ETHIO ≈ SCHOOL
2.51K subscribers
5.02K photos
10 videos
225 files
1.97K links
ይህ ለተማሪዎች እና ለትምህርት ፈላጊዎች ተብሎ የተዘጋጀ ፈጣን የሆነ መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ነው።
እንዲሁም በተጨማሪ መረጃወችን በመሰብሰብ በሁሉም የ ት/ት ደረጃ ተማሪን የሚመለከት መረጃ በፍጥነት እናደርሳለን።
ለCross ፦
👇👇👇

👍 @yesshsammmits
👍 @gashtiman1990

Join
👇👇👇
@merejamnch
Download Telegram
በቀዶ ሕክምና የስፔሻሊቲ ትምህርትን በሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የታገዘ ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስቴር ገለፀ፡፡

ይህ የተገለፀው የኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማኅበር 11ኛ ጠቅላላ ጉባኤውን ባካሔደበት ወቅት ነው።

ጤና ሚኒስቴር ለስፔሻሊስት ሐኪሞች በሚሰጠው የቀዶ ሕክምና ትምህርት በAI የታገዙ ኮርሶችን አካቶ ለመተግበር፣ ከትምህርት ሚኒስቴር ጋር እየሠራ መሆኑን የጤና ሚኒስትር ደኤታ ሳህረላ አብደላ ገልፀዋል፡፡

የጤና ስርዓቱ በቴክኖሎጂ የተቃኘ እንዲሆን ሚኒስቴሩ ከአርቴፊሻል ኢንተለጀንስ ኢንስቲትዩት ጋር አብሮ ለመሥራት ከስምምነት መድረሱን ያስታወሱት ሚኒስትር ዴኤታዋ፤ ጤና ሚኒስቴር ካለፈው አንድ ዓመት ወዲህ በሰው ሠራሽ አስተውሎት የታገዙ የጤና አገልግሎቶችን መተግበር መጀመሩን ጠቁመዋል፡፡

የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሕክምና አሰጣጥን ለማሳለጥ፣ አንዳንድ የዲያግኖስቲክ ችግሮችን ለማወቅ የሚፈጀውን ጊዜ ለማሳጠር፣ የላቦራቶሪ ውጤት ትክክለኛነትን ለማሻሻል፣ በሰው ዓይን ሊታዩ የማይችሉ ነገሮች ጎልተው እንዲታዩ ለማድረግና በሌሎችም ሕክምናዎች ላይ ከፍተኛ ዕገዛ እያደረገ እንደሚገኝ የኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ሕክምና ማኅበር ፕሬዝዳንት ዶ/ር ብሩክ ዓለማየሁ አብራርተዋል።

ይሁን እንጂ የሰው ሠራሽ አስተውሎት (AI) የሚሰጣቸው መረጃዎችን የማጥራት እንዲሁም የቁጥጥር ሥራዎች ሊጠናከሩ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ #ሪፖርተር

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
ትምህርት ሚኒስቴር በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና አዲስ ማዕቀፍ አዘጋጅቷል።

ማዕቀፉ መምህራን በክረምት ስልጠና ከዲፕሎማ ወደ መጀመሪያ ዲግሪ የሚሸጋገሩበት መሆኑ ተገልጿል።

ሚኒስቴሩ በቀን 06/11/2018 ዓ.ም ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች በጻፈው ደብዳቤ፣ ከአጠቃላይ ትምህርት ሥርዓተ ትምህርት ለውጥ ጋር ተያይዞ ከ2012 ዓ.ም ጀምሮ በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና ወደ ዩኒቨርሲቲዎች ማስገባት መቋረጡን አስታውሷል፡፡

ይሁን እንጂ በቀጣይ በአዲሱ ሥርዓተ ትምህርት መሰረት በተዘጋጀ የስልጠና ማዕቀፍ፣ በክረምት የመምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና የሚሰጥ መሆኑን ገልጿል።

በ2018 ዓ.ም የክረምት ስልጠናውን ለመስጠት ስምንት አሰልጣኝ ዩኒቨርሲቲዎች መመረጣቸውን ሚኒስቴሩ አሳውቋል።

ለክረምት ስልጠናው የተመረጡ ዩኒቨርሲቲዎች፦

1. ኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ
2. ባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ
3. ሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ
4. መቐለ ዩኒቨርሲቲ
5. ጅማ ዩኒቨርሲቲ
6. ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ
7. ጎንደር ዩኒቨርሲቲ
8. አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ

