Mohammed Seid - Miftah
3.11K subscribers
148 photos
5 videos
10 files
119 links
​🛠 Digital Skills | AI | Innovation
📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች።
👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡
https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/
Download Telegram
OpenAI ሌላ ታሪክ ላይ ነው! 🤔 DevDay 2026
OpenAI ዛሬ በሳን ፍራንሲስኮ ባካሄደው ዓመታዊው DevDay 2026 ጉባኤ ላይ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ቴክኖሎጂን ከቀላል ጥያቄና መልስ ረዳትነት አልፎ፣ ራሱን ችሎ 24/7 በጀርባ ክፍት ሆኖ የሚሰራ ዲጂታል ሰራተኛ (Autonomous Agent) ወደ መሆን የሚያሸጋግሩ በርካታ አዳዲስ ምርቶችን ይፋ አድርጓል።

ከእነዚህም መካከል ዋነኛው በGPT-6 Astra ሞዴል የሚመራውና Dot የተሰኘው ሁልጊዜ ክፍት የሆነ የኤጀንት ቴክኖሎጂ ነው። ይህ ኤጀንት የራሱ የሆነ የክላውድ ኮምፒዩተር እና ኢንተርኔት ማሰሻ (Browser) ያለው በመሆኑ፣ የእርስዎ ስልክ ወይም ኮምፒዩተር ቢዘጋም እንኳን በጀርባ ሆኖ ስራውን ይቀጥላል። በተጨማሪም ከ4,000 በላይ ከሚሆኑ እንደ Gmail፣ GitHub እና Slack ካሉ መተግበሪያዎች ጋር በመገናኘት ኢሜይል መላክን፣ ምርት መግዛትን እና ኮድ መጻፍን የመሳሰሉ ውስብስብ ተግባራትን በራሱ ማከናወን ይችላል።

ከዚህ በተጨማሪ ኩባንያው ለሶፍትዌር ልማት እና ለንግድ ድርጅቶች የሚሆኑ በርካታ የቴክኖሎጂ ማሻሻያዎችን አስተዋውቋል። ከእነዚህም መካከል ከGPT-6 Astra ጋር የተቀራረበ ከፍተኛ አቅም ያለው ነገር ግን የትራንዛክሽን ወጪው በ80% አነስተኛ የሆነውና ለኮዲንግ የታለመው GPT-6.1 Sol ሞዴል ይገኝበታል። በሌላ በኩል ቡድኖች በጋራ ከኤጀንቶች ጋር የሚሰሩበት ChatGPT Space፣ በሰከንድ እስከ 300 ቶከን ምላሽ መስጠት የሚያስችለው Ultrafast Tier፣ እንዲሁም ኤጀንቶች ውስብስብ ውሳኔዎችን በራሳቸው እንዲወስዱ የሚያስችለው Decisions API በጉባኤው ላይ ይፋ ከተደረጉት ዋና ዋና ምርቶች መካከል ይጠቀሳሉ።

ተጨማሪ በ DevDay 2026 ምን አዲስ ነገሮች ተዋወቁ የሚለውን ለመከታተል፡ https://openai.com/index/devday-2026
❤2🔥1
ጭራሽ! 😂 ይቻላል እንዴ ¿
😁4
Super Intelligence
ያለ ምንም የኮዲንግ እውቀት ከዜሮ ተነስተው የራስዎን መተግበሪያዎች (Apps) መስራት ይፈልጋሉ?

በአሁኑ ጊዜ "Vibe Coding" (በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ/AI እገዛ ብቻ ኮድ የማድረግ ዘይቤ ሲሆን) የቴክኖሎጂውን ዓለም ጨዋታ እየቀየረው ይገኛል። ይህ አብዮት ማንኛውም ሰው ያለውን ሃሳብ ወደ እውነተኛ መተግበሪያ እንዲቀይር መንገድ ከፍቷል። ዋናው ቁም ነገር ሳይንገላቱ ስራዎን ለማሳካት እና ሃሳብዎን ወደ ተግባር ለመለወጥ ግልጽ የሆነ ስትራቴጂ ያስፈልግዎታል።

ከዜሮ ተነስተው የመጀመሪያ መተግበሪያዎን ለመስራት የሚረዳዎት ቀላል የጉዞ ካርታ (Roadmap) እንደሚከተለው አዘጋጅቼላችኋለሁ፦
1️⃣ የስራ ሂደቱን ይረዱ (Workflow)
AIን እንደ አስማተኛ ሳይሆን እንደ አብሮዎት እንደሚሰራ የኮዲንግ አጋር (Co-Pilot) አድርገው ይቁጠሩት።
በመቀጠል Vibe Coding መተግበሪያ ለማበልጸግ የምንከተለውን የማበልጸግ ኡደት ( (Cycle) በድንብ ይረዱት እነሱም:
ሃሳብ ➔ ትዕዛዝ መስጠት (Prompt) ➔ መገንባት (Build) ➔ ማስኬድ እና መሞከር (Run & Test) ➔ ስህተትን ማስተካከል (Fix) ➔ ማጋራት (Publish)
ናቸው።
መጀመሪያ ላይ ዋናው ግብዎ የሚፈልጉትን ነገር ለAI በግልጽ ማስረዳት መቻል፣ ውጤቱን ማረጋገጥ እና ማሻሻል (Iterate) ነው!

