MESFIN MAGO TULAMO
192 subscribers
80 photos
18 links
Education Consultant and Tranair (ECT)

https://www.youtube.com/@mesfin_12
Download Telegram
🌟 ውድቀት የስኬት መውጫ በር ነው

በአንድ ወቅት ታላላቅ ህልሞች የነበረው አንድ ወጣት ነጋዴ ነበር። ሁሉንም ነገር ሸጦ ትንሽዬ ቡቲክ ለመክፈት ወሰነ። ለዓመታት የሰራበትን ገንዘብ፣ ከቤተሰቡ የተበደረውን እና ከባንክ ያገኘውን ብድር ሁሉ ለዚህ ስራ አዋለ። ቡቲኩን ለማስዋብ፣ ምርጥ የሚባሉ ልብሶችን ለማምጣት እና ደንበኞችን ለመሳብ ቀን ከሌት ደከመ። ሁሉም ነገር በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ይመስል ነበር። "አሁን ሁሉም ነገር ተሳክቷል" ብሎ በልቡ አሰበ።

ግን የገበያው ሁኔታ ተቀየረ። በአቅራቢያው ትላልቅ የልብስ መሸጫ ሱቆች ተከፈቱ። የደንበኞች ቁጥር እየቀነሰ መጣ። የሸቀጦቹ ሽያጭ ቆመ። ወጣቱ ነጋዴ ከባድ ኪሳራ ውስጥ ገባ። ብድሩን መክፈል አልቻለም። ሰራተኞቹን አሰናበተ። በመጨረሻም የህልሙ መገለጫ የነበረው ቡቲክ ተዘጋ።

ይህ ውድቀት ከባድ ሥቃይ ነበር። ቤተሰቦቹ የሰጡትን ገንዘብ፣ የባንኩን ዕዳ፣ የራሱን የብዙ አመታት ድካም በአንድ ጊዜ አጥቷል። ሰዎች "ለምን ሞከረው?"፣ "ከመጀመሪያውም አይሳካለትም ነበር" እያሉ ይዘባበቱበት ጀመር። ወጣቱ ነጋዴ ተስፋ ቆረጠ። ራሱን ከሰዎች አገለለ። በራሱ ላይ እምነት አጣ።

አንድ ቀን ግን በራሱ ላይ አሰበ። "በእርግጥ ምን ስህተት ሰራሁ?" በማለት ራሱን ጠየቀ። ሁሉንም ነገር በጥንቃቄ መረመረ። ለምን እንደወደቀ ተረዳ። ውድቀቱ ያስተማረው ትምህርት ከገንዘብ በላይ ዋጋ እንዳለው ተገነዘበ። "ተሳስቻለሁ፣ ግን ተስፋ አልቆረጥኩም" ብሎ በልቡ አሰበ። ከዚህ በፊት የነበረውን ስህተት ላለመድገም ቃል ገባ።

ብዙ ጊዜ ከባለ ዕዳዎቹ እየሸሸ ይኖር ነበር። "አልሞትኩም!" ብሎ ለራሱ ደጋግሞ ነገረው። ከዚያም አንድ አዲስ ሀሳብ አመጣ። ገንዘብ የማይጠይቅ እና በትክክለኛው መንገድ ከተሰራ ትልቅ ስኬት የሚያመጣ የንግድ ሀሳብ። በመጀመሪያ በኦንላይን አማካኝነት አነስተኛ የልብስ ንግድ ጀመረ። የደንበኞችን ፍላጎት በጥንቃቄ አጥንቶ፣ በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛውን ምርት ማቅረብ ጀመረ።

ውድቀቱ ባስተማረው ትምህርት እና ባዳበረው ልምድ፣ በጥቂት ወራት ውስጥ ንግዱ ማደግ ጀመረ። በመጀመሪያ ደንበኞችን መሳብ አቃተው ነበር፣ ነገር ግን ተስፋ ባለመቁረጥ፣ በወደቀበት መንገድ ላይ ተነስቶ በመጓዙ ምክንያት በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ ስኬት ላይ ደረሰ። የቀድሞ ዕዳውን ሁሉ ከፈለ። በመጨረሻም ትልቅ እና ስኬታማ የኦንላይን ልብስ መሸጫ ሱቅ ባለቤት ሆነ።

