MESFIN MAGO TULAMO
192 subscribers
80 photos
18 links
Education Consultant and Tranair (ECT)

https://www.youtube.com/@mesfin_12
Download Telegram
‎የጦር ሜዳውን ይቀይሩ፡ ጦርነቶችዎን ከላይ ያሸንፉ፣

‎የንስር ጥበብ

‎ንስር እባቡን መሬት ላይ አይዋጋም። መሬቱ ለእባቡ ይረዳል። ጥንካሬው፣ ፍጥነቱ እና ስልቱ ሁሉም እዚያ ላይ ነው። ስለዚህ ንስር ጥልቅ የሆነ ነገር ያደርጋል፤ እባቡን ወደ ሰማይ ያነሳና የጦር ሜዳውን ይቀይራል ከዚያም ይለቀዋል።

‎በአየር ውስጥ፣ እባቡ ጥንካሬ፣ ሚዛን እና ኃይል የለውም። በአንድ ወቅት አደገኛ የነበረው ነገር አቅመ ቢስ ይሆናል። በአንድ ወቅት በራስ መተማመን የነበረው ይሸነፋል። ተመሳሳይ ጠላት፣ ግን የተለየ ግዛት እና ይህ ልዩነት ውጤቱን ይወስናል።

‎በጠላት ምቾት ዞን ውስጥ አትዋጉ!

‎ብዙ አማኞች ጦርነትን የሚሸነፉት ጠላት ስለጠነከረ ሳይሆን በተሳሳተ ደረጃ ስለሚዋጉ ነው። በተፈጥሮ አመክንዮ ብቻ ስሜት፣ ፍርሃት፣ ክርክሮች እና የሰው ጥንካሬ መሬት ላይ፣ ጠላት ይበቅላል። እሱ የምቾት ቀጠና ነው።

‎ቅዱሳት መጻሕፍት “መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር…” (ኤፌሶን 6፡12) በማለት ያሳስበናል። መንፈሳዊ ውጊያዎችን በተፈጥሮ መሳሪያዎች ማሸነፍ አይቻልም። በሰው ኃይል መንፈሳዊ ተቃውሞን ስትዋጋ ድካም አይቀሬ ነው። ነገር ግን ጦርነቱን ወደ እግዚአብሔር ግዛት ስትቀይሩ፣ ድል የተረጋገጠ ይሆናል።

‎ጸሎት፡ ከፍ ያለ የመነሳት ተግባር፦

‎ጸሎት የጦር ሜዳውን የምንለውጥበት መንገድ ነው። ጸሎት ማምለጥ አይደለም፤ ከፍታ ነው። ግጭቱን ከሚታየው ወደ የማይታይ፣ ከጊዚያዊ ወደ ዘላለማዊ ያነሳል። ስትጸልዩ፣ ከሁኔታዎች በላይ ትነሳለህ እና ጦርነቶቻችሁን በእግዚአብሔር ዙፋን ፊት አቅርቡ።

‎በጸሎት ጠላት እግሩን ያጣል። ክሶች ኃይል ያጣሉ፣ ፍርሃት ድምፁን ያጣል። በምድር ላይ የሚመስለው ነገር በእግዚአብሔር ፊት ሊታከም የሚችል ይሆናል። ጸሎት የሰው ጥረት ገደብ ላይ በደረሰበት መለኮታዊ ጣልቃ ገብነትን ይጋብዛል።

‎እግዚአብሔር ጦርነቱን ሲወስድ፦

‎በመንፈሳዊ ስትሳተፍ፣ እግዚአብሔር ራሱ ወደ ጦርነቱ ገባ። "ሰልፉ የእግዚአብሔር ነው እንጂ የእናንተ አይደለም" (2ኛ ዜና 20:15) እግዚአብሔር በፍትሃዊነት አይዋጋም - የሚዋጋው ለማሸነፍ ነው። ግራ መጋባት በነበረበት ጥበብን፣ ድካም በነበረበት ጥንካሬን፣ ትርምስ ባለበት ሰላምን ያመጣል።

‎መንፈሳዊ ጦርነቶችን በራስህ ለማሸነፍ ፈጽሞ አልተፈጠርክም። የተፈጠርከው በእግዚአብሔር ላይ እንድትመካ ነው። እግዚአብሔር ስለ እናንተ ሲዋጋ ውጤቱ አያጠያይቅም፣ ተስተካክሏል።

‎ከላይ ተነሱ፣ ከዚያ ይልቀቁ፦

‎ንስር ከእባቡ ጋር ያለማቋረጥ አይታገልም፤ ያነሳዋል፤ ከዚያም ይለቀቃል፤ በተመሳሳይ፣ ጦርነቶቻችሁን በጸሎት ካነሳችሁ በኋላ፣ ለእግዚአብሔር መልቀቅን ተማሩ። መተማመን ጭንቀትን ይተካል። እምነት መጣርን ይተካል። እረፍት እጅ መስጠትን ይከተላል።

‎በጭንቀት መሰረት መሆኖ እርስ በርስ እንዲተሳሰር ያደርገዋል። በጸሎት መነሳት ነፃ ያወጣችኋል።

‎ድል ከላይ፦

‎ስለዚህ በእሱ ምቾት ዞን ውስጥ ከጠላት ጋር አይዋጉ። መሰጠት ካለበት ጋር ያለማቋረጥ አትታገል። የጦር ሜዳውን እንደ ንስር ይለውጡ። ከተፈጥሯዊው በላይ ከፍ ይበሉ። መንፈሳዊውን ያሳትፉ። አጥብቃችሁ ጸልዩ፣ በጥልቀት አምልኩ፣ በእምነት ቁሙ፣ እና እግዚአብሔር ሀላፊነቱን ይውሰድ።

🔥 ድል እግዚአብሔር ሲታገልህ የሚቻል አይደለም፤ ዋስትና ነው።

#ሻሎም!
👍3👏1
🧠 #ድብቁ_አእምሮህ፦ የሕይወትህ እውነተኛ መሪ!

ሕይወትህን የሚመራው በንቃት የምታስበው አስተሳሰብህ ብቻ ይመስልሃል? እውነታው ግን ሌላ ነው! ሕይወታችንን 90% የሚቆጣጠረው በውስጣችን ያለው ድብቁ አእምሮ (Subconscious Brain) ነው።

ሕይወታችንን በአጭር ጊዜ ውስጥ ለመቀየር የሚያስችሉ እነዚህን 4 ታላላቅ ቁምነገሮች እንማር፦

1. 🔄 አሮጌውን "Operating System" መቀየር!

ድብቁ አእምሯችን ልክ እንደ ኮምፒውተር ሶፍትዌር ነው። ከልጅነት ጀምሮ የተከማቹ ፍርሃቶች፣ እምነቶችና ልምዶች ዛሬ የምንወስነውን ውሳኔ ይወስኑታል።  እነዚህን አሮጌና ጎጂ ፕሮግራሞች እንዴት አውጥተን በአዲስና በጤናማ አስተሳሰብ መተካት እንደምንችል እንይ።

2. 🧱 መሰናክሎችን መሻገር (Overcome Obstacles)

ብዙ ጊዜ ወደ ግባችን እንዳንሄድ የሚይዘን ከውጭ የሚመጣ ተፅዕኖ ሳይሆን፣ በውስጣችን ያለው "አትችልም" የሚል ድምፅ ነው። ድብቁ አእምሯችንን በማሰልጠን ፍርሃትን ወደ ድፍረት፣ ጥርጣሬን ደግሞ ወደ በራስ መተማመን መቀየር ይቻላል።

3. 🌿 ራስን መፈወስ (Heal Your Body)

አእምሮና አካል በእጅና በጓንት የተሳሰሩ ናቸው። ድብቁ አእምሯችንን በሰላም፣ በፍቅርና በፈውስ ሐሳቦች ከሞላነው፣ ሰውነታችን ከጭንቀትና ከተለያዩ ሕመሞች የመፈወስ አቅሙ በከፍተኛ ሁኔታ ይጨምራል።

4. 🎯 ግብ ላይ መድረስ (Reach Any Goal)

ድብቁ አእምሮ ግብ ሲሰጠው እንደ ማግኔት ይሠራል፤ ወደ ግቡ የሚያደርሱ አጋጣሚዎችንና ሰዎችን እንድናስተውል ያደርጋል። አእምሮህ የሚፈልገውን ነገር በግልጽ እንዲያይ ካደረግከው፣ ወደ ስኬት የሚወስደውን መንገድ ያሳየሃል።
👍3
#Ethiopia ተስፋ_ጽናት_ደስታ!!

