Merkato Media
7.15K subscribers
289 photos
6 videos
1 file
19 links
#merkato_media
#መርካቶ_ሚድያ

በዚህ ቻናል ለኢትዮጵያ ፍቅር ሰላም አንድነት ስለ ፍትህ የምናወራበት ድምፅ ላጡ ድምፅ የምንሆንበት ቻናል ነው።

''We testify about the Truth ''
Download Telegram
🛒ታላቅ ቅናሺ ከሸገር ገበያ📣

✔️m13 Samsung 📱
✔️4ram
✔️64Gb

        ዋጋ 13200

እዚህ ላይ ያግኙን 👇👇
                  @ethio_sellerr

አዲስአበባ ያሉበት እናደርሳለን 🛵🚵
ክፍለሀገር በፖስታ ይደርሷታል።📩📮
የቻይና ከተሞች እየሰመጡ ነው❗️

ከቻይና ዋና ዋና ከተሞች ግማሽ ያህሉ ላይ የመስመጥ አደጋ መጋረጡ ተሰምቷል።  በበሚሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች በተለይ የባህር ከፍታ ሲጨምር ለጎርፍ አደጋ እየተጋለጡ ነው ሲል በአገር አቀፍ ደረጃ የወጣው የሳተላይት መረጃ  አመልክቷል። በሳይንስ ጆርናል የታተመው ይኸው ጥናት 45 በመቶው የቻይና የከተማ መሬት በአመት ከ3 ሚሊ ሜትር በላይ በፍጥነት እየሰመጠ ነው ያለ ሲሆን 16 በመቶው ደግሞ በዓመት ከ10 ሚሊ ሜትር በላይ መስመጡን ገልጿል።  በከተሞቹ የሚገኙ በርካታ ሰማይ ጠቀስ ህንፃዎች  ምክንያት መሆናቸውን ሮይተርስ በዘገባው አመልክቷል።

@merkato_media
@merkato_media
በአሜሪካ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያዊያን (የኦሮሞ እና የትግራይና ማኅበረሰብ) አባላት ጦርነት እንዲቆም የሚጠይቅ ሰልፍ አካሄዱ‼️

ዋሺንግተን ዲሲ አካባቢ የሚኖሩ ትውልደ ኢትዮጵያ የኦሮሞ ማኅበረሰብ አባላት፣ የኦነግ የፖለቲካ ዘርፍ ኃላፊ የነበሩት የአቶ በቴ ዑርጌሳ ግድያን የሚቃወም ሰልፍ እና የሻማ ማብራት ሥነሥርዐት አከናወኑ። ኢትዮጵያ ውስጥ በኦሮሞ ተወላጆች ላይ ይደርሳል ያሉትን ግድያ ተቃውመው ጦርነት እንዲቆም ጠይቀዋል። በሌላ በኩል በዚሁ አካባቢ ሰልፍ ያደረጉት ትውልደ ኢትዮጵያ የትግራይ ተወላጆች፣ ጦርነት እንዲቆም፣ የፕሪቶሪያ የሰላም ስምምነት ሙሉ ለሙሉ እንዲከበር እና ተገቢው ርዳታ ወደ ክልሉ እንዲገባ የሚጠይቅ ሰልፍ አካሂደዋል ሲል የአሜሪካ ድምፅ ዘገባ ያመላክታል።

@merkato_media
#Update

የ " ቲክቶክ " እገዳ በኪርጊስታን ተግባራዊ ሆነ።

ኪርጊስታን " ቲክቶክ " በመላ ሀገሪቱ  እንዲታገድ ውሳኔ ማስለፏ ይታወሳል በዚሁ ውሳኔ መሰረት የቴሌኮም አገልግሎት የሚሰጡ ድርጅቶች ትዕዛዙን ወደ መፈጸም #እርምጃ ገብተዋል።

በሀገሪቱ " ቲክቶክ " መስራት እንዳቆመም ተነግሯል።

ሰዎች መተግበሪያውን ሲከፍቱን የሚያገኙት መልዕክት " Unable to load, please try again." የሚል ነው።

ውሳኔው በሀገሪቱ ብሔራዊ ደህንነት መ/ቤት የተላለፈ ነው።

የኪርጊስታን ዲጂታል ሚኒስቴር ቲክቶክን የሚያስተዳድረው ' ባይት ዳንስ ' ኩባንያ ፥ " #የልጆችን
- አእምሯዊ፣
- አካላዊ፣
- መንፈሳዊ እና #ሥነምግባራዊ እድገትን ለመጠበቅ በህግ የተዘረዘሩ ህጋዊ መስፈርቶችን ማክበር አልቻለም " ብሏል።