ውድቀት መጨረሻ አይደለም። ውድቀት ለተሻለ ነገር መማሪያ መድረክ ነው። ተነስተህ ከተጓዝክ የማትደርስበት ቦታ የለም።
https://t.me/mesfeect
👍3🔥1
ከተማ መሬትና ቤት ይዞታ ስመ-ንብረት ዝውውር የሚፈጸምበት መመሪያ
======================
👉በስመ ንብረት ዝውውር ወቅት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 33 ንዑስ አንቀፅ 2 አንፃር ሲታይ፦
ሀ/ የከተማ ቤትና ይዞታ ስመ-ንብረት ዝውውር ስለመፈጸም የሚከተሉት ማስረጃዎች/ሰነዶች ሲሟሉ የስመ ንብረት ዝውውር የሚፈጸም ይሆናል፤
✍️ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት/ካርታ፣
✍️ጸድቆ የተሰጠ የግንባታ ፕላን፣ የስራ ዝርዝር ግምት ወይም የጸደቀ የነባር ግንባታ ፕላን፣
✍️ጸድቆ በተሰጠው የግንባታ ፕላን መሰረት ስለመገንባቱ እና ግንባታው ያለበት ደረጃ የተረጋገጠበት ማስረጃ/50% እና በላይ/፤
✍️ውዝፍ የሊዝ ኪራይ ዕዳ የሌለበት ስለመሆኑ የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ወይም ቀሪ የሊዝ ክፍያ ዕዳውን ገዥው ለመክፈል በፊርማ ያረጋገጠበት የስምምነት ደብዳቤ ፣
✍️በንብረቱ ላይ የባንክ እዳ/የፍ/ቤት ዕግድ የሌለበት ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሲቀርብ፣
✍️ የቤትና ይዞታ ስም ዝውውር ጥያቄው የቀረበው በህግ ባለመብት/በውርስ/በፍርድ አፈጻጸም ወይም በውክልና ከሆነ ይህንኑ የሚገልጽ ማስረጃ፤
✍️ በግለሰቦች ግዥና ሽያጭ ወይም ስጦታ ስምምነት ከሆነ በዉልና ማስረጃ በአካል ቀርቦ በእማኞች የተፈረመ የስምምነት የውል ማስረጃ ሲቀርብ፣
ለ/ በሽያጭ/በስጦታ የሚተላለፍ ቤትና ይዞታ ስም-ዝውውር መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፣
✍️ግንባታው በዋስትና ያልተያዘ እንዲሁም እዳ የሌለበት መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም እዳው በሚመለከተው አካል በደብዳቤ መነሳቱ ሲረጋገጥ፣
✍️ የቤትና ይዞታ ሽያጭ ወይም የስጦታ ውሉ በምስክሮች ሲረጋገጥና በፍትህ ወይም በመሪ ማዘጋጃ ቤት ፊት ቀርቦ ሲጸድቅ፣
✍️ ግንባታው ጸድቆ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት 50 በመቶና በላይ የተሰራ መሆኑ በባለሙያ ተረጋግጦ ሲቀርብ፣
✍️ በይዞታው ላይ ውዝፍ የቦታ ኪራይ የሌለበት ስለመሆኑ ወይም ውዝፍ የቦታ ኪራይ ክፍያ አጠናቆ የከፈለ ስለመሆኑ የቀረበ ክፍያ ደረሰኝ ማረጃ ሲቀርብ፣
✍️ የአገልግሎትና የገቢዎች ክፍያ በቤቱ ግምት መሰረት ስለመከፈሉ ሲረጋገጥ፣
ዝውውሩ የሚፈፀመው በሊዝ በተገኘ ይዞታና ግንባታ ላይ ከሆነ
✍️ የሊዝ ይዞታ ባለቤትነት ኦሪጅናል ካርታና ውል ሲቀርብ፣
✍️ በሊዝ ውል መሰረት ክፍያው የተጠናቀቀና ሌሎች ግዴታዎቹን የተወጣ መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም የሊዝ እዳው ያልተጠናቀቀ ከሆነ ስም የሚዞርለት ወገን እዳውን ለመክፈል እና ነባሩን የሊዝ ውል ግዴታዎች የተቀበለ ስለመሆኑ ከከተማው በጽሁፍና በፊርማ አረጋግጦ ሲያቀርብ፣
✍️ በሊዝ የተገዛን የመሬት ይዞታ ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ በቅድሚያ በገባው የሊዝ ውል መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የሚፈለገውን የግንባታ ደረጃ ያሟላ መሆኑ ወይም የግንባታ ፈቃድ የጊዜ ገደብ ያላለፈ ወይም የግንባታ ማራዘሚያ የተፈቀደለት መሆኑ ሲረጋጥ፣
✍️ የከተማ ቤትና ይዞታ ሽያጭ ወይም የስጦታ ውሉ በምስክሮች ሲረጋጥና በዉልና ማስረጃ ቀርቦ ሲጸድቅ ይሆናል፡፡
ሐ/ በውርስ የተገኘ ይዞታና ቤት የባለቤትነት ስመ-ንብረት ዝውውር አፈፃፀም፣
(ሀ) በውርስ የተላለፈ ነባር ይዞታ ዝውውር ለመፈፀም መሟላት ያለባቸው፡-
✍️ የሚዛወረው የመሬት ይዞታ ወይም ቤት ህጋ የባለቤትነት ማስረጃ/ካርታ ሲኖረው፣
✍️ ወራሾች የውርስ ባለመብትነትን የሚያረጋግጥ የፍርድ ቤት ውሳኔ ማስረጃ ሲያቀርቡ፣
✍️ ወራሾች በውርስ ያገኙትን ይዞታ ወይም ቤት በየግላቸው የባለቤትነት ማስረጃ ለመያዝ ሲፈልጉ ለእያንዳንዳቸው ድርሻ መጠን በፍ/ቤት የፀደቀ ማስረጃ ሲያቀርቡ ወይም የሁሉም ወራሾች የጋራ ስምምነት በውል አፅዳቂ አካል ጸድቆ ሲቀርብ፣
✍️ የእያንዳንዱ ወራሽ የድርሻ መጠን በፍርድ ቤት ያልተረጋገጠ ከሆነ የስም ዝውውሩ በሁሉም ወራሾች ስም በጋራ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
የፍርድ ቤቱ የውርሱ ውሳኔ የይዞታ ክፍፍልን የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ የሚፈፀመው የወቅቱን አነስተኛ የይዞታ መጠን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ካልሆነም በተነፃፃሪ የመሬት ይዞታ ድርሻ ህግ ወይም በጋራ ሰነድ/ካርታ መሰረት ይስተናገዳል፡፡
ይዞታው በውሉ መሰረት ግንባታ ለመጀመር የተሰጠውን የጊዜ ገደብ ያለፈበት እና ግንባታው ያልተጀመረ ከሆነ በውርስ ሊተላለፍ አይችልም፡፡
👉በሊዝ የተያዘ ይዞታ ለህጋዊ ወራሽ የሚተላለፈውና ዝውውር የሚፈፀመው፡-
✍️ አውራሹ በገባው የሊዝ ውል ግዴታ መሰረት አመታዊውን የሊዝ ክፍያ የፈፀመና ሌሎች የሊዝ ግዴታችን በተገቢው መንገድ የተወጣ ሲሆን፣
✍️ ወራሽ አውራሽ የገባቸውን የውል ስምምነቶች(የሊዝ መብት፣ክልከላና ኃላፊነት) ሙሉ በሙሉ የተቀበለ መሆኑን በፊርማው ሲያረጋግጥና ውዝፍ ክፍያ ካለ ከፍሎ ደረሰኝ ሲያቀርብ ይሆናል፡፡
✍️ በሊዝ ውሉ መሰረት አውራሹ በህይወት እያለ ለግንበታ መጀመሪያ የተሰጠው የጊዜ ገደብ ካለፈና ግንባታ ካልጀመረ ውሉ ተቋርጦ ቦታው ለከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ተመላሽ ይሆናል፡፡
አውራሽ በይዞታው ላይ ግንባታ ያልጀመረው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑ ከተረጋጠ አውራሽ በህይወት ቢኖር ኖሮ በመመሪያው መሰረት ሊፈቀድለት የሚችለው የግንባታ መጀመሪያ የማራዘሚያ ጊዜ ለወራሽ ሊፈቀድለት ይችላል፡፡
መ/ በባንክ ሃራጅ የሚሸጥ እና የሚወረስ ቤት የባለቤትነት ስም ዝውውር
✍️ በባንክ የተሸጠ ቤት የባለቤትነት ስም ዝውውር ለመፈፀም በሐራጅ ጨረታው አሸናፊ የሆነው ሰው ያሸነፈበትን ዋጋና ለዝውውሩ በውል የገባቸው ግዴታዎች ተገልፀው ከባንኩ የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤና ውል ሲቀርብ፣
✍️በባንክ ዋስትና ተይዞ የነበረው ይዞታ የባለቤትነት ማረጃ/ካርታ በማህደሩ ውስጥ ካለው ሰነድ ጋር ተገናዝቦ ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ፣
✍️ይዞታው በሌላ ባንክ ብድርና ዋስትና ያልተያዘ ወይም እገዳ የሌለበት መሆኑ ሲረጋገጥ፣
✍️ በሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ዋስትና የተመዘገበ ዋስትና ያለው ባንክ መኖሩ ከተረጋገጠ ባንኩ ስለ ይዞታው መሸጥ ሲፈቅድ፣
✍️ በባንክ ሃራጅ ሽያጭ እንዲዞር የተጠየቀው ቤትና ይዞታ የተሟላ ሰነድ የሌለው/ሰነድ አልባ ከሆነ በቅድሚያ በሥራ ላይ ባለው የሰነድ አልባ መመሪያ መሰረት ሰነድ ተሰጥቶት ሲቀርብ፣
✍️ ባንኩ ንብረቱን ባለበት ሁኔታ የሚረከብ ከሆነ የቤቱና ይዞታው ግምት እንደማንኛውም ቋሚ ንብረት ግምት ተሰልቶ ተገቢውን የአገልግሎትና የገቢ ክፍያ ሲፈጸም፣
✍️ ቤቱና ይዞታው ባንኩ በሚያወጣው ጨረታ የሚሸጥ ከሆነ ባንኩ ያቀረበው የጨረታ መነሻ ዋጋ በከተማው በኩል ተገቢ መሆኑ ተረጋግጦ በጨረታ ሲሸጥ እና የስም ማዛወሪያ ክፍያዎችን ስለመፈጸሙ የክፍያ ደረሰኝ ማስረጃ ሲያቀርብ የሥመ-ንብረት ዝውውሩ የሚፈጸም ይሆናል::