"ለመኖር ሁለት ፐርሰንት ዕድል ብቻ እንዳለኝ በሀኪሞች ተነግሮኛል:: ነገር ግን ሁለት ፐርሰንት ማለት ዜሮ ማለት አይደለም:: ሁለት ፐርሰንት ማለት የሆነ ነገር እንደሆነ ሰዎች ሁሉ እንዲያውቁ እፈልጋለሁ!!"

"ደስተኛ ልትሆን ለመወሰን ሕይወት ከዚህ በፊት ከነበረው ከባድነት ቀላል እስኪሆን መጠበቅ የለብህም!!"
____

ወደ American Got Talent የሚመጡ ተወዳዳሪዎች መድረኩን ከመርገጣቸው በፊት እጅግ ከሚጨነቁባቸው ነገሮች ዋናው "ሳይመን ምን ይለን ይሆን!?" የሚል ይሆንና ትንሽ ዘና ካሉ "ሳይመን 'yes’ ይሰጠን ይሆን!? የሚል ይሆናል:: ከሳይመን ካውል አፍ 'yes’ ከመቀበል አልፎ ከአይኖቹ እንባ እንዲወጣ ማድረግ ግን እጅግ ከባድ ነው:: ከሁሉ በላይ ከባዱ ግን የሳይመን እጆች ውዱን Golden Buzzer  እንዲጭኑ ማድረግ ነው::

አንዲት ሰውነቷ ገርጥቶ ልትቀነጠስ የደረሰች ኮሳሳ ተወዳዳሪ ወደ መድረክ መጣች:: የዕለቱ ተረኛ ጠያቂ ሀዋርድ ነበር:: "እንዴት ነሽ!?" አላት:: በጣም ደስተኛ ነኝ:: እዚህ በመሆኔ በጣም ደስ ብሎኛል" አለች:: ሁሉም ተወዳዳሪ የሚለው ስለሆነ አይደንቅም:: አራቱም ዳኞች ከተለመደው ያልተለየ ደስታቸውን ገለፁ::

ሀዋርድ ቀጠለና "ምንድነው የሚታቀርቢልን!?" አላት:: እሷም "It is Ok” የሚል የራሴን ስራ ነው" አለች:: ሁላቸውን ባንድ አፍ "አዎ! ሁሉ ደህና ነው" አሉ:: ግን ይህም አይገርምም:: ሀዋርድ ቀጠለና "ግን ሁሉ ደህና ነው ስለምንድነው?" ሲላት ከካንሰር ጋር ስትታገል የኖረችውን የሕይወት ውጣውረድ ነገረቻቸው:: የሁሉም ፊት ጨለማ:: የእሷ ፊት ግን የደስታ ጨረር ከመርጨት አላቆመም:: ኮምጨጭ አለችና "አረ ሁሉ ደህና ነው:: እኔ ሰላም ነኝ" አለቻቸው::

የዚያኔም ባለስል አስተያየቱ ሳይመን "አንድ ጥያቄ ልጠይቅሽ? አሁን እንዴት ነሽ!?" አላት:: እሷም "የመጨረሻውን ምርመራ ሳደርግ በሳንባዬ: ጣፊያዬና ጉበቴ ላይ ካንሰር እንዳለ ተነግሮኛል" ስትል ሳይመን በድንጋጤ አስፈሪ ጭጋግ ውስጥ ሆኖ "ዋው" ሲል ሀዋርድ ቀጠለና "ስለዚህ ደህና አይደለሽም ማለት ነዋ" አላት:: "በርግጥ በሁሉም መልኩ አይደለም" ስትል ሀዋርድ ተገርሞ "ማንም ምን አይነት ሁኔታ ውስጥ እንዳለሽ እስከማያውቅ ድረስ ለሌሎች የደስታ ጨረር የሚረጭ አስገራሚ ፈገግታ አለሽ" ብሎ አሞካሻት!!

Nightbird የሕይወት ታሪኳን አሳማኝ በሆነ መልኩ በዜማ ካቀረበች በኅላ የደኞች ውሳኔ የሚሰጥበት  ሰአት ደረሰ:: ሁሉም ሳግ እየተናነቃቸው በስሜት የተሞሉ አዎንታዊ አስተያየቶችን ሰጡ:: ተራው ሲደርስ ተጠባቂው ሳይመን ሌሎች ዳኞች በሰጡት አስተያየት ሙሉ በሙሉ እንደሚስማማ ገልፆ ተጨማሪ ስሜቱን እንዴት መግለጥ እንዳለበት ግራ ገብቶት ሲያመነታ ሳለ መኻል ላይ አቋርጣ በከፍተኛ ፈገግታ በመሞላት "ደስተኛ ልትሆን ለመወሰን ሕይወት ከዚህ በፊት ከነበረው ከባድነት ቀላል እስኪሆን መጠበቅ የለብህም" የሚል እጅግ አስገራሚ አስተያየት ሰነዘረች::

ያ ንግግር ብዙዎችን ያስገረመ ቢሆንም ሳይመንን ለደቂቃዎች አፍዝዞ እንባ ከሁለቱን ዓይኖቹ ፈሰሱ:: ከፊቱ ያለውን የመጠጥ ዕቃ አነሳና ተጎንጭቶ ሳግና እንባውን አወራረደ:: በመቀጠልም  አስተያየቱን ሰነዘረ:- "በዚህ ዓመት ታላላቅ ችሎታ ያለቸውን ሰዎች  አይቻለሁ:: ሆኖም ላንቺ 'yes’ አልሰጥም" ሲል ከዳኞች እስከ ታደሚ በቅሬታ አጉተመተሙ:: ሳይመን አልጨረሰም ነበር:: "የሚሰጥሽ ከ'yes’ የተሻለ ነገር ነው" አለና እጆቹ ወደ Golden Buzzer ሄደ:: አደራሹ በከፍተኛ ደስታ ሲያስተጋባ Nightbird የወርቁ ብናኝ ላይ በደስታ እንባ ተደፋች!!
—-------
Jane Marczewiski (በቅጽል ስሟ Nightbird) በ2017 ባደረገችው ምርመራ ደረጃ ሶስት የጡት ካንሰር በሽተኛ መሆኗ ታውቆ ከዚያ በኅላ በምድር የሚኖራት ዕድሜ ስድስት ወራት ብቻ እንደሆነ ተነገሯት ከሕይወት ጋር ትግሏን ቀጠለች:: ትንሽ ቆይቶ በ2018 ከካንሰር ነፃ መሆኗ ቢነገራትም መልካም ዜናው ብዙም አልቆየም:: እንደገና በሽታው እንዳለባት ተነግሯት ትግሏን ቀጠለች:: የሕይወት ትግሏን ከጎኗ ሆኖ ማገዝ የሚጠበቅበት የአምስት ዓመት የትዳር አጋሯ ጥሏት ኮበለለ::

ይቺ ምስኪን: ብቸኛ ፅኑ ሴት ናት ሰኔ 10 2020 American Got Talent መድረክ ላይ ቆማ ሳለ ሀዋርድ "እዚህ ከማንጋር መጣሽ?" ሲላት (አባባሉ "የድል ደስታሽን ከማን ጋር ሊታጣጥሚ ነው?" የሚል ድምፀት አለው) "ብቻዬን ነኝ" ብላ የመለሰችው እና ከሳይመን Golden Buzzer በኅላ ከአዳራሹ ብቻዋን እየዘለለች የወጣችው!!

