Mohammed Seid - Miftah
3.21K subscribers
152 photos
5 videos
10 files
122 links
​🛠 Digital Skills | AI | Innovation
📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች።
👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡
https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/
Download Telegram
📱 ሶሻል ሚዲያ ፍላጎታችንን አውቆ ይዘቶችን የሚያቀርብልን እንዴት ነው? (ከጀርባ ያለው የ-AI ምስጢር!)

ቲክቶክ፣ ዩቲዩብ ወይም ፌስቡክ ላይ ስንገባ የምንወዳቸው ወይም የእኛን ፍላጎት የተከተሉ ቪዲዮዎች ብቻ ለምን ተከታትለው እንደሚመጡልን አስበንበት እናውቃለን? ይሄ በአጋጣሚ የሚሆን ሳይሆን የምክር ሥርዓት (Recommendation System) የሚባለው የ-AI እና የማሽን መማር (Machine Learning) ክፍል የሚሰራው አስደናቂ ስራ ነው።

የሶሻል ሚዲያ አልጎሪዝም (Algorithm) ማለት የትኞቹ ፖስቶች፣ በምን ቅደም ተከተል እና ለማን መታየት እንዳለባቸው የሚወስን የሂሳብ ቀመር (Mathematical Rules) ነው። ሲስተሙ እኛ መተግበሪያውን በከፈትን በሰከንድ ስብርባሪ ውስጥ የሚከተሉትን 3 ዋና ዋና ደረጃዎች ያከናውናል፦

🧠 አልጎሪዝሙ የሚሰራበት ባለ 3-ደረጃ ሂደት
1️⃣ መሰብሰብ እና ማጣራት (Retrieval): ሲስተሙ በመድረኩ ላይ ካሉ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ቪዲዮዎች ውስጥ የማይጠቅሙትን ያስወግዳል። እኛ ባለንበት ቦታ፣ በምንጠቀመው ቋንቋ፣ በስልክ አይነት እና በዕድሜ ላይ በመመስረት ፖስቶቹን ወደ ጥቂት ሺዎች ያጠባቸዋል።

2️⃣ ደረጃ መስጠት (Scoring): የማሽን መማር ሞዴሉ የቀሩትን ፖስቶች በመገምገም ለእነሱ የሚሰጠውን ምላሽ ይገምታል። ቪዲዮውን እስከመጨረሻው እናየዋለን? ላይክ፣ ኮሜንት ወይስ ሼር እናደርጋለን? የሚለውን በማስላት ለእያንዳንዱ ፖስት ነጥብ ይሰጣል።

3️⃣ ማቀላቀል እና ማቀራረብ (Diversification): ይህ ደረጃ አሰልቺነትን ይከላከላል። በአንድ አይነት ርዕስ ወይም በአንድ ሰው የተሰሩ ቪዲዮዎችን በተከታታይ እንዳናይ በማድረግ፣ የተለያዩ አዳዲስ ርዕሶችን እና አዝማሚያዎችን (Trends) ቀላቅሎ ያቀርብልናል።

🔍 ፍላጎታችንን ይበልጥ የሚለይባቸው 2 ስልቶች
👥 የሰዎች ስብስብ ትስስር (Collaborative Filtering): ሲስተሙ እኛን ከእኛ ጋር ተመሳሳይ የመመልከት ልምድ ካላቸው ሌሎች ተጠቃሚዎች ጋር ያቧድናል። ለምሳሌ «ሰው ሀ» እና «ሰው ለ» ሁለቱም የእግር ኳስ ቪዲዮ የሚወዱ ቢሆኑ፤ «ሰው ሀ» በድንገት አንድ የቴክኖሎጂ ቪዲዮ አይቶ ቢጨርስ፣ አልጎሪዝሙ ያንን የቴክኖሎጂ ቪዲዮ ለ«ሰው ለ» ወዲያውኑ ይመክራል።

🎬 የይዘት መግለጫ ትንተና (Content-Based Filtering): ትኩረቱ በራሱ በፖስቱ ይዘት ላይ ነው። አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የቪዲዮውን ምስሎች ያነባል፣ የትርጉም ጽሑፉን (Captions) ያጠናል፣ እንዲሁም ሙዚቃውን ይለያል። ከዚያም ቀደም ሲል ከተከታተልነው ይዘት ጋር የሚመሳሰሉ አዳዲስ ፖስቶችን ያቀርብልናል።

📈 3. ለፊዳችን (Feed) መወሰን ትልቁን ሚና የሚጫወቱ ምልክቶች
⏱️ የማየት ቆይታ (Watch Time) [ከፍተኛው ክብደት]: በአንድ ቪዲዮ ላይ ምን ያህል ሰከንድ ወይም ደቂቃ እንደቆየን የሚጠቁመው ይሄው ምልክት ከአልጎሪዝም ሁሉ በላይ ትልቁን ኃይል ይይዛል። አንድን ቪዲዮ ደጋግመን ካየነው ወይም እስከመጨረሻው ከተከታተልነው፣ አልጎሪዝሙ ለዚያ ዘርፍ ቅድሚያ ይሰጠዋል።

💬 ንቁ ተሳትፎ (Active Engagement): ጽሑፍ መጻፍ (Comment) ወይም ለጓደኛ ማጋራት (Share) ከፍተኛ ፍላጎት እንዳለን ያሳያል። ተራ «ላይክ» (Like) ግን በጣም አነስተኛ ጥረት የሚጠይቅ በመሆኑ ለአልጎሪዝሙ ዝቅተኛ ግምት አለው።

🚫 አሉታዊ ምላሽ (Negative Feedback): ቪዲዮዎችን በፍጥነት ማሳለፍ (Fast scrolling) ወይም «Not Interested» የሚለውን መጫን ይዘቶቹ ከገጻችን ላይ ወዲያውኑ እንዲጠፉ ያደርጋል።