2️⃣ አንድ ቀላል የስራ መድረክ ብቻ ይምረጡ (Tools)
በተለያዩ መሳሪያዎች ብዛት አይጨናነቁ! ሁሉንም ለመሞከር አይድከሙ። ጀማሪዎች መሳሪያዎችን በየቀኑ ከመቀያየር ይልቅ በአንድ አካባቢ (Environment) ላይ በደንብ ሲለማመዱ የተሻለ ውጤት ያመጣሉ።
የእኔ ምክር: በሞባይልም ሆነ በኮምፒውተር በነጻ መስራት የሚያስችለውን Bolt.new የተባለውን መሳሪያ በመጠቀም ጀምሩ!

3️⃣ በትንንሽ ፕሮጀክቶች ይጀምሩ (Tiny Projects)
በመጀመሪያው ቀን ትልቅ መተግበሪያ ለመስራት አይሞክሩ። በቀላሉ ይጀምሩ፤ ለምሳሌ፡- ካልኩሌተር፣ የልምድ መከታተያ (Habit Tracker)፣ ወይም ቀላል ማስተዋወቂያ ገጽ (Landing Page)። ሁልጊዜ በአንድ ዋና አገልግሎት (Core feature) ይጀምሩ፤ እሱ በትክክል ሲሰራ ቀጣዩን ይጨምሩ።

4️⃣ ግልጽ የትዕዛዝ መዋቅር (Prompting) ይጠቀሙ
ትዕዛዝዎ ግልጽ ሲሆን AI የሚሰጠው ኮድም የተስተካከለ ይሆናል። ሁልጊዜ ለAI፡ ምን እንደሚፈልጉ፣ ለምን እንደሚያስፈልግዎ፣ የትኛው ቦታ ላይ መስተካከል እንዳለበት እና አስፈላጊ ከሆነ ጥብቅ ገደቦችን ያስቀምጡለት።

5️⃣ ስህተትን የማረም (Debugging) ልምድ ያዳብሩ
የመጀመሪያው ሙከራዎ ላይ ስህተት ሊያጋጥም ይችላል—ይህ ሙሉ በሙሉ የተለመደ ነው! የጎበዝ "Vibe Coder" ዋና ችሎታ ስህተት አለመስራት ሳይሆን፣ የትኛው ክፍል እንደተበላሸ አይቶ መለየት (Isolate) እና AIው ያንን የተወሰነ ክፍል ብቻ እንዲያስተካክልለት ጠቅሶ መጠየቅ መቻል ነው።

6️⃣ ከፋ ያሉና መሠረታዊ ነገሮችን ይጨምሩ
ትንንሽ መተግበሪያዎችን መስራት ሲለምዱ፣ ቀስ በቀስ ዋና ዋና ነገሮችን ማካተት ይጀምሩ፡ የይለፍ ቃል ማስገቢያ/ደህንነት (Authentication)፣ ዳታ ማከማቻ (Data Storage)፣ የገጽታ ውበት (UI Polish)

የ 4 ሳምንታት የድርጊት መርሃ ግብር (Action Plan)፦
ሳምንት 1: መሣሪያዎችዎን ይለማመዱ እና 2–3 ትንንሽ ገጾችን ይስሩ።
ሳምንት 2: አንድ ዋና አገልግሎት ብቻ ያለው ሙሉ አንድ ትንሽ መተግበሪያ ይገንቡ።
ሳምንት 3: ዳታ ማከማቻ፣ የመግቢያ ገጽ ወይም ቀላል የጀርባ አሰራር (Backend) ይጨምሩበት።
ሳምንት 4: መተግበሪያውን ኢንተርኔት ላይ ይልቀቁት (Deploy)፣ ለጓደኞችዎ ያጋሩ እና አስተያየት ተቀብለው ያሻሽሉት።


ለመጀመሪያ ፕሮጀክት የሚሆን ምርጥ ሃሳብ፦
ቀላል የስራ ዝርዝር መቆጣጠሪያ (Task Manager) ይስሩ፤ ስራዎችን የሚጨምር (Add)፣ የሚዘረዝር (List)፣ የተጠናቀቁትን ምልክት የሚያደርግ (Complete) እና የሚያጠፋ (Delete)።

ይህንን ፕሮጀክት ሙሉ ትዕዛዝ (Prompt):
Create a beautifully designed, full-featured Task Manager web app from scratch.
Please include all of the following requirements in the initial build:
1. UI Design: Give it a modern, clean dark-mode user interface. Put a prominent heading at the top titled "My Vibe Tasks", followed by a sleek text input field and an "Add Task" button.
2. Core Logic & Actions: When a user types a task and clicks "Add Task" (or presses Enter), add it to a neat list below. Next to each task item, include a "Complete" checkmark button and a "Delete" trash icon button. Clicking "Complete" should cross out the task text and lower its opacity. Clicking "Delete" should remove the task with a smooth fade-out animation.
3. Data Persistence: Use LocalStorage so that all tasks are saved automatically in the browser. The tasks must reload exactly as they were left even if the page is refreshed.
4. Filters & Stats: Add a filtering toggle bar right above the task list with three options: "All", "Active", and "Completed". Also, display a dynamic counter that shows how many active tasks are remaining (e.g., "3 tasks left").
Make the entire app fully interactive, highly responsive, and production-ready.

ኮፒ በማድረግ እና Bolt.new ላይ በመግባት መተግበሪያዎን መገንባት ጀምሩ!