በዚህ የኮቪድ ውጥንቅጥ ወቅት ለብዙዎች የደስታ ምስክር እንደሆነች በማመን "you are the voice we all need to hear this year” የሚል አስተያየት ከሳይምን የተሰጣት ይቺ ብርቱ ሴት ከBBC ጋር በነበራት ቃለ መጠይቅ "ወደ ኅላ የሚያስቀርብኝ መልካም ነገሮች የሉትምና እግዚአብሔር የሆነ ጊዜ ላይ ቅጽበታዊ ፈውስ እንደሚያመጣ አምናለሁ" ስትል ተናግራለች::

May 3 በለጠፈችው ብሎጏ:- "እግዚአብሔር መጀመሪያ ለእኛ ራሱን ባስተዋወቀበት ወቅት (ዘፍጥረት) ያሳየንን ነገር ረስተን ይሆናል:: አቧራ ላይ እየዳሀ ነበር የቀረበን:: እንዴት መተንፈስ እንዳለብን በማናውቅበት ጊዜ ሳንባችንን በአየር ሞልቶ መተንፈስን አስተማረን" ብላለች!!

በሌላ ጽሑፏ ሕመሟን በተመለከት "እግዚአብሔር አብዛኛውን ጊዜ ወሳጅ ሳይሆን ሰጪ ነው:: ከመውሰድ ይልቅ ይጨምራል" ትላለች:: “ጨለማዬን አልወሰደውም ግን ብርሃን ጨመረልኝ:: ብቸኝነቴን አልፈወሰውም ግን እርሱ ይበልጥ ቀረበኝ" ትላለች:: በሕመሟ ተስፋዋ ይጨምራል እንጂ ተስፋ ቢስ አይደለችም:: በመሆኑም  "በህመሜ ተስፋ የማደርገው የእግዚአብሔርን ቅርበት በዚያ ስላወቅሁ ነው" ትላለች::

"እግዚአብሔር ትሁት ሆኖ ወደ እኛ የቀረበበት ከመስቀል የተሻለ ስፍራ የለም:: በኃጢአትና በሽታ ወደ ተመታው ዓለም  እግዚአብሔር ሰው ሆኖ መጣ::  ይህም እግዚአብሔር በሙሉ ፈቃድና ትህትና የኃጢአታችን ምትክ ሆኖ ሊቤዥን ወደ መስቀል ሄደ" ትለናለች!!

በመከራና ስቃይ ውስጥ ስናልፍ ልኖረን የተገባው እምነት: ተስፋና ፅናት ይኼ ነው:: የመስቀሉ ስቁዩ ኢየሱስ ስቃይና ህመማችን ይገባዋል:: የምንጠብቀው ፍፁም ቤዛችንም እሱ ነው:: አንድ ቀን ፈጽሞ የማይታመምና የማይሰቃይ አካል እስክንለብስ አሁን ከብዶን ብንቃትትም ተስፋ ቆርጠን ግን ወደኅላ አናፈገፍግም!!

መልካምና የሚያንፁ አስተማሪ ጽሁፎችን  ለተከታታይ ቀናቶች ሼር አደርጋችኋለሁ። እናተም በደስታ ለሌሎች ማካፈላችሁን አትርሱ።
ቻናሉንም ሼር ማድረጋችሁን አትዘንጉ።
3
👏2
MESFIN MAGO TULAMO
Photo
አገልግሎት ምንድን ነው ?

አገልግሎት ማለት፡-
እውቀትን ወይም ሙያን መሰረት አድርጎ የተገልጋዮችን ፍላጎት ለማሟላት የሚደረግ ጥረት ነው። በሌላ አገላለጽ አገልግሎት የተገልጋዮችን ፍላጎት የማሟላት ሂደት ነው። አገልግሎት የተገልጋዮችን ፍላጎት መሰረት ያደረጉ ዓላማ ተኮር ተግባራት ሲሆኑ ስኬታማና ኢኮኖሚያዊ ቅልጥፍናን በተላበሰ መልኩ የሚከናወኑ በጊዜ፣ በመጠን፣ በወጭና በጥራት እንዲሁም በተገልጋይ እርካታ ሊለኩ የሚችሉ በአገልግሎት ተቀባዩ ዘንድ ፋይዳ ያለው እሴት የሚጨምሩ በአገልግሎት አቅራቢው የሚከናወኑ ተግባራት ናቸው።
የአገልግሎት መሰረታዊ ባህሪያት
አገልግሎት የራሱ የሆኑ መሰረታዊ ባህሪያት አሉት። እነዚህን መሰረታዊ ባህሪያት ማወቅ ለአንድ አገልግሎት ሰጪ ተቋም በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት የሚያጋጥሙ ችግሮችን ለመፍታት እና ውጤታማ የሆነ አገልግሎት ለተገልጋዮች ለማቅረብ ወሳኝ ጠቀሜታ ይኖረዋል። እነዚህም፡-

1. የማይጨበጥና የማይታይ /Intangeble/ መሆኑ፦
አገልግሎት ሊታይ፣ ሊዳሰስ፣ሊሸተትናሊቀመስ ወይም ሊከማች የማይችል በመሆኑ የአገልግሎቱን ጥራትና ትክክለኛ ውጤት አገልግሎት ሰጭው አስቀድሞ ለመተንበይ እንዳይችል ያደርገዋል። አገልግሎት እንደ ምርት ሁሉ ቀድሞ የሚዘጋጅና የሚከማች ሳይሆን በአገልግሎት ሰጭው አካል/ ግለሰብ የሚፈጠርና ለእያንዳንዱ ተገልጋይ ወይም ተገልጋይ የሚሰጥ ነው።

በመሆኑም በተፈለገው መንገድ አገልግሎት መሰጠቱን ለማወቅ የተገልጋዩን መኖርና አገልግሎቱን መቀበል በሂደቱም የነበረውን ስሜት ማወቅና መረዳት ያስፈልጋል። ይህንን በተገቢው ለመለካት የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ አስቀድሞ ማዘጋጀት ጠቀሜታው ከፍተኛ ነው።
2. የማይለያይ /Inseparable/ መሆኑ፦
በአገልግሎት አሰጣጥ ሂደት አገልግሎት ሰጭውና አገልግሎት ተቀባዩ ፊትለፊት ካልተገናኙ አገልግሎት ከአንዱ ወደ ሌላው አይሸጋገርም። አገልግሎት ምንጊዜም ከአገልግሎት ሰጪው ዘንድ ያለ ነው። አገልግሎቱና አገልግሎት ሰጭው ተቋም ወይም ግለሰብ ሊለያዩ አይችሉም። ስለዚህ የአገልግሎት ጥራት የሚፈጠረውም ሆነ የሚለካው ራሱ አገልግሎት ሰጭው ወይም እሱን ወክለው አገልግሎቱን በሚሰጡ ሰዎች የስነምግባርና የብቃት ደረጃ መሰረት አድርጎ ሲሆን የተገልጋዩ ፍላጎት ጋርም የሚጣጣም መሆን ይኖርበታል።

3. ተለዋዋጭ /Variable/ መሆኑ፦
አገልግሎት ልክ እንደ ምርት ሁሉ ተመሳሳይ ጥራት ያለው ምርት በማምረትና አስቀድሞ ጥራቱን በመፈተሽ የሚቀርብ አይደለም። ለተለያዩ ተገልጋዮች የሚቀርበው አገልግሎት በአገልግሎት ሰጭዎች ልምድ፣ ተሞክሮ፣ ባህሪ፤ ከተገልጋዮች አመለካከት፣ ባህሪና ሌሎች ውጫዊና ውስጣዊ ምክንያቶች ተመሳሳይ ሊሆን አይችልም። ይህንን ተለዋዋጭ ባህሪ ለማስቀረት አገልግሎት ሰጭ ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ስታንዳርድ በማውጣት እና ተከታታይ የሆነ የሰው ሃይል ልማት ተግባራትን በማከናወን ተመሳሳይ የሆነ እና ለተገልጋይ እርካታን ሊያመጣ የሚችል አገልግሎት ለመስጠት ጥረት ያደርጋሉ።

