Mohammed Seid - Miftah
3.2K subscribers
149 photos
5 videos
10 files
120 links
​🛠 Digital Skills | AI | Innovation
📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች።
👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡
https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/
Download Telegram
የአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) እና የህግ የበላይነት፡ ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ እና ዩኔስኮ የሚሰጥ ነጻ ኮርስ! 🚀

​ቴክኖሎጂ በየዕለቱ እየገሰገሰ ሲመጣ፣ የፍትህ ስርዓቶች እና የዳኝነት ስራዎችም ጭምር የ AI ድጋፍን እየተጠቀሙ ይገኛሉ። ይህ ደግሞ አዳዲስ ዕድሎችን ይዞ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ስለ ፍትሃዊነት፣ ግልጽነት እና ተጠያቂነት በርካታ ጥያቄዎችን እያስነሳ ነው።
​ዩኔስኮ (UNESCO) ከኦክስፎርድ ዩኒቨርሲቲ (Saïd Business School, Blavatnik School of Government እና Faculty of Law) ጋር በመተባበር ያዘጋጀው "AI, Justice, and the Rule of Law" የተሰኘ አለም አቀፍ ነጻ ኮርስ እድል ይኸውና!

​ስለ ኮርሱ ማወቅ የሚገቡ ዋና ዋና ነጥቦች፦

​ለማን ተዘጋጀ? ለህግ ባለሙያዎች፣ ለፖሊሲ አውጪዎች፣ እንዲሁም በቴክኖሎጂ እና በህግ ግንኙነት ዙሪያ ፍላጎት ላላቸው ሁሉ (ምንም ቅድመ የቴክኒክ እውቀት አያስፈልግም!)።

​የሚወስደው ጊዜ፦ 18 ሰዓታት አካባቢ (በራሳችን ፍጥነት self-paced መማር የሚቻል)።

​ክፍያ፦ ሙሉ በሙሉ በነጻ (በዩኔስኮ እና በአውሮፓ ህብረት ድጋፍ የተሸፈነ)።

​ሰርተፍኬት፦ ኮርሱን ሲያጠናቅቁ ኦፊሴላዊ የኦክስፎርድ ዲጂታል ሰርተፍኬት ያገኛሉ።

​አርተፊሻል ኢንተለጀንስ በህብረተሰባችን እና በፍትህ ስርዓቱ ላይ የሚያመጣውን ተጽዕኖ በሰብአዊ መብት ማዕቀፍ ውስጥ ሆኖ ለመረዳት ይህን እድል መጠቀም እንችላለን።

​🔗 ለመመዝገብ፦

https://secure.sbs.ox.ac.uk/corporate/landingPage.do?method=load&corporateGroupId=7948447

​#AI #RuleOfLaw #UNESCO #OxfordUniversity #TechEducation #Miftah@miftahcode
❤5
Stella Juva በዓለም ላይ በፀሐይ ኃይል የሚሠራ የመጀመሪያው የሞባይል ክሊኒክ (አምቡላንስ) ሲሆን፥ የኤሌክትሪክ እና የነዳጅ አቅርቦት በሌለባቸው ራቅ ያሉ የገጠር አካባቢዎች የሕክምና አገልግሎት ለማድረስ የተሰራ አስደናቂ የቴክኖሎጂ ውጤት ነው። ይህንን ዘመናዊ ተሽከርካሪ የሰሩት በኔዘርላንድስ የሚገኘው የኢንድሆቨን ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ 23 ተማሪዎች ሲሆኑ፣ ዓላማቸውም የመንገድ እና የኃይል መሠረተ ልማት በሌላቸው ቦታዎች የሚኖሩ ማህበረሰቦችን ተጠቃሚ ማድረግ ነው።