ተቋማት እና የስልጠናው አሰጣጥ አግባብነት ከትምህርት ሚኒስቴር እስከሚገለጽ ድረስ ከላይ ከተገለፁት ዩኒቨርሲቲዎች በስተቀር በክረምት መምህራን የትምህርት ደረጃ ማሻሻያ ስልጠና መስጠት የማይቻል መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

ከ2011 ዓ.ም በፊት ስልጠና ጀምረው ያላጠናቀቁ መምህራን ከዚህ በፊት በተሰጠው ውሳኔ መሰረት እንዲያጠናቅቁ እንዲደረግ በትምህርት ሚኒስትሩ ብርሃኑ ነጋ ተፈርሞ ለሁሉም ዩኒቨርሲቲዎች የተላከው ደብዳቤ ይገልጻል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#ጥቆማ

ለ2019 የትምህርት ዘመን በዘጠኝ የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች የሚማሩ ተማሪዎች ምዝገባ በቅርብ ቀን ይጀመራል።

ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ለቀጣይ ዓመት የ9ኛ አና 10ኛ ከፍል እንዲሁም የ9ኛ ክፍል ተማሪዎች (አዲስ ሥራ በሚጀምሩት) ምዝገባ ያደርጋሉ።

በ2018 ዓ.ም ትምህርት መስጠት የጀመሩ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች፦

1. ወሊሶ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
2. ቡኢ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
3. ቦንጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
4. ጅግጅጋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
5. ጋምቤላ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት

በ2019 ዓ.ም አዲስ ወደ ሥራ የሚገቡ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች፦

1. አርባ ምንጭ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
2. አሶሳ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
3. ባህርዳር ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት
4. ድሬዳዋ ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤት

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#ጥቆማ

በአዲስ አበባ ከተማ አስተደደር ትምህርት ቢሮ ገላን የወንዶች እና እቴጌ መነን የልጃገረዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች በ6ኛ እና በ8ኛ ክፍል በከተማ አቀፍ ፈተና ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገቡ ተማሪዎችን በማወዳደር ተቀብሎ በማስተማር ላይ ይገኛል፡፡

በ2018 ዓ.ም በአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ውስጥ በአማርኛ እና በአፋን ኦሮሞ ቋንቋዎች 6ኛ እና 8ኛ ክፍል ተምራችሁ ከፍተኛ ውጤት በማምጣት ወደ 7ኛ እና 9ኛ ክፍል የተዘዋወራችሁ ተማሪዎች ለወንድ ተማሪ በገላን የወንዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት እንዲሁም ለሴት ተማሪዎች በእቴጌ መነን የልጃገረዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት በውድድር ለ2019 ዓ.ም ቅበላ ይደረጋል፡፡

ስለሆነም መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች በአዳሪ ትምህርት ቤቶቹ ለመግባት መወዳደር የምትችሉ መሆኑ ተገልጿል፡፡

(ዝርዝር መስፈርቶችን ከላይ ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡)

የምዝገባ ጊዜ
ከሐምሌ 13-17/2018 ዓ.ም

ኦንላይን ይመዝገቡ 👇🏼
● ለገላን ወንዶች አዳሪ መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመልካቾች፦ https://bs.ministry.et
● ለእቴጌ መነን ልጃገረዶች መካከለኛ እና ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት አመልካቾች፦ https://bs.ministry.et

የመግቢያ ፈተና የሚሰጥበት ቀን
● 9ኛ ክፍል ለሚገቡ ተወዳዳሪ ተማሪዎች ሐምሌ 22/2018 ዓ.ም
● 7ኛ ክፍል ለሚገቡ ተወዳዳሪ ተማሪዎች ሐምሌ 23 ቀን 2018 ዓ.ም
● የፈተና ቦታና ሰዓት በቀጣይ ይገለጻል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#ጥቆማ

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ሞዴል የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት (AAU-MCS) በማቋቋም በ2019 ዓ.ም ከ1ኛ-7ኛ ክፍል ለማስተማር ዝግጅቱን በማጠናቀቅ ላይ እንደሚገኝ ገልጿል።

በመሆኑም ልጆቻችሁን በሚከፈተው የማኅበረሰብ ትምህርት ቤት ማስመዝገብ የምትፈልጉ ወላጆች የሚከተሉትን መረጃዎች ልታውቁ ይገባል፦

የምዝገባ ጊዜ
ከሐምሌ 14-21/2018 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ
5 ኪሎ በሚገኘው የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የቴክኖሎጂና ቢዩልት ኢንቫይሮንመንት ኮሌጅ ቢሮ ቁጥር E04