4. ለብልሽት ተጋላጭ /Perishable/ መሆኑ፦
አገልግሎት አስቀድሞ አዘጋጅቶ በመደርደሪያ ላይ በማስቀመጥ በሌላ ቀን ጥቅም ላይ እንዲውል ማድረግ አይቻልም። በሌላ አገላለጽ ለዛሬ ያልተጠቀምንበት አገልግሎት ለነገ ልንጠቀምበት አንችልም። ይህ ደግሞ አገልግሎት ሰጭ ተቋማት አቅርቦትና ፍላጎትን ለማጣጣምና የተገልጋዮችን ፍላጎት ለማርካት እንዳይችሉ ያደርጋቸዋል።

5. የተገልጋይን ተሳትፎ /Customer Participation/ የሚጠይቅ መሆኑ፦
አገልግሎት ያለተገልጋይው ተሳትፎ የሚታሰብ አይደለም።
በመንግስት የሚቀርቡ አገልግሎቶችና ልዩ ባህሪያቸው
1, ከህዝብ በተሰበሰበ ታክስ ፋይናንስ የሚደረግ መሆኑ
2, ለትርፍ የሚከናወን አለመሆኑ፦
3, ለንግድ አገልግሎት የሚውሉ አለመሆኑ፦
4, በመንግስት ብቻ የሚሰጡ መሆኑ፦
5, ፍትሐዊነትን እንደመርህ የሚጠቀሙ መሆናቸው
6, የህዝብ ተጠያቂነት ያለበት መሆኑ፦

ውጤታማ አገልግሎት ለመስጠት አምስት ቁልፍ አስቻዮች
👏1
ምንም ብታደርጉ ሰዎች ከማውራት ስለማይመለሱ ዝም
:
👉 ደሀ ብትሆን የመናጢ ልጅ ፤ ሀብታም ብትሆን ዶላር ያሳበጠው ይሉሀል።
👉 ከሴት ጋር ብትሄድ ሴሰኛ ፤ ብቻህን ብትሆን ወፈፌ ይሉሀል ።
👉 ብትፈጥን ቀዥቃዣ ፥ ብትዘገይ ዘገምተኛ ።
👉 ብታወራ ለፍላፊ ፥ ዝምብትል ዝጋታም ።
👉 ብትራመድ አርፎ አይቀመጥም ፥ አርፈህ ብትቀመጥ ዝፍዝፍ
👉 ብትማር አወቅሁ ባይ ፥ ባትማር የአቡጊዳ ሽፍታ ።
👉 ብትወፍር ጠብደል ፥ ብትከሳ በልቶ ማይጠረቃ ።
👉 ብትይዝ ቋጣሪ ፥ ብትለቅ መንዛሪ ።

እንደውም አንድ የሀገራችን ተረት አለ"ባልና ሚስት አህያ እየነዱ ሲሄዱ ተቺዎች አገኙዋቸውና ፦"እንከፎች አህያዋ ሳለች እንዴት አይሳፈሩባትም" ሲሉ ባል ሰማና ሚስቱን " በይ ፍጠኚና አህያዋ ላይ ተሳፈሪ" - አላት።

ትንሽ እንደሄዱ ሌሎች ተቺዎች ፦ "ይች ባለጌ ፥ ባል በእግር እየሄደ ሚስት በጋማ ከብት" ብለው ወረፏቸው።ባል ሚስቱን አስወርዶ አህያዋ ወገብ ላይ ቂብ አለ ፤ትንሽ እንደተጋዙ ሌሎች ተቺዎች አገኝዋቸው ፦ "የተረገመ ሚስቱን በእግር እያስኬደ እሱ በአህያዋ ብለው ወረዱባቸው ።

ባልና ሚስት ድንገት ቢተዉን ብለው አህያዋ ላይ ሲፈናጠጡ ሌሎች ተቺዎች ደም አገኙዋቸውና "ምን እንስሳ ብትሆን ለሁለት ይከመሩባታል ግፈኞች ..." የስድብ ናዳ ለቀቁባቸው ።

እንግዲህ ወዳጆቼ ፦ አህያዋን ቢሸከሙ ኖሮ ከዚህ አይብስምን ?
ስለዚህ ሰዎች ያሉትን ይበሉ አንተ አንተነትህን ሁንና ህሊናህ አውጥቶና አውርዶ ከተቀበለው ሀሳብ ጋር ተስማማ።
:
ለጮኸ ውሻ ሁላ ድንጋይ መወርወር ጊዜን ማባከን ነው፡፡

ደራሲ ስብሀት ገ/እግዚያብሄር
3
‎❝ማውራት ፈልገህ ነገር ግን ማውራት እንደሌለብህ አውቀህ ዝምታን ከመረጥክ እመነኝ የመኖር ትርጉሙ ገብቶሃል ማለት ነው።❞

‎የመኖር ትልቁ ምስጢር ማውራት ባለብህ ቦታ ማውራት አለብህ እና ማውራት በሌለብህ ቦታ ማውራት የለብህም። ምክንያቱም ሰሚ በሌለበት ቦታ እራስህን ትጎዳለህ፤ እራስህን ታጣለህ ብዙውን ጊዜ እኛ የምንሸወደው ማውራት በሌለብን ቦታ ስናወራ ነው።

‎በህይወት ዘመንህ ማውራት ያለብህ ሰሚ ወይም አድማጭ ባለበት ቦታ ነው ማውራት ያለብህ ። በመናገር የምትሰራውን ስህተት አይተህ ዝም ብለህ ማለፍ የለብህም። ምክንያቱም ተመልሶ አንተን መጉዳቱ ስለማይቀር ።

‎ትግል በማውራት ነው፤ ዝም በማለት አይደለም፥ ነገር ግን ዝምታ መሰናክል፣ እንቅፋትን፣ ችግርን፣ መከራን እና ስቃይን ለማለፍ ነው። ዝምታ የሚያስፈልገው ስለዚህ ዝምታ ወርቅ ነው የሚባለው ተግዳሮትን ለማለፍ ነው።

MMT Media
Yeleta-Generation-ትዉልድ
@highlight
Mesfin Mago Tulamo
5
ህይወት ጉዞ ናት። አንዳንዴ መንገዱ ጠመዝማዛ፣ አንዳንዴ ደግሞ ቀጥ ያለ ይሆናል። ነገር ግን፣ የትኛውም መንገድ ቢገጥምህ፣ ሁሌም በራስህ እመን። 💪

በውስጥህ ያለው ሃይል ከምትገምተው በላይ ነው። እያንዳንዱ ፈተና እንድትጠነክርና የበለጠ እንድትሆን እድል ነው። ተስፋ ስትቆርጥ፣ ትናንት የደረስክበትን ስኬት አስታውስ። ዛሬ የምትወስደው ትንሽ እርምጃ፣ ነገ ትልቅ ለውጥ ያመጣል።

ህልምህ ትልቅ ሊሆን ይችላል። ሰዎች ሊጠራጠሩህ ይችላሉ። ግን አትስማ! የራስህ ብርሃን አለህ። ያንን ብርሃን ተከተለው። ፍርሃትህን ወደ ጥንካሬ፣ ጥርጣሬህን ወደ እርምጃ ቀይር። 💖

አንተ ልዩ ነህ። የአንተ ታሪክ፣ የአንተ ማንነት ከማንም ጋር አይወዳደርም። ወደፊት ተመልከት፣ እራስህን አትውቀስ። በየቀኑ ለራስህ ደግ ሁን። ደስታን ምረጥ፣ ለራስህ ታማኝ ሁን። 🌟

የምትፈልገውን ሁሉ ማድረግ ትችላለህ። ወደፊት ሂድ!

Share
👍3
ሞኝ በንግግሩ፣ ብልህ ደግሞ በዝምታው ይታወቃሉ!
በየመንገዱ እየቆሞክ ለሚጮህብህ ውሻ ሁሉ ድንጋይ ከወረወርክ ካሰብክበት አትደርስም!