በዚህም ምክንያት " ቲክቶክ " በሀገሪቱ እንዳይሰራ ተደርጓል።

ውሳኔው የተቃወሙ አካላት ይህ ተገቢ እንዳልሆነ በመግለጽ ገደቡ እንዲነሳ ጠይቀዋል። ከገደብ ይልቅ ቁጥጥር ይደረግበት ብለዋል።

ከዚህ ቀደም የኪርጊስታን የባህል፣ ወጣቶችና ስፖርት ሚኒስቴር ፥ " ቲክቶክ " የተሰኘው መተግበሪያ ለልጆች አእምሯዊ እድገት እና አጠቃላይ ደህንነት ጠንቅ እየሆነ ነው " ማለቱ ይታወሳል።

መተግበሪያው #ህጻናት እጅግ ጎጂ ሊሆኑ የሚችሉ ይዘቶችን እንዳያገኙ ለመከላከል በቂ #መቆጣጠሪያ እንደሌለው ነበር የገለጸው።

በተጨማሪም ለተጠቃሚዎቹ ትክክለኛ የዕድሜ ማረጋገጫ እርምጃዎች እንደለለው እና ተጠቃሚዎችን በአጫጭር የቪዲዮ ክሊፖች ወደ ምናባዊ ግዛት በመሳብ #ሱስ የሚያስይዝ ይዘት እንዳለው አስረድቶ ነበር።

ሚኒስቴሩ " ቲክቶክ " በወጣቱ ትውልድ ደህንነት ላይ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው በአጠቃላይም ለትውልዱ ጠንቅ እየሆነ እንደመጣ አሳውቆ ነበር።

በሌላ በኩል ፤ አሜሪካ ውስጥ ከመረጃ ደህንነት ጋር በተያያዘ መተግበሪያው እንዲታገድ ከፍተኛ ግፊት እየተደረገ ሲሆን  " ቲክቶክ " ከቻይናው ኩባንያ ካልተፋታ / አሜሪካ የምትቆጣጠረው አይነት ካልሆነ በመላ ሀገሪቱ መታገድ ዕጣ ፋንታ ሊገጥመው ይችላል ተብሏል።

via tikvahethiopia

@merkato_media
Forwarded from Bura - collection
m14 Samsung 📱
✔️6ram
✔️128 GB

📌ዋጋ=16500

@ethio_sellerr   
@Birukepromo
           ላይ  ያናግሩን።
በስልክ ቁጥራችን 0946159797 ይደዉሉልን ።

አዲስአበባ ያሉበት እናደርሳለን 🛵🚵
ክፍለሀገር በፖስታ ይደርሷታል።📩📮

ተጨማሪ እቃዎችን ለመሸመት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/bura_collection
በአዲስ አበባ ከተማ በተገነቡ ማዕከላት ከመደበኛው ገበያ የጤፍ ዋጋ ላይ የ3 ሺ ብር ቅናሽ እንዳለው ተገለፀ

በአዲስ አበባ ከተማ ተገንብተው አምራችን ከሸማቾች የሚያገናኙ ሶስት ማዕከላት ሙሉ በሙሉ ስራ መጀመራቸውን የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ አስታውቋል።

ቢሮው አሁን ላይ በዋነኛነት የገበያ ማዕከላት ላይ ትኩረት አድርጎ እየሰራ እንደሚገኝ ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን የተናገሩት የአዲስ አበባ ንግድ ቢሮ የኮምኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ሰውነት አየለ ከ3.3 ሚሊየን ብር በላይ ወጪ ተደርጎባቸው እንደተገነቡ ተናግረዋል።

ከተማ አስተዳደሩ በእነዚህ ማዕከላት አምራቾችን ሙሉ በሙሉ አስገብቶ ለሸማቾች ከማሳ የተሰበሰቡ ምርቶችን በቅናሽ ዋጋ እያቀረበ ነው ብለዋል።እነዚህ ማዕከላት በሸማቹ እና በአምራቹ መሀል የነበረውን ህገ ወጥ ደላላን መስበር የቻለ ነው።

