Mohammed Seid - Miftah
3.21K subscribers
150 photos
5 videos
10 files
122 links
​🛠 Digital Skills | AI | Innovation
📢 አዳዲስ የቴክኖሎጂ ዜናዎች እና መፍትሄዎች።
👇 ፌስቡክ ላይም ያግኙኝ፡
https://www.facebook.com/share/1ANudUpgYu/
Download Telegram
የቴክኖሎጂ አቅማችሁን በነጻ ከፍ አድርጉ! 🚀

የቴክኖሎጂው ዓለም በፍጥነት እየተቀየረ ነው። እንደ AI፣ ዳታ ሳይንስ እና ሳይበር ሴኩሪቲ ያሉ ዘርፎች የወደፊቱን የሥራ ዓለም እየቀየሩ ናቸው። እናንተስ ለዚህ ዝግጁ ናችሁ?

የቴክኖሎጂው ፈር ቀዳጅ IBM የተለያዩ የዲጂታል ክህሎቶችን በነጻ ለመማር ትክክለኛ ምርጫ ነው። በ IBM SkillsBuild በኩል በነጻ የሙያ ክህሎታችሁን የምታሳድጉበትን ዕድል ማግኘት ትችላላችሁ።

ምን ልንማር እንችላለን?

➡️አርቴፊሻል ኢንተለጀንስ (Artificial Intelligence): ከዘመኑ ጋር አብሮ ለመራመድ።
➡️ሳይበር ሴኩሪቲ (Cybersecurity): የዲጂታል ደህንነትዎን ለማረጋገጥ።
➡️ዳታ መሰረታዊ እውቀት (Data Fundamentals): መረጃን በመጠቀም የተሻለ ውሳኔ ለመስጠት።

ይህ እውቀት ለሙያዊ ዕድገታችሁ ትልቅ መነሻ ሊሆን ይችላል። አሁኑኑ ጀምሩት እና የሰርቲፊኬት ባለቤት ይሁኑ! 🎓
ሊንክ፡ https://www.ibm.com/account/reg/us-en/signup

#TechSkills #IBM #SkillsBuild #FreeLearning
🥰1👏1
EthioCodersን በተመለከተ በድጋሜ ለማሳሰብ
👍5❤1
WEF_Future_of_Jobs_Report_2025.pdf
17.7 MB
የዓለም ኢኮኖሚክ ፎረም የ2025 የሥራ ዕድሎች ጥናት እንደሚያሳየው፣ የቴክኖሎጂ አቅም፣ አርቲፊሻል ኢንተለጀንስ እና አውቶሜሽን ከዳታ መግቢያ እስከ የሂሳብና የጽሕፈት ቤት ሥራዎች ድረስ ያሉ ባህላዊ የሥራ ዘርፎችን በፍጥነት እየቀየሩ ይገኛሉ። ይህ ለውጥ በተወሰኑ የሥራ ዘርፎች ላይ መቀነስን ቢያመጣም፣ ለሰው ልጅ የሥራ አቅም ማጎልበቻ (augmentation) እና አዳዲስ የፈጠራ ስራዎች ሰፊ እድልን እየከፈተ ነው። በመሆኑም፣ አሁን ያለው የሥራ ዓለም ከቴክኖሎጂ ጋር አብሮ የሚሰራ፣ አዳዲስ ዲጂታል ክህሎቶችን የሚያዳብር እና ለቀጣይ የሥራ እድሎች ዝግጁ የሆነ የሰው ኃይልን ይጠይቃል።
ለማንኛውም ሙሉ ጥናቱን እንድታነቡት ግብዣዬ ነው! 😘
❤2👍2
የኢትዮጵያ መንግስት እና የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች የ"5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች" ኢንሼቲቭን ወደ 7 ሚሊዮን ከፍ እንዲል ተደረገ
​የተባበሩት አረብ ኢምሬቶች እና ኢትዮጵያ በጋራ በመሆን ሲያካሂዱት የነበረውን "5 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን ኮደሮች" ኢንቨቲቭ ወደ 7 ሚሊዮን ከፍ ማድረጋቸውን የ ኢሚሬት የዜና ወኪል ማምሻውን ይፋ አድርጓል። ከዚህ በፊት ይፋ የተደረገው የ 5M ቁጥር መሙላቱን ተከትሎ በ Udacity በኩል ሰሞኑን አዲስ ምዝገባ እንደማይቀበል መዘገቤ የሚታወስ ሲሆን አሁን የተደረገውን የ 2M ጭማሬ መሰረት አድርጎ ምዝገባ ሲቀበል መረጃ የማደርሳችሁ ይሆናል። ኢንሻአላህ