ያገኙትን ውጤት መልሰው ሼር ያድርጉን!እኔም በዚህ መልኩ የሰራሁትን ሼር አደርጋለሁ!
#VibeCoding #NoCode #AI #TechAmharic #AppDevelopment
❤3👍2
ለምን OpenAI ብቻ እኛም ዝግጁ ነን አብሽሩ Gemini 4 Argon 🏃‍➡️
Vibe Codingን እና የ-AI የኮዲንግ ረዳቶችን በተመለከተ ግላዊ አመለካከታችንን ገለል አድርገን በሙያዊ እይታ ብንወያይበት የተሻለ ነው፡፡ ቴክኖሎጂው እኛ ስላልፈለግነው ወይም ስላጣጣልነው እድገቱ አይቆምም፡፡

​በመሆኑም አዳዲስ አሰራሮችን ከመቃወም ይልቅ፣ የ-AI መሳሪያዎችን ከጠንካራ የሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ መርሆች ጋር በማጣመር እንዴት የበለጠ ውጤታማ መሆን እንደምንችል ማተኮሩ የተሻለ አማራጭ ነው፡፡
❤2
በፌሽታው ጊዜ ያገኘነውን እድል ተጠቅመን ወደ አስመራ ተጉዘን ነበር!

አስመራ የሚል ዘገባዎች ሲበዘብኝ ትዝ ሲለኝ ስክምችት ክፍል መዘዝ ያደረግኩት ፎቶ ነው።

«ማን ብዬ ልጥራሽ ሰሜናዊት ጽብቅቲ... » ያለው በአሉ ግርማ ማንን ይሆን? አስመራን ወይስ «ፊያሜታ ጊላይ»ን ፤ ብቻ ከኢትዮጵያ ውጭ የመጀመሪያው የውጭ ሀገር ጉዞዬ ነው አትልም! ተው መሀመድ ተረጋጋ ኤርትራ እኮ ..........

በድጋሜ መሄዴ አይቀርም ኢንሻአላህ!
አስመሪኖ ጻዕዳ ፤ ትፀዳለች❤️
❤1
Andrej Karpathy & Vibe Coding — በ AI ዘመን አዲሱ የኮዲንግ ዘይቤ!

​አንድሬ ካርፓቲ (Andrej Karpathy) ማነው?
የቀድሞ የTesla AI ዳይሬክተር እና የOpenAI መስራች አባል ሲሆን፤ በየካቲት 2025 በ X (Twitter) ገጹ ላይ ለመጀመሪያ ጊዜ "Vibe Coding" የሚለውን አዲስ ፅንሰ-ሀሳብ ለአለም አስተዋወቀ።

​Vibe Coding ማለት ምን ማለት ነው?
☑️ የኮድ ዝርዝር ስራዎችን ለ AI መተው እና ሰውየው በሀሳብ/በስሜት (vibe) ብቻ መሪ ሆኖ ሶፍትዌር የሚያለማበት አዲስ አሰራር ነው።
☑️ ​ፕሮግራመሩ የኮድ መስመሮችን (syntax) መጻፉን ያቆማል።
​በምትኩ ሀሳቡን፣ ፍላጎቱንና ስሜቱን (Vibe) በጽሁፍ ለ AI ይነግረዋል።
☑️ ​AI ደግሞ አጠቃላይ ፕሮግራሙን ይገነባል፤ ፕሮግራመሩ ውጤቱን እያየ «ይህንን አስተካክል»፣ «ይህንን ጨምር» እያለ በሀሳብ ይመራዋል።


​
Vibe Coding ተረት ሳይሆን እውነት ነው! ሁላችንም እንደምናውቀው ይህ ነገር እውን ሆኖ ሁላችን ዘንድ ደርሶ አይተነዋል፣ ሞክረነዋል አለያም ብዙ እየሰራንበት ነው።

​ግን አሁንም የሚነሱ ጥያቄዎች አሉ፦
በ Vibe coding ብቻ Production-ready ሶፍትዌር ማበልፀግ ይቻላል?
መሰረታዊ እውቀትስ ግዴታ አይደለም?
ደህንነት (Security) እንዲሁም ውስብስብ የ Back-end ስራዎችስ እንዴት ይፈታሉ?

​እነዚህን እና ሌሎች የሚነሱ ጥያቄዎችን የሞከራችሁት በደንብ ሙያዊ ሀሳብ በመስጠት ልንወያይበት እንችላለን፤ የእኔን እይታ ደጋግሜ አስቀምጫለሁ አሁንም እቀጥላለሁ... ኢንሻአላህ!

​
በእርግጥ Vibe coding በዘርፉ ላይ ያሉ ሰዎችን የበለጠ ውጤታማ እንደሚያደርግ ምንም ጥያቄ የለውም!

ዘርፉም አሁን ካየነው በላይ እያደገ ይሄዳል፤ «አይ» ብሎ የሚያጣጥል ደግሞ ሲስተሙ እየበላው ሲመጣ ይገባዋል ብዬ አስባለሁ!

