Mohammed Seid - Miftah
3.16K subscribers
149 photos
5 videos
10 files
119 links
​🛠 Digital Skills | AI | Innovation
📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች።
👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡
https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/
Download Telegram
AI በእርግጥ የሰው ልጆችን ሊያጠፋ ይችላል?

​ሰሞኑን በትልልቅ የዓለም ሚዲያዎች ዘንድ ዋና መነጋገሪያ የሆነው አጀንዳ የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ፈጣን እድገት እና ስጋቱ ነው።

​የዘርፉ ፈር ቀዳጅ እና "የ AI አባት" በመባል የሚታወቁት ጄፍሪ ሂንተን (Geoffrey Hinton) ጨምሮ በርካታ ተመራማሪዎች "የ AI እድገት ቁጥጥር ካልተደረገበት የሰው ልጆችን ሕልውና አደጋ ላይ ሊጥል ይችላል፤ ስለዚህ እድገቱ ሊገታ ወይም ደንብ ሊወጣለት ይገባል" የሚል ጠንካራ አቋም እያንጸባረቁ ይገኛሉ።

​በሌላ በኩል ደግሞ እንደ ዶናልድ ትራምፕ ያሉ ፖለቲከኞች እና የኢንዱስትሪ መሪዎች "እድገቱን ማገድ የቴክኖሎጂ የበላይነትን እና የኢኮኖሚ እድገትን ያደናቅፋል" በሚል ፉክክሩ መቀጠል እንዳለበት ይከራከራሉ።

​እናንተ ከአሁኑ የቴክኖሎጂው እድገት ደረጃ በመነሳት ምን ታስባላችሁ?

​AI በእርግጥ የሰው ልጆችን የመደምሰስ አቅም ላይ ሊደርስ ይችላል ወይስ ስጋቱ ከአቅሙ በላይ ተጋኖ ቀርቧል?

​እድገቱ በሕግ መገደብ አለበት ወይስ ቁጥጥር ሳይደረግበት መቀጠል አለበት?

ሀሳባችሁን ኮሜንት ላይ አጋሩን!👇
❤2
"የ AI አወንታዊ ወደፊት የሚረጋገጠው እድገቱን በማቀጨጭ ወይም ስልጣንን በጥቂት ወገኖች እጅ በማከማቸት ሳይሆን፤ ቴክኖሎጂውን ለሁሉም በማደል፣ የደህንነት ቁጥጥርን በማጠናከር እና ትክክለኛውን የኃይል ሚዛን በግለሰቦች እጅ በማድረግ ነው"
___የሜታ CEO ማርክ ዛከርበርግ

ሰሞኑን ሁሉም የራሱን አቋም እየገለፀ ነው ፤ ከ Al ካምፓኒ እስከ ሀገር መሪዎችና ሳይንቲስቶች ጥሩ ነው! ሰዎች የበለጠ AI ምንድን ነው? እስከምን መሄድ አለበት የሚለውን እንዲረዱ ፣ እንዲማሩ እና እንደጠይቁ በር የሚከፋት ጥሩ አጋጣሚ ይመስለኛል።

ሙሉውን ኮሜንት ላይ ማንበብ ትችላላቸሁ!👇
❤2
በፌስቡክ መንደር AI (የሰው ሰራሽ አስተውሎት) “ሰይጣን ነው” የሚሉ ፖስቶችን አያለሁ፤ እናንተም አይታችኋል ብዬ አስባለሁ። ማንኛውም ሰው በተረዳውና ባመነበት ልክ ሀሳቡን የማንሸራሸር መብት አለው። ነገር ግን ቁልፍ ጥያቄው፡ በእርግጥ AI ሰይጣን ነው ወይ?

​በፍፁም አይደለም! AI የሰው ልጆች ድንቅ የማሰብ ክህሎት ውጤት የሆነ የሳይንስና ቴክኖሎጂ ፈጠራ ነው። በታሪክ አጋጣሚዎችም አዳዲስ የቴክኖሎጂ ግኝቶች ሲመጡ ቀድሞ ለመቀበል የሚቸገሩ እና በፍርሃት የሚመለከቱ ወገኖች አልታጡም። ቀደም ሲል ራዲዮ፣ ስልክ፣ ቴሌቪዥን እና የህትመት ማሽን (Printing Press) ሲፈጠሩም ) ልክ እንደዚሁ "ሰይጣናዊ ናቸው፤ ራቋቸው" ብለው የሚከራከሩ ሰዎች ነበሩ። ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው ግን እነዚህ ቴክኖሎጂዎች የሰው ልጅን ህይወት ያቀለሉ መሳሪያዎች ሆነዋል። ቴክኖሎጂዎቹ የፈጠሩት ተፅዕኖንም ሳልዘነጋ!

​ቢላዋ ምግብ ለማዘጋጀትም ሆነ ሰውን ለመጉዳት እንደሚያገለግለው ሁሉ፣ AI የህክምና ምርምርን ለማፋጠን፣ ትምህርትን ለማቃለል እና ስራዎችን ለማቀላጠፍ ሊውል ይችላል፤ ወይም ደግሞ ለሀሰተኛ መረጃ ማሰራጫነት እና ሰዎችን ለመጉዳት ሊያገለግል ይችላል። ስለሆነም የብዙ ሰዎች ፍርሃት የሚመነጨው የቴክኖሎጂውን አሰራር በደንብ ካለመረዳት እና ከተጋነኑ ወሬዎች ነው።