https://t.me/mesfeect
1. ሕይወት ሁልጊዜም ፍትሐዊ አይደለችም፡፡ ጥሩ ያልሆኑ ሁኔታዎች ይከሰታሉ፡፡ በዚህ ውስጥ መቆየትህ ደግሞ አንተን የበለጠ ሊጎዳህ ይችላል፡፡ ስህተት ከሠራህ፣ ውድቀት ካጋጠመህ ሁልጊዜም ለአንተ እንደገና እድል እንዳለና መጨረሻህም እንዳይደለ እወቅ፡፡

2. እያንዳንዱ ሰው ችግሮች ይኖሩበታል፡፡ ግን ያ ሰው ችግሮቹን ለመወጣት ፈጣን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ያለማቋረጥ በሕይወቱ ውስጥ በተፈጠሩት ስህተቶች ላይ ቢያተኩር ችግሮቹን ከማወሳሰብ ውጪ መፍትሄ አይኖርም። አንተ ግን ችግሩ ላይ ሳይሆን መፍትሔ ላይ አተኩር።

3. እያንዳንዱ ሰው ስህተት መሥራቱ ዓለም አቀፋዊ ሐቅ ነው፤ ማንም ፍፁም አይደለምና፡፡ ስለዚህ ስህተትህን ሊያስተካክል እና ከውድቀትህ ሊያነሣህ የሚችል የሆነ ነገር ካለ ግፋበት፡፡ እናም አስፈላጊ የሆነውን አድርግ፡፡ ሊተገበር የማይቻል ነገር
ቢሆን ግን እርሳው፡፡ በአዲስ ሁኔታም ጀምር፡፡ ከሆነ ብቻ ብለህ አታስብ፡፡ ይህ የተስፋ መቁረጥ ስሜት እርግጠኛው መንገድ ነውና፡፡ አሁን ልታደርግ ስለሚገባህ ነገር በርትተህ አስብ፡፡

4. ራስህን መቀበልና የተቀበልከውንም ማንነት ማፍቀርን ተማር፡፡ ሕይወት በመንገድህ በምታመጣቸው በእያንዳንዱ ልምድ ውስጥ ራስህን የተሻለ ለማድረግ መጣርህን አታቋርጥ፡፡