​📌 ቴሌግራም ቻናላችንን ለማግኘት፦
https://t.me/miftahcode
👍3
የሙያ ስኬትህን ለመወሰን የሚያስፈልጉህ 3ቱ ዋና የዕድገት ምሰሶዎች!
​
ዓለም በየዕለቱ በከፍተኛ ፍጥነት እየተለወጠች ነው። አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና አዳዲስ ቴክኖሎጂዎች የስራ ዓለምን እየቀየሩ ባለበት በዚህ ዘመን፣ ወደፊት ለመራመድ የታወቀ ዲግሪ ወይም የቀደመ እውቀት ብቻውን በቂ አይደለም ተወዳዳሪም አያደርግም። እውነተኛው የስኬት ሚስጥር የሚገኘው ሁልጊዜ እራስን በማደስ እና በነዚህ 3 ወሳኝ የህይወትና የሙያ ክህሎቶች (Soft Skills) ላይ በሚደረግ የዘወትር ትጋት ውስጥ ነው፡
​
📚 1. Continuous Learning
ዛሬ ያወቁት ነገር ነገ አሮጌ ሊሆን በሚችልበት ዘመን፣ መማር ማቆም ማለት ወደ ኋላ መቅረት ማለት ነው። በየቀኑ አዳዲስ የቴክኖሎጂ ውጤቶችን (እንደ AI ያሉ)፣ የኮምፒዩተርና የዲጂታል ክህሎቶችን እንዲሁም የሙያ ብቃቶችህን ለማሳደግ በቀላሉ ቢያንስ ከ15-30 ደቂቃ መድብ። ሁሉንም ነገር በአንድ ጀምበር ማወቅ አይጠበቅብህም፤ በየቀኑ የምታደርጋቸው ትንንሽ የመማር እርምጃዎች በሂደት ትልቅ ለውጥ ያመጣሉ። ዋናው ቁልፍ ጉዳይ ሁልጊዜ ለአዲስ እውቀት ክፍት መሆን፣ የማወቅ ፍላጎት (Curiosity) ማዳበር ላይ ነው።
​
🗣️ 2. Effective Communication
ምንም ያህል ታላቅና ድንቅ ሃሳብ ቢኖርህ፣ ለሰዎች በግልጽ ማቅረብ ካልቻልክ ዋጋ የለውም። ጥሩ የመግባባት ክህሎት የመናገር ችሎታ ብቻ ሳይሆን፤ ሰዎችን በትኩረት ማዳመጥን፣ ሃሳብን በጽሁፍ አጥርቶ ማስፈርን እና ከተለያዩ አካላት ጋር በቀላሉ መገናኘትን ያጠቃልላል። ሃሳብህን በግልጽ ማቅረብ ስትችል በሰዎች ዘንድ እምነትን ትገነባለህ፣ በውሳኔዎች ላይ ተፅዕኖ ፈጣሪ ትሆናለህ፣ እንዲሁም አዳዲስ የሙያና የንግድ ዕድሎችን ታገኛለህ። በዚህ ዘመን ሃሳብህን አጥርተህ፣ አጭርና ግልጽ በሆነ መንገድ ማቅረብ መቻል ትልቅ የሙያ ብልጫ ነው።
​
🔄 3. Adaptability & Flexibility
በተለይም በዚህ በዲጂታል ዘመን፣ አሸናፊ የሚሆነው የቀደመ እውቀቱ ላይ ብቻ ተንተርሶ የሚቆየው ሳይሆን ለለውጥ አወንታዊ አመለካከት ያለው ነው። ተላማጅነት ማለት አዳዲስ አሰራሮችን፣ የቴክኖሎጂ ለውጦችን እና ተቀያያሪ የሥራ ሁኔታዎችን በጥልቀት በመገምገም በብልሃትና በፍጥነት ከአዳዲስ ነገሮች ጋር መጣጣም መቻል ነው። ለውጥ ሲመጣ ከመደናገጥ ወይም በነበረው አሰራር ብቻ ከመጸናት ይልቅ፣ ሁኔታዎችን እንደ አዲስ የዕድገትና የፈጠራ አጋጣሚ አድርጎ መመልከት (Growth Mindset) አስፈላጊ ነው። አስተሳሰብህ ለለውጥ ክፍትና ተለዋዋጭ በሆነ ቁጥር፣ ፈታኝ ሁኔታዎች ውስጥ ሳይወዛወዝ የሚቆም እና ተፈላጊ ሰው ትሆናለህ።
​
አዳዲስ ነገሮችን የመማር፣ ሃሳብህን በግልጽ የመግለጽ እና ከለውጥ ጋር በፍጥነት የመላመድ ብቃትህ የስኬት ጉዞህ አስተማማኝ ዋስትናህ ነው።

📌 ቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል
https://t.me/miftahcode
❤5
ብዙ የተማርኩበት YouTube 🎬

ዩቲዩብ በየካቲት 2005 እ.ኤ.አ. ቻድ ኸርሊ፣ ስቲቭ ቼን እና ጃዌድ ካሪም በተባሉ ሶስት የቀድሞ የPayPal ባልደረቦች ተመሰረተ። ዩቲዩብን ለመፍጠር ያበቃቸው ዋናው ምክንያት
ቪዲዮዎችን በኢንተርኔት ላይ በቀላሉ ለማጋራት የሚያስችል ምቹ መንገድ በማጣታቸው ነበር።


​በዚያው በተመሰረተበት ዓመት የተለቀቀው
"Me at the zoo" የተሰኘው የ19 ሰከንድ አጭር ቪዲዮ በዩቲዩብ ታሪክ ውስጥ የመጀመሪያው መነሻ ነው።

ቪዲዮውን የጫነው የዩቲዩብ መስራች ጃዌድ ካሪም ሲሆን፣ በሳን ዲዬጎ እንስሳት Zoo ከዝሆኖች ፊት ለፊት ቆሞ የተቀረፀው ይህ ምስል የመድረኩን መከፈት ይፋ አድርጓል።