​በእንደዚህ አይነት አሳሪ ሀሳብ ታጥሮ ከመሸሽ ይልቅ፣ ቀረብ ብሎ በመፈተሽ ቴክኖሎጂው እንዴት እንደሚሰራ እና ምን እድሎች እንደሚያመጣ በጥበብ መረዳት የተሻለ ነው። ለትምህርት፣ ለስራ፣ ለፈጠራ እና ህይወትን ለማቃለል በበጎ መንገድ አውቆ መጠቀም፣ እንዲሁም ከቴክኖሎጂው ጋር ተያይዘው የሚመጡ የውሸት መረጃዎችን እና ስነ-ምግባራዊ ስጋቶችን ተረድቶ በጥንቃቄ አውቆ መጠንቀቅ አስፈላጊ ነው። የቴክኖሎጂን እድገት በፍርሃት መግታት ስለማይቻል፣ የተሻለው አማራጭ በፍርሃት ታጥሮ ከመቅረት ይልቅ እውቀት ላይ ተመስርቶ በጥበብ መጠቀም ነው።

በእርግጥ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስጋት ከላይ የጠቀስኩት ብቻ አይደለም ብዙ ጊዜ በዚሁ ገጽም በስፋት እያነሳሁት ነው፡፡

ስንጠቀም በምክንያት ፤ ስንርቅም በምክንያት!
መልአክቴ ነው።

መልካም ምሽት! 😍
👍2
አንድ አማርኛ ብቻ የሚናገሩ እናታችን ለህክምና ህንድ ሀገር ቢሄዱ፤ ዶክተሩ ደግሞ ህንደኛ (Hindi) ብቻ የሚችል ቢሆን... በመካከላቸው Artificial Intelligence (AI) ገብቶ በቅጽበት እየተረጎመ እንዲነጋገሩ ቢያደርግስ?

ለምሳሌ እንደ Google Gemini 3.5 live translate ሞዴል ማለት ነው።

እዚህ ሂደት ውስጥ ምን ጥቅም ይታያችኋል? ጉዳቱስ
❤4🔥4
🎉 እንኳን አደረሰን! የ STEM ቤተሰቦቻችን 2ኛ ዓመታችንን በጋራ እያከበርን ነው!
Ethio Coders ኢትዮ ኮደርስ

​ከሁለት ዓመት በፊት ይህንን መድረክ ስንጀምር ዓላማችን አንድ ነበር—አስተማሪ፣ አዳዲስ እና ጥራት ያላቸው የ STEM (Science, Technology, Engineering & Math) መረጃዎችን የምንለዋወጥበት እና በጋራ የምንማርበት ትልቅ ቤተሰብ መፍጠር!

​ዛሬ በሁለት ዓመት ጉዞአችን 99,000 (99K) አባላትን ያቀፈ ታላቅ ማህበረሰብ ለመሆን በቅተናል። ለዚህ ስኬት አብራችሁን ለነበራችሁ እና ለደገፋችሁን በሙሉ ከልብ የመነጨ ምስጋና እናቀርባለን! 🙏

ነገር ግን ገና ብዙ ይቀረናል!
እስከ አሁን በዋናነት ጥቂት አባላት ብቻ በቋሚነት አስተማሪ ይዘቶችን ሲያካፍሉን ቆይተዋል። ይህ ግሩፕ የሁላችንም እንደመሆኑ መጠን የሁላችሁንም እውቀት፣ ጥያቄ እና ተሳትፎ ይፈልጋል። ጥራት ያላቸውን የ STEM መረጃዎች፣ አዳዲስ የቴክኖሎጂ አዝማሚያዎችን እና ትምህርታዊ ይዘቶችን ብናጋራ ይበልጥ እንጠቀማለን።
​
ከእንግዲህ በግሩፑ ላይ ሁልጊዜ አስተማሪ እና አጋዥ የሆኑ ይዘቶችን በቋሚነት ለሚያጋሩ አባላት የModerator እና Admin ሚና የምንሰጥ ይሆናል!

​ያላችሁን እውቀት ለሌሎች በማካፈል ግሩፓችንን ወደ ላቀ ደረጃ በጋራ እንገንባ። እያልኩ ጥሪዬን አቀርባለሁ!

​የጋራችን ነው፤ በጋራ እናሳድገው!
በጋራ እንማርበት! ✨
❤2
Free_AI_ML_books_byMIT.zip
80.1 MB
🔥 የታዋቂው MIT ነፃ AI እና Machine Learning መፃህፍት!
በሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በተለይም Machine Learning ዘርፍ እውቀታችሁን ከመሰረቱ ለመገንባት የሚያግዙ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ ተቀባይነት ያላቸው 5 የ MIT መፃህፍት፦

1️⃣Foundations of Machine Learning
2️⃣ Understanding Deep Learning
3️⃣ Machine Learning Systems
4️⃣ Algorithms for Decision Making
5️⃣ Deep Learning

📌 Zip code: 1234
💡 ለ AI እና Machine Learning ፍላጎት ላላቸው ወዳጆቻችሁ #Share አድርጉት!
#ArtificialIntelligence #MachineLearning #TechEducation #FreeResources #Ethiopia #Tech
❤10👍2🔥1
አይገርምም? 🤔

​በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ምንም ዓይነት መስዋዕትነት ሳያስከፍልህ በፍጥነትና በብልህነት ውሳኔ እንድትወስን የሚያስችል አዲስ መንገድ ተከፍቷል።

​በቀደሙት ጊዜያት አንድን ትልቅ ውሳኔ ለመወሰን ረጅም ጊዜ፣ ከፍተኛ ድካምና በርካታ ስህተቶችን ማለፍ ግድ ይል ነበር። ዛሬ ግን ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) እንደ ዋና ስትራቴጂካዊ የሃሳብ አጋርህ በማድረግ ብቻ፣ የወደፊት ውሳኔዎችህን በከፍተኛ ጥራትና ፍጥነት መምራት ትችላለህ!

​ያለ ድካም ውስብስብ መረጃዎችን በሰከንዶች ውስጥ ይተነትንልሃል።

​ያለ ስጋት የተሻሉ አማራጮችንና ሊመጡ የሚችሉ አደጋዎችን አስቀድሞ ያሳየሃል።

​ያለ ገደብ በየትኛውም ሰዓትና ቦታ አብሮህ የሚሰራ የሃሳብ ምንጭ ይሆንሃል።

​ቴክኖሎጂው እጃችን ላይ ነው፤ አሁኑኑ AIን እንደ ስትራቴጂካዊ አጋርህ Copilot በመጠቀም ውሳኔዎችህን ወደ አዲስ ደረጃ አሸጋግር!