ከወደዳችሁት ሼር አድርጉት⤴️
ተጨማሪ ሀሳብ ወይም ጥያቄ ኮሜንት ላይ አስቀምጡልኝ?
መልካም ምሽት Mohammed Seid
#TechInnovation #ArtificialIntelligence #SocialMediaAlgorithm #MachineLearning
❤3👍1
#TechNews
Google ያለ ኮዲንግ Android አፕሊኬሽን መስራት የሚያስችል አዲስ የ-AI ቴክኖሎጂ ይፋ አደረገ
ጎግል ምንም ዓይነት የኮዲንግ እውቀት ሳይኖር፣ በፅሁፍ ትዕዛዝ (Prompt) ብቻ ሙሉ አንድሮይድ አፕሊኬሽኖችን መፍጠር የሚያስችል አዲስ የ-No Code AI አሰራር በይፋ ማስተዋወቁን አስታወቀ።
​ይህ በGoogle AI Studio አማካኝነት የቀረበው አዲስ ቴክኖሎጂ "Vibe Coding" የሚል ስያሜ የተሰጠው ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች የሚፈልጉትን የአፕሊኬሽን ሃሳብ በፅሁፍ በመግለጽ ብቻ በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ሙሉ የኮትሊን (Kotlin) አፕ ማዘጋጀት እንዲችሉ ያደርጋል።
​አዲሱ አሰራር የተሰራውን አፕሊኬሽን በብሮውዘር ላይ በቀጥታ ለመሞከር የሚያስችል ኤሙሌተር (Embedded Emulator) ያካተተ ሲሆን፣ ተጠቃሚዎች የሰሩትን አፕ በ-USB አማካኝነት በቀጥታ ወደ ስልካቸው መጫን ወይም ወደ Google Play ማስተላለፍ እንደሚችሉ ተገልጿል። ይህ ቴክኖሎጂ የአፕሊኬሽን እድገት ፈጠራን ለሁሉም ሰው ተደራሽ ለማድረግ ትልቅ እመርታ መሆኑ ተነግሮለታል።

አፕሊኬሽን በሌሎቹ LLMs እንዴት እናውርድ የሚለው ጥያቄ ይፈታል ማለት ነው! ምክንያቱም የሰራነውን ፕሮጀክት ወደ ተጠቃሚ ለማድረስ የግድ በትንሹም ቢሆን የኮዲንግ እውቀት ግድ ነበር። በዚህ ደግሞ ሁሉንም መጨረስ እንደምንችል ነው የተነገረው።

ስለ አጠቃቀሙ በቀጣይ ቀናት መረጃ የማደርሳቸሁ ይሆናል።

#ShareThisPost
🦾 ቴክኖሎጂውን ተረድተን እንምራው እንጂ እሱ እንዲመራን አንፍቀድ!
🏫 በ AI ዘመን የፕሮግራሚንግ መሰረታዊ እውቀቶች (Foundations) ፋይዳ ምንድነው? መማርስ አስፈላጊ ይሆን?

በአሁኑ ጊዜ የሰው ሰራሽ አስተዋፅኦ (AI) እድገት ፈጣን መሆን ብዙዎችን እያነጋገረ ይገኛል። በተለይም እንደ ChatGPT እና GitHub Copilot ያሉ መሳሪያዎች ውስብስብ ኮዶችን በሰከንዶች ውስጥ መጻፍ መጀመራቸው፣ "በዚህ ዘመን የፕሮግራሚንግ መሰረታዊ እውቀቶችን መማር እና መጻሕፍትን ማንበብ ምን አስፈለገው?" የሚል ጥያቄ በብዙዎች ዘንድ እንዲነሳ አድርጓል። ይሁን እንጂ የዘርፉ ከፍተኛ ምሁራን እና የኮምፒውተር ሳይንስ ተመራማሪዎች የሚነግሩን እውነታ ከዚህ ፍጹም የተለየ ነው። የ AI መምጣት የሰው ልጅን አስፈላጊነት አላጠፋውም፤ ይልቁንም የመማርን አስፈላጊነት ከመቼውም ጊዜ በላይ አግዝፎታል።

የዘርፉ ሊቃውንት እንደሚናገሩት፣ AI የሚያመነጨው ኮድ ሁልጊዜ ፍጹም እና ከስህተት የጸዳ አይደለም ብዙ ጊዜ ትክክል የሚመስል ግን በተግባር የማይሰራ ወይም ከፍተኛ የደህንነት ጉድለት ያለበት ኮድ (Code Hallucination) ሊያቀርብ ይችላል ፣ ይህንን ስህተት ለይቶ ለማረም ፣ ኮዱን ለመፈተሽ እና አስተማማኝነቱን ለማረጋገጥ ደግሞ ጠንካራ መሰረታዊ እውቀት ያለው የሰው ኃይል የግድ ያስፈልጋል። መሰረቱን ያልተማረ ሰው AI የሰጠውን ስህተት መለየት ስለማይችል የቴክኖሎጂው ምርኮኛ ለመሆን ይገደዳል።

በተጨማሪም የሶፍትዌር መሃንዲስነት (Software Engineering) ዋና ተግባር ኮድ መጻፍ ብቻ ሳይሆን ውስብስብ የሆኑ ችግሮችን መተንተን (problem solving) እና ትልልቅ ሲስተሞችን መቀየስ (System Architecture) ነው ፣ AI በአሁኑ ጊዜ የሚተካው መስመራዊ የኮድ አጻጻፍ ስልቶችን (Syntax) ብቻ ነው። አንድን AI ውጤታማ በሆነ መንገድ ለማዘዝ (Prompting) እንኳን ትዕዛዝ ሰጪው ሰው የኮምፒውተር ሳይንስ ህጎችን፣ የአልጎሪዝም አስተሳሰብን እና የዳታ ስትራክቸር መርሆዎችን ጠንቅቆ ማወቅ ይኖርበታል።

AIን በጥራት ለመምራት መጀመሪያ እራስን በዕውቀት ማነጽ ያስፈልጋል።
በጥቅሉ ሲታይ፣ የ AI መምጣት እኛን ከድካም እና ከተደጋጋሚ እና አሰልቺ ስራ ያድነናል እንጂ ከማሰብ እና ከፈጠራ አያግደንም። የዘርፉ መሪዎች እንደሚሉት "AI ፕሮግራመሮችን ሙሉ በሙሉ አያጠፋም፤ ነገር ግን AIን በአግባቡ ተጠቅመው ስራቸውን የሚያቀላጥፉ ባለሙያዎች፣ የቴክኖሎጂውን ፍልስፍና ሳይረዱ በባህላዊ መንገድ ብቻ የሚጓዙትን መተካታቸው አይቀሬ ነው"። ስለዚህ አሁንም መሰረታዊ መጻሕፍትን ማንበብ፣ ፅንሰ-ሀሳቦችን መረዳት እና ጠንካራ መሰረት መጣል የነገው የስኬታችን ብቸኛ ዋስትና ነው። ቴክኖሎጂውን ተረድተን እንምራው እንጂ እሱ እንዲመራን አንፍቀድ!

