Mohammed Seid - Miftah
3.21K subscribers
149 photos
5 videos
10 files
121 links
​🛠 Digital Skills | AI | Innovation
📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች።
👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡
https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/
Download Telegram
⚠️ ጠቃሚ ማሳሰቢያ ለEthioCodars የኮርስ ተሳታፊዎች!

​የኮርስ ምዝገባ ስርዓታችን ሙሉ በሙሉ ተስተካክሎ በመስራት ላይ ይገኛል። ይሁን እንጂ አንዳንዶቻችሁ አሁንም "Application Pending" የሚል መልእክት እያያችሁ እንደሆነ እየገለጻችሁልን ይገኛል።

​ምክንያቱ ምንድን ነው?
ብራውዘሮች (Browsers) ቀደም ሲል የነበረውን መረጃ (Cache) በመያዛቸው፣ አዲሱን የሲስተም ማሻሻያ መቀበል ሳይችሉ ሲቀር የሚከሰት ነው ፤ ችግሩ ከሲስተሙ ሳይሆን ከብራውዘራችን የማስታወስ ችሎታ ጋር የተያያዘ ነው።

​እንዴት ይስተካከል?
የምትጠቀሙበትን ብራውዘር Cache እና Cookies በማጽዳት (Clear በማድረግ) ወይም ሳይቱን በድጋሚ (Hard Refresh) በማድረግ ችግሩን በቀላሉ መፍታት ትችላላችሁ።

​ለበለጠ ግንዛቤ ከዚህ በታች የተያያዘውን የምስል መመሪያ በመከተል ብራውዘራችሁን አጽዱ፤ ችግሩ ወዲያውኑ ይስተካከላል!
❤7
❤1
ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ: የኦፕንኤአይ (OpenAI) ሰው ሰራሽ አስተውሎት ሞዴሎች በራሳቸው ሌላ ኩባንያ መጥለፋቸውን አስታወቁ

የ OpenAI ዋና ስራ አስፈጻሚ ሳም አልትማን ፣ በጣም የላቁ ሁለት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) ሞዴሎቹ ቁጥጥር ከሚደረግበት የሙከራ አካባቢ አምልጠው ሌላ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መጥለፋቸው ታወቀ።

ኩባንያው ማክሰኞ ዕለት እንደገለጸው፣ ይህ “ ከዚህ በፊት ታይቶ የማይታወቅ የሳይበር ጥቃት ክስተት” የተከሰተው የሞዴሎቹን የሳይበር አቅም ለመፈተሽ በተደረገ የውስጥ ሙከራ ወቅት ነው።

በአዲሱ የ GPT 5.6 Sol እና እስካሁን ይፋ ባልሆነ ይበልጥ ኃይለኛ ሞዴል የሚመራው ራሱን የቻለ (autonomous) አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ወኪል (agent) ከሙከራ አካባቢው አምልጦ ወደ ኢንተርኔት አለሙ በመውጣት የ Hugging Face ሰርቨሮችን መድረስ ችለዋል። ይህንን ለማድረግም የተሰረቁ የመግቢያ መረጃዎችን (login details) መጠቀማቸውን እና ከዚህ ቀደም የማይታወቅ የደህንነት ግድፈት (security flaw) ማግኘቱን ኩባንያው ገልጿል።

የ Hugging Face ተባባሪ መስራች ክሌመንት ዴላንግ (Clement Delangue) ጥቃቱ የደረሰው ከዋና ዋናዎቹ የላቦራቶሪዎች ውስጥ በአንዱ እንደሆነ ጥርጣሬ እንደነበራቸው ገልጸው፣ የኦፕንአይ ድርጊት ሆነ ተብሎ የታሰበ የክፉ አድራጎት ዓላማ ያለው እንዳልሆነ እንደሚያምኑ ተናግረዋል።

“ይህ ሁሉ በራሳቸው በኤጀንት ሞዴሎቹ መፈጸሙ በጣም የሚያስገርም ነው!” ሲሉ የገለጹት ክሌመንት፣ይህ ጥቃት “በዓይነቱ የመጀመሪያው ክስተት ሊሆን ይችላል” ብለዋል።

የዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስ ግዛት የምክር ቤት አባል የሆኑት ግሬግ ካሳር፣ ክስተቱን “አስደንጋጭ” ሲሉ ገልጸውታል።

“አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ደህንነታችንን የሚጠብቅ እውነተኛ ደንብ ሳይኖር በከፍተኛ ፍጥነት እያደገ ነው” በማለት አስጠንቅቀዋል። በ ኤአይ ደህንነት ዙሪአ ዓለም አቀፍ ትብብር እንዲኖር ጥሪ አቅርብዋል።

ይህ ሪፓርት ይፋ የተደረገው ፣ የአሜሪካው ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ እጅግ የላቁ የሰው ሰራሽ አስተውሎት ስርዓቶች ለህዝብ ከመለቀቃቸው በፊት ብሄራዊ የደህንነት ስጋቶቻቸውን የሚገመግም ማዕቀፍ የሚፈጥር አስፈፃሚ ትዕዛዝ ከፈረሙ ከጥቂት ሳምንታት በኋላ ነው።

የቴክኖሎጂ ባለሙያዎች በአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ አማካኝነት ስለሚፈጸሙ የሳይበር ጥቃቶች እና ሞዴሎች ከሰው ቁጥጥር ውጭ ስለመውጣታቸው በተደጋጋሚ ማስጠንቀቂያዎችን ሲሰጡ ቆይተዋል።

ጎበዝ ህልውናችን አደጋ ላይ ነው! ይህን ዜና እንዴት አያችሁት ፤ ምንስ ተረዳችሁ?
❤1😁1
አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (AI)፣ ክላውድ ኮምፒውቲንግ እና ዲጂታል ትራንስፎርሜሽን በዓለም አቀፍ ደረጃ ከፍተኛ እመርታ እያሳዩ እየሄዱ ሲሆን ፣ የሳይበር አደጋዎችም ይበልጥ እየተወሳሰቡ እና እየተስፋፉ መጥተዋል።

​በመሆኑም አሁን ላይ ጥንቃቄ ማድረግ አለብን ፤ ራሳችንንም ሆነ ድርጅታችንን ከሳይበር ጥቃት እንዴት ልንጠብቅ እና ልንከላከል እንችላለን የሚለውን አጥብቀን ልናስብበት ይገባል! የሳይበር ደህንነት (Cybersecurity) ክህሎት ለዚህ ወሳኝ መፍትሄ ነው።

በዚህ ዘርፍ የሚሰማራ የሰው ሀይልም ተፈላጊነቱ አጠያያቂ አይደለም!
👍1
🛑 የባንክ ፒን (PIN) እና የይለፍ ቃል፡ ሊያነቡት የሚገባ እጅግ ወሳኝ የዲጂታል ደህንነት መረጃ!
ቀላል የሚመስለው እና በቀላሉ ልንረሳው ስለማንችል የምንጠቀመው ባለ 4 አሃዝ ፒን (PIN) ምን ያህል አደገኛ ሊሆን እንደሚችል አስበን እናውቃለን?

ከ 0000 እስከ 9999 ያሉት አጠቃላይ የቁጥር አማራጮች 10,000 ብቻ ናቸው። የሳይበር ጠላፊዎች የሚጠቀሙባቸው ዘመናዊ የኮምፒውተር ሶፍትዌሮች (Brute Force Attack) እነዚህን ጥቂት አማራጮች በሰከንዶች ውስጥ በመፈተሽ ሊሰብሯቸው ይችላሉ። ይህ ማለት 4 ዲጂት ኮድ ስንጠቀም አደጋ ውስጥ ነን ማለት ነው።

🤔 ታዲያ ይህ ከሆነ ባንኮች እና ድርጅቶች ለምን ባለ 4 አሃዝ ፒን እንድንጠቀም ያደርጉናል?
ባንኮች ይህንን ቁጥር እንዲጠቀሙ የሚፈቅዱት ለከፍተኛ ደህንነታቸው ሲሉ ሳይሆን ለተጠቃሚ ምቾት (Usability) ብለው ነው። ሆኖም ግን ከጀርባ የሚከተሉትን ጠንካራ የደህንነት ግድግዳዎች ይጠቀማሉ፦

የሙከራ ገደብ (Rate Limiting / Lockout): ፒኑን ከ 3 እስከ 5 ጊዜ በላይ ከተሳሳቱ አካውንቱ በራሱ ይዘጋል። ይህ ደግሞ ጠላፊዎች በኮምፒውተር አማካኝነት 10,000ውንም ቁጥር በአንድ ጊዜ እንዳይሞክሩ አግዶ ይይዛል።

ተጨማሪ ማረጋገጫ (OTP / 2FA): ባንክ ውስጥ ገንዘብ ሲያስተላልፉ ከሞባይልዎ የሚመጣውን የአጭር ጊዜ ኮድ (OTP) ሳያካትቱ ፒኑ ብቻውን ምንም ስራ አይሰራም።

🛡️ ራሳችንን እንዴት እንጠብቅ?