ዝም ብለህ ቀጥል!!!
👏5
🌟 ውድቀት የስኬት መውጫ በር ነው

በአንድ ወቅት ታላላቅ ህልሞች የነበረው አንድ ወጣት ነጋዴ ነበር። ሁሉንም ነገር ሸጦ ትንሽዬ ቡቲክ ለመክፈት ወሰነ። ለዓመታት የሰራበትን ገንዘብ፣ ከቤተሰቡ የተበደረውን እና ከባንክ ያገኘውን ብድር ሁሉ ለዚህ ስራ አዋለ። ቡቲኩን ለማስዋብ፣ ምርጥ የሚባሉ ልብሶችን ለማምጣት እና ደንበኞችን ለመሳብ ቀን ከሌት ደከመ። ሁሉም ነገር በጥሩ ሁኔታ እየሄደ ይመስል ነበር። "አሁን ሁሉም ነገር ተሳክቷል" ብሎ በልቡ አሰበ።

ግን የገበያው ሁኔታ ተቀየረ። በአቅራቢያው ትላልቅ የልብስ መሸጫ ሱቆች ተከፈቱ። የደንበኞች ቁጥር እየቀነሰ መጣ። የሸቀጦቹ ሽያጭ ቆመ። ወጣቱ ነጋዴ ከባድ ኪሳራ ውስጥ ገባ። ብድሩን መክፈል አልቻለም። ሰራተኞቹን አሰናበተ። በመጨረሻም የህልሙ መገለጫ የነበረው ቡቲክ ተዘጋ።

ይህ ውድቀት ከባድ ሥቃይ ነበር። ቤተሰቦቹ የሰጡትን ገንዘብ፣ የባንኩን ዕዳ፣ የራሱን የብዙ አመታት ድካም በአንድ ጊዜ አጥቷል። ሰዎች "ለምን ሞከረው?"፣ "ከመጀመሪያውም አይሳካለትም ነበር" እያሉ ይዘባበቱበት ጀመር። ወጣቱ ነጋዴ ተስፋ ቆረጠ። ራሱን ከሰዎች አገለለ። በራሱ ላይ እምነት አጣ።

አንድ ቀን ግን በራሱ ላይ አሰበ። "በእርግጥ ምን ስህተት ሰራሁ?" በማለት ራሱን ጠየቀ። ሁሉንም ነገር በጥንቃቄ መረመረ። ለምን እንደወደቀ ተረዳ። ውድቀቱ ያስተማረው ትምህርት ከገንዘብ በላይ ዋጋ እንዳለው ተገነዘበ። "ተሳስቻለሁ፣ ግን ተስፋ አልቆረጥኩም" ብሎ በልቡ አሰበ። ከዚህ በፊት የነበረውን ስህተት ላለመድገም ቃል ገባ።

ብዙ ጊዜ ከባለ ዕዳዎቹ እየሸሸ ይኖር ነበር። "አልሞትኩም!" ብሎ ለራሱ ደጋግሞ ነገረው። ከዚያም አንድ አዲስ ሀሳብ አመጣ። ገንዘብ የማይጠይቅ እና በትክክለኛው መንገድ ከተሰራ ትልቅ ስኬት የሚያመጣ የንግድ ሀሳብ። በመጀመሪያ በኦንላይን አማካኝነት አነስተኛ የልብስ ንግድ ጀመረ። የደንበኞችን ፍላጎት በጥንቃቄ አጥንቶ፣ በትክክለኛው ጊዜ ትክክለኛውን ምርት ማቅረብ ጀመረ።

ውድቀቱ ባስተማረው ትምህርት እና ባዳበረው ልምድ፣ በጥቂት ወራት ውስጥ ንግዱ ማደግ ጀመረ። በመጀመሪያ ደንበኞችን መሳብ አቃተው ነበር፣ ነገር ግን ተስፋ ባለመቁረጥ፣ በወደቀበት መንገድ ላይ ተነስቶ በመጓዙ ምክንያት በአጭር ጊዜ ውስጥ ትልቅ ስኬት ላይ ደረሰ። የቀድሞ ዕዳውን ሁሉ ከፈለ። በመጨረሻም ትልቅ እና ስኬታማ የኦንላይን ልብስ መሸጫ ሱቅ ባለቤት ሆነ።