መልካም ቀን 😍

የእናንተን ሀሳብ ኮሜንት ላይ ሼር አድርጉን ፣ ምን ትላላቸሁ AI Code ከፃፈ መማር አስፈላጊ ነው? ፣ ሀሳቤን በመረጃ የመደገፍ እና የመንቀፍ ሙሉ መብት አላችሁ!
#TechPerspectives #ProgrammingFoundations #SoftwareEngineering #ContinuousLearning #EthiopiaInTech
👏3❤1👍1
“ቫይብ ኮዲንግ” (Vibe Coding)🔥💻
​ዛሬ ዛሬ አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ሁሉንም ነገር ያቃልላል እየተባለ ይነገራል። ነገር ግን AI ከምንም በላይ ጎልቶ የወጣው እሱን በራሱን በሰራው ነገር ላይ ነው—ያ ደግሞ ኮዲንግ (Coding) ነው። በአንድ ወቅት ከፍተኛ የቴክኒክ ክህሎት እና የዓመታት ትምህርት የሚጠይቀው የኮምፒውተር ፕሮግራም መጻፍ፣ ዛሬ ላይ ተራ የሰውኛ ቋንቋን በመጠቀም ብቻ ማንኛውም ሰው ሊደርስበት የሚችል ቀላል ነገር ሆኗል። ይህ አዲስ ክስተት በቴክኖሎጂው ዓለም “ቫይብ ኮዲንግ” (Vibe Coding) የሚል ስም ተሰጥቶታል።
​
ቫይብ ኮዲንግ ምንድን ነው?
ይህ ቃል ለመጀመሪያ ጊዜ ይፋ የሆነው የOpenAI መስራች በነበረው አንድሬ ካርፓቲ (Andre Karpathy) ሲሆን፣ ትርጉሙም የኮዲንግ ህጎችን እና ሲንታክስን (Syntax) ሳያውቁ፣ ልክ ከሰው ጋር እንደምናወራው በተራ እንግሊዝኛ ለAI በመንገር ብቻ ሙሉ የሶፍትዌር መተግበሪያዎችን የመስራት ሂደት ነው። በአሁኑ ሰዓት በርካታ የፈጠራ ሃሳብ ያላቸው ነገር ግን የኮዲንግ እውቀት የሌላቸው ሰዎች (Non-technical creators) የራሳቸውን የሞባይል አፕሊኬሽኖች እየሰሩ ወደ App Store እና Play Store እያወጡ ይገኛሉ። የንግድ ድርጅቶችም ያለምንም የሶፍትዌር ቡድን ድጋፍ በAI አማካኝነት የራሳቸውን ሲስተም በጥቂት ቀናት ውስጥ እየገነቡ ነው።
​
ታዲያ የሶፍትዌር መሃንዲሶች (Software Engineers) እጣ ፈንታ ምን ሊሆን ነው?
ብዙዎች AI መሃንዲሶችን ሙሉ በሙሉ ይተካቸዋል ብለው ቢሰጉም፣ የዘርፉ ምሁራን እና የGoogle Cloud AI መሪዎች ግን የሚሉት ሌላ ነው። AI የሶፍትዌር መሃንዲሶችን አያጠፋቸውም፤ ይልቁንም ሚናቸውን ከኮድ ጸሃፊነት (Coder) ወደ ውጤት መሪነት (Manager) ይቀይረዋል። በአሁኑ ጊዜ በጎግል ውስጥ ያሉ ዋና ዋና መሃንዲሶች ስራቸውን የሚያሳልጡት የ AI ወኪሎችን (Virtual Agents) በማዘዝ እና በማስተዳደር ነው። የአንድ መሃንዲስ ዋና ዋጋ ኮድ መተየብ ሳይሆን የሲስተሙን ጥራት መጠበቅ፣ ደህንነቱን ማረጋገጥ እና በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ተጠቃሚዎች የሚሆን ጠንካራ መዋቅር (Architecture) መገንባት ላይ ይሆናል።

ስለ Vibe Coding ምን ሀሳብ አላችሁ? እድል ወይስ ስጋት ? Vibe Coding በመጠቀም ምን ችግር ፈታችሁ ?

ሀሳባችሁን ሼር አድርጉን 👇
https://t.me/ethio_codersofficial
👍3❤1
Artificial Intelligence: A Modern Approach (AIMA) - የአለም አቀፍ እውቅና

ለቴክኖሎጂ አፍቃሪዎች እና ለኮምፒውተር ሳይንስ ተማሪዎች፣ በዘርፉ ቁንጮ የሆነው መጽሐፍ "Artificial Intelligence: A Modern Approach" (AIMA) መሆኑ ይታወቃል። ይህ መጽሐፍ በአለም ዙሪያ በሚገኙ 1,556 ዩኒቨርሲቲዎች በመማሪያ መጽሐፍነት ጥቅም ላይ ይውላል።➡️Artificial Intelligence: A Modern Approach, 4th Global ed.
👍3❤2
መጽሀፉን አውርዶ ለማንበብ ይህን ተጠቀሙ፡ books/Artificial-Intelligence-A-Modern-Approach-4th.pdf at main · sxcong/books
👍2🔥1
አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና የሥራ ገበያው የወደፊት ዕጣ ፈንታ
በአሁኑ ወቅት አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ መነጋገሪያ በመሆን በሥራ ገበያው ላይ ትልቅ ስጋት እና ተስፋን ደቅኗል። በቢቢሲ (BBC) አስተናጋጅነት በተደረገው ውይይት መሠረት፣ ይህ ቴክኖሎጂ በሰው ልጅ የሥራ ሕይወት ላይ የሚያሳድረው ተጽዕኖ የሚከተሉትን ቁልፍ ነጥቦች ተነስተዋል።

የሥራ አጥነት ስጋት እና የምጣኔ ሀብት ተጽዕኖ
አሁን ባለው የቴክኖሎጂ ሽግግር፣ ብዙ ሠራተኞች የሥራ ቦታቸውን ሊያጡ እንደሚችሉ ከፍተኛ ስጋት አድሮባቸዋል። ጥናቶች እንደሚያመለክቱት፣ ከ10 ሠራተኞች መካከል 7ቱ (70%) AI ሥራቸውን ሊቀማቸው እንደሚችል ይሰጋሉ። በሚቀጥሉት 2 እና 3 ዓመታት ውስጥ በአንዳንድ ዘርፎች የሥራ አጥነት መጠን እስከ 30% ሊደርስ እንደሚችል የተገመተ ሲሆን፣ ይህ ደግሞ የሰዎችን የመግዛት አቅም በማዳከም ለጠቅላላው አገራዊ ምጣኔ ሀብት (GDP) አደገኛ ሊሆን ይችላል።