​ይህ አጭር ምስል ዩቲዩብን በዓለም ደረጃ ግዙፍ የሚያደርገውና በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎችን የሚያገናኝ የቪዲዮ ማጋሪያ ፕላትፎርም እንዲሆን መሰረት ጥሏል። የቴክኖሎጂውን ዓለም መቀየር ብቻ ሳይሆን፣ በርካታ ሰዎችም የራሳቸውን ይዘት ለዓለም እንዲያካፍሉ መንገድ ከፍቷል። ይህ ታሪካዊ ቪዲዮ እስካሁን 439M+ ዕይታዎችን አግኝቷል።

​YouTube በፈጣን ዕድገቱ ምክንያት ከተመሰረተ ከአንድ ዓመት ከግማሽ በኋላ በጥቅምት 2006 እ.ኤ.አ. በግዙፉ የቴክኖሎጂ ኩባንያ Google በ1.65 ቢሊዮን ዶላር ተገዛ።

​በዚህ መልኩ የተጀመረው YouTube
ዛሬ ላይ በየወሩ ከ 2.5 እስከ 2.7 ቢሊዮን በላይ ንቁ ተጠቃሚዎች ያሉት ሲሆን፣ በየደቂቃው ከ 500 ሰዓታት በላይ የቪዲዮ ይዘት ይጫንበታል።

​ይህ የቪዲዮ ማጋሪያ ፕላትፎርም እኛም ብዙ ነገር እንድንማር በር ከፍቶልናል፤ በብልጠት ለተጠቀመበት በርካታ ነገሮችን ማወቅ ይቻላል፤ ከፈለገም ጥሩ ይዘት በመፍጠር የገቢ ምንጭ ማድረግም ይቻላል!

አሁን ደግሞ Create video with Edit with AI በማለት አዲስ ነገር አስተዋውቋል ሌላ ጊዜ እመለሰበታለሁ!

​📌 Me at the zoo ቪዲዮ ለማየት!
❤1
AI የሶፍትዌር መሐንዲሶችን ይተካል?

በአሁኑ ወቅት "አርቲፊሻል ኢንተሊጀንስ (AI) የሶፍትዌር መሐንዲሶችን ሙሉ በሙሉ ይተካል ወይ?" የሚለው ጥያቄ በቴክኖሎጂው ዓለም በስፋት እየተነሱ ካሉ አጀንዳዎች አንዱ ነው። ነገር ግን ለዚህ ጥያቄ ትክክለኛው እና እውነተኛው ምላሽ የሚገኘው ከጽንሰ-ሀሳባዊ ግምቶች ይልቅ መሬት ላይ ካለው እውነታ እና ከዘርፉ ባለሙያዎች እውነተኛ ልምድ ነው። በቅርቡ ከሲኒየር ሶፍትዌር መሐንዲስ ብርሃን ነጋ የተሰጠው ሙያዊ አስተያየት እንደሚያሳየው፣ አሁን ላይ ያለው ዋና ፈተና AI የሰዎችን ስራ መተካቱ ሳይሆን የሞዴሎቹ ከፍተኛ የዋጋ ውድነት እና የአገልግሎት ገደብ (Token/Rate limits) ነው።

እንደ ብርሃን ነጋ ገለጻ፣ ለትላልቅ እና ለተወሳሰቡ ፕሮጀክቶች እንደ Claude እና Codex Pro ያሉ ከፍተኛ አቅም ያላቸውን AI ሞዴሎች ያለማቋረጥ ለመጠቀም በወር እስከ 200 ዶላር እና ከዚያ በላይ ማውጣት ግድ ይላል። በተለምዶ የምናውቀው የ20 ዶላር ወርሃዊ ክፍያ (Plan) ቢሆን እንኳ፣ ለሙያዊ የኮዲንግ ስራዎች ሲውል የሳምንቱን አገልግሎት በአንድ ቀን ውስጥ ጨርሶ ገደብ ላይ ሊደርስ ይችላል። ይህም የሚያሳየው AI የኢንጂነሮችን ቦታ ሙሉ በሙሉ ከመውሰድ ይልቅ የሥራችንን ፍጥነት የሚያሳድግ ድንቅ ረዳት ሆኖ እያገለገለ ቢሆንም፣ የዋጋው እና የቶክን ገደቡ ጉዳይ ገና ብዙ ማሻሻያ የሚፈልግ መሆኑን ነው።

ከዚህ እውነታ በመነሳት ሁለት ዋና ዋና ጥያቄዎች ይነሳሉ። የመጀመሪያው፣ አቅም ያላቸው ሞዴሎች ክፍያቸው እንዲህ ውድ ከሆነ፣ አብዛኛው ሰው በሚጠቀመው ነፃ አማራጭ (Free plan) ላይ ተመስርተን እስከ ምን ያህል ጥራት ያለው ስራ መስራት እንችላለን የሚለው ነው።
በሌላ በኩል ደግሞ፣ እንደ ቻይና ያሉ ሀገራት (ለምሳሌ በ Kimi K3 በኩል) አነስተኛ ዋጋ ያላቸው እና ተወዳዳሪ AI ሞዴሎችን ወደ ገበያ ማቅረባቸው የ AI አገልግሎት ዋጋን ወደ ታች ያወርደው ይሆን የሚለው ትልቅ አጀንዳ ነው። በዚህ ረገድ ካላችሁ ልምድ በመነሳት የምታስቡትን ሀሳብ በኮሜንት መስጫው ላይ ብታካፍሉን መልካም ውይይት ይሆናል።👇

📌 ለተጨማሪ የቴክኖሎጂ መረጃዎች ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፦ https://t.me/miftahcode
❤1👍1
የእውቀት፣ የፈጠራ እና የታላቅ ትስስር ጥሪ! 🇪🇹

​በፍጥነት እየተለወጠ ባለው የዲጂታል ዘመን፣ የሰው ልጅ እውቀትና ፈጠራ ድንበር ሳይበግረው ከምንም በላይ ዋጋ የሚያገኘው በስራ እና በጋራ ትብብር ውስጥ ነው!
​በሳይንስ፣ በቴክኖሎጂ፣ በሶፍትዌር ልማት፣ በ AI (ሰው ሰራሽ አስተውሎት) እና በዲጂታል ፈጠራ ላይ የተሰማራችሁ ኢትዮጵያውያንና የቴክኖሎጂ አፍቃሪያን ያላችሁን ተሰጥኦ ለብዙሃኑ የምታካፍሉበት ጊዜ ከመቼውም ጊዜ በላይ አሁን ነው!