ውድቀት መጨረሻ አይደለም። ውድቀት ለተሻለ ነገር መማሪያ መድረክ ነው። ተነስተህ ከተጓዝክ የማትደርስበት ቦታ የለም።
https://t.me/mesfeect
👍3🔥1
ከተማ መሬትና ቤት ይዞታ ስመ-ንብረት ዝውውር የሚፈጸምበት መመሪያ
======================
👉በስመ ንብረት ዝውውር ወቅት መሟላት ያለባቸው መረጃዎች የከተማ ቦታን በሊዝ ስለመያዝ በወጣው አዋጅ ቁጥር 721/2004 አንቀፅ 33 ንዑስ አንቀፅ 2 አንፃር ሲታይ፦
ሀ/ የከተማ ቤትና ይዞታ ስመ-ንብረት ዝውውር ስለመፈጸም የሚከተሉት ማስረጃዎች/ሰነዶች ሲሟሉ የስመ ንብረት ዝውውር የሚፈጸም ይሆናል፤
✍️ህጋዊ የይዞታ ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት/ካርታ፣
✍️ጸድቆ የተሰጠ የግንባታ ፕላን፣ የስራ ዝርዝር ግምት ወይም የጸደቀ የነባር ግንባታ ፕላን፣
✍️ጸድቆ በተሰጠው የግንባታ ፕላን መሰረት ስለመገንባቱ እና ግንባታው ያለበት ደረጃ የተረጋገጠበት ማስረጃ/50% እና በላይ/፤
✍️ውዝፍ የሊዝ ኪራይ ዕዳ የሌለበት ስለመሆኑ የተሰጠ የማረጋገጫ ደብዳቤ ወይም ቀሪ የሊዝ ክፍያ ዕዳውን ገዥው ለመክፈል በፊርማ ያረጋገጠበት የስምምነት ደብዳቤ ፣
✍️በንብረቱ ላይ የባንክ እዳ/የፍ/ቤት ዕግድ የሌለበት ስለመሆኑ ማረጋገጫ ሲቀርብ፣
✍️ የቤትና ይዞታ ስም ዝውውር ጥያቄው የቀረበው በህግ ባለመብት/በውርስ/በፍርድ አፈጻጸም ወይም በውክልና ከሆነ ይህንኑ የሚገልጽ ማስረጃ፤
✍️ በግለሰቦች ግዥና ሽያጭ ወይም ስጦታ ስምምነት ከሆነ በዉልና ማስረጃ በአካል ቀርቦ በእማኞች የተፈረመ የስምምነት የውል ማስረጃ ሲቀርብ፣
ለ/ በሽያጭ/በስጦታ የሚተላለፍ ቤትና ይዞታ ስም-ዝውውር መሟላት ያለባቸው መስፈርቶች፣
✍️ግንባታው በዋስትና ያልተያዘ እንዲሁም እዳ የሌለበት መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም እዳው በሚመለከተው አካል በደብዳቤ መነሳቱ ሲረጋገጥ፣
✍️ የቤትና ይዞታ ሽያጭ ወይም የስጦታ ውሉ በምስክሮች ሲረጋገጥና በፍትህ ወይም በመሪ ማዘጋጃ ቤት ፊት ቀርቦ ሲጸድቅ፣
✍️ ግንባታው ጸድቆ በተሰጠው ዲዛይን መሰረት 50 በመቶና በላይ የተሰራ መሆኑ በባለሙያ ተረጋግጦ ሲቀርብ፣
✍️ በይዞታው ላይ ውዝፍ የቦታ ኪራይ የሌለበት ስለመሆኑ ወይም ውዝፍ የቦታ ኪራይ ክፍያ አጠናቆ የከፈለ ስለመሆኑ የቀረበ ክፍያ ደረሰኝ ማረጃ ሲቀርብ፣
✍️ የአገልግሎትና የገቢዎች ክፍያ በቤቱ ግምት መሰረት ስለመከፈሉ ሲረጋገጥ፣
ዝውውሩ የሚፈፀመው በሊዝ በተገኘ ይዞታና ግንባታ ላይ ከሆነ
✍️ የሊዝ ይዞታ ባለቤትነት ኦሪጅናል ካርታና ውል ሲቀርብ፣
✍️ በሊዝ ውል መሰረት ክፍያው የተጠናቀቀና ሌሎች ግዴታዎቹን የተወጣ መሆኑ ሲረጋገጥ ወይም የሊዝ እዳው ያልተጠናቀቀ ከሆነ ስም የሚዞርለት ወገን እዳውን ለመክፈል እና ነባሩን የሊዝ ውል ግዴታዎች የተቀበለ ስለመሆኑ ከከተማው በጽሁፍና በፊርማ አረጋግጦ ሲያቀርብ፣
✍️ በሊዝ የተገዛን የመሬት ይዞታ ለሌላ ሰው ለማስተላለፍ በቅድሚያ በገባው የሊዝ ውል መሰረት በተቀመጠው የጊዜ ገደብ የሚፈለገውን የግንባታ ደረጃ ያሟላ መሆኑ ወይም የግንባታ ፈቃድ የጊዜ ገደብ ያላለፈ ወይም የግንባታ ማራዘሚያ የተፈቀደለት መሆኑ ሲረጋጥ፣
✍️ የከተማ ቤትና ይዞታ ሽያጭ ወይም የስጦታ ውሉ በምስክሮች ሲረጋጥና በዉልና ማስረጃ ቀርቦ ሲጸድቅ ይሆናል፡፡
ሐ/ በውርስ የተገኘ ይዞታና ቤት የባለቤትነት ስመ-ንብረት ዝውውር አፈፃፀም፣
(ሀ) በውርስ የተላለፈ ነባር ይዞታ ዝውውር ለመፈፀም መሟላት ያለባቸው፡-
✍️ የሚዛወረው የመሬት ይዞታ ወይም ቤት ህጋ የባለቤትነት ማስረጃ/ካርታ ሲኖረው፣
✍️ ወራሾች የውርስ ባለመብትነትን የሚያረጋግጥ የፍርድ ቤት ውሳኔ ማስረጃ ሲያቀርቡ፣
✍️ ወራሾች በውርስ ያገኙትን ይዞታ ወይም ቤት በየግላቸው የባለቤትነት ማስረጃ ለመያዝ ሲፈልጉ ለእያንዳንዳቸው ድርሻ መጠን በፍ/ቤት የፀደቀ ማስረጃ ሲያቀርቡ ወይም የሁሉም ወራሾች የጋራ ስምምነት በውል አፅዳቂ አካል ጸድቆ ሲቀርብ፣
✍️ የእያንዳንዱ ወራሽ የድርሻ መጠን በፍርድ ቤት ያልተረጋገጠ ከሆነ የስም ዝውውሩ በሁሉም ወራሾች ስም በጋራ የሚፈፀም ይሆናል፡፡
የፍርድ ቤቱ የውርሱ ውሳኔ የይዞታ ክፍፍልን የሚያስከትል ሆኖ ሲገኝ የሚፈፀመው የወቅቱን አነስተኛ የይዞታ መጠን መስፈርት የሚያሟላ ከሆነ ብቻ ነው፡፡ ይህ ካልሆነም በተነፃፃሪ የመሬት ይዞታ ድርሻ ህግ ወይም በጋራ ሰነድ/ካርታ መሰረት ይስተናገዳል፡፡
ይዞታው በውሉ መሰረት ግንባታ ለመጀመር የተሰጠውን የጊዜ ገደብ ያለፈበት እና ግንባታው ያልተጀመረ ከሆነ በውርስ ሊተላለፍ አይችልም፡፡
👉በሊዝ የተያዘ ይዞታ ለህጋዊ ወራሽ የሚተላለፈውና ዝውውር የሚፈፀመው፡-
✍️ አውራሹ በገባው የሊዝ ውል ግዴታ መሰረት አመታዊውን የሊዝ ክፍያ የፈፀመና ሌሎች የሊዝ ግዴታችን በተገቢው መንገድ የተወጣ ሲሆን፣
✍️ ወራሽ አውራሽ የገባቸውን የውል ስምምነቶች(የሊዝ መብት፣ክልከላና ኃላፊነት) ሙሉ በሙሉ የተቀበለ መሆኑን በፊርማው ሲያረጋግጥና ውዝፍ ክፍያ ካለ ከፍሎ ደረሰኝ ሲያቀርብ ይሆናል፡፡
✍️ በሊዝ ውሉ መሰረት አውራሹ በህይወት እያለ ለግንበታ መጀመሪያ የተሰጠው የጊዜ ገደብ ካለፈና ግንባታ ካልጀመረ ውሉ ተቋርጦ ቦታው ለከተማ መሪ ማዘጋጃ ቤት ተመላሽ ይሆናል፡፡
አውራሽ በይዞታው ላይ ግንባታ ያልጀመረው ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት መሆኑ ከተረጋጠ አውራሽ በህይወት ቢኖር ኖሮ በመመሪያው መሰረት ሊፈቀድለት የሚችለው የግንባታ መጀመሪያ የማራዘሚያ ጊዜ ለወራሽ ሊፈቀድለት ይችላል፡፡
መ/ በባንክ ሃራጅ የሚሸጥ እና የሚወረስ ቤት የባለቤትነት ስም ዝውውር
✍️ በባንክ የተሸጠ ቤት የባለቤትነት ስም ዝውውር ለመፈፀም በሐራጅ ጨረታው አሸናፊ የሆነው ሰው ያሸነፈበትን ዋጋና ለዝውውሩ በውል የገባቸው ግዴታዎች ተገልፀው ከባንኩ የተፃፈ ህጋዊ ደብዳቤና ውል ሲቀርብ፣
✍️በባንክ ዋስትና ተይዞ የነበረው ይዞታ የባለቤትነት ማረጃ/ካርታ በማህደሩ ውስጥ ካለው ሰነድ ጋር ተገናዝቦ ትክክለኛነቱ ሲረጋገጥ፣
✍️ይዞታው በሌላ ባንክ ብድርና ዋስትና ያልተያዘ ወይም እገዳ የሌለበት መሆኑ ሲረጋገጥ፣
✍️ በሁለተኛና ሶስተኛ ደረጃ ዋስትና የተመዘገበ ዋስትና ያለው ባንክ መኖሩ ከተረጋገጠ ባንኩ ስለ ይዞታው መሸጥ ሲፈቅድ፣
✍️ በባንክ ሃራጅ ሽያጭ እንዲዞር የተጠየቀው ቤትና ይዞታ የተሟላ ሰነድ የሌለው/ሰነድ አልባ ከሆነ በቅድሚያ በሥራ ላይ ባለው የሰነድ አልባ መመሪያ መሰረት ሰነድ ተሰጥቶት ሲቀርብ፣
✍️ ባንኩ ንብረቱን ባለበት ሁኔታ የሚረከብ ከሆነ የቤቱና ይዞታው ግምት እንደማንኛውም ቋሚ ንብረት ግምት ተሰልቶ ተገቢውን የአገልግሎትና የገቢ ክፍያ ሲፈጸም፣
✍️ ቤቱና ይዞታው ባንኩ በሚያወጣው ጨረታ የሚሸጥ ከሆነ ባንኩ ያቀረበው የጨረታ መነሻ ዋጋ በከተማው በኩል ተገቢ መሆኑ ተረጋግጦ በጨረታ ሲሸጥ እና የስም ማዛወሪያ ክፍያዎችን ስለመፈጸሙ የክፍያ ደረሰኝ ማስረጃ ሲያቀርብ የሥመ-ንብረት ዝውውሩ የሚፈጸም ይሆናል::

https://t.me/mesfeect
1. ሕይወት ሁልጊዜም ፍትሐዊ አይደለችም፡፡ ጥሩ ያልሆኑ ሁኔታዎች ይከሰታሉ፡፡ በዚህ ውስጥ መቆየትህ ደግሞ አንተን የበለጠ ሊጎዳህ ይችላል፡፡ ስህተት ከሠራህ፣ ውድቀት ካጋጠመህ ሁልጊዜም ለአንተ እንደገና እድል እንዳለና መጨረሻህም እንዳይደለ እወቅ፡፡

