደው የተለያዩ ሀገሮች እንደ መልክዐ ምድራዊ አቀማመጣቸው ረዥም እና አጭር የጾም ሰዐታት ያሳልፋሉ፡፡ በሰሜናዊው ንፍቀ ክበብ ከሚኖሩት ሕዝቦች መካከል ወደ 90 በመቶ ገደማ የጾም ሰዓታቸው አጭር የሚባል ነው፡፡ ይህ የመቀነስ ሒደት እስከ 2023 ድረስ ይቆያል፡፡ በንፍቀ ክበቡ ውስጥ ወቅቱ ክረምት በመሆኑ በጣም አጭሩ የጾም ርዝማኔ ይኖራቸዋል፡፡ በመጀመሪያው ቀን ርዝማኔው ከ12 እስከ 13 ሰዓታት ያህል ይቆያል፡፡ በምድር መቀነት (ኢኩዌተር) በተለይም በመቀነቱ ደቡባዊ ክፍል የሚኖሩ ምዕመናን ባለፈው ዓመት ከነበረው የጾም ሰዐት የሚረዝም ሰዐት ያሳልፋሉ፡፡ በዘንድሮ ዐመት በቺሊ፣ በኒውዚላንድና በደቡብ አፍሪካ ያሉ የደቡባዊ ሀገሮች ነዋሪዎች በመጀመሪያው ቀን ከ14 እስከ 15 ሰዓታት የሚደርስ ረዥም ጾም ይኖራቸዋል። ይሁን እንጂ የጾም ሰዓቶች ርዝማኔ በወሩ እየቀነሰ ይሄዳል፡፡ በወሩ የእኛዋ አዲስ አበባ ነዋሪዎች በቀዳሚው ቀን 13 ሰዐት ከ2 ደቂቃ ይጾማሉ፡፡ በመጀመሪያው ቀን ሱሑር ንጋት 11 ሰዐት ከ33 ደቂቃ ይጠናቀቃል፡፡ የኢፍጣር ሰዐት ደግሞ 12 ከ35 ደቂቃ ይሆናል፡፡ ቀናት እየጨመሩ በሄዱ ቁጥር የከተማው ነዋሪዎች 13 ሰዐት ከ15 ደቂቃ በጾም ያሳልፋሉ፡፡ የሱሑር ሰዐት እየቀነሰ በመጨረሻው ቀን 11 ሰዐት ከ21 ደቂቃ ይሆናል፡፡

#ሞሮኮ፡ የሞሮኮው ንጉሥ ሙሐመድ ስድስተኛ ለረመዳን ወር በመላ ሀገሪቱ አዲስ የተገነቡና የታደሱ 157 መስጂዶች ክፍት እንዲሆኑ መመርያ አስተላልፈዋል። እንደ ሞሮኮ ወርልድ ኒውስ ዘገባ ከሆነ፤ 95 የሚሆኑት መስጊዶች አዲስ የተገነቡ ናቸው፡፡ 42 ገደማ ደግሞ እድሳት ተድርጎላቸዋል። መስጂዶቹ የተገነቡትና የታደሱት በንጉሡ ልዩ ክትትልና ድጋፍ ነው። ይህም በረመዳን ወቅት የሚኖረውን ከፍተኛ የምእመናን ቁጥር ለማስተናገድ ታስቦ የተከናወነ መሆኑ ተገልጿል። የሞሮኮ መንግሥት ለመስጂዶች ግንባታና እድሳት ከ64 ነጥብ 7 ሚሊዮን ዶላር በላይ ወጪ ማድረጉን ገልጿል።