በወጣቶች እና በጀማሪዎች ላይ ያለው ከፍተኛ ፈተና
ከዚህ ለውጥ ጋር ተያይዞ በተለይ አዲስ ተማሪዎች እና በሥራው ዓለም አዲስ የገቡ (entry-level) ወጣቶች ከፍተኛ ፈተና እየገጠማቸው ነው። የቻት ጂፒቲ (ChatGPT) መውጣትን ተከትሎ ለጀማሪዎች የሚወጡ የሥራ ማስታወቂያዎች በ16% ቀንሰዋል። የኮምፒውተር ሳይንስ ምሩቃን እንኳ ለበርካታ የሥራ ቦታዎች ቢያመለክቱም አጥጋቢ ምላሽ ማግኘት አለመቻላቸው የቴክኖሎጂው ተጽዕኖ በጀማሪዎች ላይ ምን ያህል የከፋ እንደሆነ የሚያሳይ ማሳያ ነው።

የሥራ መጥፋት ወይስ የሥራ እና አሰራር ለውጥ?
ምንም እንኳን ስጋቱ ትልቅ ቢሆንም፣ ብዙዎች AI ሥራን ሙሉ በሙሉ ከማጥፋት ይልቅ በሥራ ሂደት ላይ ለውጥ እንደሚያመጣ ይከራከራሉ። ከዚህ ቀደም የስርጭት ሰንጠረዦች (Spreadsheets) መምጣት የሂሳብ ባለሙያዎችን ሥራ አላጠፉም፣ ይልቁንም የሥራውን ጥራት አሻሽለዋል። በተመሳሳይ፣ AI አሰልቺ የሆኑ የዕለት ተዕለት ሥራዎችን በመተካት፣ ሠራተኞች በፈጠራ እና በውሳኔ አሰጣጥ ላይ እንዲያተኩሩ ዕድል ሊፈጥር ይችላል።

የሰው ልጅ የፈጠራ እና የስሜታዊ ብልጫ
ቴክኖሎጂው እየተስፋፋ ሲሄድ፣ እንደ ሶፍትዌር ልማት ያሉ ሙያዎች በAI ታግዘው ቀላል እየሆኑ ይመጣሉ። ሆኖም በዚህ ጊዜ፣ የሰው ልጅ ልዩ ችሎታዎች የሆኑት ስሜታዊ ግንኙነት (Human Connection) እና የፈጠራ ክህሎት የሚጠይቁ ሥራዎች ዋጋቸው እጅግ ይጨምራል። ማሽን ሊሰራው የማይችለውን የሰው ልጅ የውስጥ ጥበብ እና የሰዎችን ስሜት መረዳት፣ ለወደፊቱ የሥራ ገበያ ዋና መለኪያዎች ይሆናሉ።

መፍትሄው፡ ክህሎትን ማዘመን እና የመንግሥት ድጋፍ
በውይይቱ ላይ እንደተነሳው ለዚህ ፈተና መፍትሄው ሠራተኞች ራሳቸውን ከAI ጋር ማላመድ እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎችን የመጠቀም ክህሎት ማዳበር ነው። በሌላ በኩል መንግሥታት የሕዝብ አገልግሎቶችን በAI ከማዘመን ባለፈ፣ ለወጣቶች አዳዲስና ተፈላጊ ክህሎቶችን የሚያስተምሩበትን ሥርዓት መዘርጋት ይኖርባቸዋል። ቴክኖሎጂውን እንደ ስጋት ከመመልከት ይልቅ እንደ አጋዥ መሣሪያ መጠቀም ለወደፊቱ የሥራ ስኬት ቁልፍ ነው።

እኔም የማምነው እና ሁሌም የምላቹሁ ለውጦች ይኖራሉበፍጥነት አሰራሮች ይቀየራሉ ፤ እናንተም እያያችሁት ነው ስለዚህ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ክህሎቶችን መላመድ ቅንጦት ሳይሆን ግዴታ ነው።
እንፍጠን! እንማር ፣ እንተግብር ፣ እናሳይ

እናንተስ ምን ታስባላችሁ? AI ለሥራችሁ ስጋት ነው ወይስ አጋዥ? ሀሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን! 👇
በ BBC የቀረበውን ሙሉ ውይይቱን ለማየት 👇
https://youtu.be/fpHOCyFesxI?si=csaPITVT7lSX9xc3

#AI #FutureOfWork #Technology #Employment #Innovation #BBCDiscussion
🔥1
ጀሚኒ (Gemini) አዲስ ታሪክ ላይ ነው! 🚀✨

​ከጉግል ስነ-ምህዳር (Google Ecosystem) ጋር የምንኖር ሰዎች Geminiን ብቻውን መጠቀም ግማሽ አቅሙን እንደመተው ነው። የጉግል መተግበሪያዎቻችንን (Extensions) ከ Gemini ጋር ስናገናኛቸው የስራ ፍጥነታችንን ወደ ሌላ ደረጃ ያሳድጉታል!

​ልክ በምስሉ ላይ እንደምታዩት Workspace፣ Photos፣ YouTube እና Searchን አንዴ ካገናኘን በኋላ ሁሉንም መተግበሪያዎች በተናጠል መክፈት አበቃ! በአንድ ማዕከል (በ Gemini) ሆነን ሁሉንም በብልሃት ማዘዝ እንችላለን።

​🛠️ በስልካችሁ ላይ ለመጫን እነዚህን 3 ቀላል ደረጃዎች ተከተሉ፦
​1️⃣ ደረጃ 1፦ በ Gemini መተግበሪያ ውስጥ የፕሮፋይል ፎቶአችሁን በመጫን "Personal Intelligence" የሚለውን ምረጡ።
2️⃣ ደረጃ 2፦ በሚመጣው ገጽ ላይ "Connected apps" የሚለውን ክፍል መጫን።
3️⃣ ደረጃ 3፦ "Google Workspace" የሚለውን ማብሪያ (Toggle) ያብሩት። ፍቃድ ሲጠይቃችሁ Connect በሉት።