ተሽከርካሪው በላዩ ላይ በተገጠሙ የሶላር ፓነሎች አማካኝነት ንጹህ ኃይል የሚያመነጭ ሲሆን፥ ፀሐያማ በሆነ ቀን እስከ 715 ኪሎ ሜትር የመጓዝ አቅም አለው። የሕክምና መሣሪያዎቹ የሚጠቀሙት የኃይል ሥርዓት ከተሽከርካሪው መሪ ባትሪ የተለየ በመሆኑ የሕክምና አገልግሎቱ በጉዞ ርቀቱ ላይ ምንም ዓይነት ተጽዕኖ አይፈጥርም። በቅርቡም ከአምሬፍ ጤና አፍሪካ (Amref Health Africa) ጋር በመተባበር በኬንያ ወጣ ገባ መንገዶች ላይ የ800 ኪሎ ሜትር የሙከራ ጉዞን በስኬት አጠናቋል።

ይህ ፈጠራ ዘላቂነት ያለው የፈጠራ ቴክኖሎጂ ፈታኝ በሆኑ የዓለማችን ክፍሎች ላይ እንዴት የሰዎችን ሕይወት ማዳን እንደሚቻል ያሳየ ትልቅ ተስፋ ነው።

#SolarTeamEindhoven #StellaJuva #GreenTech #SolarPower #GlobalHealth #AmrefHealthAfrica
ለሂሳብ (Math) ትምህርት ልዩ ድጋፍ የሚሰጡ፣ ጥያቄዎችን በፎቶ ወይም በፅሁፍ ተቀብለው ደረጃ በደረጃ የሚያብራሩ 5 ምርጥ የAI መተግበሪያዎች፦

1️⃣ Photomath: አስቸጋሪ የሂሳብ ጥያቄዎችን በስልክ ካሜራ ፎቶ በማንሳት ብቻ እያንዳንዱን የአሰራር ደረጃ በዝርዝር የሚያሳይ መተግበሪያ። photomath.com

2️⃣ Symbolab: ለአልጀብራ፣ ካልኩለስ እና ትሪጎኖሜትሪ ጥያቄዎች እጅግ በጣም ዝርዝር የሆነ የአሰራር ቅደም ተከተል እና ግራፎችን የሚሰጥ የሂሳብ መፍቻ። symbolab.com

3️⃣ Mathway: ከመሰረታዊ ሂሳብ እስከ ከፍተኛ የኮሌጅ ሂሳብ ጥያቄዎችን በፍጥነት የሚመልስ የካሊኩሌተር እና የAI ጥምረት። mathway.com

4️⃣ Wolfram Alpha: የተወሳሰቡ የሂሳብ ቀመሮችን፣ እኩልዮሾችን (equations) እና የሳይንስ ጥያቄዎችን በከፍተኛ ትክክለኛነት የሚሰላ የምርምር ሞተር። wolframalpha.com

5️⃣ Microsoft Math Solver: በነጻ ጥያቄዎችን በስክሪኑ ላይ በመጻፍ ወይም ፎቶ በማንሳት መፍትሄ የሚሰጥ እና ተመሳሳይ ተጨማሪ የማለማመጃ ጥያቄዎችን የሚያቀርብ። |https://mathsolver.microsoft.com/

ለተጨማሪ መረጃ፦
ፌስቡክ: https://www.facebook.com/Miftahcode
❤3👍1
ነፃ የ Generative AI ኮርስ ከ Microsoft! (Version 3)

የ AI መተግበሪያዎችን ከባዶ መገንባት ይማሩ! በ Microsoft Cloud Advocates የተዘጋጀው Generative AI for Beginners ኮርስ በ 21 ክፍሎች ተሻሽሎ ቀርቧል።

ዋና ዋና ይዘቶች፡
🎥 አጫጭር የማብራሪያ ቪዲዮዎች እና ዝርዝር የፅሁፍ ትምህርቶች
💻 በ Python እና TypeScript የተዘጋጁ የተግባር (Coding) ልምምዶች
🔄 ቲዎሪ ("Learn") እና ተግባራዊ ኮዲንግ ("Build") ያካተተ
🌐 ሞዴሎችን ያለ ኢንተርኔት በራስዎ መሣሪያ ላይ ማስኬድ የሚያስችል Foundry Local አገልግሎት
🤝 የ Microsoft Foundry Discord ማህበረሰብ ድጋፍ እና ለ Startup ፈጣሪዎች የ Azure Credits እድል