5. እጅግ የበራ የወደፊት ዘመን የተመሠረተው የትላንቱን በመርሳት ላይ ነው፡፡ ያለፉ ውድቀቶችህንና የልብ ስብራቶችህን እስካላስወገድካቸው ድረስ በሕይወት ውስጥ ወደፊት መራመድ አይቻልህም፡፡ ስለዚህ በተደናቀፍክበት እንደገና ቶሎ ለመነሳት
አንዲት ቅጽበት እንኳን በጸጸት ሳታባክን ወደፊት ተጓዝ፡፡

6. ለመጣው ሁሉ ጠንካራ፣ ለቀጣዩ ደግሞ ዝግጁ ሁን፡፡
ምክንያቱም እያንዳንዳቸው ከዚህ በኋላ ለሚመጣው እንደ መሪ የተላኩ ናቸው፡፡ ያለ ዕለት ከዕለት ግጥሚያዎቻችንና ፈተናዎቻችን ሕይወት ባዶና አንድ ዓይነት ትሆናለች፡፡ ችግሮች አብዛኛውን ጊዜ ልንማራቸው ግድ የሚሉን እውቀቶች ናቸው፡፡
ስለዚህ ሁሉንም የሕይወት ተሞክሮዎች ደስተኝነት ከሰፈነበት አቀባበልና ከእምነት ጋር ተግባባቸው፡፡

7. በሚያጋጥምህ በእያንዳንዱ ችግር ውስጥ የተደበቁትን ስጦታዎች በማስተዋል ሆነህ መርምር፡፡ ሰው መሆንእንደ እንግዳ ቤት ነው፡፡ እያንዳንዱ ማለዳ አዲስ አዳራሽ ነው፡፡ ደስታ፣ ሐዘን እና ጊዜያዊ ግንዛቤዎች እንዳልተጠበቀ ጎብኚ ሆነው ይመጣሉ፡፡ ሁሉንም በጸጋ ተቀበላቸውና ተደሰትባቸው፡፡

8. ከተሳሳትክ አርም፣ ከወደቅክ ተነሣ እንጂ ፈጽሞ
አታጉረምርም፡፡ ከተስፋ መቁረጥ ክፉ ጠላት ጠንቀቅ፡፡ ከሐቁ አትሽሽ፣ ጥፋተኛ ስትሆነ ጥፋተኝነትህን ተቀበል፡፡ ነገሮች ሲበላሹም ስህተት መቀነስ ላይ አተኩር፣ ከጥፋትህ ተምረህ ወደ ቀጣዩ ተግባር ተሻገር፣ ምክንያቱም የሕይወት ግብ ወደ ፊት መገስገስ እንጂ ክስና ሰበብ አልያም ጸጸት ላይ መቆዘም አይደለም፡፡ ያለፉ ስህተቶችህንና ውድቀቶችህን እዚያው ተዋቸው፡፡

9. አንድ ሕፃን ለመራመድ ሲፍጨረጨር ብናስተውል ማብቂያ የሌላቸውን ውድቀቶች እናያለን፡፡ ስኬቶቹ ግን በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ ነገር ግን በተደጋጋሚ ውድቀቶቹ እንዳሉ ሆነው የማይቻል የሚመስለውን ነገር ማድረግ የቻለው ሕጻን በኃይለኛ ደስታ ውስጥ ይዋጣል፡፡ በጊዜው አቋሙን ስለ መጠበቁ እንጂ ስለ ወደቀባቸው ጊዜያት ያን ያህል ሳይጨነቅ ከደስታ ወደ ደስታ ይሸጋገራል፡፡ አንተም አታማር፣ ጊዜም አታጥፋ፡፡ ተስፋ
በማድረግና ጠንክረህ በመሥራት ሕይወትህን በደስታ ሞልተሃት ኑር፡፡ እርግጥ ነው አስቸጋሪ ይሆንብናል፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜም ቢሆን ሕይወትህን ስኬታማ የምታደርግበት፣ ራስህን በውብ ልጅነት የምትቀርጽበትና በውስጣዊ ሕይወትህ ያለህን ብልጽግና የምትጨምርበት መንገድ አለ፡፡ ስለዚህ ሙሉ ዓለም ቢታሰብ ለአንተ የተሻለ ቦታና ሁኔታ ሊኖር እንደማይችል ማሰብህን አቁም፡፡

10. ስኬት የምታመራው ፈጽሞ ተስፋ ወደ ማይቆርጡ ሰዎች ነው፡፡ ምንም እንኳን ያልተሳኩ ነገሮችን፣ የውደቀት መጠናችንና የስህተታችን ብዛት ቢያይልም ተስፋ አትቁረጥ።

https://t.me/mesfeect
👍3
አንዳንዴ እምንት የሚመስሉ ነገሮች ጥንቃቄ ካልወሰደን ብዙ ዋጋ ያስከፍላሉ፡፡ ትንሽ ነገሮች ትልቅ ዋጋ መኖሩን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ትልቁን በር ለመክፈት፣ በሩን የሚያክል መክፈቻ ቁልፍ ሳይሆን በጣም ትንሽ መክፈቻ ቁልፍ ያስፈልጋ፡፡ ያ ትንሽ ቁልፏ ከጠፋች በሩን ሰብረን ብዙ ዋጋ እንከፍላለን፡፡
ለጥቃቅን ነገሮች የምንሰጠውን ትኩረት መቼም ቢሆን ቸል አንበል። የመጀመሪያው የአሜሪካ የቬኑስ ሮኬት (Venus rocket) የጠፋው በኮምፒውተር ስህተት ምክንያት ነበር፤ ይህም በነጥብ ፋንታ ኮማ በመጠቀሙ ነው! ፕሮግራሙ የተጻፈው DO31=1.3 ተብሎ ነበር፣ መሆን የነበረበት ግን DO31=1,3 ነበር።
በዚህም ምክንያት ሮኬቱ በከፍተኛ ፍጥነት ሰው ወደሚኖርበት አካባቢ አቅጣጫውን ስለቀየረ፣ በአየር ላይ እያለ እንዲጋይ ተደርጓል።
ለማነኛውም ለእምንት ነገሮች ትኩረት ሰጥተን በጥንቃቄ እንሥራ!
❤5👏1
ቢራቢሮዎች ለመያዝ እያባረርክ ጊዜ አታጥፋ፤ ይልቁንም ይሽሹሃል፡፡ በቀላሉ ለመያዝ ከፈለግህ ምርጥ አበባ እየተከልክ ጊዜህን ቢታጠፋ ቢራቢሮዎች ብቻቸውን ካሉበት ወደ አበባው ይመጣሉ፡፡

በጥበብ እንኖር!