​🌐 Ethio Coders — ከ 99K+ በላይ የቴክኖሎጂ ቤተሰቦች የተሰባሰቡበት፣ የምንማማርበት እና አዳዲስ ሀሳቦችን የምንጎለብትበት የጋራ መኖሪያችን ነው!
​
በግሩፑ ውስጥ ይዘቶችን ማጋራት ለእርስዎ ምን ይጠቅማል?
​🌟 Personal Brand መገንባት: የተዘጋጀ አድማጭና ተመልካች በማግኘት የዲጂታል ህልውናዎን በፍጥነት እንዲገነቡ ያግዛል።
​🤝 Strong Networking: በየዘርፉ ካሉ ባለሙያዎች ጋር ጠንካራ ትስስር ይፈጥራሉ።
​🚀 የስራ እድሎች: ነገን የሚቀይሩ ትልልቅ የጋራ ፕሮጀክቶችንና የስራ እድሎችን ለመፍጠር መንገድ ይከፍታል።
​📚 የእውቀት እድገት: እውቀት ሼር ሲደረግ አይቀንስም፤ ይልቁንም ይበዛል፣ ያድጋል!

📌 ምን አይነት ይዘቶችን ማጋራት ይችላሉ?
​💻 Coding Tips: አጫጭር የኮዲንግ ትምህርቶችና ጠቃሚ ምክሮች
​🤖 AI & Tech Tools: አዳዲስ የ AI እና የቴክኖሎጂ መሳሪያዎች አጠቃቀም
​🛠️ Project Showcase: የራሳችሁን ስራዎች እና ፕሮጀክቶች
​🗺️️ Roadmaps: የትምህርት እና የሙያ እድገት ፍኖተ-ካርታዎች እና ሌሎች የዲጀታል ክህሎቶች
​
ዛሬ የምታካፍሉት አንዲት አጭር መረጃ የሌላውን ሰው ህይወትና የሙያ ጉዞ ፍፁም ሊቀይር ይችላል!


​ኢትዮ ኮደርስ የሁላችንም ነው፤ ይቀላቀሉን፣ እውቀትዎን ያጋሩ፣ አብረንም እንደግ!

​🔗 ወደ ግሩፑ ለመግባት እና ለመሳተፍ: Ethio Coders ኢትዮ ኮደርስ

​ጥሪው ለብዙዎች እንዲደርስ ሼር (Share) በማድረግ ደግፉን! 🙏❤️
❤1
ጀኔሬቲቭ ኤአይን (GenAI) ከመጠቀማችን በፊት ማወቅ ያለብን 3 ወሳኝ ነጥቦች

​ጀኔሬቲቭ ኤአይ (GenAI) ምርታማነታችሁን በ10 እጥፍ ሊጨምርላችሁ ይችላል፤ ወይም ደግሞ በተሳሳተ መረጃ ሙሉ በሙሉ ሊያሳስታችሁ ይችላል። 🤯

​እንደ ChatGPT፣ Gemini፣ ወይም Claude ያሉ የኤአይ መሣሪያዎችን ለሥራችሁ ወይም ለትምህርታችሁ ከመጠቀማችሁ በፊት እነዚህን 3 መሠረታዊ ሕጎች ሁልጊዜ ያስታውሱ፦

​1️⃣ ንድፎችን ይተነብያል እንጂ እውነታዎችን አያውቅም
ኤአይ እንደ ሰው "አያስብም" ወይም እውነታውን ለይቶ አያውቅም፤ ይልቁንም ቀጥሎ የሚመጣውን በጣም ተዛማጅ ቃል የመተንበይ ችሎታ ነው ያለው። ይህም ማለት ሙሉ በሙሉ የተሳሳቱ መረጃዎችን፣ የሌሉ ምንጮችን ወይም የተበላሹ የኮድ መስመሮችን በእርግጠኝነት ሊፈጥር ይችላል ይህም Hallucination ይባላል። ስለዚህ ማንኛውንም ወሳኝ መረጃ ከመጠቀማችሁ በፊት ሁልጊዜ እውነተኝነቱን አረጋግጡ!
​
2️⃣ የውጤቱ ጥራት የሚወሰነው በሰጣችሁት ትዕዛዝ (Context) ነው !
ደካማ ወይም ግልጽ ያልሆነ ትዕዛዝ (Prompt) ከሰጣችሁት፣ የሚሰጣችሁ መልስም የተለመደና ደካማ ይሆናል። የተሻለና ጥራት ያለው ውጤት ለማግኘት ለኤአይዩ ግልጽ ድርሻ (Role) ስጡት፣ ደንቦችን ወስኑለት፣ ማብራሪያዎችን እና ምሳሌዎችን አካቱበት፤ እንዲሁም ውይይቱን ደረጃ በደረጃ ቀጥሉ። የተሻለ ውጤት እስኪመጣ እዚያው ቻት ውስጥ ቆዩ!