Telegram 👇
https://t.me/miftahcode
👍5❤2🔥1
Mohammed Seid - Miftah pinned «አይገርምም? 🤔 ​በታሪክ ለመጀመሪያ ጊዜ፣ ምንም ዓይነት መስዋዕትነት ሳያስከፍልህ በፍጥነትና በብልህነት ውሳኔ እንድትወስን የሚያስችል አዲስ መንገድ ተከፍቷል። ​በቀደሙት ጊዜያት አንድን ትልቅ ውሳኔ ለመወሰን ረጅም ጊዜ፣ ከፍተኛ ድካምና በርካታ ስህተቶችን ማለፍ ግድ ይል ነበር። ዛሬ ግን ሰው ሰራሽ አስተውሎትን (AI) እንደ ዋና ስትራቴጂካዊ የሃሳብ አጋርህ በማድረግ ብቻ፣ የወደፊት ውሳኔዎችህን በከፍተኛ…»
AI ዛሬ የተጀመረ ወይም አዲስ አይደለም!

​የሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) ዛሬ ላይ የቴክኖሎጂው ዓለም ዋና ትኩረት እና መነጋገሪያ ቢሆንም፣ ታሪኩ ግን ከብዙ አሥርተ ዓመታት በፊት የጀመረ ነው። ይኸውም ገና በ1950ዎቹ እ.ኤ.አ. ታዋቂው አላን ቱሪንግ (Alan Turing) "ማሽኖች ማሰብ ይችላሉ?" የሚለውን ደፋር ጥያቄ በማንሳት ለዘርፉ መወለድ የመጀመሪያውን መሰረት ጥሏል።

በመቀጠልም በ1956 እ.ኤ.አ. በተካሄደው የዳርትማውዝ ኮንፈረንስ (Dartmouth Conference) ላይ ጆን ማካርቲ (John McCarthy) "Artificial Intelligence" የሚለውን ስያሜ ለመጀመሪያ ጊዜ በመጠቀም ዘርፉ እንደ አንድ ገለልተኛ የጥናት መስክ በይፋ እንዲመሰረት አድርጓል።

ስለዚህ የዘርፉ ተመራማሪዎች ኮምፒውተሮች እንደ ሰው ማሰብና መማር እንዲችሉ የማድረግ ራዕይ የነበራቸው ከ70 ዓመታት በፊት በመሆኑ፣ AI አሁን ከ ChatGPT ጋር አዲስ የመጣ ሳይሆን የረጅም ጊዜ ታሪክ ያለው የቴክኖሎጂ ጉዞ ውጤት ነው። (ማሳሰቢያ፦ በጽሁፉ ውስጥ የተጠቀሱት ዓመታት በሙሉ እንደ አውሮፓውያን አቆጣጠር (እ.ኤ.አ.) ናቸው።)

​እናንተስ AIን ለመጀመሪያ ጊዜ የተጠቀማችሁት ወይም ያወቃችሁት በየትኛው (እ.ኤ.አ.) ዓመት ነበር? ኮሜንት ላይ ያካፍሉን!

​የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ ⤵️
https://t.me/miftahcode
👍1
AI የመጨረሻ ፈጠራ ወይስ የፈጠራ መጨረሻ?

በእኔ እይታ ድንቅ የምርምር ጥያቄ ነው! Solo kassa
❤2
የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ስጋት እና የአሜሪካ የመሪነት ጥሪ!

ኦፕንኤአይ (OpenAI) ኩባንያ ሰኞ ዕለት ባወጣው መግለጫ፣ በፈጣን ፍጥነት እያደገ የመጣውን የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የደህንነት ስጋቶችን ለመቆጣጠር አሜሪካ ዓለም አቀፍ ደረጃዎችን የማውጣቱን ጥረት በግንባር ቀደምትነት እንድትመራ ጥሪ አቀረበ። የድርጅቱ ዋና ሥራ አስፈፃሚ ሳም አልትማን በዚህ ሳምንት ለተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የጸጥታው ምክር ቤት ልዩ ማብራሪያ ለመስጠት እየተዘጋጁ ሲሆን፣ በቴክኖሎጂው ምክንያት ሊፈጠሩ የሚችሉ አስከፊ አደጋዎችን ለመቀነስ ዓለም አቀፍ ትብብር ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል።

የደህንነት ስጋቱ የጎላው በቅርብ ጊዜ በሃጊንግ ፌስ (Hugging Face) የኮድ ማከማቻ ድረ-ገጽ ላይ የተከሰተውን የደህንነት ጥሰት ጨምሮ በርካታ ኩባንያዎች ላይ የሳይበር ጥቃቶች በመፈጸማቸው ነው። በተጨማሪም የ AI ቴክኖሎጂዎች የሰው ልጅ ጣልቃ ገብነት ሳይኖርባቸው "ራሳቸውን በራሳቸው በራስ-ገዝ የማስተማር እና የማሻሻል" (RSI) ደረጃ ላይ ከደረሱ ሊያመጡ የሚችሉት አደጋ ከፍተኛ በመሆኑ፣ ሙሉ በሙሉ ደህንነታቸው እስካልተረጋገጠ ድረስ ይህ ሂደት ሊገታ እንደሚገባ ኦፕንኤአይ አሳስቧል።