🛠 ለመጀመር፡ የ Python/TypeScript መሰረታዊ እውቀት፣ GitHub አካውንት እና የ API መዳረሻ (Azure OpenAI፣ OpenAI API፣ Microsoft Foundry Models ወይም Foundry Local) ያስፈልጋል።

🎯 አሁኑኑ ይጀምሩ፡ GitHub ላይ "Generative AI for Beginners by Microsoft" ብለው ይፈልጉ! ማከማቻውን (Repository) Star (🌟) ማድረግ እንዳይረሱ!

የኮርሱን እና ሌሎች ጠቃሚ ሊንኮችን:
↗️ Generative AI for Beginners (Version 3)

↗️ How to Create a GitHub Account (Step-by-Step for Beginners)Amharic ጊትሃብ አካውንት መክፈት በአማርኛ

↗️ Run local AI on any PC or Mac - Microsoft Foundry Local

↗️ Microsoft AI foundry Discord
👍4
ሂሳብ ማለት ቁጥር መደመር ብቻ ነው ወይንስ የአስተሳሰብና የፈጠራ መሠረት? ለዚህ አስተያየት የሚሆን ጠንከር ያለ ምላሽ ያላችሁ የሂሳብና የኮምፒዩተር ሳይንስ ሰዎች ድምፃችሁን አሰሙ!

በነገራችን ላይ ብዙዎች እንደዚህ ያስባሉ በትምህርት ቤት ውስጥ ያሉ ተማሪዎች ሳይቀር !
❤3
ችግሩ ለምን እንደሚጠቅም መቼ እና የት እንደሚተገበር አልነገሩንም እንጂ ሒሳብ እማኮ ...😍 እናም እንውደደው በቅጡ እንማረው!
❤2
mit6_042js15_textbook.pdf
5.5 MB
📚 Mathematics for Computer Science

​ለኮምፒውተር ሳይንስ፣ ለሶፍትዌር ኢንጂነሪንግ እና ለ-AI/ML መሠረታዊ የሆነውን ሂሳብ (Mathematics) በጥበብ የሚያስረዳ ድንቅ መጽሐፍ!
በ Massachusetts Institute of Technology ምሁራኖች የተዘጋጀ !

OR

https://ocw.mit.edu/courses/6-042j-mathematics-for-computer-science-spring-2015/mit6_042js15_textbook.pdf
📚 ለሁለተኛ ደረጃ እና ለኮሌጅ ተማሪዎች የሚሆን ድንቅ የትምህርት መረጃ!
​
የፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ ባዮሎጂ ወይም የጠፈር ሳይንስ (Astronomy) ትምህርቶችን በነፃ እና በከፍተኛ ጥራት ማጥናት ይፈልጋሉ?
​
OpenStax በታወቀው Rice University የሚዘጋጅ፣ በዓለም አቀፍ ደረጃ እውቅና ያላቸውን የሳይንስ መጽሐፍት በነፃ (PDF) ማውረድ የሚያስችል ድንቅ ገፅ ነው!
​
📌 የሚገኙ ዋና ዋና የትምህርት ዘርፎች፡
↗️​Physics (Introductory, College & University Physics)
↗️​Chemistry (General Chemistry, Organic Chemistry)
↗️​Biology (Concepts of Biology, Anatomy & Physiology)
↗️​Astronomy
↗️Mathematics
↗️Computer Science እና ሌሎችም
​
መጽሐፍቶችን በነፃ ለማውረድ እና ለማንበብ ከታች ያለውን ሊንክ ይጠቀሙ፡
👉 https://openstax.org/
​መረጃውን ለወንድም፣ እህቶቻችሁ እና ለተማሪ ወዳጆቻችሁ በማጋራት (Share) ተደራሽ አድርጉት!
❤6👍2
🚀 በነጻ የዲጂታል ማርኬቲንግ ሰርቲፊኬት ማግኘት ይፈልጋሉ?
ዓለም ወደ ዲጂታል እየተቀየረች ባለችበት በዚህ ጊዜ፣ የዲጂታል ማርኬቲንግ እውቀት ለምንም አይነት ቢዝነስ ወይም ሙያ ወሳኝ ነው!