Stay Connected 🥰
👍19❤2
ማሽኖች መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ፤ ነገር ግን ውሳኔው የሰው መሆን አለበት!" - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ
ማሽኖች መረጃ ሊሰጡ ይችላሉ፤ ነገር ግን ውሳኔው የሰው መሆን አለበት!" - የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ዋና ጸሐፊ 🚨🤖
​በጄኔቫ በተካሄደው የመጀመርያው የተባበሩት መንግሥታት የሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI) አስተዳደር ዓለም አቀፍ ውይይት ላይ፣ ዋና ጸሐፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ በቴክኖሎጂው ዙሪያ አስቸኳይ ዓለም አቀፍ ቁጥጥር እንዲደረግ ጥሪ አቅርበዋል።
​ዋና ጸሐፊው በንግግራቸው ያነሷቸው ዋና ዋና ነጥቦች፡
​🔹 "ገዳይ ሮቦቶች"፦ ለሰላማዊ አገልግሎት የተፈጠሩ ኃይለኛ የAI ቺፖች ወደ ጦር ሜዳ እየገቡ መሆናቸው አደገኛ አዝማሚያ መሆኑን ገልጸዋል። በራስ ገዝ የሚንቀሳቀሱ "ገዳይ ሮቦቶች" በአሁኑ ወቅት የተለመዱ መሆናቸውን በመጥቀስ፣ የዓለም መንግሥታት የቴክኖሎጂውን አጠቃቀም በሕግ ሊገድቡ እንደሚገባ አስጠንቅቀዋል።
​🔹 የሕጻናት ደህንነት ቅድሚያ ይስጠው፦ "ምንም ሕጻን ለተቆጣጠርነው የAI ቴክኖሎጂ የሙከራ አይጥ መሆን የለበትም" ያሉት ዋና ጸሐፊው፣ ኩባንያዎች የAI ምርቶቻቸውን ለሕጻናት ከማቅረባቸው በፊት ደህንነታቸው የተረጋገጠ መሆኑን ማረጋገጥ እንዳለባቸው አሳስበዋል። በተለይም ሕጻናትን የሚያካትቱ የወሲብ ይዘቶች ላይ "ዜሮ መቻቻል" (Zero Tolerance) ሊኖር እንደሚገባ አስምረውበታል።
​🔹 የሰው ልጅ ውሳኔ፦ AI በፍትህ፣ በጤና እና በፖሊስ ዘርፎች መረጃ ሊሰጥ ቢችልም፣ የመጨረሻው ውሳኔ ሰጪና ተጠያቂ የሰው ልጅ መሆን እንዳለበት አጽንኦት ሰጥተዋል።
​🔹 የዲጂታል ክፍፍልን ማጥበብ፦ AI የሀብታሞች ብቻ መሆን የለበትም። በማደግ ላይ ያሉ አገራት የቴክኖሎጂው ተጠቃሚ እንዲሆኑ ዓለም አቀፍ የትብብር መረብ እንዲቋቋም ጥሪ አቅርበዋል።
​🔹 አካባቢ ጥበቃ፦ በ2030 ሁሉም የAI መረጃ ማዕከላት (Data Centres) በታዳሽ የኃይል ምንጭ እንዲሰሩ ጉቴሬስ ጥሪ አቅርበዋል።
​ቴክኖሎጂው ለሰው ልጅ ትልቅ ዕድል ቢሆንም፣ በአግባቡ ካልተያዘ ግን አደጋው የከፋ ሊሆን እንደሚችል ተመልክቷል።
​ለበለጠ መረጃ እና ዝርዝር ጉዳዮች፣ ይህንን የUN News ሊንክ ይመልከቱ፡ https://news.un.org/en/story/2026/07/1167873
❤2
ብያችሁ ነበር ! 😱
ኢኮደርስን በተመለከተ ፡