የተመድ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉተሬዝ በአሁኑ ወቅት የሀገር ውስጥ ቁጥጥር ብቻ በቂ እንዳልሆነና ዓለም አቀፍ ቅንጅት የግድ እንደሚያስፈልግ ለጋዜጠኞች ገልጸዋል። እንደ ኤሎን ማስክ እና የጎግል ዲፕማይንድ ዴሚስ ሃሳቢስ ያሉ የቴክኖሎጂው ዘርፍ ግዙፍ መሪዎች የ AI ልማት ፍጥነት እንዲቀንስ እና በአሜሪካ የሚመራ ዓለም አቀፍ ተቆጣጣሪ አካል እንዲቋቋም ድጋፋቸውን እየሰጡ ቢሆንም፣ ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን የተሰነዘሩትን ማስጠንቀቂያዎች "ሐሰተኛ ወሬ" በማለት ውድቅ አድርገውታል።

ሌላ ከፍታ አትሉም ! እንዲህ ወደ መፍትሔ ሲመጣ ሀሪፍ ነው ፤ አሜሪካ ትምራ የሚለው ጉዳይ ተቀባይነት ይኖረው ይሆን? የትራምፕስ የ Al እድገት ይቀጥል ሀሳብ ይቀለበስ ይሆን? በተመድ የፀፅታው ምክር ቤት ምን ይወሰን ይሆን? ቻይናስ አቋሟ ምንድን ነው? በጋራ እንመለከታለን!

#AI #ArtificialIntelligence #OpenAI
❤1
አሜሪካ እና ቻይና የኤአይ (AI) አደጋ ማስጠንቀቂያ ሥርዓት ለመዘርጋት እያሰቡ ነው!

የአሜሪካ እና የቻይና ከፍተኛ ባለሥልጣናት በዚህ ሳምንት በዋሽንግተን ከሚካሄደው የፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ እና የፕሬዚዳንት ሺ ጂንፒንግ ጉባኤ ቀደም ብለው በኒውዮርክ ተገናኝተው መክረዋል። የአሜሪካው የገንዘብ ሚኒስትር ስኮት ቤሰንት እንደገለጹት፥ ሁለቱ የዓለም የኤአይ ኃያላን አገራት በቴክኖሎጂው ዙሪያ ካለው ስውር አሠራር ወጥተው ይበልጥ ግልጽነት ለመፍጠር እና የብሔራዊ ደህንነት አደጋዎችን ለመቆጣጠር የሚያስችል “የጋራ አደጋ ማሳወቂያ ሥርዓት” ለመዘርጋት እያሰቡ ነው።

ይህ የትብብር ሐሳብ የቀረበው ሰሞኑን ከአንትሮፒክ (Anthropic) ተመራማሪዎች የተሰጠውን “ኤአይ በአሥር ዓመት ውስጥ የሰውን ልጅ ሊያጠፋ ይችላል”የሚለውን አስደንጋጭ ማስጠንቀቂያ ተከትሎ በዋሽንግተን ከፍተኛ ክርክር ባለበት ወቅት ነው። እንደ አንትሮፒክ፣ ኦፕንኤአይ እና ጎግል ያሉ መሪ የኤአይ ኩባንያዎች ሞዴሎቻቸውን በሚሞክሩበት ወቅት ከቁጥጥር ውጪ በመሆን የሌሎች ኩባንያዎችን ሥርዓት መጥለፋቸውን ይፋ ማድረጋቸው ስጋቱን ይበልጥ አጋግሎታል።

ፕሬዚዳንት ዶናልድ ትራምፕ ግን ቻይናን በኤአይ ልማት ቀድሞ መገኘት ትልቁ ግብ መሆን አለበት በማለት የልማት ፍጥነቱ እንዲቀንስ የሚቀርቡትን ጥሪዎች በጽኑ ተቃውመዋል። ትራምፕ ባለፈው ሳምንት በሰጡት መግለጫ “እኛ በኤአይ ከቻይና እየመራን ነው፤ በግልጽ ለመናገር በዚያው እንዲቀጥል እፈልጋለሁ፤ ምክንያቱም በኤአይ ያሸነፈ ሁሉንም ያሸንፋል” ሲሉ የዘርፉን የፉክክር ጥንካሬ ገልጸዋል።

ይህ የጋራ ማስጠንቀቂያ ስርአት ሁለቱ ሀገራት ተሰማምተውበት እውን አድርገውት ወደ ስራ ይገባ ይሆን?
በነገራችን ላይ ከዚህ ዘገባ የምንረዳው ቻይና ምን ያክል በAl አሜሪካን እየተገዳደረቻት እንደሆነ ትልቅ ማሳያ ነው።
❤3🔥2
"አርተፊሻል" የሚለው ስያሜ ወደ "ሱፐር" መቀየር አለበት!
ዶናልድ ትራምፕ በሀገራቸው እየተካሄደ ባለው 81 ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት (ተመድ) ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የወደፊት እጣ ፈንታን በተመለከተ መላውን ዓለም ያስገረመ አዲስ አቋም ይዘው ቀርበዋል። ትራምፕ ቴክኖሎጂውን ለመቆጣጠር የሚደረጉ ዓለም አቀፍ ጥረቶችን ሙሉ በሙሉ ውድቅ ማድረጋቸውን ይፋ አድርገዋል።

እንደ እሳቸው አገላለጽ፣ ይህ ዓይነቱ ዓለም አቀፍ ቁጥጥር የአሜሪካን የፈጠራ ስራዎች የሚያደናቅፍ እና የአገሪቱን ብሔራዊ ጥቅም አሳልፎ የሚሰጥ “የግሎባሊስት ሴራ” ነው። ይህ ንግግራቸው አሜሪካ በቴክኖሎጂው ዘርፍ ከቻይና እና ከሌሎች የዓለም ኃያላን አገራት ቀድማ ለመውጣት ማንኛውንም ዓይነት ዓለም አቀፍ እገዳ እንደማትቀበል በግልጽ ያሳየ አቋም ነበር።