#ሻሎም!
👍4
Live stream started
Live stream finished (33 seconds)
የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ!
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።" ኢሳያስ 53፣6
❤2👍2
ከሰው ጋር እያወራን መዘንጋት የሌለብን 15 ጥበቦች
1.  ዳኛ በየሌለበት አትከራከር፡፡
2.  አስታራቂ ከሌለ አትጣላ፡፡
3.  ለመማር ዝግጁ ያልሆኑትን ለማስተማር አትልፋ፡፡
4.  ሁሌ "አውቃለሁ" የምለውን ለመምከር አትሞክር፡፡
5.  አንተን እንደ ዕቃ ከሚጠቀመው ጓደኛህ ቶሎ መሸሽ አለብህ፡፡
6.  አንተ መፍት ለማትሰጠው ችግር ከንፈር አትምጠጥ፡፡
7.  ከማነኛው ሰው ጋር ግንኙነት ማለፍ የሌለባቸው ቀይ መስመሮችን ማወቅ አለብህ፡፡
8.  ከሰው መቀበል ከፈለግህ መስጠት አለብህ፡፡
9.  ግንኙነት ጊዜ ብዙ ከማውራት ብዙ መስማት አለብህ፡፡
10.  መልስ ከመስጠትህ ንግግር መጨረሱን አረጋግጥ
11.  ከወዳጅህ ጋር ባለው ግንኙነት በተቻለ መጠን የፊትህ ፈገግታህን አትነፍግ፡፡
12.  ተግባቦት ጊዜ የወዳጅህን ፊት እያየህ መሆን አለብህ፡፡
13.  ወዳጅህ እያወራ እያለህ ሌላ ተግባራትን አታደርግ፡፡
14.  በተግባቦት ውስጥ የግል ምስጢርህ ለይተ መናገርህን እንዳትረሳ፡፡
15.  ያልገባህን ነገር ማብራሪያ ጠይቅ፡፡
https://t.me/mesfeect
❤7
😢1
MESFIN MAGO TULAMO
Photo
አቶ ማጎ ቱላሞ ፃራ ከአባታቸው ከአቶ ቱላሞ ፃራ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ቦሮዴ ቦሼ በጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር በ1884 ዓ.ም አካባቢ መወለዳቸውን በሕይወት ታሪካቸው ዙሪያ የተሰበሰቡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የትውልድ ዘመናቸውን ለማወቅ በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ መጠይቆች እንደሚያስረዱት፤ አቶ ማጎ የጋሞ ዘማቾች ወደ ዓድዋ ሲሄዱ ባያስታውሱም፣ በጦርነቱ ድል አድርገው ሲመለሱ ግን በሚገባ እንደሚያውቁ በተጨባጭ ያስረዳሉ፡፡ ይህም በ1888 ዓ.ም አካባቢ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የዳግማዊ አፄ ሚኒልክን፣ የእቴጌ ጣይቱን እና የልጅ ኢያሱን የዘመነ መንግሥት አጀማመር በሚገባ እንደሚያስረዱ ከታሪክ ጋር ለማመሳከር ተችሏል፡፡

‎አቶ ማጎ ከቤተሰባቸው በወረሱት ሥልጣን፣ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ከጋሞ ዴሬዎች አንዷ የሆነችውን ጉጌ ዴሬን (ግዛትን) በባላባትነት እስከ ደርግ መንግሥት መጀመሪያ ድረስ አገልግለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የ1966 ዓ.ም ለውጥ ሲመጣ የነበራቸው ንብረት ሁሉ ተዘርፎባቸዋል፤ "አዳሪ" እየተባሉ በተደጋጋሚ በመገረፍም ለረጅም ጊዜ በእስር ቤት ቆይተዋል፡፡ በሥልጣን ዘመናቸው ማብቂያ አካባቢ ከሌሎች የጋሞ ዳናዎችና መሪዎች ጋር በመሆን የአርባ ምንጭ ከተማን ለመመሥረት ሕዝቡን እንደመሩ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