ዛሬም አዲስ Application እየተቀበለ አይደለም ። እንደሚታወቀው ቁጥሩ ከ 5 ሚሊዮን ወደ 7 ሚሊዮን ያደገ ቢሆንም ኮርሱን የሚያቀርበው Udacity እስከ አሁን አዲስ ምዝገባ እየተቀበለ አይደለም። ቁጥሩ መጨመሩን መንግስትም በ Ministry of Innovation and Technology - Ethiopia በኩል ይፋ አድርጓል።

አንዳንድ ነገሮች ተስተካከለው ወደ ስራ እስከሚመለስ በትዕግስት ተጠባበቁ። አዲስ Application መቀበል እንደጀመረ ኢንሻአላህ መረጃ ሼር ስለማደርጋችሁ እስከዚያው ከዚህ በፊት ሼር ሳደርጋቸው የነበሩ እና ሌሎች ነፃ የኦላይን ኮርሶችን ተከታተሉ።

Stay Connected 🥰
👍13❤6
ኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር አዳዲስ የፈጠራ ሃሳብ ያላችሁ ስራ ፈጣሪዎች እድል ይዞ መጥቷል!

​ሃሳባችሁን ወደ ተጨባጭ ምርት (MVP) ለመቀየር የምትፈልጉ፣ በኢኖቢዝ-ኬ (Innobiz-K) 🇪🇹 ኢንኩቤሽን ማዕከል አማካኝነት የቴክኖሎጂ ድጋፍ በነጻ ማግኘት ትችላላችሁ።

ሀሳብ ያላችሁ እና ይህን እድል መጠቀም የምትፈልጉ ከታች በተቀመጠው ሊንክ ተመዝገቡ። 👇 Registration Link
❤3
OpenAI እና Anthropic ጠንካራ ተፎካካሪ ገጠማቸው! በቻይና Z.AI የተለቀቀው GLM-5.2 ሞዴል የ AI ውድድሩን እየቀየረ ነው።

• ከምዕራባውያን ሞዴሎች በ5-7 እጥፍ ያነሰ ዋጋ መኖሩ
• የአሜሪካ ካምፓኒ ቺፕ ሳይጠቀም በራሷ በቻይና (Huawei Ascend ብቻ) የተሰራ እና

ለሁሉም ክፍት መሆኑ ውድድሩን የተቀላቀለ ሲሆን የአሜሪካ ኩባንያዎችን አስደንግጧል።

በተለይም በኮድ አፃፃፍ (coding) እና ውስብስብ የሆኑ ስራዎችን በራስ-ገዝ በመስራት (agentic capabilities) ችሎታው ከፍተኛ አድናቆትን እያገኘ ነው።

ሞክሩት 😍👇https://chat.z.ai/
❤3👍1
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አዲሱ የChatGPT የድምፅ (GPT-Live) ተለቋል! 🎙️✨

​ከአሁን በኋላ ከChatGPT ጋር የሚኖረን ውይይት እንደ ማሽን ሳይሆን፣ እንደ ሰው ተፈጥሯዊ ይመስላል ተብሏል።

​✅ ምን አዲስ ነገር አለው?
• Full-Duplex: እየተናገርን ማቋረጥ ወይም መደራረብ እንችላለን።
• የበለጠ ተፈጥሯዊ: የሰው ልጅን የማመንታትና የማዳመጥ ባህሪን ይጋራል፤ በአፍታ መቆራረጦች አይዘናጋም።
• በቅጽበት የመተርጎም እና ውስብስብ መረጃዎችን የማቅረብ አቅም አለው።

​ከዛሬ ጀምሮ በiOS፣ በአንድሮይድ እና በድረ-ገጽ ላይ ሞክሩት! 🚀
​#ChatGPT #GPTLive #AI #TechInnovation #OpenAI #EthiopiaTech
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
1K ቤተሰብ ደርሰናል አብራችሁን ስላላችሁ እና ስለ ድጋፋችሁ ከልብ ❤️ አመሰግናለሁ!