​3️⃣ የግል ፣ የመንግስት እና የድርጅታችሁን ምስጢራዊ መረጃዎቻችሁን ጠብቁ 🔒
በየትኛውም የኤአይ መሣሪያዎች ላይ የምታስገቡት ማንኛውም መረጃ ሊቀመጥ ወይም ሞዴሉን ለወደፊቱ ለማሰልጠን ሊያውሉበት ይችላሉ። ስለዚህ የራሳችሁን፣ የመስሪያ ቤታችሁን አለያም የድርጅታችሁን ምስጢራዊ መረጃዎችን፣ የይለፍ ቃሎችን (Passwords)፣ የባለቤትነት ኮዶችን እና የግል መረጃዎችን በጭራሽ ኤአይ ውስጥ አታስገቡ። በግልፅ አማርኛ ይጠቀሙበታል!

​Simple rule: ኤአይ የእናንተ ረዳት (Co-pilot) እንጂ ምትካችሁ አይደለም። ሥራችሁን ለማፋጠንና አዳዲስ ሀሳቦችን ለማመንጨት ተጠቀሙበት፤ ነገር ግን
የመጨረሻውን ውሳኔ በራሳችሁ ምክንያታዊነት ላይ ብቻ አድርጉ!


📌 ለበለጠ መረጃ ቴሌግራም ቻናላችንን ለመቀላቀል
https://t.me/miftahcode
👍4❤1
SWE-bench Leaderboard 🔝 5
የ AI እጅግ አስደናቂው የኮዲንግ ፉክክር እና የአለካኩ ምስጢር!

የኮምፒውተር ፕሮግራም ስህተቶችን (Bugs) በራሱ በመፍታት ረገድ የትኛው AI ሞዴል ይበልጣል? ይህንን ብቃታቸውን ለማወቅ የወጣው የ SWE-bench Verified መመዘኛ ውጤት አስገራሚ መረጃዎችን በየጊዜው እያስመለከተን ይገኛል።

📊 ለመሆኑ የ AI ሞዴሎቹ ብቃት እንዴት ነው የሚለካው?
ይህ ውድድር ዝም ብሎ ቀላል ጥያቄዎችን በመጠየቅ የሚደረግ አይደለም። SWE-bench Verified በተባለው እጅግ ጥብቅ መመዘኛ መድረክ ላይ አለካኩ የሚከናወነው በሚከተለው መልኩ ነው፦
✔️ በዓለም ዙሪያ ያሉ የሶፍትዌር ባለሙያዎች በጋራ በሚሰሩበት (GitHub) ላይ ከገጠሟቸው እውነተኛ እክሎች መካከል በባለሙያዎች የተመረጡ 500 ውስብስብ የሶፍትዌር ችግሮች ለ AI ሞዴሎቹ ይሰጣቸዋል።
✔️ AIው ማንም ሰው ሳይረዳው በሺዎች የሚቆጠሩ የኮድ ማህደሮችን አንብቦ በመረዳት፣ ስህተቱ ያለበትን ቦታ ፈልጎ ያገኛል፤ ከዚያም በራሱ አዲስ የኮድ ማስተካከያ ይጽፋል።
✔️ AIው የጻፈው ኮድ በትክክል መስራቱን ለማረጋገጥ አውቶማቲክ የሙከራ ሲስተም ውስጥ ያልፋል። ኮዱ ሁሉንም የጥራት እና የደህንነት መስፈርቶች 100% ካለፈ ብቻ ነው "ችግሩን ፈትቷል" ተብሎ ነጥብ ይሰጠዋል።

በዚህ ጥብቅ አለካክ መሰረት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡት 5 የ AI ሞዴሎች፦
1️⃣ Claude 4.5 Opus (high) — 76.80% (እጅግ አስደናቂ ማሰብ የሚችልበትን ሰፊ ጊዜ በመጠቀም የዓለማችን መሪነቱን ይዟል!)
2️⃣ Gemini 3 Flash (high) — 75.80% (የጉግል እጅግ ፈጣን እና ብልህ ሞዴል)
3️⃣ MiniMax M2.5 (high) — 75.80% (ከጉግል ጋር እኩል በመሆን ትልቅ አስገራሚ ውጤት ያመጣ)
4️⃣ Claude 4.6 Opus — 75.60% (ያለ ተጨማሪ ልዩ አሰራር መደበኛ ብቃቱን ያሳየ)
5️⃣ Claude 4.5 Opus (medium) — 74.60% (መካከለኛ የማሰብ አቅምን በመጠቀም ውጤታማ የሆነ)

ይህ ውጤት የሚያሳየው AI አሁን ላይ የሰውን ልጅ እገዛ ሳይጠይቅ ከ76% በላይ ውስብስብ የሶፍትዌር ችግሮችን በራሱ መፍታት ወደሚችልበት አስደናቂ ደረጃ ላይ መድረሱን ነው። የቴክኖሎጂው ዓለም በከፍተኛ ፍጥነት እየተቀየረ ነው! ስለዚህ ለ ኮዲንግ ስራዎች የ Al ሞዴሎቹን ስንገዛ ይህን ከግምት ውስጥ እያስገባን ቢሆን የተሻለ ይመስለኛል።

እናንተስ በዕለት ተዕለት ስራችሁ ወይም ህይወታችሁ በብዛት የምትጠቀሙት የትኛውን AI ነው? የወደፊቱ የ AI ጉዞ ወዴት የሚያመራ ይመስላችኋል? አስተያየታችሁን በኮሜንት አጋሩን👇
Source: SWE- bench
#AI #Coding

📌 ለተጨማሪ መረጃ ቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ
https://t.me/miftahcode
👍1
Ask Al: "How to stop you from killing my critical thinking?"
ሁላችንም መጠየቅ ያለብን ጥያቄ ነው!

