የሰላም ስምምነቱ ትክክለኛ ሰነድ በመንግሥት እና በህወሓት የተፈረመውና ከዚህ በላይ የቀረበው ነው
በደቡብ አፍሪካ ጥቅምት 23 ቀን 2015 ዓ.ም የተፈረመው የሰላም ስምምነት ኢትዮጵያ ባለፉት ሁለት ዓመታት የገባችበትን ጦርነት በማስቆም ዘላቂ ሰላምን ለማረጋገጥ አዲስ ምዕራፍ የሚከፍት ነው።
በዚህም፥
• ህወሓት ትጥቅ እንዲፈታ፣
• የኢትዮጵያን ሉዓላዊነት እና የግዛት አንድነት እንዲጠበቅ፣
• ኢትዮጵያ አንድ ብሔራዊ የመከላከያ ኃይል ብቻ እንደሚኖራት፣
• ግጭትን በዘላቂነት ለማስወገድ፣
• የጥላቻ ፕሮፓጋንዳን ለማቆም፣
• በትግራይ ክልል መሰረታዊ አገልግሎትን ወደ ነበረበት ለመመለስ ከስምምነት ተደርሷል።
ሁሉንም አንቀጾች ያካተተው የሰላም ስምምነቱ ትክክለኛ ሰነድ በመንግሥት እና በህወሓት ተወካዮች የተፈረመውና ከዚህ በላይ የቀረበው ነው። አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን ብዙ የቡድን እልህ አስጨራሽ ክርክሮች ተደርጎ የተፈረመበት ያሉትን ትክክለኛውና ዝርዝር ስምምነቱን የያዘውን ወረቀት አሰራጭተዋል።

የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኢታማዦር ሹም ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ በጥቂት ቀናት ወስጥ ከህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ የኢትዮጵያ ሀገር መከላከያ ሰራዊት አሳውቋል።
የሀገር መከላከያ ሰራዊት ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ " መንግስት ከህወሓት ጋር ያደረገውን የሠላም ስምምነት ተከትሎ የሁለት ወራት የግንባር ቆይታቸውን አጠናቀው ወደ ጠቅላይ መምሪያ ቢሯቸው ተመልሰዋል " ብሏል።
ከውጊያ ኮማንድ ፖስት ወደ መደበኛ ማዘዣ ቢሮአቸው ከተመለሱ በኋላ በመንግስት እና በህወሓት በተደረገው የሰላም ስምምነት መሠረት በጥቂት ቀናት ወስጥ ከህወሓት ወታደራዊ አመራሮች ጋር ውይይት እንደሚያደርጉ ይጠበቃል ሲል ገልጿል።
ዛሬ ጥዋት ላይ የጠቅላይ ሚኒስትሩ የብሄራዊ ደህንነት አማካሪና በፕሪቶሪያው የሰላም ስምምነት የኢትዮጵያን መንግስት ወክለው በሰላም ስምምነት ሰነዱ ላይ የፈረሙት አምባሳደር ሬድዋን ሁሴን የተደረሰው ስምምነትን ተከትሎ የመንግስት እና የህወሓት ወታደራዊ አመራሮች የስልክ ልውውጥ ማድረጋቸውንና በጎረቤት ሀገር ኬንያ ፣ ናይሮቢ ውስጥ እንደሚገናኙ ማሳወቃቸው አይዘነጋም።

#Update
የኢትዮጵያ እና የህወሓት ወታደራዊ አዛዦች ኬንያ፣ ናይሮቢ ላይ ተገናኝተዋል።
ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ ጁላ እና ጀነራል ታደስ ወረዳ ናቸው እየተነጋገሩ ይገኛሉ።
በሰላም ስምምነቱ በ5 ቀናት ወታደራዊ አመራሮች እንዲገናኙ በሚያዘው መሠረት ነው የአዛዦቹ ውይይት የተጀመረው።
ይህ በተመለከተ አፍሪካ ህብረት ባወጣው መግለጫ ፦ ሁለቱ የጦር አመራሮች በደቡብ አፍሪካ በተደረሰው የሰላም ስምምነት መሰረት ነው ምክክር የጀመሩት።
ዛሬ የጀመረው ውይይት በትግራይ አስችኳይ የሰብአዊ ድጋፍ መስመር ተከፍቶ የተቋርጡ አገልግሎቶች እንዲጀምሩ ምክክር ይደረግብታል።
በአፍሪካ ህብረት መሪነት እየተካሄደ ያለው ንግግር ለቀጣይ ቀናትም ይቀጥላል ተብሏል።
በደቡብ አፍሪካ በፌደራል መንግስት እና በህወሓት መካከል በተደረሰው የሰላም ስምምነት ህወሓት ታጣቂዎቹ ትጥቅ እንዲፈቱ መስማማቱ ይታወሳል።

ከተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የአየር ንብረት ለውጥ ጉባኤ ጎን ለጎን ከወንድም የአፍሪካ ሀገራት መሪዎች ጋር በሁለትዮሽ እና ቀጣናዊ ጉዳዮች ላይ ተወያይተናል። ለአፍሪካ ችግሮች አፍሪካዊ መፍትሔዎችን ለመፈለግ እና አህጉራችንን ጽኑ ለማድረግ በአብሮነት መሥራታችንን እንቀጥላለን። ጠ/ሚ አብይ