ታዋቂው እና ልምድ ያለው HubSpot Academy ሙሉ በሙሉ በነጻ የሚሰጠውን Digital Marketing Certification Course ጥቆማ ልስጣችሁ። በብዙ የገጻችን ተከታዮች የተወደደ ኮርስ ነው።

ከዚህ ኮርስ ምን ያተርፋሉ?
➡️SEO (Search Engine Optimization): ዌብሳይትን በፍለጋ አማራጮች ላይ የመጀመሪያ ደረጃ እንዲታይ ማውጣት
➡️Social Media & Content Strategy: ሳቢ ይዘቶችን በመፍጠር የሶሻል ሚድያ ተከታዮችን ማሳደግ
➡️Email & Ads Strategy: ውጤታማ የኢሜይል እና የክፍያ ማስታወቂያዎችን መስራት
➡️ Inbound Marketing: ደንበኞችን በራስ አቅም መሳብ እና ማቅረብ

🎯 ለማን የሚሆን ኮርስ ነው? የራሳቸውን ቢዝነስ ማሳደግ ለሚፈልጉ፣ ማርኬተሮች፣ የኦንላይን ስራ ጀምረው ገቢ ማግኘት ለሚፈልጉ እና አዳዲስ የዲጂታል ክህሎቶችን ማዳበር ለሚፈልግ ማንኛውም ሰው!

📌 ትምህርቱ በራስዎ ጊዜ የሚወሰድ (Self-paced) ሲሆን ሲጨርሱም ዓለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርቲፊኬት ያገኛሉ።

🔗 አሁኑኑ ይመዝገቡ፦ የምዝገባ ሊንክ⤵️
https://academy.hubspot.com/courses/digital-marketing
ይህንን መረጃ ለሌሎችም Share ያድርጉት! 💡
❤4
🤖 ChatGPT የኬንያውያንን ወጣቶች ጉሮሮ ዘጋው! 😂

ለዓመታት የአሜሪካና የአውሮፓ ተማሪዎችን የቤት ሥራ እና Essay በገንዘብ በመጻፍ Freelance ዶላር ሲያፍሱ የነበሩ የኬንያ ወጣቶች፣ አሁን ላይ ሥራቸውን በ #ChatGPT ተነጥቀዋል።

«ተማሪዎቹ ከእኛ ይልቅ AIን በነፃ ማዘዝ መረጡ» ያሉት ወጣቶቹ ፣ አሁን ደግሞ አዲስ ሥራ ጀምረዋል፦ “AI የጻፈውን ጽሑፍ የሰው ልጅ የጻፈው ለማስመሰል ማስተካከል!” 🏃‍♂️💨
አይ ቴክኖሎጂ... ምን እነሱን ብቻ! 😄

ይህን መረጃ ያጋራው The New York Times ነው!
👍8❤1
በቻናላችን መረጃዎች😍 ደስተኛ ናችሁ?
Anonymous Poll
67%
እጅግ በጣም
22%
በጣም
11%
ደህና
ከቴሌግራም ቻናላችን ፋይል ማውረድ ፣ የወደዳችሁትን ሼር ለማረግ መቸገራችሁ ይታወቃል። በሰጣችሁኝ አስተያየት መሰረት ክልክላውን አንስቻለሁ!

ፋይል ማውረድ ፣ ለሌሎቹ ሼር ማድረግ አሁን ይቻላል!

አ መ ሰ ግ ና ለ ሁ!