ከዋጋም አኳያ ከእሁድ ገበያ አንፃር የተሻሉ መሆናቸውን ገልፀዋል።ምርቶች በበቂ ሁኔታ በገበያ ማዕከላት ቢገቡም ህብረተሰቡ ስለ ማዕከላቱ በቂ ግንዛቤ ስሌለው የሚበላሹ  ምርቶች አሉ በተለይ ደግሞ  የአትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶች ብልሽት እንደሚገጥማቸው ተናግረዋል።

ሸማቹ ወደ እነዚህ ማዕከላት በመምጣት ሁሉንም ምርቶች በአንድ እንዲሁም በቅናሽ ዋጋ ማግኘት እንደሚችል ገልፀዋል።ከመደበኛ ገበያዎች የጤፍ ዋጋ በእነዚህ ማዕከላት ውስጥ የ3ሺ ብር ቅናሽ እንዳለው አንስተዋል። እንዲሁም አትክልት እና ፍራፍሬ ምርቶችም ከእሁድ ገበያው ቅናሽ እንዳለውም አቶ ሰውነት አየለ ጨምረው ለብስራት ሬድዮና ቴሌቭዥን ተናግረዋል።

ማዕከላቱ በኮልፌ ፣በአቃቂ እና በለሚ ኩራ ክፍለ ከተሞች ይገኛሉ ተብሏል።

ዳጉ_ጆርናል

@merkato_media
መረጃ‼️
የአለም የባሎች ቀን በአለም ዙሪያ እየተከበረ ይገኛል ።
ሶሻል ሚዲያ ይሺጡ ይግዙ

✔️የቴሌግራም ግሩፕ እና ቻናል
✔️የዩትዩብ ቻናል
✔️የፌስቡክ ፔጅ
✔️የቲክቶክ ገፅ

መግዛት እና መሸጥ የምትፈልጉ አናግሩን ሁሉም እኛ ጋር አለ።
    @ethio_sellerr
@birukpromo ላይ አናግሩን

በስልክ ቁጥራችን 0946159797 ይደዉሉንን::
ኢራን አፋጣኝ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ እቅድ የላትም ሲሉ አንድ የኢራን ባለስልጣን ተናገሩ

አንድ የኢራን ከፍተኛ ባለስልጣን ለሮይተርስ የዜና ወኪል እንደተናገሩት "ኢራን በእስራኤል ላይ አፋጣኝ የበቀል እርምጃ ለመውሰድ እቅድ የላትም" ሲሉ እስራኤል በኢራን ኢስፋሃን ከተማ ላይ ጥቃት መሰንዘሯ ተከትሎ ተናግረዋል፡፡

ሁለት የአሜሪካ ባለስልጣናት ጥቃቱ ከእስራኤል የመጣ መሆኑን ለመገናኛ ብዙሃን ቢናገሩም እስራኤል ኃላፊነቱን ለመዉሰድ ወዲያዉ መግለጫ አላወጣችም ነበር።አንድ ኢራናዊ ተንታኝ ለኢራን መንግስት ቲቪ እንደተናገሩት "በኢስፋሃን በአየር መከላከያ የተተኮሱ ሚኒ ሰው አልባ አውሮፕላኖች ወደ ኢራን ውስጥ ሰርጎ ገቦች ገብተዋል" በማለት እስራኤል ጥቃቱን ፈጽማለች የሚለውን ዘገባ አሳንሰዉ ተናግረዋል፡፡

በሌላ በኩል እስራኤል በኢራን ላይ የበቀል ጥቃት መፈጸሙን ተከትሎ ዩናይትድ ስቴትስ በእስራኤል ለሚገኙ የኤምባሲ ሰራተኞቿ እና ቤተሰቦቻቸው “ከከፍተኛ ጥንቃቄ የተነሳ” የጉዞ ገድብ ጥላለች።ኤምባሲው ሰራተኞቹ ከታላቋ ቴል አቪቭ ክልል ውጭ  ወደ ሄርዝሊያ ፣ ኔታንያ እና ዩሁዳን ጨምሮ ወደ እየሩሳሌም እና ቢየር ሼቫ አካባቢዎች እንዳይጓዙ አስጠንቅቋል፡፡
"እስራኤል በወታደሮቿ ላይ የሚጣልን ማዕቀብ ትታገላለች" - ኒታንያሁ