ትምህርት ቤቱ የሚገኝበት ቦታ፦
5 ኪሎ (በቀድሞው የድኅረ ምረቃ/ፋርማሲ ትምህርት ቤት ግቢ)

የመመዝገቢያ ክፍያ ብር 1,000 ሲሆን፤ በቀጣይ ወርሃዊ የክፍያ መጠን ይገለጻል ተብሏል።

የሚያስፈልጉ ሰነዶች
● የተመዝጋቢ ልጆች የልደት ካርድ
● ከቀድሞ ትምህርት ቤት ያጠናቀቁበት ሰርተፊኬት
● ሁለት የወላጅ እና አራት የልጅ ፎቶግራፍ
● ወላጆች ህጋዊ አሳዳጊ መሆናቸውን የሚገልፅ ደብዳቤ
● የክፍያ ደረሰኝ እና የመመዝገቢያ ክላሰር

ትምህርት ቤቱ ቅድሚያ ለዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ልጆች ዕድል የሚሰጥ ቢሆንም፣ ባለው ክፍት ቦታ መሠረት ከዩኒቨርሲቲው ማኅበረሰብ ውጭ ላሉ ተማሪዎች በውድድር ተደራሽ የሚሆን መሆኑ ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#ጥቆማ

አዲስ ሠልጣኞችን ለመቀበል ዝግጅት ማጠናቀቁን የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክ አካዳሚ አሳውቋል።

በኢትዮጵያ ባሕር ትራንስፖርትና ሎጅስቲክስ (ESL) ስር የሚገኘው የባቦጋያ ማሪታይምና ሎጅስቲክስ አካዳሚ፣ አዳዲስ ሠልጣኞችን ተቀብሎ ለማስተማር የሚያስችለውን የትምህርት እና የመሠረተ ልማት ዝግጅት ሙሉ በሙሉ ማጠናቀቁን ገልጿል።

አካዳሚው ዘመናዊ የማስተማሪያ መሠረተ ልማት፣ ዓለም አቀፍ ደረጃን የጠበቁ ካሪኩለሞች እና ብቁ የማስተማር አቅም በማሟላት ለአዲሱ የትምህርት ዘመን ዝግጁ መሆኑን የአካዳሚው ዲን ሲራጅ አብዱላሂ ገልፀዋል።

ሲሙሌተሮች በመጠቀም እና በባቦጋያ ሐይቅ ላይ በሚካሄዱ የተግባር ስልጠናዎች በከፍተኛ የደህንነት እና የጥራት ደረጃ ለማከናወን ምቹ ሁኔታ መፍጠሩንም ጠቁመዋል።

አካዳሚው ከመሠረታዊ የባህር ላይ ደህንነት ስልጠናዎች ጀምሮ እስከ የመርከብ መኮንንነት ፕሮግራሞች በዓለም አቀፉ የባህር ድርጅት (IMO) መስፈርቶች መሰረት የተዘጋጁ ስልጠናዎችን ለመስጠት መዘጋጀቱን አረጋግጠዋል። #ESL

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት በዛሬው ዕለት ይፋ ሆኗል።

በክልሉ በ2018 ዓ.ም የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ 85,531 ተማሪዎች መካከል 83,342 ተማሪዎች ወደ 9ኛ ክፍል የሚያሸጋግራቸውን ውጤት አምጥተዋል፡፡

ዘንድሮ ለፈተና ከተቀመጡ ተማሪዎች 97.4% የሚሆኑት ያለፉ ሲሆን፤ ይህም በክልሉ ባለፉት ዓመታት ከተመዘገበው ከፍተኛው ውጤት መሆኑን የክልሉ የትምህርት ቢሮ ኃላፊ አንተነህ ፈቃዱ ገልፀዋል፡፡

የማለፊያ ነጥብ ለመደበኛ ተፈታኞች 50% እና ከዚያ በላይ ሲሆን፤ ለአካል ጉዳተኞች እና ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተማሪዎች ደግሞ 45% እና ከዚያ በላይ ሆኖ ተቀምጧል።

ፈተናውን ካስፈተኑ 1,538 ትምህርት ቤቶች መካከል 1,017 ትምህርት ቤቶች ሙሉ በሙሉ ተማሪዎቻቸውን ማሳለፋቸውን የገለፁት ኃላፊው፤ ዘንድሮ አንድም ተማሪ ያላሳለፈ ትምህርት ቤት የለም ብለዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
በማዕከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የ2018 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ተለቋል።
 
ተማሪዎች ቀጥሎ ባለው ሊንክ መለያ ቁጥራችሁን እና ስማችሁን በማስገባት ውጤታችሁን ማየት ትችላላችሁ 👇 http://ce.ministry.et
 
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
6ኛው ዙር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል ሀገር አቀፍ ፈተና ዛሬ መሠጠት ጀምሯል።

በዚህ የመጨረሻው ዙር ፈተና፣ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ከዛሬ ሐምሌ 14/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ፈተናቸውን በኦንላይን የሚወስዱ ይሆናል። ምስል፦ ዓዲግራት ዩኒቨርሲቲ

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#ጥቆማ
 
በ2019 የትምህርት ዘመን ወደ ሸገር ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት (SIT) ለመግባት ያመልክቱ!
 