Stay Connected 🥰
❤6👍3
ስቴፈን ሃውኪንግን ከዛሬ 10 አመት በፊት ስለ Al የተናገረውን ንግግር ስመለከት በጣም ገረመኝ። 🤔

ዛሬ እኛ የምንገረምበትን የ-AI እድገት ሳያይ ነበር ያኔ ያስጠነቀቀው። 'ካወቅንበት ምርጡ ነገር ነው፣ ካልተጠነቀቅንበት ግን የከፋው አደጋ ነው' ያለው ሃሳብ ዛሬ ላይ ሆነን ስናየው ይበልጥ እውነት ሆኗል!

የሳይንቲስቱን ሀሳብ እንዴት አያችሁት?
❤1
በጣም የገረመኝ እና ደፋር ሪፖርት ነው።

ጫናው ዘርፈ- ብዙ ነው ፤ ከአሜሪካ ዶላር ጋር በተያያዘ ኢኮኖሚያችንን ጠፍሮ የያዘው ሳያንሰን በዚህ በኩልም ምክረ-ሀሳብ አለኝ እያለ ነው፡፡

በተከታይ እዳስሰዋለሁ!

እስኪ ኮሜንት ላይ እንወያይበት? እውነት የአለም ባንክ ምክረ-ሀሳብ ነው ምርጫችን? ለዚህ የሚሆን ዝግጁነትስ የለንም?

ለበለጠ ቴሌግራም ቻናሌ ⤵️
https://t.me/miftahcode
ብዙ ጊዜ የተለያዩ ጥናቶችን ስንመለከት ወይም ሚዲያ ላይ ስንሰማ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ለ White-Collar Jobs ስጋት ነው ይባላል። በመሆኑ ምን ማለት ይሆን? ለምንስ ስጋት ሆነባቸው?

ቴሌግራም⤵️
https://t.me/miftahcode
❤4
Mohammed Seid - Miftah
C++ Programing In Amharic Part I Yohannes Ezezew.pdf
C++ ኘሮግራሚንግ በአማርኛ ክፍል አንድ (C++ Programing In Amharic Part I)
👍6❤1
🤖 ከ AI ቻትቦቶች ጋር የምንፈልገውን ምርጥ ውጤት ለማግኘት ቁልፉ ያለው ጥያቄ አጠያየቃችን (Prompt Engineering) ላይ ነው!

​ከ AI ጋር ውጤታማ ውይይት ለማድረግ እነዚህን 2 ወሳኝ ነጥቦች ተግብሩ፡

​1️⃣ ጥሩ ጥያቄ (Prompt) ማዘጋጀት፡ የምትፈልጉትን ነገር በግልጽ፣ በዝርዝር እና ለ AIው ሚና (Role) ሰጥታችሁ ጠይቁት።

2️⃣ ውይይቱን እዚያው ማሻሻል (Iterate)፡ የመጀመሪያው መልስ ካልረካችሁ አዲስ Chat ከመክፈት ይልቅ፣ እዚያው የጀመራችሁት ውይይት ላይ ጥያቄያችሁን እያስተካከላችሁና እያጠራችሁ ሂዱ።

​💡 አስተውሉ፡ AI መልስ የሚሰጠው እኛ በሰጠነው መመሪያ ልክ ነው!

​📌 ለተጨማሪ ጠቃሚ የቴክኖሎጂና AI መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡
👉 https://t.me/miftahcode

👉 ምስሉ ላይ ያለውን ጥያቄ ውጤቱን ለማየት በዚህ ሊንክ ማየት ትችላላቸሁ፡ https://share.gemini.google/2mEBqlt51NDC
❤2
Alን ተጠቅመን የሞባይል መተግበሪያ ለማበልፀግ ለ Al agent ወይም ቻትቦት እንዴት ትዕዛዝ እንሰጣለን ⤵️

👉 ምሳሌውን በ Google Al Studio መሞከር ትችላላችሁ

​📌 ለተጨማሪ ጠቃሚ የቴክኖሎጂና AI መረጃዎች የቴሌግራም ቻናላችንን ይቀላቀሉ፡
👉 https://t.me/miftahcode
❤2👍2