2. እያንዳንዱ ሰው ችግሮች ይኖሩበታል፡፡ ግን ያ ሰው ችግሮቹን ለመወጣት ፈጣን እርምጃ ከመውሰድ ይልቅ ያለማቋረጥ በሕይወቱ ውስጥ በተፈጠሩት ስህተቶች ላይ ቢያተኩር ችግሮቹን ከማወሳሰብ ውጪ መፍትሄ አይኖርም። አንተ ግን ችግሩ ላይ ሳይሆን መፍትሔ ላይ አተኩር።

3. እያንዳንዱ ሰው ስህተት መሥራቱ ዓለም አቀፋዊ ሐቅ ነው፤ ማንም ፍፁም አይደለምና፡፡ ስለዚህ ስህተትህን ሊያስተካክል እና ከውድቀትህ ሊያነሣህ የሚችል የሆነ ነገር ካለ ግፋበት፡፡ እናም አስፈላጊ የሆነውን አድርግ፡፡ ሊተገበር የማይቻል ነገር
ቢሆን ግን እርሳው፡፡ በአዲስ ሁኔታም ጀምር፡፡ ከሆነ ብቻ ብለህ አታስብ፡፡ ይህ የተስፋ መቁረጥ ስሜት እርግጠኛው መንገድ ነውና፡፡ አሁን ልታደርግ ስለሚገባህ ነገር በርትተህ አስብ፡፡

4. ራስህን መቀበልና የተቀበልከውንም ማንነት ማፍቀርን ተማር፡፡ ሕይወት በመንገድህ በምታመጣቸው በእያንዳንዱ ልምድ ውስጥ ራስህን የተሻለ ለማድረግ መጣርህን አታቋርጥ፡፡

5. እጅግ የበራ የወደፊት ዘመን የተመሠረተው የትላንቱን በመርሳት ላይ ነው፡፡ ያለፉ ውድቀቶችህንና የልብ ስብራቶችህን እስካላስወገድካቸው ድረስ በሕይወት ውስጥ ወደፊት መራመድ አይቻልህም፡፡ ስለዚህ በተደናቀፍክበት እንደገና ቶሎ ለመነሳት
አንዲት ቅጽበት እንኳን በጸጸት ሳታባክን ወደፊት ተጓዝ፡፡

6. ለመጣው ሁሉ ጠንካራ፣ ለቀጣዩ ደግሞ ዝግጁ ሁን፡፡
ምክንያቱም እያንዳንዳቸው ከዚህ በኋላ ለሚመጣው እንደ መሪ የተላኩ ናቸው፡፡ ያለ ዕለት ከዕለት ግጥሚያዎቻችንና ፈተናዎቻችን ሕይወት ባዶና አንድ ዓይነት ትሆናለች፡፡ ችግሮች አብዛኛውን ጊዜ ልንማራቸው ግድ የሚሉን እውቀቶች ናቸው፡፡
ስለዚህ ሁሉንም የሕይወት ተሞክሮዎች ደስተኝነት ከሰፈነበት አቀባበልና ከእምነት ጋር ተግባባቸው፡፡

7. በሚያጋጥምህ በእያንዳንዱ ችግር ውስጥ የተደበቁትን ስጦታዎች በማስተዋል ሆነህ መርምር፡፡ ሰው መሆንእንደ እንግዳ ቤት ነው፡፡ እያንዳንዱ ማለዳ አዲስ አዳራሽ ነው፡፡ ደስታ፣ ሐዘን እና ጊዜያዊ ግንዛቤዎች እንዳልተጠበቀ ጎብኚ ሆነው ይመጣሉ፡፡ ሁሉንም በጸጋ ተቀበላቸውና ተደሰትባቸው፡፡

8. ከተሳሳትክ አርም፣ ከወደቅክ ተነሣ እንጂ ፈጽሞ
አታጉረምርም፡፡ ከተስፋ መቁረጥ ክፉ ጠላት ጠንቀቅ፡፡ ከሐቁ አትሽሽ፣ ጥፋተኛ ስትሆነ ጥፋተኝነትህን ተቀበል፡፡ ነገሮች ሲበላሹም ስህተት መቀነስ ላይ አተኩር፣ ከጥፋትህ ተምረህ ወደ ቀጣዩ ተግባር ተሻገር፣ ምክንያቱም የሕይወት ግብ ወደ ፊት መገስገስ እንጂ ክስና ሰበብ አልያም ጸጸት ላይ መቆዘም አይደለም፡፡ ያለፉ ስህተቶችህንና ውድቀቶችህን እዚያው ተዋቸው፡፡

9. አንድ ሕፃን ለመራመድ ሲፍጨረጨር ብናስተውል ማብቂያ የሌላቸውን ውድቀቶች እናያለን፡፡ ስኬቶቹ ግን በጣም ጥቂት ናቸው፡፡ ነገር ግን በተደጋጋሚ ውድቀቶቹ እንዳሉ ሆነው የማይቻል የሚመስለውን ነገር ማድረግ የቻለው ሕጻን በኃይለኛ ደስታ ውስጥ ይዋጣል፡፡ በጊዜው አቋሙን ስለ መጠበቁ እንጂ ስለ ወደቀባቸው ጊዜያት ያን ያህል ሳይጨነቅ ከደስታ ወደ ደስታ ይሸጋገራል፡፡ አንተም አታማር፣ ጊዜም አታጥፋ፡፡ ተስፋ
በማድረግና ጠንክረህ በመሥራት ሕይወትህን በደስታ ሞልተሃት ኑር፡፡ እርግጥ ነው አስቸጋሪ ይሆንብናል፡፡ ነገር ግን ሁልጊዜም ቢሆን ሕይወትህን ስኬታማ የምታደርግበት፣ ራስህን በውብ ልጅነት የምትቀርጽበትና በውስጣዊ ሕይወትህ ያለህን ብልጽግና የምትጨምርበት መንገድ አለ፡፡ ስለዚህ ሙሉ ዓለም ቢታሰብ ለአንተ የተሻለ ቦታና ሁኔታ ሊኖር እንደማይችል ማሰብህን አቁም፡፡

10. ስኬት የምታመራው ፈጽሞ ተስፋ ወደ ማይቆርጡ ሰዎች ነው፡፡ ምንም እንኳን ያልተሳኩ ነገሮችን፣ የውደቀት መጠናችንና የስህተታችን ብዛት ቢያይልም ተስፋ አትቁረጥ።

https://t.me/mesfeect
👍3
አንዳንዴ እምንት የሚመስሉ ነገሮች ጥንቃቄ ካልወሰደን ብዙ ዋጋ ያስከፍላሉ፡፡ ትንሽ ነገሮች ትልቅ ዋጋ መኖሩን ማወቅ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ትልቁን በር ለመክፈት፣ በሩን የሚያክል መክፈቻ ቁልፍ ሳይሆን በጣም ትንሽ መክፈቻ ቁልፍ ያስፈልጋ፡፡ ያ ትንሽ ቁልፏ ከጠፋች በሩን ሰብረን ብዙ ዋጋ እንከፍላለን፡፡
ለጥቃቅን ነገሮች የምንሰጠውን ትኩረት መቼም ቢሆን ቸል አንበል። የመጀመሪያው የአሜሪካ የቬኑስ ሮኬት (Venus rocket) የጠፋው በኮምፒውተር ስህተት ምክንያት ነበር፤ ይህም በነጥብ ፋንታ ኮማ በመጠቀሙ ነው! ፕሮግራሙ የተጻፈው DO31=1.3 ተብሎ ነበር፣ መሆን የነበረበት ግን DO31=1,3 ነበር።
በዚህም ምክንያት ሮኬቱ በከፍተኛ ፍጥነት ሰው ወደሚኖርበት አካባቢ አቅጣጫውን ስለቀየረ፣ በአየር ላይ እያለ እንዲጋይ ተደርጓል።
ለማነኛውም ለእምንት ነገሮች ትኩረት ሰጥተን በጥንቃቄ እንሥራ!
5👏1
ቢራቢሮዎች ለመያዝ እያባረርክ ጊዜ አታጥፋ፤ ይልቁንም ይሽሹሃል፡፡ በቀላሉ ለመያዝ ከፈለግህ ምርጥ አበባ እየተከልክ ጊዜህን ቢታጠፋ ቢራቢሮዎች ብቻቸውን ካሉበት ወደ አበባው ይመጣሉ፡፡

በጥበብ እንኖር!