አሜሪካ በእስራኤል ወታደሮች ላይ ማዕቀብ ለመጣል እያቀደች መሆኗ ዘግቦ ነበር።

እንደ South China Morning Post ዘገባ አሜሪካ እጥለዋለሁ ያለችው ማዕቀብ በዌስት ባንክ የሰፈሩ የጦር አባላት ላይ ነው።

"የተፈፀመ የሰብዓዊ መብት ጥሰት የለም" ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትር ኒታንያሁ በበኩላቸው፣"በእስራኤል የጦር አባላት ላይ የሚጣልን የትኛውንም ማዕቀብ እታገላለሁ" ብለዋል።

@merkato_media
@merkato_media
የትምህርት ሚኒስቴር ዛሬ እንዳስታወቀው፤ "በኢትዮጵያ በተፈጥሮና ሰው ሰራሽ ችግሮች ምክንያት ከ5 ሚሊዮን በላይ ተማሪዎች ከትምህርት ገበታቸው ውጪ ናቸው።"
ሰውዬው ተገኝተዋል

ኦሮሚያ ክልል ሸገር ከተማ ለገጣፎ አቅራቢያ 44 ማዞሪያ ጅዳ ኩራ በተባለ ፖሊስ ጣቢያ መታሰራቸው ታውቋል።

እኝህ ሰው በተደበደቡ፣በተበደሉ፣ጥቃት በደረሰባቸው እንደት ሊታሰሩ ቻሉ ለሚለው ምላሽ አልተገኘም።

በወቅቱ እሳቸውን ከፍ ዝቅ እያደረኩ ርካሽ የዘረኝነት ተግባር ሲፈፅሙባቸው የነበሩ ወጣቶች ተሰብስበው መታሰራቸውም ተሰምቷል።(wasu)

@merkato_media
ስለ ጊዜ.....

ኒዉዬርክ ከካሊፎርኒያ በ 3 ሰዓት ትቀድማለች ነገር ግን ይህ ካሊፎርኒያን ቀርፋፋ አያደርጋትም ምክንያቱም የራሷ ጊዜ አላትና ፡፡

አንዳንድ ሰዉ በ22 አመቱ ይመረቃል ነገር ግን ጥሩ ስራ ለመያዝ 5 አመት ይፈጅበታል፡፡

አንዳንዱ በ25 አመቱ የድርጅት ሃላፊ ሆኖ በ5ዐ አመቱ ሲሞት ሌላዉ በ50 ዓመቱ ሃላፊ ሆኖ እስከ 9ዐ ዓመት ይኖራል፡፡

ኦባማ በ55 ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን ጨረሰ ነገር ግን ትራምፕ በ7ዐ ዓመቱ ኘሬዝዳንትነቱን ጀመረ! ይሄ ትራምፕን ኀላ ቀር አያደርገዉም፡፡

ጊዜ በሕይወታችን ወሳኝ ነገር ነዉ ፡፡ ፈጣሪ በጊዜዉ ሁሉን ነገር ዉብ ያደርጋል

ስለዚህ.... ከሁሉ በኋላ የቀረን ወይም ወደፊት የቀደምን አይምሰለን ሁሉም ሰዉ የራሱ የሆነ የኑሮ ሩጫና የተፈጠረበት አላማ አለዉ! ሁላችንም የራሳችን የሆነ የጊዜ ክልል አለን!

Dr. Mihret Debebe
አዲስ አበባ፤ ተኝተዉ በነበሩ ሰዎች ላይ ቤት ተደርምሶ ሰባት ሰዎች ሞቱ

ዛሬ ለሊት ሊነጋ ሲል 11 ሰኣት አከባቢ በአዲስ አበባ ከተማ አዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ወረዳ 12 በተለምዶ ጠሮ መስጊድ በሚባል አከባቢ በደረሰ የቤት መፍረስ አደጋ የሰባት ሰዎች ህይወት አለፈ፡፡