​(💡 ፈጣን መንገድ፦ ይህንን ሁሉ ከመከተል ይልቅ እዚያው ቻት ውስጥ በቀጥታ @Gmail ወይም @Google Drive ብላችሁ በመጻፍ በቀላሉ ማገናኘት ትችላላችሁ!)
ዛሬ ሰኔ 1 ቀን 2026 እ.ኤ.አ በታይዋን በተጀመረው የ #Computex 2026 / GTC Taipei ኤግዚቢሽን ላይ የ NVIDIA ዋና ስራ አስፈፃሚ ጄንሰን ሁዋንግ (Jensen Huang) የግል ኮምፒውተሮችን እና የሮቦቲክስ ዘርፍን የሚቀይሩ በርካታ ታላላቅ ቴክኖሎጂዎችን አስተዋውቀዋል።

ከእነዚህ ውስጥ ትኩረቴን የሳበው እና ዋነኛው፦

RTX Spark Superchip

Nvidia ከ Microsoft እና MediaTek ጋር በመተባበር ለግል ኮምፒውተሮች (PCs) የሚሆን አዲስ RTX Spark Superchip የተባለ ፕሮሰሰር አስተዋውቋል። ይህ ቺፕ በ "Windows on Arm" ላፕቶፖች እና ዴስክቶፖች ላይ እጅግ ከፍተኛ የ AI አቅም እና የጌሚንግ ብቃት (High-end Gaming) ለማስገኘት የተሰራ ነው። ቺፑ 20 የ Arm CPU ኮሮች፣ 6144 CUDA ኮሮች ያሉት Blackwell GPU እና 128GB RAM ይዟል።

ዋጋቸው የሚቀመስ ከሆነ ለመግዛት ዝግጁ ነኝ! ከዚያ በኋላ የራሳችንን Al ማበልፀግ እንጀምራለን! ሚጢጢ ኢንፍራ ስትራክቸር ልመና እናቆማለን ! በቃ ይመቻችሁ የቴክኖሎጂ ልዩነታችን ግን በጣም ሰፋ ........... እንደርስባችሁ ይሆን?

ለማንኛውም ጧት ተከታተሉት ያልኳችሁ ለዚህ ነበር ሌሎቹንም ሼር አድርጋቸኋለሁ ! ባለፈውም "A New era of PC" ማለታቸው አይዘነጋም !
👍3
የጥቂት ቢሊየነሮች ወይስ የመላው የሰው ልጅ የጋራ ሀብት? ?
የጥቂት ቢሊየነሮች ወይስ የመላው የሰው ልጅ የጋራ ሀብት? 🤖

​ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ዛሬ ላይ የደረሰበት አስደናቂ ከፍታ የትናንት ምናብ የዛሬ እውነታ መሆኑን አሳይቶናል። ነገር ግን ከዚህ ታላቅ የቴክኖሎጂ ምጥቀት በስተጀርባ ማንም ሊሸሸገው የማይችለው አንድ መራራ እውነት አለ፦ AI የተገነባው በሰው ልጅ የጋራ እውቀት ላይ ነው ፣ አዎ! ለዘመናት በተደከመባቸው እውቀቶች።
​
ታዋቂው አሜሪካዊ ሴናተር በርኒ ሳንደርስ በቅርቡ ባስተላለፉት መልዕክት (በምስሉ ላይ እንደምትመለከቱት) ይህንን እውነት ቁልጭ አድርገው አውጥተውታል። "AI የተገነባው በሰው ልጅ የጋራ እውቀት ላይ ነው፤ ስለዚህ የሚያመነጨው እጅግ ግዙፍ ሀብት መላውን የሰው ልጅ መጥቀም አለበት እንጂ እንደነ ሳም አልትማንና ኢሎን ማስክ ያሉ ጥቂት የኤአይ ኦሊጋርኮችን (ባለሀብቶችን) ብቻ ማበልጸግ የለበትም" ሲሉ ይከራከራሉ። ይህንን ፍትሃዊነት ለማረጋገጥም ህዝቡ ቀጥተኛ የባለቤትነት ድርሻ እንዲኖረው የሚያደርግ "American AI Sovereign Wealth Fund Act" የተባለ ታሪካዊ የህግ ረቂቅ እንደሚያስተዋውቁ በ X ገፃቸው አስታውቀዋል።
​
ይህ ሃሳብ ዛሬ ላይ ሁላችንም ልናስብበት የሚገባ ትልቅ የፍትሃዊነት ጥያቄ ነው። በአሁኑ ወቅት የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች የሰውን ልጅ የጋራ እውቀት ያለክፍያና ያለ ግልጽ ፍቃድ እየወሰዱ (Scraping) ሞዴሎቻቸውን ያሰለጥኑበታል። ይህ አሰራር ህጋዊ ይሁን አይሁን ገና በህግ አውጪዎችና በፍርድ ቤቶች ዘንድ ግራጫ ቀጠና ቢሆንም፣ የሞራልና የፍትህ ጥያቄው ግን ግልጽ ነው፦ መረጃውንና እውቀቱን የሰጠው መላው የዓለም ህዝብ ሆኖ ሳለ፣ ትርፉና ስልጣኑ ለምን በጥቂት ግለሰቦች እጅ ብቻ ይከማቻል?
​
ኤአይ በሄደበት ፍጥነት የሰዎችን ስራ እየተካ ከመጣ፣ ተራው ህዝብ የኢኮኖሚ ተጎጂ እየሆነ፣ የቴክኖሎጂ ባለቤቶቹ ግን በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እያጋበሱ የሀብት ልዩነቱን የሰማይና የምድር ያህል ሊያሰፉት ይችላሉ። የሴናተሩ መከራከሪያ ደግሞ ይህንን አደጋ አስቀድሞ ለመከላከል ነው፤ "መረጃው የህዝብ ከሆነ፣ ከትርፉ ላይም ህዝቡ ቀጥተኛ ድርሻ (Dividend) ሊኖረው ይገባል!" የሚል ፅኑ አቋም።
​
እናንተስ በዚህ ጉዳይ ላይ ምን ታስባላችሁ?
የኤአይ ባለቤትነትና የሚያስገኘው ጥቅም ለሁሉም ህዝብ በእኩልነት የሚከፋፈልበት የህግ ማዕቀፍ መፈጠሩን ትደግፋላችሁ? ወይስ የቴክኖሎጂ ፈጠራን ያቀጭጫል የሚል ስጋት አለባችሁ?
​ሃሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን! 👇
"ይህ ሀሳብ በአንድ ወቅት ትልቅ አለም አቀፍ አጀንዳ የሚሆንበት ቀን ይመጣል ኢንሻአላህ! " ፅሁፋም ለታሪክ ይቀመጥ!
​#AI #ArtificialIntelligence #TechEquity
❤2👍1
🚀 የAI ውድድሩ ቀጥሏል ማይክሮሶፍት 7 አዳዲስ የ ‘MAI’ ሞዴሎች ይፋ አድርጓል! 💥