#ሻሎም!
👍4
Live stream started
Live stream finished (33 seconds)
የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ!
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን፤ ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ፤ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።" ኢሳያስ 53፣6
2👍2
ከሰው ጋር እያወራን መዘንጋት የሌለብን 15 ጥበቦች
1.  ዳኛ በየሌለበት አትከራከር፡፡
2.  አስታራቂ ከሌለ አትጣላ፡፡
3.  ለመማር ዝግጁ ያልሆኑትን ለማስተማር አትልፋ፡፡
4.  ሁሌ "አውቃለሁ" የምለውን ለመምከር አትሞክር፡፡
5.  አንተን እንደ ዕቃ ከሚጠቀመው ጓደኛህ ቶሎ መሸሽ አለብህ፡፡
6.  አንተ መፍት ለማትሰጠው ችግር ከንፈር አትምጠጥ፡፡
7.  ከማነኛው ሰው ጋር ግንኙነት ማለፍ የሌለባቸው ቀይ መስመሮችን ማወቅ አለብህ፡፡
8.  ከሰው መቀበል ከፈለግህ መስጠት አለብህ፡፡
9.  ግንኙነት ጊዜ ብዙ ከማውራት ብዙ መስማት አለብህ፡፡
10.  መልስ ከመስጠትህ ንግግር መጨረሱን አረጋግጥ
11.  ከወዳጅህ ጋር ባለው ግንኙነት በተቻለ መጠን የፊትህ ፈገግታህን አትነፍግ፡፡
12.  ተግባቦት ጊዜ የወዳጅህን ፊት እያየህ መሆን አለብህ፡፡
13.  ወዳጅህ እያወራ እያለህ ሌላ ተግባራትን አታደርግ፡፡
14.  በተግባቦት ውስጥ የግል ምስጢርህ ለይተ መናገርህን እንዳትረሳ፡፡
15.  ያልገባህን ነገር ማብራሪያ ጠይቅ፡፡
https://t.me/mesfeect
7
😢1
MESFIN MAGO TULAMO
Photo
አቶ ማጎ ቱላሞ ፃራ ከአባታቸው ከአቶ ቱላሞ ፃራ እና ከእናታቸው ከወይዘሮ ቦሮዴ ቦሼ በጋሞ ጎፋ ክፍለ ሀገር በ1884 ዓ.ም አካባቢ መወለዳቸውን በሕይወት ታሪካቸው ዙሪያ የተሰበሰቡ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ የትውልድ ዘመናቸውን ለማወቅ በተለያዩ ጊዜያት በተደረጉ መጠይቆች እንደሚያስረዱት፤ አቶ ማጎ የጋሞ ዘማቾች ወደ ዓድዋ ሲሄዱ ባያስታውሱም፣ በጦርነቱ ድል አድርገው ሲመለሱ ግን በሚገባ እንደሚያውቁ በተጨባጭ ያስረዳሉ፡፡ ይህም በ1888 ዓ.ም አካባቢ መሆኑን ያመላክታል፡፡ ከዚህም በተጨማሪ የዳግማዊ አፄ ሚኒልክን፣ የእቴጌ ጣይቱን እና የልጅ ኢያሱን የዘመነ መንግሥት አጀማመር በሚገባ እንደሚያስረዱ ከታሪክ ጋር ለማመሳከር ተችሏል፡፡

‎አቶ ማጎ ከቤተሰባቸው በወረሱት ሥልጣን፣ በአፄ ኃይለ ሥላሴ ዘመነ መንግሥት ከጋሞ ዴሬዎች አንዷ የሆነችውን ጉጌ ዴሬን (ግዛትን) በባላባትነት እስከ ደርግ መንግሥት መጀመሪያ ድረስ አገልግለዋል፡፡ በዚህም ምክንያት የ1966 ዓ.ም ለውጥ ሲመጣ የነበራቸው ንብረት ሁሉ ተዘርፎባቸዋል፤ "አዳሪ" እየተባሉ በተደጋጋሚ በመገረፍም ለረጅም ጊዜ በእስር ቤት ቆይተዋል፡፡ በሥልጣን ዘመናቸው ማብቂያ አካባቢ ከሌሎች የጋሞ ዳናዎችና መሪዎች ጋር በመሆን የአርባ ምንጭ ከተማን ለመመሥረት ሕዝቡን እንደመሩ መረጃዎች ያስረዳሉ፡፡

‎አቶ ማጎ ከሕፃን እስከ አዋቂ ጋር ተግባቢ በመሆናቸው አብዛኛውን ዘመናቸውን ሰዎችን በማስታረቅ አሳልፈዋል፡፡ ከቡድን እስከ ግለሰብ፣ ከቤተሰብ እስከ ማኅበረሰብ በማስታረቅ ሕዝብን አገልግለዋል፡፡ ከደርግ እስር ከተፈቱበት ጊዜ ጀምሮ እስከ ሕይወታቸው ፍጻሜ ድረስ በማስታረቅ ተግባር ላይ እንደቆዩ ትውልድ ይመሰክራል፡፡ አቶ ማጎ ጉልበታቸው ከመድከሙ በፊት ፀብና ግጭት ባለበት ቦታ ሁሉ በአካል በመገኘት ያስታርቁ ነበር፡፡ በመጨረሻዎቹ አራት ዓመታት መንቀሳቀስ ባለመቻላቸው ደግሞ የእርቅ ፈላጊዎች ወደ ቤታቸው ይመጡ ነበር፡፡ ቤታቸው "የእርቅ ክሊኒክ"፣ እሳቸው ደግሞ "የፀብና ግጭት ሐኪም" ነበሩ፡፡ ከማስታረቅ ጥበባቸው የተነሳ ለብዙ ጋሞ ዴሬዎች "ኦጋዴ" ነበሩ፡፡ "ኦጋዴ" ማለት የጋሞ ዴሬዎች (ግዛቶች) እርስ በርስ እንዳይጋጩ ቅድመ መከላከል የሚሠራ እና ግጭቶች ሲከሰቱም በባህላዊ የእርቅ ሥርዓት የሚያስታርቅ ሰው ማለት ነው፡፡ አቶ ማጎ ለራሳቸው ከመኖር ይልቅ ለሕዝብ ሰላም ዕድሜ ዘመናቸውን የሰጡ፣ የቀደሙ አባቶችን አደራ ተቀብለው የተወጡ የሰላምና የእርቅ አምባሳደር ነበሩ፡፡

‎አቶ ማጎ ቱላሞ ባለትዳር እና የስድስት ወንድና የሦስት ሴት ልጆች አባት ነበሩ፡፡ ምንም እንኳ አንዱ ወንድ ልጃቸው ቢሞትም፣ በአሁኑ ወቅት ስምንት (8) ልጆች፣ አርባ ሦስት (43) የልጅ ልጆች እና ሃያ አንድ (21) ቅድመ-ልጅ ልጆች(Great grang-son)፣ በአጠቃላይ ሰባ ሁለት (72) ከዘራቸው የተገኙ ተተኪዎች በሕይወት ይገኛሉ፡፡

‎አቶ ማጎ እስከ እለተ ሞታቸው የማስታረቅ ሥራቸውን ሲያከናውኑ ቆይተው፣ ባደረባቸው ሕመም በሚያዝያ 16 ቀን 2018 ዓ.ም በ134 ዓመታቸው ከዚህ ዓለም በሞት ተለይተዋል፡፡
👍4👏4