ሊንኩን ሼር በማድረግ ልትደግፉኝ ትችላላችሁ!
https://t.me/miftahcode
👍4
መረጃ ሀብት ነው 👇
ነጻ መተግበሪያዎች እና የተደበቀው የውሂብ ዋጋ! 📱⚠️
​
ብዙዎቻችሁ Truecallerን ስትጠቀሙ የምታዩት ጥቅሙን ብቻ ነው። "ማነው የደወለው?" የሚለውን ጥያቄ በመመለሱ እና አይፈለጌ ጥሪዎችን (Spam calls) በመዝጋቱ ረገድ እጅግ ጠቃሚ በመሆኑ በብዙዎች ዘንድ ይወደዳል። ነገር ግን "ለምን ይህ አገልግሎት ነጻ ሆነ?" ብላችሁ ጠይቃችሁ ታውቃላችሁ?
​
የእውነት እንነጋገር ከተባለ፡ Truecaller ነጻ አይደለም፤ ክፍያው በእናንተ እና በእውቂያዎቻችሁ (Contacts) መረጃ ነው!
​
እንዴት ይሰራል?
​የእናንተ መረጃ፡ መተግበሪያውን ስትከፍቱ ስለ እናንተ ማንነት ሙሉ መረጃ ይወስዳሉ።
​
የሌሎች መረጃ፡ ትልቁ ጉዳይ ያለው እዚህ ላይ ነው። Truecaller በእናንተ ስልክ ውስጥ ያሉትን ኮንታክቶች በሙሉ "ይቀዳል።" ማለትም፣ መተግበሪያውን የማይጠቀሙ የጓደኞቻችሁ፣ የቤተሰባችሁ እና የሥራ ባልደረቦቻችሁ ስም እና ቁጥር ሳይቀር ወደ ዳታቤዛቸው ይገባል።
​
ነዳጅ ለኢንዱስትሪው፡ ይህ የተሰበሰበው ትልቅ መረጃ (Big Data) ለድርጅቱ እንደ ነዳጅ ያገለግላል። ይህንን መረጃ ለተለያዩ ዓላማዎች ይጠቀሙበታል፦
​
🚩 ለማስታወቂያ: ግላዊነት የተላበሱ ማስታወቂያዎችን ለመላክ።
🚩 ​ለጥናት እና ስለላ: የሰዎችን ባህሪ ለመከታተል።
🚩 ​ለማጭበርበር (Scammers): መረጃው መጥፎ ዓላማ ላላቸው ሰዎች ሊጋለጥ የሚችልበት ከፍተኛ ዕድልም አለ።

ቴክኖሎጂን ስትጠቀሙ ሁሌም አንድ ነገር አስታውሱ፤ "አንድ አገልግሎት በነፃ እያገኛችሁ ከሆነ፣ የድርጅቱ ምርት እናንተ (ወይም መረጃችሁ) ነው።"
​
በዲጂታል ዓለም ውስጥ ግላዊነታችሁ ዋጋ አለው። ውሳኔያችሁን በጥንቃቄና አውቃችሁት ውሰዱ!

AIን እዚህ ያደረሰው መረጃ ነው! True Caller እንደምሳሌ አነሳሁት እንጂ ሌሎችም ከ privacy አንጻር ጥያቄ የሚነሳባቸው በርካታ መተግበሪያዎች አሉ!
​
💬 ስለዚህ ጉዳይ ምን ታስባላችሁ? መረጃችሁን ለደህንነት ሲባል እየሰጣችሁ ነው ወይስ የግላዊነት ጥሰት እንደሆነ ይሰማችኋል? ሃሳባችሁን በኮሜንት ላይ አጋሩን
​#TechPrivacy #DataSecurity #Truecaller
❤2
AI ኮድ ይጽፋል ሲባል "ዝም ብሎ ፅሁፍ" ነው ወይስ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነ ሶፍትዌር? 🤖💻
"በ AI ሙሉ ዌብሳይት ሰራሁ" የሚሉ ፖስቶችን ስናይ ብዙዎቻችን ChatGPT ወይም Claude ላይ ሄደን "ለካፌ አገልግሎት ሽያጭ የሚውል አፕ ስራልኝ" እንላለን። ቦቶቹ ግን የኮድ ናዳ ያዘንቡብናል እንጂ ክሊክ ተደርጎ የሚከፈትና ወዲያው የሚሰራ መተግበሪያ አይሰጡንም በእርግጥ ቅድመ–እይታ የሚያሳዩን አሉ። ለመሆኑ እውነታው ምንድነው?