​የ AI ዓለም ወደ አዲስ ምዕራፍ ተሻግሯል! የማይክሮሶፍት AI ዋና ስራ አስፈፃሚ ሙስጠፋ ሱሌይማን፣ ኩባንያው ከሌሎች ሳይቀዳ (Zero distillation) ሙሉ በሙሉ በማይክሮሶፍት አቅም የገነባቸውን 7 አዳዲስ የ MAI ሞዴሎችን አስተዋውቋል። እነዚህ ሞዴሎች ሰዎችን ለመተካት ሳይሆን፣ በሰው ልጅ ቁጥጥር ስር ሆነው ሰዎችን ለማገዝ የተሰሩ ናቸው (Humanist Superintelligence) በማለት ተናግረዋል። የኤአይ ሞዴሎች ሲሰለጥኑ መረጃ ያለ ፈቃድ ይጠቀማሉ ለሚለው ሀሳብ ምላሽ ሰጥተዋል ! "በራሳችን አቅም እና መረጃ ነው የገነባነው" በማለት አስፋርዋል።

​📌 ሙስጠፋ በማይክሮሶፍት ድረ-ገፅ እና በ X ገፃቸው ስለ ሞዴሎቹ ይህን አስፍረዋል፡-
​
🧠 MAI-Thinking-1 (የማሰብ ብቃት)፦ በ Blind side-by-side evaluations ውድድር ታዋቂውን Sonnet 4.6 እኩል ተፎካክሮ የሰዎችን ምርጫ ማግኘት የቻለ ግዙፍ የአመክንዮ ሞዴል ነው።

​💻 MAI-Code-1-Flash (ለኮደሮች)፦ 5 ቢሊዮን ፓራሜትር ብቻ ያለው ፣ እጅግ ርካሽ እና ለ GitHub Copilot ልዩ ማሻሻያ የተደረገለት ፈጣን የኮዲንግ ረዳት ነው።
​
🎨 MAI-Image-2.5 & Flash፦ በምስል ፈጠራ እና ማስተካከል (Editing) ረገድ የ Nano Banana Proን የ Arena ነጥብ በልጦ አንደኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።

​🎙️ MAI Transcribe & Voice፦ ከተወዳዳሪዎቹ በ 5 እጥፍ ፈጣን የድምጽ ግልባጭ (በ43 ቋንቋዎች) እና የሰውን ድምጽ በአጭር ናሙና የመምሰል አስደናቂ አቅም ያለው ነው!
​
💼 Microsoft Frontier Tuning፦ ተቋማት የራሳቸውን የውስጥ መረጃ ብቻ በመጠቀም የራሳቸውን Custom AI Agent እንዲሰሩ ይፈቅዳል። ለምሳሌ ለ Excel የተገነባው ሞዴል ከ GPT-5.4 ጋር እኩል እየሰራ እስከ 10 እጥፍ ቀልጣፋ ሆኗል!

ሙሉውን ለማንበብ 👇
https://microsoft.ai/news/building-a-hillclimbing-machine-launching-seven-new-mai-models/
❤2👍1
የዳታ ግላዊነት (Data Privacy)፦ ትርጉም ፣ ተግዳሮቶች እና የሕግ ማዕቀፎች
https://www.linkedin.com/pulse/%E1%8B%A8%E1%8B%B3%E1%89%B3-%E1%8C%8D%E1%88%8B%E1%8B%8A%E1%8A%90%E1%89%B5-data-privacy-%E1%89%B5%E1%88%AD%E1%8C%89%E1%88%9D-%E1%89%B0%E1%8C%8D%E1%8B%B3%E1%88%AE%E1%89%B6%E1%89%BD-%E1%8A%A5%E1%8A%93-%E1%8B%A8%E1%88%95%E1%8C%8D-%E1%88%9B%E1%8B%95%E1%89%80%E1%8D%8E%E1%89%BD-mohammed-seid-endris-bkhfe?utm_source=share&utm_medium=member_android&utm_campaign=share_via
በ21ኛው ክፍለ ዘመን ቴክኖሎጂ የሰው ልጅን የእለት ተእለት ሕይወት ሙሉ በሙሉ ቀይሮታል። በምናከናውናቸው ዲጂታል እንቅስቃሴዎች ሁሉ—ከማኅበራዊ ሚዲያ ግንኙነቶች እስከ ባንክ አሠራር፣ ከሕክምና መረጃዎች እስከ ኦንላይን ግብይት—ሰፊ የመረጃ አሻራዎችን (Digital Footprints) እንተዋለን።

ሙሉ ጽሁፉን በ LinkedIn አካውንቴ ላይ ገብታችሁ እንድታነቡት ግብዣዬ ነው! ጠቃሚ ሀሳቦችን ታገኛላችሁ ብዬ አስባለሁ👇
❤2
በዲጂታል ማርኬቲንግ ዓለም ስኬታማ ለመሆን ማወቅ ያለብን 7 መሠረታዊ ነገሮች!
🚀 በዲጂታል ማርኬቲንግ ዓለም ስኬታማ ለመሆን ማወቅ ያለብን 7 መሠረታዊ ነገሮች! 🚀

በአሁኑ ጊዜ የንግድ ድርጅትን ማሳደግም ሆነ በዲጂታል ክህሎት መበልጸግ ያለ ዲጂታል ማርኬቲንግ እውቀት የማይታሰብ ነው! በምስሉ ላይ እንደሚታየው ፣ በዘርፉ ውጤታማ ለመሆን ማስተር ልናደርጋቸው የሚገቡ 7 ወሳኝና መሰረታዊ ነጥቦች፦

1️⃣ SEO & SEM (የፍለጋ ሞተር ማርኬቲንግ)፦

SEO (Search Engine Optimization)፦ ድረ-ገጻችን በGoogle ፍለጋዎች ላይ ያለ ምንም ክፍያ (Organically) መጀመሪያ መስመር ላይ እንዲወጣ የማድረግ ጥበብ ነው። ይህንን ለማሳካት ቁልፍ ቃላትን (Keywords) በአግባቡ መጠቀም እና ጥራት ያለው ይዘት መፍጠር ይጠይቃል።

SEM (Search Engine Marketing)፦ በክፍያ ማስታወቂያዎች (Paid Ads) አማካኝነት ምርት ወይም አገልግሎታችንን በፍለጋ ውጤቶች ላይ በግንባር ቀደምትነት ማሳየት ነው። ፈጣን ውጤት እና ደንበኛ ለማግኘት ተመራጭ ዘዴ ነው።