በንግግራቸው ውስጥ እጅግ መነጋገሪያ የሆነው ሌላው ነጥብ፣ “አርተፊሻል ኢንተለጀንስ” የሚለውን የዘመናት ስያሜ ወደ "ሱፐር ኢንተለጀንስ" (SI) ለመቀየር የወሰኑት ውሳኔ ነው። ትራምፕ “አርተፊሻል” (ሰው ሰራሽ) የሚለው ቃል ቴክኖሎጂውን የውሸት ወይም ቀላል ነገር እንደሚያስመስለው በመጥቀስ፣ ከእንግዲህ በሁሉም የአሜሪካ መንግስት ሰነዶች ላይ ቴክኖሎጂው በላቀና ይበልጥ ትክክለኛ በሆነው “ሱፐር” በሚለው ቃል እንደሚተካ አስታውቀዋል። የዓለም መሪዎችንም ወደ አዲሱ የሱፐር ኢንተለጀንስ (SI) ዓለም እንኳን ደህና መጣችሁ በማለት ተቀብለዋል። ይሁን እንጅ በዚህ ስያሜያቸው ያጨበጨበ እና የተደነቀ ያለ አልመስለኝም! በሌላ መልኩ ቴክኖሎጂው ከኢንዱስትሪ አብዮትም ሆነ ከኢንተርኔት ፈጠራ በበለጠ የዓለምን ታሪክ እንደሚቀይር እና “ SIን ያሸነፈ፣ ሁሉንም ያሸንፋል” በሚል ጽኑ እምነት እንደሚመሩትም አስምረውበታል።

በተጨማሪም ትራምፕ ከተለያዩ ታዋቂ ሳይንቲስቶች እና ተመራማሪዎች የሚሰነዘሩትን የህልውና ስጋቶች በተለየ መልኩ አጣጥለዋል። “ይህ ቴክኖሎጂ የሰውን ልጅ ሊያጠፋ ይችላል” የሚሉ የጭንቀት ማስጠንቀቂያዎችን ቀደም ሲል “የውሸት ወሬ” (Hoax) ካሏቸው የአየር ንብረት ለውጥ ክርክሮች ጋር በማነጻጸር ውድቅ አድርገዋቸዋል። እርግጥ ነው፣ “ጥንቃቄ ማድረግ አለብን” የሚለውን ሃሳብ ባይክዱም፣ የእሳቸው አስተዳደር ዋነኛ ትኩረት ቴክኖሎጂውን መገደብ ሳይሆን እድገቱን በከፍተኛ ሁኔታ ማበረታታት እንደሆነ ግልጽ አድርገዋል።

ይሁን እንጂ ይህ የትራምፕ አቋም እንደ OpenAI እና Anthropic ካሉ የዓለማችን ግዙፍ የቴክኖሎጂ ኩባንያዎች ዋና ሥራ አስፈፃሚዎች ጋር የእውነት ይሁን የውሸት ባናውቅም ከፍተኛ ፍጥጫን ፈጥሯል። እነዚህ የቴክኖሎጂ መሪዎች በተመድ የፀጥታው ምክር ቤት ላይ ባደረጉት ገለፃ፣ የላቁ የAI ሞዴሎች ሊያመጡ የሚችሉትን አደጋ ለመከላከል ጠንካራ ዓለም አቀፍ የደህንነት ማዕቀፍ እና የጋራ ቁጥጥር የግድ እንደሚያስፈልግ አጥብቀው አሳስበዋል።

ይህ በትራምፕ አገራዊ የነፃነት ፖሊሲ እና በቴክኖሎጂ መሪዎቹ ዓለም አቀፍ የቁጥጥር ጥሪ መካከል የተፈጠረው ፍጥጫ፣ የወደፊቱን የቴክኖሎጂ ዓለም ወደ የት አቅጣጫ ሊመራው እንደሚችል የብዙዎችን ትኩረት ስቧል።

እናንተስ ይህን የፕሬዚዳንቱን ንግግር እና አቋም እንዴት አገኛችሁት? ወደ ተግባርስ ይገባ ይሆን? የቴክኖሎጂውን እድገትስ የት ያደርሰው ይሆን? ፖለቲካ ወይም የግል ሀሳብ የቴክኖሎጂ ፈጠራ ስያሜንስ የመቀየር አቅም? አለው ሀሳባችሁን አካፍሉን!

📌ቴሌግራም ቻናሌን ለማግኘት👇
https://t.me/miftahcode
❤3👍2
AI እና የኢትዮጵያ ቢዝነሶች!

የ10X ዕድገት ህልም ወይስ እውን ሊሆን የሚችል ዕድል?

​"የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) መምጣት በሰው ልጅ ታሪክ የታዩትን የቴክኖሎጂ አብዮቶች (እንደ ኢንተርኔትና የእንፋሎት ሞተር) ፍጥነት በ10 እጥፍ የሚበልጥ ነው። ይህ ቴክኖሎጂ በሚቀጥሉት ጥቂት ዓመታት ውስጥ የቢዝነሶችን ምርታማነት በ10 እጥፍ የማሳደግ (10x Productivity Upside) እምቅ አቅም አለው።"
— ከባንክ ኦፍ አሜሪካ የግሎባል ቴክኖሎጂ ሪፖርት የተወሰደ
​
አርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) የንግድ ድርጅቶችን በ10 እጥፍ (10X) የማሳደግ አቅም አለው የሚለው ሀሳብ በዓለም አቀፍ ደረጃ ትልቅ መነጋገሪያ ከሆነ ሰነባበተ። ነገር ግን ይህንን ቁልፍ ሀሳብ ከኢትዮጵያችን ነባራዊ ሁኔታ አንፃር እንዴት እንመዝነው? የሀገራችን የቢዝነስ መሪዎችስ ወደ ተግባር እየቀየሩት ነው ወይስ ገና በጉጉት ደረጃ ላይ ነን?
​
እውነታውን ስንገመግመው በኢትዮጵያ የAI ጉዞ ሁለት ገጽታዎች አሉት፦
1️⃣ ​በአንድ በኩል ትልቅ ተስፋ አለ!
🔹 የኢትዮጵያ አርተፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት መቋቋም እና የተለያዩ ተስፋ ሰጭ ስራዎችን እያከናወነ መሆኑ
🔹 የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ እና የ AI ፖሊሲ መፅደቅ
🔹 የስታርትአፕ አዋጅ ትግበራ እንዲሁም የግል ዳታ ጥበቃ አዋጅ መውጣት
🔹 በግብርና፣ ጤና፣ ሎጂስቲክስ እና ሌሎች ዘርፎች ላይ የተሰማሩ የሀገር ውስጥ ስታርትአፖች ወደ እንቅስቃሴ መግባታቸው
🔹 ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት ለዘርፉ የሰጡት ትኩረት እና ብቁ ባለሙያ ለመፍጠር እያደረጉት ያለው ጥረት እንደ ትልቅ ተስፋ የሚወሰዱ ናቸው።