‎አቶ ማጎ ከሕፃን እስከ አዋቂ ጋር ተግባቢ በመሆናቸው አብዛኛውን ዘመናቸውን ሰዎችን በማስታረቅ አሳልፈዋል፡፡ ከቡድን እስከ ግለሰብ፣ ከቤተሰብ እስከ ማኅበረሰብ በማስታረቅ ሕዝብን አገልግለዋል፡፡ ከደርግ እስር ከተፈቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ በማስታረቅ ተግባር ላይ እንደቆዩ ትውልድ ይመሰክራል፡፡ አቶ ማጎ ጉልበታቸው ከመድከሙ በፊት ፀብና ግጭት ባለበት ቦታ ሁሉ በአካል በመገኘት ያስታርቁ ነበር፡፡ በመጨረሻዎቹ አራት ዓመታት መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ደግሞ የእርቅ ፈላጊዎች ወደ ቤታቸው ይመጡ ነበር፡፡ ቤታቸው "የእርቅ ክሊኒክ"፣ እሳቸው ደግሞ "የፀብና ግጭት ሐኪም" ነበሩ፡፡ ከማስታረቅ ጥበባቸው የተነሳ ለብዙ ጋሞ ዴሬዎች "ኦጋዴ" ነበሩ፡፡ "ኦጋዴ" ማለት የጋሞ ዴሬዎች (ግዛቶች) እርስ በርስ እንዳይጋጩ ቅድመ መከላከል የሚሠራ እና ግጭቶች ሲከሰቱም በባህላዊ የእርቅ ሥርዓት የሚያስታርቅ ሰው ማለት ነው፡፡ አቶ ማጎ ለራሳቸው ከመኖር ይልቅ ለሕዝብ ሰላም ዕድሜ ዘመናቸውን የሰጡ፣ የቀደሙ አባቶችን አደራ ተቀብለው የተወጡ የሰላምና የእርቅ አምባሳደር ነበሩ፡፡

‎አቶ ማጎ ቱላሞ ባለትዳር እና የስድስት ወንድና የሦስት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡ ምንም እንኳ አንዱ ወንድ ልጃቸው ቢሞትም፣ በአሁኑ ወቅት ስምንት (8) ልጆች፣ አርባ ሦስት (43) የልጅ ልጆች እና ሃያ አንድ (21) ቅድመ-ልጅ ልጆች(Great grang-son)፣ በአጠቃላይ ሰባ ሁለት (72) ከዘራቸው የተገኙ ተተኪዎች በሕይወት ይገኛሉ፡፡

‎አቶ ማጎ እስከ እለተ ሞታቸው የማስታረቅ ሥራቸውን ሲያከናውኑ ቆይተው፣ ባደረባቸው ሕመም በሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በ134 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
👍4👏4
Channel photo updated
ሙሴ ከሲና ተራራ እስኪወርድ ድረስ የአርባ ቀን ትዕግስት በማጣት ጣዖትን ማምለክ የጀመረው ከግብፅ የወጣው የእስራኤል ህዝብ፣ የአርባ ዓመታትን መከራ ከማየት ባለፈ አብዛኛው በበረሃው አልቋል። ትንሽ አለመታገስ ብዙ ዋጋ ያስከፍላል፤ ትንሽ ታገስ፣ ሁሉ ያልፋል!
👍7
🎴አንዳንዴ መጨረሻዎች እንደ ቡና መራራ ቢሆኑም ያነቁናል! ☕️💡


“አንዳንድ መጨረሻዎች እንደ ቡና መራራ ናቸው፤ ነገር ግን ንቁ ሰው ያደርጉናል።”
ይህ ማለት፣ በህይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን አንዳንድ ክስተቶች ወይም ግንኙነቶች ሲያበቁ ከባድ እና አሳዛኝ ሊሆኑ ይችላሉ።

🎴ልክ እንደ መራራ ቡና መጀመሪያ ላይ ለመዋጥ የሚያስቸግር ቢሆንም፣ ከዛ በኋላ ግን አይናችንን እንድንከፍት፣ ነገሮችን በተለየ መንገድ እንድናይ እና አዲስ ትምህርት እንድንቀስም ይረዱናል።
መራራ መጨረሻዎች ለቀጣይ ጉዟችን ጠቃሚ ትምህርት ሰጥተውን፣ ይበልጥ ጠንካራ እና ንቁ እንድንሆን ያደርጉናል።
👍3
Channel photo updated
ደካማ መንጋዎች ጣት በመቀሰር ላይ ያተኩራሉ። ነገሮች ሲበላሹ፣ ተሰባሪ ለሆነ ማንነታቸው መሸሸጊያ እንዲሆንላቸው የሚያሳብቡበትን ምስኪን አካል ይፈልጋሉ። እውነተኛ መሪዎች ግን ፍጹም ኃላፊነትን መውሰድ የብዙ ሚሊዮን ዶላር ግዛት የማይናወጥ መሠረት መሆኑን በሚገባ ይረዳሉ። የውጭ ሁኔታዎችን መቆጣጠር አትችልም፤ በራስህ እድገት ላይ ግን ፍጹም ቁጥጥር አለህ። ስለ ነፋሱ በማማረር ጉልበትህን ማባከን አቁም፤ ይልቁንም ክንፎችህን አስተካክል! የማይበገር ጥንካሬን ገንባ፣ ድርጊቶችህን ያለ ርህራሄ መርምር፣ እና በራስን በመግራት ላይ በከፍተኛ ሁኔታ አተኩር። ዛሬ ሙሉ ኃላፊነትን በመውሰድ ሕይወትህን ተቆጣጠር! 🦅

https://t.me/mesfeect
❤4
በህይወቱ ለመጀመሪያ ጊዜ በአውሮፕላን የተሳፈረ ሰው፣ የበረራ አስተናጋጇ በሰጠችው ጥቆማ መሰረት የአውሮፕላኑን መጸዳጃ ቤት መጠቀም ይጀምራል። በዚያው መሃል አንዲት ቀይ ማብሪያና ማጥፊያ የምትመስል ነገር ያይና ነካ ያደርጋታል።

​በዚያች ቅጽበት አውሮፕላኑ በኃይል መገጫገጭና ወደ ጎን ማጋደል ይጀምራል። ሰውዬውም ደንግጦ “ወይኔ! ሳላውቅ የማይነካ ነገር ነክቼ ህዝብ ጨረስኩኝ!” ብሎ በነካት ቀይ ነገር ይጸጸታል። ከጥቂት ቆይታ በኋላ ግን መንገጫገጩ ይቆምና ስራውን ጨርሶ ከመጸዳጃ ቤት ይወጣል።