2️⃣ Content & Social Media Marketing፦

Content Marketing፦ "ይዘት ንጉሥ ነው (Content is King)" እንደሚባለው፣ ለታላሚ (Target Customers) ደንበኞቻችን እውነተኛ እሴት የሚጨምሩ ጽሑፎችን፣ ቪዲዮዎችን ወይም መረጃዎችን ማዘጋጀት ነው። ይህ ደንበኞች በእኛ ላይ እምነት እንዲጥሉ ያደርጋል።

Social Media Marketing፦ እንደ Facebook, TikTok እና LinkedIn ያሉ ማኅበራዊ ሚዲያዎችን በመጠቀም ከደንበኞች ጋር ቀጥተኛ ግንኙነት መፍጠር ነው። ብራንዳችንን በሰዎች አእምሮ ውስጥ ለመቅረጽ እና የራሳችንን ማኅበረሰብ (Community) ለመገንባት ወሳኝ ነው።

3️⃣ PPC (Pay-Per-Click)፦

ይህ ስትራቴጂ የታለሙ(ምርቶቻችንን እንዲጠቀሙ የምንፈልጋቸው) ደንበኞችን በቀጥታ ወደ ድረ-ገጻችን ለማምጣት የምንጠቀምበት የኦንላይን ማስታወቂያ ዘዴ ነው። ልዩነቱ ማስታወቂያው ስለታየ ብቻ ሳይሆን፣ ፍላጎት ኖሮት ማስታወቂያውን ጠቅ (Click) አድርጎ ወደ እኛ የመጣ ሰው ሲኖር ብቻ ክፍያ የምንፈጽምበት በመሆኑ የበጀት ብክነትን ይከላከላል።

4️⃣ Affiliate Marketing፦

ሰፊ የሽያጭ መረብ ለመዘርጋት የሚረዳ የትብብር ስትራቴጂ ነው። ሌሎች ተጽዕኖ ፈጣሪዎች (Influencers) ወይም ድርጅቶች የእኛን ምርት ለተከታዮቻቸው አስተዋውቀው ሽያጭ ሲያመጡ፣ ከሽያጩ ላይ የተወሰነ መቶኛ ኮሚሽን የምንከፍልበት አዋጭ የንግድ መንገድ ነው።

5️⃣ Email Marketing፦

ብዙዎች በዚህ ሰአት ውጤቱ የቀነሰ ቢመስላቸውም፣ አሁንም ድረስ ከፍተኛ የትርፍ ምጣኔ (Highest ROI) ያለው ዘዴ ነው። አዳዲስ ምርቶችን ለማስተዋወቅ፣ ቅናሾችን ለማሳወቅ እና ከነባር ደንበኞቻችን ጋር የረጅም ጊዜ የንግድ ትስስር ለመፍጠር በቀጥታ ወደ ኢሜይላቸው መልዕክት መላክን ያካትታል።

6️⃣ Inbound Marketing፦

ደንበኞችን በማስታወቂያ ከመውረር እና ከማስጨነቅ ይልቅ፣ እነሱ የሚፈልጉትን መፍትሔ እና ጠቃሚ ይዘት በማቅረብ በራሳቸው ፍላጎት ተማርከው ወደ እኛ እንዲመጡ የማድረግ ዘመናዊ ስልት ነው። ደንበኛው ራሱ ፈልጎ ስለሚመጣ የሽያጭ ዕድሉ በጣም ከፍተኛ ነው።

7️⃣ Online PR (ዲጂታል ሕዝብ ግንኙነት)፦

በዲጂታል ዓለም ውስጥ ስምና ዝናን የመገንባት ሥራ ነው። በተለያዩ ታዋቂ ድረ-ገጾች፣ ዲጂታል ጋዜጦች፣ ብሎጎች እና ሪቪውዎች ላይ ስለ እኛ ብራንድ በጎ ገጽታ የሚፈጥሩ ጽሑፎች እንዲወጡ በማድረግ በገበያው ውስጥ ያለንን ተቀባይነት ማረጋገጥ ነው።

💡 "Master these fundamentals to succeed in digital marketing"

እነዚህን ሰባት መሠረታዊ ስልቶች በሚገባ አጣምሮ መተግበር መቻል በኦንላይን ገበያ ውስጥ ሁልጊዜ መሪ እና ቀዳሚ ያደርገናል።

እነዚህን ሁሉ በነጻ የት እንማር ብላችሁ መጠየቃችሁ አይቀርም ኮሜንት መስጫው ላይ ሁሉት ተመራጭ ኮርሶችን 👇

🔸.Digital Marketing Certification Course: Get Certified in Digital Marketing

🔸. Google Fundamentals of Digital Marketing

ዛሬውኑ ይጀምሩ!😍

#DigitalMarketing
👍3
🚀 የ Generative AI ነፃ ኮርስ ለጀማሪዎች
ማይክሮሶፍት (Microsoft) ያዘጋጀውና በከፍተኛ ደረጃ የተሻሻለው "Generative AI for Beginners" ኮርስ አሁን በ 21 ክፍሎች (Lessons) ቀርቧል። ይህ ኮርስ የ AI መተግበሪያዎችን ከባዶ እንዴት መገንባት እንደምንችል በተግባር የሚያስተምር ነፃ ስልጠና ነው።

📚 ኮርሱ ምን ምን ይካተታል?
እያንዳንዱ ክፍል በቀላሉ እንድትሩዱት ተደርጎ የተዘጋጀ ሲሆን የሚከተሉትን ይዟል፡

🎥 አጫጭር ቪዲዮዎች፡ ስለ ርዕሱ ማብራሪያ የሚሰጡ።

📝 የፅሁፍ ትምህርቶች፡ በዝርዝር የተፃፉ ማብራሪያዎች።

💻 የኮዲንግ ምሳሌዎች፡ በ Python እና TypeScript የተዘጋጁ ተግባራዊ ልምምዶች።

🔄 ሁለት የትምህርት መንገዶች፡ ቲዎሪ የሚያስረዱ ("Learn") እና በተግባር ኮድ የሚያሰሩ ("Build") ክፍሎች።

🛠️ ለመጀመር ምን ያስፈልጋል?
መሰረታዊ እውቀት፡ የ Python ወይም TypeScript መሰረታዊ እውቀት (ለጀማሪዎች የሚሆኑ ኮርሶችም አብረው ተካተዋል)።