2️⃣ ​በሌላ በኩል የሚገጥሙን ዋና ዋና ማነቆዎች፡
🔸 የመሠረተ ልማት እጥረት፡ AIን በስፋት ለመጠቀም አስተማማኝ ዳታ ሴንተሮች፣ ከፍተኛ የኮምፒዩቲንግ አቅም (High-Performance GPUs) እና ያልተቆራረጠ የሃይል አቅርቦት ማነስ።
🔸 የኢንተርኔት እና Cloud ፈተና፡ የኢንተርኔት ፍጥነትና ተደራሽነት ማነስ፣ እንዲሁም የCloud አገልግሎቶችን በውጭ ምንዛሬ ለመግዛት ያለው ፈተና።
🔸 የተደራጀ መረጃ (Data) አለመኖር
🔸 የክህሎት ክፍተት በተለይም Enduring Capability እና የኢንቨስትመንት ካፒታል ማጣት

​በአጭሩ የሀገራችን ቢዝነሶች የ10X ዕድገት እውን ሊሆን የሚችል ዕድል ነው ፤ ነገር ግን መጀመሪያ መሰረታዊ የቤት ስራዎቻችንን በሚገባ መስራት ይጠበቅብናል ብዬ አስባለሁ።
​
እናንተስ ምን ታስባላችሁ? የእናንተ መስሪያ ቤት ወይም ቢዝነስ የተደራጀ መረጃ አለው? AIንስ መጠቀም ጀምሯል? አስተያየታችሁን ኮሜንት ላይ አጋሩን👇
​
📩 AIን ወደ ቢዝነስዎ እንዴት ማካተት እንዳለብዎ የማማከር አገልግሎት የምትፈልጉ የቢዝነስ መሪዎች በ DM ልታናግሩኝ ትችላላችሁ።

​📌 የቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ፡ https://t.me/miftahcode
❤1👍1
Meta Page Assistant አገልግሎት መስጠት ጀምሯል!

ይህ በሰው ሰራሽ አስተውሎት (Artificial Intelligence) የተደገፈ ረዳት የፌስቡክ ገጻችሁን (Page) እድገትና ተደራሽነት ለማፋጠን የተዘጋጀ ሲሆን ረዳቱ የገጻችሁን እንቅስቃሴ መሰረት በማድረግ ቀጣይ ምን አይነት ይዘት (Content) ፖስት ማድረግ እንዳለባችሁ አዳዲስ እና ሳቢ ሀሳቦችን ያመነጫል። በተጨማሪም የፅሁፎቻችሁን እና የReels እይታዎች በጥቅል በመተንተን፣ እንዲሁም ተከታዮቻችሁ በብዛት መቼ Online እንደሚሆኑ በመንገር ፖስት የምታደርጉበትን ትክክለኛ ሰዓት እንድታውቁ ይረዳችኋል።

ይህንን አገልግሎት ለመጠቀም ወደ ገጻችሁ Professional Dashboard በመግባት የ AI ረዳቱን ምልክት (Icon) ከስር የተቀመጠ የትዕዛዝ ምርጫዎችን በመጫን መጀመር ትችላላችሁ። ረዳቱ የገጻችሁን የጎደሉ መረጃዎች በራሱ በማሟላት፣ የምክር ሀሳቦችን በመስጠት እና በተከታዮቻችሁ የተሰጡ ብዙ አስተያየቶችን (Comments) በአጭሩ በማጠቃለል ስራችሁን በእጅጉ ያቃልላል። አሁኑኑ በዳሽቦርዳችሁ በኩል ገብታችሁ በመሞከር የገጻችሁን እድገት ማፍጠን ትችላላችሁ!

📌 ለተጨማሪ ቴሌግራም ቻናሌን ይቀላቀሉ
https://t.me/miftahcode
👍6
እ.ኤ.አ. በ2000 ብሎክባስተር (Blockbuster) በፊልም ኪራይ ዘርፍ ላይ ፍጹም የበላይነት የነበረው መሪ ኩባንያ ነበረ። በሚሊዮን የሚቆጠሩ ደንበኞች በየሳምንቱ መጨረሻ ወደ የአካባቢያቸው መደብሮች ይጎርፉ ነበር፤ ይህም ኩባንያው በዓመት እስከ 5.9 ቢሊዮን ዶላር የሚደርስ ከፍተኛ ገቢ እንዲያገኝ አስችሎት ነበር። በድንገት ግን ኔትፍሊክስ (Netflix) የተባለች አንዲት ትንሽ አዲስ ኩባንያ (startup) አዲስ እሳቤ ይዛ ብቅ አለች ይህም ዲቪዲዎችን (DVDs) በፖስታ መላክ እና ምንም ዓይነት የዘገየ ክፍያ (late fees) አለማስከፈል።