እውነታው የ AI መሳሪያዎች በአሁኑ ሰዓት በሁለት ትልልቅ ጎራ መከፈላቸው ነው፦

❌ 1. መደበኛ ቻት ቦቶች (ChatGPT, Claude Chat, Gemini, Xai, DeepSeek)፦
እነዚህ ቦቶች ልክ እጅና እግር እንደሌለው "በጣም ጎበዝ መሐንዲስ" ናቸው። Frontend እና Backend ኮዱን ጠንቅቀው ያውቃሉ፤ ነገር ግን ያንን ኮድ ኮምፒውተራችን ላይ ፋይል ፈጥሮ የመለጠፍ (Paste)፣ እርስ በእርስ የማገናኘት እና ለተጠቃሚ ዝግጁ አድርጎ የማውጣት አቅም የላቸውም። እኛ መሃል ላይ ገብተን ወደ IDE (Integrated Development Environment ) like:- VS Code ላይ ኮዱን ኮፒ-ፔስት ካላደረግንላቸው ዝም ብሎ ጽሑፍ ብቻ ናቸው።

✅ 2. የዘመኑ AI Coding Agents (Bolt.new, Cursor, Windsurf, GitHub Copilot, Android AI Studio)፦
አሁን ላይ ጨዋታውን የቀየሩት እነዚህ ናቸው! ለምሳሌ Bolt.new ላይ በፅሁፍ ብቻ ስታዙት፣ እራሱ Frontend እና Backend ፋይሎችን ይከፍታል፣ ኮዱን ይለጥፋል፣ ሰርቨር አስነስቶ አፑ ሲሰራ ምን እንደሚመስል (Preview) ያሳያችኋል፤ በመጨረሻም በአንድ ክሊክ ሙሉ በሙሉ ተጠናቆ ለአገልግሎት ዝግጁ የሆነ (Production-ready) ሊንክ ይሰጣችኋል። Cursor እና GitHub Copilot ደግሞ ኮምፒውተራችሁ ላይ ያሉ ፋይሎች ውስጥ ገብተው እራሳቸው ኮዱን ይፅፋሉ፣ ያሻሽላል።

ሲጠቃለል ቻት ቦቶች ኮዱን ያዘጋጃሉ፤ ስራ ላይ ለማዋል ግን የእኛ የእጅ ስራ ያስፈልጋቸዋል። AI Agents ግን ሙሉ ስራውን ሰርተው ለአጠቃቀም የበቃ ሶፍትዌር ያስረክባሉ ከነስስታቸው እና ችግራቸው እነሱም ቢሆኑ የሰጡህን መልሰው አጥፍተው ሲያደናብሩን ይውላሉ። በሌላ አባባል አሁንም ቦሆንም መሰረታዊ እውቀት ከሌለን እጅግ ፈታኝ ነው። በዘርፉ ፍላጎት ያላችሁ አሁንም ከ አኤአይ እገዛው ጎን ለጎን መሰረታዊ እውቀቱን ተማሩ ምክሬ ነው። አሁንም ነጻ በሚሰጡን ቶክን ውስብስብ ሶፍትዌሮችን መጨረስ ራሱ ከባድ እና ሌላ ራስ ምታት ነው ፤ ለቀላል ታስክ የሚያገለግሉ ልንጨርስ እንችላለን። እያወሳሰብኩት አይደለም በ 0 ኮዲንግ እውቀት መስራት አይቻልም እያልኩም አይደለም በዘርፉ ተወዳዳሪ እና ውጤታማ ለመሆን Foundation እውቀት መሰረት እና ሁሌም የማይሻር ነው። እይታዬ ነው! የእናንተን እይታ አካፍሉን? ለመማማር እና ውጤታማ ለመሆን በማሰብ ያዘጋጀሁት ነው፡፡

❓ እናንተስ አሁን ላይ በ AI ኮዲንግ እያገዛችሁ ነው? የትኛውን መሳሪያ (Tool) ይበልጥ ወደዳችሁት? ሃሳባችሁን የውይይት መስጫው ላይ አጋሩን👇
❤6👍2
AI ኮድ እየፃፈ ስለሆነ ኮዲንግ መማር አያስፈልግም ምን ሊረባ ? ትልቅ ❌ ነው። አሁንም ውጤታማ የሚሆኑት ያወቁት ናቸው።
❤1
ኮዲንግ ኮምፒውተርን ማዘዝ ብቻ ሳይሆን፣ ውስብስብ ችግሮችን በሎጂክ የመፍታት ክህሎትን ያዳብራል።
❤2