የ GitHub አካውንት፡ የኮርሱን ፋይሎች ወስደው ለመለማመድ።

ኮዱን ለመሞከር Azure OpenAI፣ OpenAI API ወይም አዲሱን GitHub Model Catalog መጠቀም ትችላላችሁ።

🤝 አብሮ የመማር እና የድጋፍ መድረኮች
የ Discord ማህበረሰብ፡ በ Azure AI Foundry Discord ላይ በመቀላቀል ከሌሎች ተማሪዎች ጋር መገናኘትና እገዛ ማግኘት ይቻላል።

ለስራ ፈጣሪዎች (Startups)፡ የራስዎን የ AI ድርጅት ማቋቋም ከፈለጉ፣ የ Azure Credits ድጋፍ የሚያገኙበት የ Microsoft for Startups ዕድል አለ።

💡 እንዴት መጀመር ይቻላል?
ከስር ባለው ሊንክ ወደ GitHub ድህረ-ገጽ በመሄድ አካውንት በመክፈት እና መመሪያውን በማንበብ ወዲያውኑ መጀመር ትችላላችሁ። በቀላሉ መልሰው ለማግኘት ማከማቻውን (Repository) Star (🌟) ማድረግ አትርሱ! 👇
https://github.com/microsoft/generative-ai-for-beginners/tree/main?WT.mc_id=academic-105485-koreyst
ተጨማሪ ጥያቄ ካላችሁ ኮሜንት ላይ አሰቀምጡልኝ!
NeverNever Trust, Always Verify ✅
❤2
አንዱ በ Whatsapp ሊያጠምደኝ የላከልኝ መልዕክት ነው ... ጉድ እኮ ነው 😂 የእኔ principle "Never Trust, Always Verify " ✅ እንደሆነ ኦያውቅም መሰል🤔

በ"Telebirr" ስም እንደዚሁም በሽልማት መልክ እየተሰራጨ ስላለው አደገኛ የማጭበርበሪያ (Scam) ሊንክ!

​በተለያዩ የሶሻል ሚዲያ ግሩፖች እና በውስጥ መስመር (Inbox) "የቴሌብር አንቨርሰሪ ስጦታ" (Telebirr Anniversary Offer) በሚል እየተዘዋወረ ያለውን ሊንክ አስተውላችኋል?
​እባካችሁ በፍጹም እንዳትከፍቱት! ❌ ሊንኩ ሙሉ በሙሉ የውሸት እና የሰዎችን መረጃ ለመስረቅ የተዘጋጀ የፊሺንግ (#Phishing) ማጭበርበሪያ ነው።

​🛑 ሊንኩን ስንከፍተው ምን ይፈጠራል? (የደህንነት አደጋው)

1️⃣​የግል መረጃ ስርቆት (Data Theft): ሊንኩን ስትነኩ "እድለኛ ነዎት" በማለት ስም፣ ስልክ ቁጥር እና ሌሎች ሚስጥራዊ መረጃዎችን እንድታስገቡ ይጠይቃል። ይህ መረጃችሁ በቀጥታ ወደ አጭበርባሪዎቹ እጅ ይገባል።

2️⃣​አካውንታችሁን ለሌላ አደጋ ማጋለጥ: የማረጋገጫ (Verification) ሂደት በሚል ስም ስልክ ቁጥራችሁን ወይም የቴሌብር መለያችሁን ለመስረቅ የሚሞክሩ አደገኛ ድረ-ገጾች ላይ ይወስዳችኋል።

3️⃣​እናንተን ተጠቅሞ ሌሎችን ማጥመድ: "ስጦታውን ለማግኘት ሊንኩን ለ15 ወይም ለ20 የዋትስአፕ/ቴሌግራም ወዳጆችዎ ወይም ግሩፖች ያጋሩ" ይላል። በዚህ ጊዜ ሳታውቁት የሳይበር ወንጀለኞቹን ተባባሪ በመሆን የቅርብ ጓደኞቻችሁን ለአደጋ ታጋልጣላችሁ።

4️⃣​የውሸት አስተያየቶች (Fake Comments): ከስር "እኔ ደርሶኛል"፣ "እውነት ነው" የሚሉ የሰዎች አስተያየቶች ታያላችሁ። እነዚህ ሁሉ ሰዎችን ለማታለል በሲስተም የተሰሩ የውሸት (Bot) አካውንቶች ናቸው።

​💡 ራሳችንን እንዴት እንጠብቅ? (ቁልፍ ጥንቃቄዎች)
​ሊንኩን (URL) አስተውሉ: ማንኛውም የቴሌብር ወይም የኢትዮ ቴሌኮም ትክክለኛ መረጃ የሚለጠፈው በይፋዊ ድረ-ገጻቸው (telebirr.et ወይም ethiotelecom.et) ላይ ብቻ ነው። tinyurl... ወይም ሌላ የተለየ ስም ያላቸው ሊንኮች በሙሉ ማጭበርበሪያ ናቸው።

​"በነጻ ስጦታ" አትታለሉ: በሶሻል ሚዲያ ላይ "ለማጋራት" ወይም "ፎርም ለመሙላት" በሚሰጥ ነጻ ስጦታ በፍጹም አትመኑ።
​አታሰራጩ፣ አታጋሩ: ሊንኩ ሲላከላችሁ ለሌላ ሰው ባለማጋራት ሰንሰለቱን ቁረጡት።

​በይፋዊ ገጾች ብቻ አረጋግጡ: ማንኛውንም አይነት ስጦታ ወይም ማስተዋወቂያ ስትመለከቱ የግድ አስፈላጊ ከሆነ በቀጥታ ወደ ቴሌብር ይፋዊ የፌስቡክ ገጽ (የሰማያዊ ምልክት ወይም Verified Checkmark ያለበት) በመግባት እውነተኝነቱን አረጋግጡ።

ይህን ጉዳይ ትላንትም ነግርያችኋለሁ Telegram Whatsapp ሌሎች ሶሻል ሚድያ ቻናሎች የማጥመጃ መንገዶች እየሆኑ ነው። በየጊዜው ይከሰታል በየጊዜው ሼር እናደርጋለን ፤ አሁንም ግን የሚሸወዱት በርካቶች ናቸው።

​ሳይበር ደህንነት በጋራ የሚገነባ ነው! ይህ መረጃ ለብዙዎች እንዲደርስ እና ወገኖቻችን ከአጭበርባሪዎች እንዲጠበቁ Share እናድርግው። 👇
​#CyberSecurity
❤5👍1