ሃሳቡ በፍጥነት ተቀባይነትን እያገኘ ሲመጣ የኔትፍሊክስ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ሪድ ሐስቲንግስ (Reed Hastings) አንድ ዕድል ተመለከተ። ለብሎክባስተር ዋና ሥራ አስፈጻሚ ጆን አንቲኦኮ (John Antioco) መጠነኛ የሆነ የሽያጭ ጥያቄ አቀረበለት ኔትፍሊክስን በ50 ሚሊዮን ዶላር እንዲገዛው ጠየቀው ፤ ይህ ዋጋ የብሎክባስተርን ዓመታዊ ገቢ ከ1% ያነሰን ድርሻ የሚሸፍን ነበር። በንግድ ታሪክ ውስጥ ትልቅ ከሚባሉት ስልታዊ ስህተቶች (strategic misses) መካከል አንዱ በሆነው ውሳኔ፣ አንቲኦኮ ጥያቄውን በሳቅ ውድቅ አደረገው።

በወቅቱ አንቲኦኮ በብሎክባስተር የንግድ ሞዴል ላይ ሙሉ እምነት ነበረው በአካል የሚገኙ መደብሮች፣ የደንበኞች መመላለስ እና ደንበኞችን በዘገየ ክፍያ መቅጣት ይሁን እንጂ ኔትፍሊክስ ገበያውን እያሸነፈ ሲመጣ አንቲኦኮ ብሎክባስተር በማንኛውም ጊዜ ሊፈነዳ የሚችል ፈንጂ ላይ መሆኑን መገንዘብ ጀመረ።

ብሎክባስተር በዘርፉ መሪ ሆኖ ለመቀጠል እና ተወዳዳሪነቱን ለማስጠበቅ ካሰበ የንግድ ሞዴሉን መቀየር እንዳለበት የተረዳው አንቲኦኮ በ2004 እ.ኤ.አ ሁለት ትልልቅ ስልታዊ ውሳኔዎችን አስተላለፈ ፤ የራሱን የቪዲዮ ማሰራጫ አገልግሎት "ብሎክባስተር ኦንላይን" (Blockbuster Online) ለመፍጠር ሚሊዮኖችን ኢንቨስት ማድረግ እና ደንበኞችን ላለማጣት የዘገየ ክፍያን (Late Fees) ማስቀረት።

ነገር ግን የውስጥ የሥልጣን ሽኩቻ ነገሮችን አበላሸው። ቪያኮም (Viacom) የነበረውን ድርሻ ከሸጠ በኋላ ታዋቂው ባለሀብት ካርል ኢካን (Carl Icahn) የብሎክባስተርን አክሲዮኖች በብዛት በመግዛት የቦርድ አባል ሆነ። ኢካን ትኩረቱ ፈጣን ትርፍ ማግኘት ላይ ስለነበር የአንቲኦኮን የኦንላይን ኢንቨስትመንት እና የዘገየ ክፍያ መቅረትን አበክሮ ተቃወመ። በዚህ ሳቢያ በተፈጠረው አለመግባባት አንቲኦኮ በ2007 ኩባንያውን ለቆ ወጣ፤ ጂም ኬይስ (Jim Keyes) ሥልጣኑን ተረከበ። የኦንላይን ስትራቴጂው ትኩረት በማጣቱ ምክንያት በ2010 እ.ኤ.አ ብሎክባስተር በኪሳራ ሙሉ በሙሉ ከገበያ ጠፋ።

ስለ ብሎክባስተር ውድቀት መለስ ብሎ ሲያስብ አንቲኦኮ እንዲህ ሲል አምኗል “የእኛ የኦንላይን ስትራቴጂ ባይተው ኖሮ፤ ዛሬ ብሎክባስተር ኦንላይን አሥር ሚሊዮን ተመዝጋቢዎች ይኖሩት ነበር። በኢንተርኔት የማውረድ (downloading) ንግድ ውስጥ መሪ ለመሆን ከኔትፍሊክስ ጋር እንፎካከር ነበር።”

አንቲኦኮ ገና በ2000 ለውጥን እና ፈጠራን ተቀብሎ ቢሆን ኖሮ ምን ሊፈጠር ይችል ነበር? ኔትፍሊክስን በ50 ሚሊዮን ዶላር ቢገዛው ወይም ስለ ንግድ ሞዴሉ ዘላቂነት የነበረውን ቅድመ-ግምት እና አመለካከት ቢጠራጠር ኖሮስ? ብሎክባስተር አሁንም የፊልም ኪራይ ንጉሥ ሆኖ ይቀጥል ነበር? ይህንን መቼም አናውቅም።

እኛ የምናውቀው ነገር ቢኖር የምታደርጓቸው ውሳኔዎች የኩባንያችሁን ዕጣ ፈንታ የሚወስኑ እና የወደፊት ህልውናውን የሚቀርጹ መሆናቸውን ነው። ውሳኔዎች በጥሩ ሁኔታ ሲተገበሩ ኩባንያችሁ ውድድርን ቀድሞ እንዲወጣ እና ዘላቂ የፉክክር ብልጫ (sustainable competitive advantage) እንዲገነባ ይረዱታል። በአንጻሩ በተሳሳተ መንገድ ሲወሰኑ ግን ወደ ኪሳራ (bankruptcy) ሊያመሩ ይችላሉ። ንግድዎን በማሳደግ ወይም ከገበያ መውጣት መካከል ያለው ልዩነት በስትራቴጂካዊ አስተሳሰብዎ (Strategic Thinking) ላይ የተመሠረተ ነው።

ቁልፍ ጥያቄው ግን ቀጣዩ ብሎክባስተር እንዳትሆኑ እንዴት ፈጣን እና ብልህ ውሳኔዎችን ታደርጋላችሁ? የሚለው ነው። የአራዳ ልጅ አለያም ስትራቴጂክ አስተሳሰብ ካለህ ለምን በዚህ ጊዜ ይህንን ታሪክ እንዳቀረብኩት ይገባሀል።

ከወደዱት ሼር ያድርጉት!