የተለያዩ ኮዶችን መጠቀም፡ ለሁሉም አካውንቶቻችን አንድ አይነት ባለ 4 አሃዝ ፒን ከመጠቀም መቆጠብ ፤ ተመሳሳይ ፒን እና ፓስወርድ በተጠቀምን ቁጥር ለሳይበር ጥቃት የመጋለጥ እድላችን እየጨመረ ይሄዳል።

ረዘም ያሉ የይለፍ ቃሎችን ተጠቀሙ፡ የማህበራዊ ሚዲያ እና የኢሜል አካውንታችሁ ላይ ቁጥሮችን ብቻ ሳይሆን ፊደላትን እና ምልክቶችን በማቀላቀል ረዘም ያለ የይለፍ ቃል አድርጉ። ይህን ካደርግን የመጠልፍ እድላችንን እናጠባለን።

ባዮሜትሪክ (Biometrics) ተጠቀሙ፡ የጣት አሻራ (Fingerprint) ወይም የፊት መለያ (Face ID) መጠቀም ተጨማሪ እና አስተማማኝ የደህንነት ሽፋን ይሰጣችኋል።

ዲጂታል ህይወታችሁን ከሳይበር አደጋዎች ጠብቁ! 🔒💻

#CyberSecurity #TechTips #DigitalSafety #MiftahTech #Ethiopia
❤4👏3
ዛሬ ስለአንድ አደገኛ እና በፍጥነት እየተስፋፋ ስለመጣ የቴክኖሎጂ ክስተት – ዲፕፌክ (Deepfake) እና ከወትሮው ሐሰተኛ ዜና (Fake News) ጋር ስላለው ልዩነት እናወራለን።
​
ዲፕፌክ (Deepfake) ምንድን ነው?
​«ዲፕፌክ» ማለት በአርተፊሻል ኢንተለጀንስ (AI) ቴክኖሎጂ የሚዘጋጅ የሐሰት ቪዲዮ፣ ድምጽ ወይም ፎቶ ነው። በቀላል አነጋገር፤ በእውነት ያልተደረገ ወይም ያልተነገረ ነገር ግን እጅግ በተቀናጀ ቴክኖሎጂ እንደ እውነት ተደርጎ የሚቀርብ ማሽን ሰራሽ ምስል ወይም ድምጽ ማለት ነው።

ቴክኖሎጂው ሁለት ዋና ዋና መንገዶች አሉት። አንደኛው የፊት ቅያሬ (Face Swap) ሲሆን፣ አንድ ታዋቂ ሰው ፈጽሞ ያላደረገውን ነገር ሲያደርግ የሚያሳይ ቪዲዮ በኮምፒዩተር ይዘጋጃል። በዚህ ጊዜ ፊቱም ድምጹም የእሱ ቢሆንም፣ ፈጽሞ ያንን አላደረገም። ሁለተኛው ደግሞ የድምጽ ቅጂ (Voice Cloning) ሲሆን፣ የሰውን ድምጽ ንግግር በጥቂት ሰከንዶች ብቻ በማዳመጥ/ በመኮረጅ ያ ሰው በህይወት የሌለውን ወይም በጭራሽ ያልተናገረውን ነገር በራሱ ድምጽ እንዲናገር አድርጎ ማቀናበር ይቻላል።
​
ከሐሰተኛ ዜና (Fake News) በምን ይለያል?
​ብዙ ሰዎች ዲፕፌክን እና ሐሰተኛ ዜናን አንድ አድርገው ያስባሉ፤ ነገር ግን ትልቅ ልዩነት አላቸው። ሐሰተኛ ዜና (Fake News) አብዛኛውን ጊዜ በጽሁፍ፣ በወሬ ወይም በተራ ፎቶ የሚሰራጭ ሐሰተኛ መረጃ ሲሆን፦ "እነከሌ ይህንን ተናገሩ" እያለ በጽሁፍ ይነገራል።