​ሁሉም ሰው “አንተ የማትረባ! ጨርሰኸን ነበር እኮ!” ብሎ ይጮህብኛል ብሎ ቢጠብቅም፣ ዞር ብሎ ያየው ሰው እንኳን አልነበረም።

​መቀመጫው ላይ እንደደረሰም አጠገቡ የተቀመጠውን ሰው በስጋት ቀስ ብሎ፣ “ይቅርታ፣ የማይነካ ነገር ነክቼ ጨርሻችሁ ነበር አይደል?” ይለዋል። ሰውዬውም “ኧረ በፍጹም እንደዛ እንዳታስብ! ይህን ያህል ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች እኮ መፀዳጃ ቤት ውስጥ አይቀመጡም፤ ካፒቴኑ ያለበት ክፍል ውስጥ ነው ያሉት። የአየሩ ሁኔታ ትንሽ አስቸጋሪ ስለነበረ ነው አውሮፕላኑ የተንገጫገጨው” ይለዋል።

​ብዙ ጊዜ ሰዎች እንደዚህ ያስባሉ፤ የሆነች ነገር ነክተው ህይወትህን የሚያንገጫግጩ እና መጨረሻህን የሚወስኑ ይመስላቸዋል። የረሱት ነገር ቢኖር ይህን ያህል ጥንቃቄ የሚፈልገው ነገር እነሱ አጠገብ ሳይሆን፣ የህይወትህ ካፒቴን ክርስቶስ ኢየሱስ ጋር እንዳለ ነው።

​እንደዚያማ ባይሆን ኖሮ፣ ያቺን ቀይ ነገር እየነካኩ ህይወታችንን መንገጫገጭ ብቻ ያደርጉት ነበር። ምስጋና ለካፒቴኑ ይሁንና፣ እንደዚህ ያሉ ጥንቃቄ የሚፈልጉ ነገሮች በእሱ እጅ ብቻ እንዲገኙ አድርጓቸዋል!
👍7❤4
​ከውቅያኖስ ፊት ለፊት ተቀምጠህ ማዕበሉን ስትመለከት፣ አእምሮህ ከውኃው ምት (ሪትም) ጋር መጣጣም እንደሚጀምር እና ሀሳብህ በተፈጥሮው እየረጋጋና እየሰከነ እንደሚሄድ የሚገልጽ አንድ ቲዎሪ አለ!" (ታይኒ ቡድሃ)
​ታላላቅ ውኃዎች ነፍሳችንን በሚጠሩበት መንገድ ውስጥ አንድ ረቂቅ እውነት አለ። በባሕሩ ዳርቻ ላይ ተቀምጠህ ዓይኖችህ በውቅያኖሱ ማብቂያ በሌለው እንቅስቃሴ ላይ እንዲያርፉ ስታደርግ፣ በውስጥህ አንድ ቅዱስ ነገር መሆን ይጀምራል።

​ውቅያኖስ አይቸኩልም። ዓለም ከተፈጠረችበት ጊዜ ጀምሮ ተቋርጦ በማያውቅ ጽኑ እና ጥንታዊ ምት ወደ ፊት እየተንከባለለ እና ወደ ኋላ እየተሳበ ይተነፍሳል፣ ያስተነፍሳል። በፊቱ ስትቀመጥ፣ አእምሮህ በተፈጥሮው ማዳመጥ ይጀምራል። የዚህችን ዓለም ከባድ ሸክም የተሸከሙትና የተጣደፉት ሐሳቦችህ፣ ያንን ዘላለማዊ መነሳትና መውደቅ ቀስ በቀስ መንጸባረቅ (መከተል) ይጀምራሉ።

​በአንድ ጥራዝ ባለው የውኃ ብርጭቆ ውስጥ ያለው ደለል ወደ ታች እንደሚሰምጠው ሁሉ፣ በውስጥህ ያለው መቅበዝበዝም መሟጠጥ ይጀምራል። አተነፋፈስህ ይጠልቃል፣ ትከሻዎችህ ይላላሉ፣ እና ሐሳቦችህ በተፈጥሮአቸው ይረጋጋሉ። ነፍስህ ከማዕበሉ ጸጥታና ጥንካሬ ጋር ስትስማማ፣ ወደ ራሷ የተፈጥሮ የሰላም ሁኔታ የምትመለስበትን መንገድ ታገኛለች።

​ውቅያኖሱ ታሪክህን አይቀይረውም፣ ነገር ግን ከላይኛው ገጽ ላይ ካለው ማዕበል በታች፣ አንተም ጭምር ሰፊና ጥልቅ የሆነ ጸጥታ እንዳለህ ያስታውስሃል።🌊🙏
❤6👍1
👏1
MESFIN MAGO TULAMO
Photo
🚀 ታላላቅ መሪዎች የሚያደርጓቸው 10 ነገሮች

​ታላላቅ መሪዎች የሚለዩት በስልጣን ማዕረጋቸው ሳይሆን በሚያሳዩት የዕለት ተዕለት ልማዳቸው ነው።
​የላቁ መሪዎች በቋሚነት የሚያደርጓቸው 10 ነገሮች እነሆ፦

​💡 1. ግልጽ የሆነ ራዕይ ይፈጥራሉ
ታላላቅ መሪዎች የት እንደሚሄዱ ያውቃሉ፤ ሌሎችም ይህንን ራዕይ እንዲያዩ ይረዳሉ። ለሰዎች አቅጣጫን እና ዓላማን ይሰጣሉ።

​💡 2. በግልጽ እና በተደጋጋሚ ይነጋገራሉ
ጥሩ አመራር ማለት ውስብስብ ንግግሮችን ማቅረብ አይደለም። ታላላቅ መሪዎች ግቦችን በግልጽ ያስረዳሉ፣ በጥሞና ያዳምጣሉ፣ እንዲሁም የሐሳብ ልውውጥን ክፍት ያደርጋሉ።