የማመልከቻ ጊዜው የሚያበቃው 👇
ሐምሌ 23/2018 ዓ.ም
 
የትምህርት መስኮች
● Electrical Engineering
● Biotechnology
● Space Science
● Mechanical Engineering
● AI
● Nuclear engineering
 
መስፈርቶች
● የ11ኛ እና 12ኛ ክፍል አማካኝ ውጤት 90%
● የ12ኛ ክፍል ብሔራዊ ፈተና ውጤት 95 ፐርሰንታይል
● ከ500-700 ቃላት የግል መግለጫ መጻፍ ይኖርብዎታል
● የድጋፍ ደብዳቤ ከ2ኛ ደረጃ መምህርዎ/ሜንተርዎ ማጻፍ
● የማኅበረሰብ በጎ አገልግሎት የሰጡት ካለ ቢያይዙ ጥሩ ነው

ያመልክቱ 👉 https://sitedu.info

የማመልከቻ ሒደቱን የሚያስረዳ ቪዲዮ ለመመልከት 👇
https://web.facebook.com/share/v/1Bg5mV7Kur/
 
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#የሥራ_ቅጥር_ዕድል_ጥቆማ

ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ፍላጎት ያላቸውና ብቁ የሆኑ ባለሙያዎችን አወዳድሮ ለሐረማያ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት መቅጠር ይፈልጋል፡፡

➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የስራ መደቦች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 23
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ ከመጀመሪያ እስከ ሦስተኛ ዲግሪ
➤ የሥራ ቦታ፦ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት
➤ ልምድ፦ ዜሮ ዓመት እና 2 ዓመት
➤ የቅጥር ሁኔታ፦ በቋሚነት

አመልካቾች ከሐምሌ 15/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ሰባት (7) የሥራ ቀናት በአካል ማመልከት ትችላላችሁ ተብሏል፡፡ (መስፈርቶችን ከተያያዘው ምስል ይመልከቱ፡፡)

አመልካቾች CV እና ሙሉ የትምህርት ማስረጃችሁን ዋናውና የማይመለስ ኮፒ በመያዝ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት የብቃትና ሰው ሀብት አስተዳደር ክላስተር ቢሮ ቁጥር 1 ወይም አዲስ አበባ ሐረማያ ዩኒቨርሲቲ ወኪል ቢሮ፣ አራት ኪሎ፣ የቀድሞው የጀርመን ባህል ኢንስቲትዩት ህንፃ ቢሮ ቁ. 15 በአካል በመቅረብ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡

ለቃል ፈተና የተመረጡ አመልካቾች የማመልከቻው ጊዜ ባበቃ በጥቂት ቀናት ጥሪ ይደረግላቸዋል ተብሏል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
በሲዳማ ክልል የ2018 ዓ.ም የ6ኛ እና የ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና ውጤት ይፋ አለመደረጉን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አረጋግጧል፡፡

በተለያዩ የማኅበራዊ ሚዲያ ቻናሎች ላይ በክልሉ የተፈታኞች ውጤት ተለቀቀ በሚል እየተሰራጭ ያለው መረጃ ሐሰተኛ መሆኑን ቢሮው ገልጿል፡፡

የተፈታኞቹ ውጤት በቅርቡ በክልሉ ትምህርት ቢሮ በኩል ይፋ እንደሚደረግ የተገለጸ ሲሆን፤ እስከዛ ድረስ ከሐሰተኛ መረጃ እንዲጠበቁና ውጤት ይፋ እስከሚደረግ በትዕግስት እንዲጠብቁ ቢሮው ጠይቋል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#EHPLE

ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በመጀመሪያ ዲግሪ የተመረቃችሁ የጤና ባለሙያዎች በነሐሴ ወር 2018 ዓ.ም በጤና ሚኒስቴር የሚሰጠውን የጤና ሙያ ፈቃድ ፈተና ለመውሰድ ከሰኔ 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ መረጃችሁን በማስተሳሰር ላይ እንደምትገኙ ይታወቃል፡፡