​በሌላ በኩል ዲፕፌክ (Deepfake) ከዚህ በላይ የሄደ ነው። ማስተባበያ የማይሰጥበት ደረጃ ለማድረስ የሰዎችን ፊት እና ድምጽ ራሱ በማቀናበር ዓይንህ እያየ እውነት አስመስሎ የሚያቀርብ የከፍተኛ ቴክኖሎጂ ማታለያ ነው። በአጭሩ፤ ሐሰተኛ ዜና የሐሰቱ መልእክት ሲሆን፣ ዲፕፌክ ደግሞ ያንን ሐሰት እውነት ለማስመሰል የሚጠቀሙበት የቪዲዮ እና የድምጽ ማታለያ መሳሪያ ነው።

በሌላ መልኩ እና በግልጽ ቋንቋ ቴክኖሎጂ በጣም እያደገ ሲመጣ deep fake'ን መለየት የሚቻለው በስሜት ህዋሳችን ሳይሆን በረቀቀ መሳሪያ ብቻ ነው።

​ቴክኖሎጂው እየተሻሻለ ሲመጣ ማየት እና መስማት ብቻውን እውነት መሆኑን ለማመን አያስደፍርም። ስለዚህ በማህበራዊ ሚዲያ የምናያቸውን ነገሮች ሁሉ ከማጋራታችን በፊት በንቃት እንመርምር!

ለምሳሌ ከታች ያያዝኩት ምስል AI ሰራሽ ሲሆን እንዴት ሚዲያዎች እንደተጠቀሙበት ተመልከቱ

​ይህ መረጃ ጠቃሚ ሆኖ ካገኛችሁት ሼር (Share) በማድረግ ለሌሎች ግንዛቤ እንፍጠር
❤3👍1
🌐 ዲጂታል ማርኬቲንግ በነፃ ለመማር ለምትፈልጉ ሁሉ ተመራጭ ኮርስ!

100% 🆓 ነው!
🎓 ኮርሱን ስትጨርሱ አለም አቀፍ እውቅና ያለው ሰርተፊኬት ታገኛላችሁ!

ኮርሱን ለመጀመር ⬇️
https://academy.hubspot.com/courses/digital-marketing
PHISHING
ነገረ ሳይበር ደህንነት (#Phishing) Part 03

ፊሺንግ (Phishing) ወይም የዲጂታል ማታለያ ወጥመድ፡ ምንነቱ፣ አደጋው እና እራሳችንን የምንጠብቅባቸው መንገዶች ፦

በአሁኑ ዲጂታል ዘመን የቴክኖሎጂ አጠቃቀማችን እየጨመረ በመጣ ቁጥር፣ የሳይበር ወንጀለኞች ሰዎችን ለማጭበርበር የሚጠቀሙባቸው ስልቶችም እጅግ ረቂቅ እየሆኑ መጥተዋል። ከእነዚህ የሳይበር ጥቃቶች መካከል በስፋትና በተደጋጋሚ የሚከሰተው ፊሺንግ (Phishing) ወይም የማታለያ ወጥመድ ይባላል። ፊሺንግ ማለት ዲጂታል ሌቦች እንደ ባንክ፣ የኢንተርኔት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶች፣ ታዋቂ የንግድ ተቋማት ወይም የቅርብ ጓደኛ በመምሰል የሐሰት መልዕክቶችን የሚያሰራጩበት መንገድ ነው። ዋና ዓላማቸውም የተጠቃሚዎችን የልብ ትኩረት በመሳብ ወይም በማስፈራራት የእጅ ስልክ ቁጥርን፣ የባንክ ሚስጥራዊ ቁጥርን (PIN)፣ የሶሻል ሚዲያ የይለፍ ቃላትን (Password) ወይም የገንዘብ ማስተላለፊያ ማረጋገጫ ኮዶችን (OTP) ሰርቆ መውሰድ ነው። ይህንን ወጥመድ ልክ አንድ ዓሣ አጥማጅ መንጠቆው ላይ ትል አድርጎ ዓሣ እንደሚያጠምደው ሁሉ፣ እነሱም የሐሰት አሸናፊነት ማስታወቂያዎችን ወይም አስፈሪ ማስጠንቀቂያዎችን እንደ ማጥመጃ በመጠቀም ሰዎችን ያጠምዳሉ።