ለአደጋው መንስኤ የሆነው በጎረቤት የተከማቸው ለቤት ግንባታ የሚውል ከፍተኛ መጠን ያለው አፈርና ድንጋይ ከመሬት እየወጣ ካለው ግንባታ ጋር ተደርምሶ መኖሪያ ቤቶች ላይ በማረፉ በጠዋት ተኙ የነበሩ ሰባት ሰዎች አንዳቸውም በህይወት መውጣት ሳይችሉ በዚያው አልቀዋል፡፡
አፈርና በግንባታ ላይ ያለው ድንጋይ ተደርምሶባቸው ያለቁት የአንድ ቤተሰብ አባላት እና ጎረቤታቸው ነው ተብሏል፡፡ እድሜያቸው ከ11፤ 12፣ 25 እና 28 የሆኑ አራት ሴቶች እንዲሁም እድሜያቸው የ4፣ የ12 እና የ30 ዓመት እድሜ ያላቸው ሶስት ወንዶች ባጠቃላይም ሰባት ሰዎች በተኙበት ቤትን የደረመሰባቸው የአፈር እና የድንጋይ ክምር አንዳቸውም በህይወት እንዳይወጡ አድርጓል፡፡

የአደጋውን ዝርዝር ጉዳይ ፖሊስ እያጣራ መሆኑን ያስረዱት የአዲስ አበባ አደጋ ስጋት አመራር ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ንጋቱ ማሞ ኮሚሽናቸው ያደረገው የህይወት አድን ሙከሪያ ከቦታው አመቺ አለመሆን ጋር ተያይዞ ሳይሳካ መቅረቱን አስረድተዋል፡፡ ቦታው ላይ ደርሶ አደጋውን የተመለከተው የአዲስ አበባው ዘጋቢችን ከላይ ወደ ታች የተደረመሰው የአፈር ክምችትና ግንብ ስር የወጡ የሰው አስከሬን የመቅበር እና ቤት ላይ የተደረመሰውን አፈርና ድንጋይ የማንሳት ስራ በአከባቢው ህብረተሰብ ስከወን ነበር ብሏል፡፡

በቦታው ላይ ከነበሩ የሟቾች ጎረቤት መካከል አቶ አሊ አማን የተባሉ የአይን እማኝ ጎረቤት በሌሊቱ ተነስተው የደረሱት የድንጋይ መደርመስ ከፍተኛ ድምጽ በመስማት ነው ብለዋል፡፡
በልዩ ቅናሽ ኦርጅናል ስልኮች ይሸምቱ

Brand #Samsung

A15- 4 ram 128 GB - 16,500

A05 -4 ram 64 GB - 11,500

A34- 6ram 128 GB - 28,000

A54- 8ram 256GB - 38,000

S24 Ultra -12 ram - 512 GB -126,000

ይደውሉልን 👉 0913366506

Telegram @Birukepromo

ተጨማሪ እቃዎችን ለመሸመት የቴሌግራም ገፃችንን ይቀላቀሉ👇👇
https://t.me/bura_collection
ኢትዮጵያ ፤ የአፍሪካ ዋንጫ ለማዘጋጀት እቅድ እንዳላትና ለእርሱም እየሰራች ነዉ ተባለ

ኢትዮጵያ በሚቀጥሉት አመታት የአፍሪካ ዋንጫ ውድድርን እንድታዘጋጅ ለማድረግ እየተሰራ እንደሚገኝ የባህልና ስፖርት ሚኒስትር አቶ ቀጄላ መርዳሳ መናገራቸውን ዳጉ ጆርናል ታዝቧል።

የአፍሪካ ዋንጫን እ.ኤ.አ በ 2029 ወይም በ2031 ለማዘጋጀት እየሰራን ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለእቅዱ መሳካትም ቢያንስ ስድስት ደረጃቸውን የጠበቁ ስታዲየሞች አስፈላጊ መሆናቸውን ጠቁመዋል።

ካፍ ከዚህ በፊት ያልነበሩ አዳዲስ መስፈርቶችን በማስቀመጡ ኢትዮጵያ አንድም ደረጃውን የጠበቀ ስታዲየም እንዳይኖራት አድርጓል ሲሉም አቶ ቀጀላ መርዳሳ አስረድተዋል። ኢትዮጵያ የካፍን ደረጃ የሚመጥኑ ስታዲየሞች የሌላት በመሆኑ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ረዘም ላሉ ጊዜያት ከሀገሩ ዉጪ ለመጫወት ተገድዶ የነበረ መሆኑ ይታወቃል።