መረጃችሁን ወደ ሲስተም ያላስገባችሁ ነባር እና አዲስ ተመዛኞች ማስተሳሰር የምትችሉት እስከ አርብ ሐምሌ 17/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ መሆኑን ተገንዝባችሁ በ https://hple.moh.gov.et/ ላይ በመግባት የብሔራዊ መታወቂያ መለያ ቁጥር (16 Digit FAN) በማስገባት አስፈላጊ መረጃዎችን በማሟላት ለምዝገባ እንድትዘጋጁ ሚኒስቴሩ አሳስቧል።

🔔 መረጃ የማስተሳሰር ሒደት እንዳለቀ የፈተና ጣቢያ መረጣ ሒደት ይቀጥላል ተብሏል፡፡

በሰኔ 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ተፈትናችሁ ያለፉችሁ ተመዛኞች የስም ዝርዝራችሁን በተማራችሁበት ተቋም አማካኝነት ወደ ሲስተም ማስጫን የሚጠበቅባችሁ መሆኑ ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
በሲዳማ ክልል ከሚገኙ ትምህርት ቤቶች በክረምት መርሐግብር ከዲፕሎማ ወደ ዲግሪ ፕሮግራም ለማሻሻል ስልጠና ለመከታተል ሐምሌ 11/2018 ዓ.ም የመግቢያ ፈተና በበይነ መረብ የተፈተናችሁና 50 ከመቶና ከዚያ በላይ ያመጣችሁ መምህራን የስልጠና ቦታ በሀዋሳ ዩኒቨርርቲ እና በአርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ መሆኑን የክልሉ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል፡፡

በዚህም በታሪክ ትምህርት የተፈትናቸሁና ያለፋችሁ መምህራን ብቻ አርባ ምንጭ ዩኒቨርሲቲ የምትሰለጥኑ ሲሆን፤ ሌሎች ቀሪ ሰልጣኞች በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ የምትሰለጥኑ መሆኑ ተገልጿል፡፡

የመግቢያ ቀን በቀጣይ የሚገለፅ መሆኑን ቢሮው አሳውቋል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#MekelleUniversity

በትግራይ ብሔራዊ ክልል በወረቀት የሚፈተኑትን ተፈታኞች ጨምሮ በመላ ሀገሪቱ የሚሰጠው 4ኛው ዙር የ2018 ዓ.ም የ12ኛ ክፍል የወረቀት ፈተና ከሐምሌ 22-24/2018 ዓ.ም እንደሚሰጥ መገለፁ ይታወቃል።

​መቐለ ዩኒቨርሲቲ በተቋሙ ለተመደቡ ተፈታኞች የፈተናውን መርሐግብር ይፋ አድርጓል።

● ​ሐምሌ 20/2018 ዓ.ም
አቀባበል፣ ምዝገባ እና የመኝታ ክፍል ምደባ
● ሐምሌ 21/2018 ዓ.ም
ስለፈተናው አሰጣጥና ደንቦች አጠቃላይ ገለጻ
● ከ​ሐምሌ 22-24/2018 ዓ.ም
ሀገራዊ ፈተናው የሚሰጥበት ጊዜ

ተፈታኞች ​የግል መታወቂያ እና ሀገራዊ ፈተና መለያ ካርድ፣ ለፈተና የተፈቀዱ የመጻፊያ ቁሳቁሶች እና የግል አልባሳት ይዛችሁ መሔድ ይጠበቅባችኋል።

ተንቀሳቃሽ ስልክ፣ ዲጂታል ሰዓት፣ ጌጣጌጦች እና መሠል የተከለከሉ ነገሮችን ይዞ ወደ ተቋሙ መሔድ አይፈቀድም።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
በኦሮሚያ ክልል የ8ኛ ክፍል ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 86 በመቶ የሚሆኑት የማለፊያ ውጤት ማምጣታቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ገለፀ።

በክልሉ የ8ኛ ክፍል ከተፈተኑ 415 ሺህ ተማሪዎች መካከል 354 ሺህ ተማሪዎች (86 በመቶ) 50 እና ከዚያ በላይ ውጤት በማምጣት ወደ 9ኛ ክፍል መሸጋገራቸውን የክልሉ ትምህርት ቢሮ ምክትል ኃላፊ ቡልቶሳ ኢርኮ (ዶ/ር) ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

ተፈታኞች ውጤታቸውን https://oromia.ministry.et/#/ ላይ በመግባትና የአድሚሽን ካርድ ቁጥር በማስገባት ውጤታቸውን መመልከት እንደሚችሉ ገልፀዋል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]