እነዚህ አጥማጆች መልዕክቶቻቸውን ለማድረስ የተለያዩ የዲጂታል መገናኛ ዘዴዎችን ይጠቀማሉ። በብዛት የሚታወቀውና ስልካችን ላይ የሚመጣው የኤስኤምኤስ (SMS) ማጭበርበር ሲሆን፣ "የባንክ አካውንትዎ ወይም የቴሌብር አካውንትዎ ተቆልፏል፤ አሁኑኑ በዚህ ሊንክ ገብተው ካላስተካከሉ አካውንትዎ ይዘጋል" የሚሉ መልዕክቶችን ይልካሉ። በሌላ በኩል ደግሞ በቴሌግራም፣ በፌስቡክና በዋትስአፕ ግሩፖች ላይ "ይህንን ሊንክ ተጭነው የነፃ ኢንተርኔት ወይም የነፃ የገንዘብ ስጦታ ያግኙ፣ ለሌሎች 50 ሰዎችም ያጋሩ" የሚሉ የሐሰት ማስታወቂያዎችን ያሰራጫሉ። ከዚህ በተጨማሪም በቀጥታ የስልክ ጥሪ በመደወል "ከባንክ ዋና መሥሪያ ቤት ወይም ከኢትዮ ቴሌኮም ቴክኒክ ክፍል ነው የምንደውለው፤ ሲስተም እየቀየርን ስለሆነ አሁን ስልክዎ ላይ የሚመጣውን 6 አሃዝ ኮድ ይንገሩን" በማለት ሰዎችን ግራ በማጋባት አካውንታቸውን ሙሉ በሙሉ ይቆጣጠሩታል።

ይህንን የዲጂታል ሌቦች ወጥመድ በቀላሉ ለይተን የምናውቅባቸው ጥቂት የአደጋ ምልክቶች (Red Flags) አሉ። የመጀመሪያው ምልክት 'አስቸኳይነት' ነው፤ ወንጀለኞቹ ቆም ብለን እንድንጠረጥርና እንድንመራመር ጊዜ አይሰጡንም። "አሁኑኑ ካላደረጉት አካውንትዎ ይዘጋል" በማለት እንድንደናገጥ ያደርጉናል። ሁለተኛው ምልክት ደግሞ የተሳሳቱና የተለወጡ ሊንኮች (URLs) ናቸው። ለምሳሌ የባንኩን ትክክለኛ ድረ-ገጽ ስም በትንሹ በመለወጥ (ከመደበኛው cbe. com. et ፋንታ cbe-bonus. com ወይም cbe-lottery. net በማድረግ) የሐሰት ገጽ ያዘጋጃሉ። ሌላው ትልቁ ምልክት፣ ሳይወዳደሩ ወይም ሳይሳተፉ "እጅግ ከፍተኛ የገንዘብ ወይም የዕቃ ስጦታ አሸነፉ" የሚሉ ከመጠን ያለፉና እውነት የማይመስሉ ማባበያዎች ናቸው።

እራሳችንን እና ንብረታችንን ከዚህ የፊሺንግ አደጋ ለመጠበቅ ሁልጊዜም ተግባራዊ ልናደርጋቸው የሚገቡ ወሳኝ መከላከያዎች አሉ። ከሁሉም በላይ በማንኛውም ሁኔታ ስልካችን ላይ የሚመጣን የባንክ ወይም የሶሻል ሚዲያ ማረጋገጫ ኮድ (OTP) ለባንክ ሠራተኛም ቢሆን በፍጹም አሳልፎ አለመስጠት ዋናው መከላከያ ነው። ባንኮችም ሆኑ ታዋቂ ድርጅቶች ደንበኞቻቸውን ሚስጥራዊ ቁጥር እንዲናገሩ በስልክ ወይም በቴክስት በፍጹም አይጠይቁም። በተጨማሪም የማናውቀው ሰው በቴሌግራም ወይም በኤስኤምኤስ የላከልንን ማንኛውንም ሊንክ (Link) ከመንካት መቆጠብ እና ጥርጣሬ ሲኖር ወደ ድርጅቶቹ ይፋዊ እና መደበኛ ስልክ ደውሎ ማረጋገጥ ተገቢ ነው። ዲጂታል ደህንነት የሚጀምረው በንቃትና ባለመቸኮል በመሆኑ፣ ማንኛውንም መልዕክት ስናይ ቆም ብለን ማስተዋል ከሳይበር ሌቦች ይጠብቀናል።

እስኪ በዚህ ወጥመድ ውስጥ ገብታችሁ የነበራችሁ ታሪካችሁን ሼር አድርጉን ? ሰዎች እንዲማሩበት መልካም ፈቃዳችሁ ከሆነ⬇️
❤4👍2
🆓ነፃ የ Cybersecurity ኮርስ ⤵️

ከ Cisco Networking Academy
🎓 ሰርተፊኬት እና ባጅ ያለው!