የዉድድሩ አዘጋጅ ሀገራት ቢያንስ ስድስት ስታዲየሞችን እንዲያዘጋጁ ካፍ ቢያዝም ኢትዮጵያ በዚህ ረገድ ምን ያህል ዝግጁ ናት የሚለዉ ግን አጠያያቂ ነዉ።

Via ዋልታ
ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለሆሳዕና በዓል በሰላም አደረሳችሁ፡፡

@merkato_media
እግር ኳስ በኢትዮጵያ ተዓምራቱ እንደቀጠለ ነው።

ይህ ክስተት ጎል አግብተው ደስታቸውን እየገለፁ ይመስላል ግን አይደለም ዳኛውን ከበው እያናገሩት ነው። አንዱ ተጨዋች ለማናገር ሜዳው ሁላ አልበቃውም ተጨዋች ላይ ወጥቶ ነው የሚያናግረው።
የ2016 ዓ.ም የሪሚዲያል ፈተና መቼ ይሰጣል ?

እንደ ትምህርት ሚኒስቴር መረጃ ፤ የ2016 ዓ/ም የሪሚዲያል ተማሪዎች ፈተና በሰኔ ወር መጀመሪያ ይሰጣል።

ፈተናው ለ15 ቀናት በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት እየተሠራ ነው።

70 በመቶ የሚዘጋጀው ፈተና በኦንላይንና በወረቀት ወይም በጥብቅ ቁጥጥር በወረቀት ይሰጣል ተብሏል።

ባለፈው ዓመት የተፈጠረውን ችግር ለመቅረፍ የሪሚዲያል ፈተናውን በሁሉም የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ብቻ ለመስጠት ታቅዶ እየተሰራበት ነው።

ዘንድሮ 32,500 ተማሪዎች 50 በመቶ በላይ ውጤት በማምጣት በቀጥታ ዩኒቨርሲቲ ገብተው መደበኛ ትምህርት እየተከታተሉ ሲሆን ከ78 ሺህ በላይ ተማሪዎች ደግሞ በመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ሪሚዲያል ትምህርት እየወሰዱ እንደሚገኙ ሚኒስቴሩ ለኢፕድ ከሰጠው መረጃ ተመልክተናል።

በሌላ በኩል ፤ በተለያዩ ዩኒቨርሲቲዎች የተመደቡ የሬሜዲያ ተማሪዎች ከታህሳስ ወር ጀምሮ ትምህርታቸውን እየተከታተሉ የሚገኙ ቢሆንም በባህርዳር ዩኒቨርሲቲ የሪሚዲያል ትምህርታቸውን እንዲከታተሉ የተመደቡ ተማሪዎች እስካሁን ጥሪ አልተደረገላቸውም።

@merkato_media
@merkato_media
ጌታቸው ረዳ‼️

"በየጊዜው ወጣቶች የምገብርበት የጦርነት ምዕራፍ መዘጋት አለበት " - አቶ ጌታቸው ረዳ

የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዜዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ በክልሉ ኮሚኒኬሽን ቢሮ በኩል ዛሬ መልዕክት አሰራጭተው ነበር።

በዚህም ፤ " የህዝባችን ሁለንተናዊ መብትና ጥቅም ከማረጋገጥና አስተማማኝ ከማድረግ የሚቀድም ሌላ አጀንዳ የለንም " ብለዋል።

" የህዝባችን ጥቅምና መብት የሚያረጋግጥ መንገድ ሁሉ እንጓዘዋለን " ያሉት አቶ ጌታቸው " ጉዞው እንዲሳካ የህዝቡ ተሳትፎ ወሳኝ ነው " ሲሉ አክለዋል።

ፕሬዜዳንቱ ፤ " ከሚገባው በላይ ያበረከተ ህዝብ በቅንነትና ታማኝነት ማገለገል ይገባል " ሲሉም ገልጸዋል።

" ህዝቡ ከጦርነትና ጦርነት ወለድ ችግሮች በማላቀቅ ወደ አስተማማኝ ሰላም እንዲሸጋገር መስራት ይገባል " ሲሉም አስገንዝበዋል።

አቶ ጌታቸው ረዳ  ፤ " በየጊዜው ትኩስ ሃይል የሆኑትን ወጣቶች የምንገብርበት የጦርነት ምዕራፍ ተዘግቶ ፤ የልማትና የእድገት ፍላጎታችን እንዲሳካ መስራት አለብን " ብለዋል። (Tikvah)