#ፍልስጤም፡ በጋዛ የደረሰውን ጥፋት ተከትሎ የአካባቢው ባለሞያዎች በእጅ የተሠሩ የረመዳን ጌጣ ጌጦችን ከፍርስራሾች ላይ በማንሳትና ጥቅም ላይ የዋሉ ቆርቆሮዎችን በመጠቀም በማኅበረሰባቸው ውስጥ የደስታ ስሜት ለመፍጠር ሙከራ እያደረጉ መሆኑ ተነግሯል፡፡ በከተማዋ መስጂዶች የወደሙ ሲሆን፤ የጦርነቱ ተፅዕኖም በየቦታው ይገኛል፡፡ የጋዛ ነዋሪዎችም ያገኙትን አነስተኛ ቁሳቁስ በመጠቀም የተባረከው ወር ከመድረሱ በፊት መጠለያዎቻቸውን እያስጌጡ እንደሚገኙ ዘገባዎች አመልክተዋል፡፡ ወላጆች ይህን የሚያደርጉት በግጭት እና መፈናቀል ውስጥ ብቻ ለሚያልፉ ልጆቻቸው መደበኛ ሕይወትን እና ደስታን ለመፍጠር መሆኑን ተናግረዋል። እነዚህ ወላጆች እንዲህ ዓይነቱን ጥረት ሲያደርጉ ልጆቻቸው በአደጋው ውስጥ ቢሆን ተስፋ እንዲኖራቸው ለማስቻል በጣም አስፈላጊ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)

እርስዎ የት ነው የሚኖሩት? በአካባቢዎ የተለየ የረመዳን ዝግጅት አለ? እንግዲያውስ መረጃውን በቴሌግራም @minbertv1 ያድርሱን
10
የ1447ኛውን የረመዳን ወር ፆም በመተሳሰብ ማሳለፍ ይገባል - የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት

የአዲስ አበባ እስልምና ጉዳዮች ከፍተኛ ምክር ቤት የ1447ኛውን የረመዳን ወር ፆም አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት አስተላልፏል። የከፍተኛ ምክር ቤቱ ምክትል ፕሬዚዳንት ሸይኽ ሙሐመድ ሸሪፍ የረመዳን ወር ፆምን “በመተሳሰብ፣ ምህረት በመጠየቅ፣ ዘካን በመስጠትና ለተቸገሩ ወገኖች በመድረስ” መሆን እንዳለበት ያሳሰቡት ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 10/2018 በተሰጠው መግለጫ ነው።

መግለጫው የረመዳን ወር ከወንጀል ርቀን የምንፆምበት እንዲሁም እጆቻችን ለልገሳ የሚዘረጉበት በመሆኑ የተቸገሩትን በማገዝ መፆም እንዳለበት አሳስቧል። የመስጂድ ኮሚቴዎች ከማኅበረሰብ፣ ወጣቶችና ከባለሀብቶች ጋር በመሆን በኢኮኖሚ አቅም ደካሞች በተረጋጋ ሁኔታ እንዲፆሙ ማድረግ ይገባል ተብሏል። ኢማሞችና ዱዐትች በኹጥባዎቻቸው የእስልምና አስተምህሮትን ማህበረሰብ በሚረዳው መልኩ እንዲያቀርቡ ጥሪ ቀርቧል፡፡ (ሚንበር ቲቪ)
7
የቱርክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን አዲስ አበባ ገቡ

የቱርክ ፕሬዝዳንት ረጀብ ጠይብ ኤርዶጋን አዲስ አበባ የገቡት ዛሬ ማክሰኞ የካቲት 10/2018 ነው። ፕሬዝዳንቱ አዲስ አበባ ሲደርሱ ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ አቀባበል አድርገውላቸዋል።

‎ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሠፈሩት ጽሑፍ፤ ለፕሬዝዳንቱ ወደ ኢትዮጵያ እንኳን በደህና መጡ ብለዋል። ይፋዊ የሥራ የጉብኝት ልውውጣችን በቱርክዬ እና በኢትዮጵያ መካከል ያለውን ጥልቅ የአጋርነት ጥንካሬ የሚያንጸባርቅ ሲሉም አክለዋል።

‎ከአንካራ እስከ አዲስ አበባ፤ በሁለቱ ጥንታዊ ሀገራት መካከል ያለውን ትብብር ይበልጥ የሚያጠናክሩ እና ዘላቂ ትስስርን የሚያረጋግጡ ውጤታማ ውይይቶች እንዲኖሩን እመኛለሁ ሲሉ አስፍረዋል። (ሚንበር ቲቪ)

★ ★ ★
Ethio Sat | 11545 | H | 45000
#ሚንበር_ቲቪ #ሁለንተናዊ_ከፍታ! #MinberTV
19👍7