Link⬇️
Introduction to Cybersecurity
❤1
የሰው ልጅ አእምሮ እውነትም ድንቅ ነው!

💡ዛሬ በአለማችን ላይ የምናያቸው፣ በስጋትም ይሁን በአዎንታ የምንገረምባቸው ታላላቅ ቴክኖሎጂዎች በሙሉ የዚሁ ድንቅ አእምሮ ውጤቶች ናቸው።

የሰው ልጅ አእምሮ ተአምረኛ ነው። ✨🧠

ለመሆኑ እናንተን ይበልጥ ያስደመማችሁ ወይስ ስጋት የፈጠረባችሁ ቴክኖሎጂ የትኛው ነው? ከታች በኮሜንት እንወያይበት👇
👍2
አንዳንዴ የሰው ልጅ ምንለ Alን ባልፈጠረ ብዬ የማስብባቸው አጋጣሚዎች አሉ! በተለይ ጉዳቶቹን ሳስባቸው የሚፈጠርብኝ ስሜት ነው። እኔም ሆንኩ ብዙሀኑ እያወራን ያለነው ስለ ጥቅሙ ስለሆነ!

እርግጥ ነው AI ከግብርና እስከ ህክምና Transform ማድረጉ አይቀሬ ነው። ኧረ እንዳውም የአለምን GDP ከ 7 -14% ይለውጣል እያለን የምዕራባውያን ጥናት! መታወቅ ያለበት መራራ ሐቅ ግን ከነ ጉዳቱ ነው። ያው ሁሉም የሳይቴክ ፈጠራዎች የራሱ የሆነ ጥቅምና ጉዳት እንዳላቸው ሁሉ! የሚደንቀው ደግሞ ከዚህ በፊት ከነበሩት እንደ ኤሌክትሪክ ፣ ስልክና ኢንተርኔት ፈጠራዎች እድገት ፍጥነት በላይ (Exponential Speed) መሆኑ ነው፡፡ ዛሬ መብራት የሌለበት አካባቢ Al አለ!

በ 2023 በ Al ዘርፍ የኖቤል ተሸላሚው (Godfathers of AI) ዶ/ር ጄፍሪ ሂንተን ስጋት ውስጥ ገብቶ "AI የሰውን ዘር እስከ ማጥፋት ሊደርስ የሚችል አደጋ አለው በማለት ጥንቃቄ እንዲደረግ እና የእድገት ፍጥነቱ እንዲመረመር ሲጠይቅ" በሌላ ጎራ ደግሞ የሜታ ዋና የአይ አይ ሳይንቲስት ያንግ ለኩን እና የጉግል ብሬይን ተባባሪ መስራች አንድሪው ንግ በ ዶ/ር ጄፍሪ ሀሳብ አይሰማሙም ሁለቱ ሳይንቲስቶች የሂንተን ስጋት "እጅግ የተጋነነ እና ሳይንሳዊ መሰረት የሌለው (Overhyped)" ነው ብለው ይመለከቱታል። የጎራ ልዩነቱ እና ክርክሩ እንደቀጠለ ቴክኖሎጂውም ከቀን ወደ ቀን እየተሻሻለ እና እያደገ ነው።

ይህ ቴክኖሎጂ አሁን ካየነው አቅም በላይስ ያድግ ይሆን? 🤔 የእናንተስ እይታ ምንድን ነው? እንወያይበት
👍1
ቴክኖሎጂው (AI) እንደ ረዳት መሳሪያ (Tool) እንጂ እንደ ዋና ውሳኔ ሰጪ መሆን የለበትም።
❤2
ኤሮቢክ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ (Aerobic exercise) ለአንጎል ጤና ከሁሉ በላይ ጠንካራው መሣሪያ ተደርጎ ይወሰዳል።

ለአንጎል ክፍልፋዮች (ሂፖካምፐስ እና ቅድመ ግንባር አንጎል ክፍሎች) ድጋፍ የሚሰጡ የእድገት ሆርሞኖች እንዲለቀቁ በማድረግ ስሜትን፣ ማስታወስን እና ትኩረትን ያሻሽላል።