ታሪክ፡ ከተለይዩ ድረ-ገጾች እና The AI-Driven Leader by Geoff Woods, 2024 የተወሰደ

📌 የቴሌግራም ቻናሌ፡ https://t.me/miftahcode
“ቴክኖሎጂ ብቻውን አያሸንፍም—አሸናፊ የሚያደርገው ዘላቂ አቅም (Enduring Capability) ነው!”

ይህንን ከታች የምጠቅሳቸው ሁሉ በደንብ ሊያስቡበት ይገባል፡-

የፖሊሲ አውጪዎች እና የመንግስት አካላት
የሀገር መከላከያ እና የደህንነት ተቋማት
የግል ባለሀብቶች እና የቢዝነስ መሪዎች
ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት (ዩኒቨርሲቲዎች)

Enduring Capability ላይ በሚገባ ሊሰራ ይገባል ሀሳቤ ነው፡፡
🔥2❤1👏1
መረጃን (Data) ወደ ውሳኔ መቀየር ለንግድ እና ለፕሮጀክት ስኬት ወሳኝ ነው! 📊

እንደ Power BI እና Tableau ያሉ የዳታ ማቅረቢያ (Data Visualization) መሣሪያዎች የተበታተኑ መረጃዎችን በቀላሉ ወደሚረዱ ግራፎች እና ሪፖርቶች በመቀየር የንግድ ድርጅቶች ፈጣንና ትክክለኛ ውሳኔ እንዲወስኑ ያግዛሉ። Al assisted ጨመር ካደረጋችሁበት ደግሞ ሌላ ታሪክ ነው።

ለተቋማችሁ ወይም ለግል ስራችሁ የትኛውን የዳታ ትንተና መሣሪያ (SPSS, Power BI, Excel, Tableau) በብዛት ትጠቀማላችሁ? አስተያየታችሁን ኮሜንት ላይ አጋሩን! 👇

አስፈላጊ ሊንኮች:-
1️⃣ Power BI ሶፍትዌር ለማግኘት እና አካውንት ለመክፈት
https://app.powerbi.com/
2️⃣ Tableau ሶፍትዌር ለማግኘት እና ለማውረድ
https://www.tableau.com/access/download/public
3️⃣ ስለ Tableau አጠቃቀም ለመማር
https://www.tableau.com/learn
4️⃣ ስለ Power Bl ለመማር
https://learn.microsoft.com/en-us/training/powerplatform/power-bi
❤1
ባለፉት አመታት ፌስቡክ ላይ ያዋልኩትን ጊዜ 1/4 እንኳን LinkedIn አውየው በነበር የማገኘው ግላዊ ጥቅም በጣም ብዙ ይሆን ነበር።

አላማዬ የማውቀውን ማሳወቅ፣ ወገኖቼን በምችለው ሁሉ ማገዝ ነው! ይህን አላማዬን ለማሳሳት ደግሞ ትክክለኛው መድረክ ፌስቡክ ነው። እዚያኛው መድረክ ላይ ገና ነን ገና!

በዚህ አጋጣሚም የ LinkedIn አካውንት እንዲኖራችሁ እመክራለሁ ምክንያቱም ፕሮፌሽናል በሆነ መልኩ Interact ማድረግ ካሰብን ትክክለኛው ቦታ ያ ነው! ምክንያቱም እዚያ ያሉት Silicon valley to Addis የትልልቅ ቢዝነስ እና ተቋማት መሪዎች ፣ የኢንዱስትሪ ባለቤቶች ፣ ዲቨሎፐሮች ወ.ዘ.ተ

በእናንተ ፍቅር ❤️ እና ወዳጅነት ብዙ እያተረፍኩ ስለሆነ ባጣሁት እና ባለፈው አልቆጭም ፤ ባይሆን ጎን ለጎን እመራዋለሁ!

​📌 LinkedIn ላይ እንገናኝ/Connect እናድርግ:
👉 https://www.linkedin.com/in/mohammedet
❤1
ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) በንግድ እና በስራው ዓለም ላይ የሚያሳድረው ተፅዕኖ!

ዛሬ ላይ AI የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች ብቻ የሚወያዩበት ርዕስ መሆኑ አብቅቷል። ከምርት ዲዛይን እና ከፋይናንስ ትንበያ ጀምሮ እስከ የስራ አፈፃፀም እና ገበያ ማስተዋወቅ (Marketing) ድረስ AI እና Machine Learning የማንኛውም ድርጅት መሪዎች የዕለት ተዕለት መሣሪያ እየሆኑ መጥተዋል። በተለይ በውጩ አለም በፍጥነት እያደገ እና እየተለመደ ነው። እኛ ሀገር ገና ጅምር ቢሆንም ማደጉ ግን አይቀሬ ነው።

🤔 ታዲያ ከእኛ ምን ይጠበቃል?
1️⃣ መሠረታዊ ግንዛቤ መጨበጥ፦ ቴክኖሎጂውን በመሠረታዊ ደረጃ ካልተረዳነው፣ በድርጅታችን የተጣራ ትርፍ (Bottom line) እና ስትራቴጂካዊ ዕድገት ላይ ተፅዕኖ የሚያሳድሩ ብልህ ውሳኔዎችን ማሳለፍ አንችልም።

2️⃣ የነገውን የስራ ዓለም መረዳት፦ AI የሥራ አስኪያጆችን እና የመሪዎችን ሚና ጨምሮ የነገውን የሙያ ዓለም ሙሉ በሙሉ እየለወጠው ነው። ይህንን ለውጥ አለመገንዘብ በሙያዊ ጉዞአችን ላይ ትልቅ መሰናክል ሊፈጥር ይችላል።

ለወደፊቱ የስራ ዓለም ዝግጁ ለመሆን ቴክኖሎጂውን አሁኑኑ መማር እና መተግበር መጀመር የጊዜው ጥያቄ ነው!

#ArtificialIntelligence #MachineLearning
❤1