​💡 3. በአርዓያነት ይመራሉ
ሰዎች ከቃላት ይልቅ ለድርጊት የበለጠ ትኩረት ይሰጣሉ። ታላላቅ መሪዎች ከሌሎች የሚጠብቋቸውን መስፈርቶች፣ ዲሲፕሊን እና አመለካከቶች በራሳቸው ሕይወት በተግባር ያሳያሉ።

​💡 4. እምነትን ይገነባሉ
እምነት የሚመነጨው ከቋሚነት፣ ከሐቀኝነት እና ከኃላፊነት ነው። ታላላቅ መሪዎች የገቡትን ቃል ይጠብቃሉ፤ ስህተት ሲሠሩም በግልጽ ይቀበላሉ።

​💡 5. አስቸጋሪ ውሳኔዎችን ይወስናሉ
አመራር ማለት ብዙ ጊዜ በቂ መረጃ ሳይኖር ውሳኔዎችን መወሰን ነው። ታላላቅ መሪዎች ከውሳኔ መዘግየት ይልቅ፣ ለውጤቱ ኃላፊነት በመውሰድ እርምጃ ይወስዳሉ።

​💡 6. ሌሎች ሰዎችን ያበረታታሉ (ስልጣን ይሰጣሉ)
ሁሉንም ነገር በራሳቸው ከመቆጣጠር ይልቅ፣ ታላላቅ መሪዎች የሰዎችን ችሎታ ያዳብራሉ፣ ኃላፊነትን በሌሎች ላይ ይጥላሉ፣ እንዲሁም ሌሎች እንዲያድጉ ይረዳሉ።

​💡 7. በጭንቀት ውስጥ ሳይቀር ይረጋጋሉ
ቡድኖች እርግጠኛ ባልሆኑ ጊዜያት ወደ መሪዎቻቸው ይመለከታሉ። መረጋጋት፣ ጽናት እና ስሜትን መቆጣጠር ፈታኝ በሆኑ ጊዜያት መረጋጋትን ለመፍጠር ይረዳሉ።

​💡 8. ይለማመዳሉ እና መማራቸውን ይቀጥላሉ
ታላላቅ መሪዎች ሁሉንም ነገር እንደሚያውቁ አያስቡም። የማወቅ ጉጉታቸውን ይጠብቃሉ፣ ለውጦችን ይቀበላሉ፣ እና ያለማቋረጥ ራሳቸውን ያሻሽላሉ።

​💡 9. ሌሎችን ያደንቃሉ እና ያከብራሉ
ሰዎች ዋጋ እንዳላቸው ሲሰማቸው የተሻለ ውጤት ያመጣሉ። ታላላቅ መሪዎች ስኬቶችን ያከብራሉ፣ ምስጋናን በልግስና ይሰጣሉ፣ እንዲሁም የሰዎችን ጥረት ይገነዘባሉ።

​💡 10. ከራሳቸው በላይ ለሆነ ትልቅ ዓላማ ይሠራሉ
ምርጥ መሪዎች ትኩረት የሚያደርጉት በግል ጥቅማቸው ወይም ስልጣናቸው ላይ ሳይሆን በተልዕኮ፣ በዕሴቶች እና በሚያመጡት በጎ ተጽዕኖ ላይ ነው።

​አመራር ማለት በስልጣን ላይ መሆን አይደለም። አመራር ማለት ሰዎች በአንድነት ሆነው የተሻለ ውጤት እንዲያመጡ ማነሳሳት ነው።
👏4
‎ሕይወት ልክ እንደ ዛፎች ሁሉ የየራሷ ወቅቶች አሏት።
‎ሁሉም ነገር ሞልቶ የተትረፈረፈ የሚመስልባቸው ጊዜያት አሉ፤ እንደዚሁም ሁሉም ነገር በዝምታ የሚረግፍባቸውና የሚበታተኑባቸው ጊዜያት አሉ።

‎ምናልባት ሰዎችን፣ አጋጣሚዎችን፣ ዕቅዶችን ወይም በአንድ ወቅት ትተማመንባቸው የነበሩ የራስህን ክፍሎች ልታጣ ትችላለህ። በእነዚያ ወቅቶች፣ ሕይወት ያለህን ነገር ሁሉ የምትወስድብህ ይመስል ይሆናል።

‎ነገር ግን ዛፎች አንድ ውብ ትምህርት ያስተምሩናል፦ ቅጠል መርገፍ የዛፉ መጨረሻ አይደለም፤ ለዕድገትና ለዕድሳት ዝግጅት እንጂ።

‎ከአውሎ ነፋስና ከብርቱ ክረምት በኋላ እንኳን ባዶ ሆነው ቢቆዩም፣ ሥሮቻቸው ግን አሁንም በምድር ተተክለዋል፤ ታጋሽ ሆነውም እንደገና የሚያብባበትን ጊዜ ይጠባበቃሉ።

‎ስለዚህ፣ ሕይወት በአሁኑ ሰዓት ከባድ መስላ ከታየችህ ይህንን አስታውስ፦ ጊዜያዊ መጥፋት ዘላቂ ሽንፈት ማለት አይደለም። አንዳንዴ ወቅቶች የሚመጡት ገና ባልተመለከትከውና ባልተረዳኸው መንገድ እንድታድግ ነው።

‎እንዲህ የሚል የጃፓን ምሳሌ አለ፦
‎"ሁሉንም ነገር እያጣህ እንደሆነ ከተሰማህ፣ አስታውስ፤ ዛፎች በየዓመቱ ቅጠሎቻቸውን ያረግፋሉ፣ ነገር ግን አሁንም እንደቆሙ ናቸው እና የተሻሉ ቀናት እስኪመጡ ድረስ ይጠባበቃሉ።"

#ታገስ!
https://t.me/mesfeect
❤3