ምን ይደረጋል ስፖርት ላይ ሰነፍ ነኝ! ማሻሻል አለብን በአርግጥ እንደ ዘርፉ ባለሙያዎች ከሆነ የስፖርት ጥቅም የትየለሌ ነው።
❤4👍1
🍿POPCORN BRAIN
🍿 "ፖፕኮርን ብሬን" (Popcorn Brain) ምንድን ነው? አእምሯችን በዲጂታል ዓለም ውስጥ እየጠፋ ይሆን? 🧠📱
ስራ ላይ ወይም ፊልም እያያችሁ ስልካችሁን ትከፍታላችሁ? ወይስ መጽሐፍ ማንበብ ጀምራችሁ ገና ሁለት ገጽ ሳትጨርሱ ወደ ቲክቶክ ወይም ፌስቡክ ትሮጣላችሁ? ይህ አሁን ላይ የአብዛኞቻችን የዕለት ተዕለት ፈተና ሆኗል። ሳይንቲስቶች ይህንን ክስተት "ፖፕኮርን ብሬን" (Popcorn Brain) ይሉታል።
ይህ ስያሜ እ.ኤ.አ በ2011 በዋሽንግተን ዩኒቨርሲቲ ተመራማሪ ዴቪድ ሌቪ የተዋወቀ ሲሆን፥ ሀሳባችን ልክ በሙቀት ላይ እንዳለ የበቆሎ ፍሬ (ፖፕኮርን) ከአንዱ ርዕስ ወደ ሌላው፣ ከአንዱ መተግበሪያ ወደ ሌላው በፍጥነት የሚፈናጠርበትን የአእምሮ መበታተን ሁኔታ ይገልጻል። ይህ የህክምና በሽታ አይደለም፤ ነገር ግን አእምሯችን ከመጠን በላይ ለፈጣን የዲጂታል መረጃዎች በመጋለጡ ምክንያት ትኩረት የማሰባሰብ አቅሙ ሲዳከም የሚፈጠር "የለመደው ስንፍና" ነው።
🔍 የ"ፖፕኮርን ብሬን" ዋና ዋና ምልክቶች
የዚህ ክስተት የመጀመሪያው ምልክት ፈጣን የስራ መለዋወጥ (Task-Switching) ሲሆን፣ አንድን ስራ ወይም ጥናት ሳትጨርሱ በየደቂቃው ስልክ ማየትን ያካትታል። ሌላው ደግሞ ሁለት ስክሪን በአንድ ጊዜ መጠቀም ነው፤ ለምሳሌ ቲቪ ወይም ላፕቶፕ ላይ እየሰራችሁ በሌላ እጅ ስልክ መጎብኘት። በተጨማሪም ስልክን ያለ ምክንያት የመንካት አባዜ ይታያል፤ ማለትም ስልኩ ምንም አይነት ድምፅ ወይም የፅሁፍ ምልክት ሳይሰጥ "እስቲ ልክፈተው" በሚል ስሜት በየደቂቃው መክፈት ነው። በመጨረሻም እረፍት ማጣት እና መሰልቸት ይከተላል፤ ለምሳሌ ባንክ ውስጥ ወይም ትራንስፖርት እየጠበቃችሁ ለ5 ደቂቃ እንኳን ስልክ ሳትነኩ መታገስ አለመቻልን ያሳያል።
🔬 ከጀርባው ያለው ሳይንስ
እኛ ፌስቡክ ላይ ስንገባ፣ አጫጭር ቪዲዮዎችን (Reels) ስናይ፣ ወይም የላይክ (Like) እና ኮሜንት ቁጥሮችን በየደቂቃው ስናድስ በአእምሯችን ውስጥ "ዶፓሚን" (Dopamine) የተባለ የደስታ ኬሚካል ይረጫል። የማህበራዊ ሚዲያ ስልተ-ቀመሮች (Algorithms) የተሰሩት አእምሯችን ይህንን ፈጣን እና ቀላል እርካታ እንዲለምድ አድርገው ነው።
በዚህ ምክንያት፣ እንደ መጽሐፍ ማንበብ፣ ስራ መስራት ወይም ጥልቅ ውይይት ማድረግ ያሉ "ቀስ ያሉ" እና ትኩረት የሚሹ ተግባራት ለአእምሯችን እጅግ አሰልቺ እና ከባድ ይሆኑበታል። በጥናቶች መሠረት፣ እ.ኤ.አ በ2004 የሰው ልጅ በአማካይ በአንድ ስክሪን ላይ የሚሰጠው ትኩረት 2.5 ደቂቃ የነበረ ሲሆን፥ አሁን ግን ከ50 ሰከንድ በታች ወርዷል!