ChatGPT ለእኔ በሰጠኝን ምላሽ ላይ "እኔን መጠቀም ማቆም አያስፈልግህም ይልቁን መቀየር ያለብህ እኔን እንዴት መጠቀም እንዳለብህ ነው።" በማለት ሰባት የአጠቃቀም ህግ አስቀምጦልኛል!

ሙሉ ምላሹን ኮሜንት ላይ ታገኙላቸሁ! የእናንተንም ሼር አድርጉን👇
👍3❤1
የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ሞዴሎችን ስንጠቀም ትክክለኛ እና አስተማማኝ ምላሽ ለማግኘት የምንሰጠው ጥያቄ ወይም ትዕዛዝ (Prompt) አወቃቀር በጣም ወሳኝ ነው!

ምርታማነታችሁን የሚጨምሩ 7 የመልካም አጠቃቀም ህጎች፦

1️⃣ ግልጽ ሚና መስጠት (Assign a Role)
AIው ከማን አንጻር ማሰብ እንዳለበት መንገር።
ለምሳሌ፦ "እንደ ልምድ ያለው የሶፍትዌር ኢንጂነር/የማርኬቲንግ ባለሙያ ሆነህ መልስልኝ" በማለት የሚፈልጉትን የዕውቀት ደረጃና የድምጸ-መልስ (Tone) ጥራት ማረጋገጥ ።

2️⃣ የሁኔታውን ዝርዝር ማስረዳት (Provide Context)
ምን እየሰራችሁ እንደሆነና የትኛው ደረጃ ላይ እንዳላችሁ ከጀርባ ያለውን ታሪክ ማብራራት።
ለምሳሌ፦ "ለአዲስ ጀማሪ ተማሪዎች የሚሆን የፕሮግራሚንግ ትምህርት ማጠቃለያ እያዘጋጀሁ ነው..."

3️⃣ የውጤቱን ቅርጽ መወሰን (Specify Output Format)
ምላሹ በምን አይነት ፎርማት እንዲቀርብላችሁ የምትፈልጉትን መንገድ ማስቀመጥ።
ለምሳሌ፦ "በሰንጠረዥ (Table)፣ በአጫጭር ነጥቦች (Bullet points) ወይም በ3 አንቀጽ አቅልለህ አቅርብልኝ" ማለት።

4️⃣ ደረጃ በደረጃ እንዲያስብ ማድረግ (Chain-of-Thought)
ቀጥታ ወደ መጨረሻው ድምዳሜ ከመሄድ ይልቅ የመልሱን ሂደት በቅደም ተከተል እንዲያሰላስል ማዘዝ።
ለምሳሌ፦ "መልሱን ከመጻፍህ በፊት ደረጃ በደረጃ ተንትነህ አስብበት" ማለት AIው የሌለ መረጃ (Hallucination/ቅዠት) እንዳይፈጥር ይረዳል::

5️⃣ ገደቦችን ማስቀመጥ (Constraints)
በምላሹ ውስጥ መካተት የሌለባቸውን ወይም የግድ መኖር ያለባቸውን ድንበሮች መወሰን።
ለምሳሌ፦ "ከባድ የቴክኒክ ቃላትን አትጠቀም" ወይም "ከ200 ቃላት ባልበለጠ አጭር ጽሁፍ አዘጋጅ"።

6️⃣ ምሳሌዎችን ማካተት (Few-shot Prompting)
የምትፈልጉትን ውጤት አይነት በአንድ ወይም በሁለት አጭር ምሳሌ ማሳየት።
ለምሳሌ፦ "የምፈልገው የጽሁፍ ስልት ልክ እንደዚህ አይነት ነው፦ [ምሳሌ እዚህ አስገቡ]" ብሎ ማሳየት ውጤቱ ልክ እንዳሰባችሁት እንዲሆን ያደርገዋል።

7️⃣ ተመልሶ ጥያቄ እንዲጠይቅ ማዘዝ (Interactive)
ወዲያውኑ ሙሉ መልስ ከመስጠት ይልቅ ያልተብራራ ነገር ካለ ጠይቆ እንዲረዳ ማድረግ።
ለምሳሌ፦ "ምላሹን ከመስጠትህ በፊት የተሻለ ውጤት እንድትሰጠኝ የሚረዱህን 3 ጥያቄዎች ጠይቀኝ" ማለት።

እነዚህን ህጎች በመጠቀም ከ ChatGPT፣ Claude፣ Gemini እና ከሌሎች የLLM ሞዴሎች የተሻለና የጠራ ውጤት ማግኘት ይቻላል!

📌 ሶስት ጥሩ ምሳሌዎችን ኮሜንት ላይ አስቀምጫለሁ

👇 እስካሁን በብዛት የምትጠቀሙበት የ Prompt ስልት የትኛው ነው? አስተያየታችሁን ኮሜንት ላይ ያጋሩን!

Telegram: https://t.me/miftahcode
❤3👍2
AI (አርተፊሻል ኢንተለጀንስ) ነገሮችን በፍጥነት የሚያነበውና የሚመልሰው እያሰበ ይሆን?🤔