🛠 አእምሯችንን ለመታደግ እና ትኩረታችንን ለመመለስ የሚረዱ የመፍትሄ እርምጃዎች
ይህ የተለመደ ልማድ እንጂ የአእምሮ ጉዳት ስላልሆነ በትዕግስት እና በተግባራዊ እርምጃዎች መቀየር ይቻላል። በመጀመሪያ የማህበራዊ ሚዲያ ማስታወቂያዎችን (Notifications) አጥፉ፤ የላይክ፣ የኮሜንት እና የቡድን መልዕክቶች ድምፅ አእምሯችሁን በየደቂቃው እንዳይረብሸው ሙሉ በሙሉ (Turn Off) አድርጉት። ስልኩ አይጥራችሁ፤ እናንተ ስትፈልጉ ብቻ ክፈቱት። 📴
ሁለተኛው መፍትሔ ለማህበራዊ ሚዲያ የጊዜ ገደብ መስጠት (Time-Blocking) ነው፤ ለምሳሌ "ፌስቡክ የምከፍተው ጠዋት፣ ከሰዓት እና ማታ ለ15 ደቂቃ ብቻ ነው" ብላችሁ ወስኑ። ስልኩን ስትከፍቱ የሰዓት መቆጣጠሪያ (Timer) ሞልታችሁ ግቡ እና ሰዓቱ ሲያልቅ ወዲያውኑ ውጡ። ⏳
ሦስተኛው ደግሞ አንድ ስራ ላይ ብቻ ማተኮርን መልመድ (Single-Tasking) ነው፤ በቀን ውስጥ ቢያንስ ለ20 ደቂቃ ስልካችሁን ሙሉ በሙሉ አጥፍታችሁ ወይም አርቃችሁ በማስቀመጥ መጽሐፍ አንብቡ፣ ፅሁፍ ጻፉ ወይም የአካል ብቃት እንቅስቃሴ አድርጉ። 📖
በመጨረሻም አጭር የአእምሮ እረፍት መውሰድ ተመራጭ ነው፤ ደክሟችሁ ማረፍ ስትፈልጉ ስልክ ከመነካካት ይልቅ፥ ዓይኖቻችሁን ጨፍናችሁ ለ5 ደቂቃ ጥልቅ ትንፋሽ መውሰድ ወይም ፀጥ ባለ ቦታ መቀመጥ አእምሯችሁ ራሱን እንዲያድስ (Reset) ይረዳዋል። 🚶‍♂️
📌 ማጠቃለያ
መልዕክቴ ለሁላችንም ነው፦ ቴክኖሎጂን ህይወታችንን ለማቅለል እንጠቀምበት እንጂ እሱ እኛን እና ውድ ጊዜያችንን እንዲቆጣጠረን አንፍቀድለት። ዛሬውኑ የመጀመሪያውን እርምጃ ጀምሩ!
💬 እስቲ እንወያይ፦
እናንተስ ዘንድ ይህ የ"ፖፕኮርን ብሬን" ምልክት ይታያል? ከላይ ከተጠቀሱት መፍትሔዎች ውስጥ የትኛውን ዛሬውኑ ለመጀመር ትመርጣላችሁ? (ማስታወቂያዎችን ማጥፋት ወይስ ስልክን ከአይን ማራቅ?) ሀሳባችሁን በኮሜንት አጋሩን ፤ ለወዳጃችሁም ሼር (Share) በማድረግ አድርሱት! 👇
❤4👍1
ሶሻል ሚዲያን ለበጎ አላማ የሚጠቀሙትን ያብዛልን! 🤲
​ዲጂታል መድረኮቻችንን ለትክክለኛና በጎ ዓላማ እንጠቀምባቸው።

​✅ ሰዎችን ለመርዳትና ለማነቃቃት፣
✅ ማህበረሰባችንን በአዎንታዊ መልኩ ለመለወጥ፣
✅ ሀገራችንን በሰናይ ተግባር ከፍ ለማድረግ።

​መልካም ነገር እናስብ፤ መልካም እናጋራ! 🌍🤝
❤3👏1
በርከት የፌስቡክ ገፅ እና የቴሌግራም ቻናላችን ተከታዬች የወስዷቸው እና የወደዷቸው ነፃ ኮርሶች:
1. Data Fundamentals and more free course
2. Networking Basics
3. Digital Marketing
❤1