ETHIO ≈ SCHOOL
2.51K subscribers
5.02K photos
10 videos
225 files
1.97K links
ይህ ለተማሪዎች እና ለትምህርት ፈላጊዎች ተብሎ የተዘጋጀ ፈጣን የሆነ መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ነው።
እንዲሁም በተጨማሪ መረጃወችን በመሰብሰብ በሁሉም የ ት/ት ደረጃ ተማሪን የሚመለከት መረጃ በፍጥነት እናደርሳለን።
ለCross ፦
👇👇👇

👍 @yesshsammmits
👍 @gashtiman1990

Join
👇👇👇
@merejamnch
Download Telegram
#EHPLE

የጤና ባለሙያዎች የብቃት ምዘና ፈተና ከነገ ሰኔ 17/2018 ዓ.ም ጀምሮ ለሦስት ተከታታይ ቀናት ይሰጣል፡፡

ነገ ሰኔ 17/2018 ዓ.ም የሚሰጡ ፈተናዎች፦

● ሕክምና
● ማኅበረሰብ ጤና
● ሜዲካል ላቦራቶሪ ሳይንስ
● ሚድዋይፈሪ
● ሜዲካል ራዲዮሎጂ ቴክኖሎጂ
● የሕጻናት ሕክምናና የሕጻናት ጤና ነርሲንግ

ተፈታኞች በዛሬው ዕለት አጠቃላይ የፈተና ገለጻ የተሰጣቸው ሲሆን፤ የመለማመጃ ፈተና (Mock Exam) እየወሰዱ ነው።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
ቅሬታዎን ያስገቡ!

በመውጫ ፈተና ውጤትዎ ላይ ቅሬታ ካለዎት ቅሬታዎን በኦንላይን ያስገቡ፡፡

➫ ውጤትዎ ያልተገኘ ከሆነ
➫ Disqualified የተባሉ ከሆነ
➫ ፊርማ ቢፈርሙም NG የተባሉ ከሆነ
➫ የተሳሳተ ጾታ ከመረጡና መሠል ቅሬታ ካለዎ ማቅረብ ይችላሉ፡፡

የመውጫ ፈተና ውጤት ባዩበት ሊንክ (https://result.ethernet.edu.et) ላይ Submit Complaint የሚለውን ይጫኑ፣ Complaint Category ከሚለው ይምረጡ፣ Description የሚለው ባዶ ቦታ ላይ ቅሬታውን አጠር አድርገው ይግለፁ፣ ስልክ ቁጥርዎን ያስገቡና Submit Complaint የሚለውን በመጫን ያጠናቅቁ፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
ቅሬታችሁን እስከ ሰኔ 23/2018 ዓ.ም ድረስ ብቻ ማቅረብ ትችላላችሁ። - የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት

ከመውጫ ፈተና ውጤት ጋር በተያያዘ ቅሬታ ያላችሁ ተፈታኞች፣ ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት ገልጿል።

ውጤት ያያችሁበትን ሊንክ https://result.ethernet.edu.et/usernamepage በመጠቀም፣ በገፁ ላይ የሚገኘውን "Submit Complaint" የሚለውን አማራጭ በመጫን ቅሬታችሁን ማቅረብ የምትችሉ መሆኑን አገልግሎቱ አስረድቷል።

ቅሬታ የማቅረቢያ ጊዜ 👇
ከሰኔ 17-23/2018 ዓ.ም

ቅሬታ አቅራቢዎች በአካል ወደ  የትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት መሔድ ሳይጠበቅባችሁ በኦንላይን ብቻ ቅሬታችሁን እንድታቀርቡ ተብሏል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#MizanTepiUniversity

ከሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ ተመርቃችሁ ዋናውን ዲግሪ (Original Degree) ያልወሰዳችሁ እና እንዲሠራላችሁ የምትፈልጉ የተቋሙ ምሩቃን ትምህርት ሚኒስቴር ባስቀመጠው አቅጣጫ መሠረት ዋናው ዲግሪ የመጀመሪያ ዙር ህትመት ለማድረግ ከታች በተቀመጠው ማስፈንጠሪያ እስከ ሰኔ 30/2018 ዓ.ም ድረስ አስፈላጊውን መረጃ እንድትሞሉ ዩኒቨርሲቲው ጠይቋል፡፡

ከሰኔ 30/2018 ዓ.ም በኋላ የምትመዘገቡ በሁለተኛው ዙር የሚታተምላችሁ መሆኑ ተገልጿል፡፡

በወጭ መጋራት የተማራችሁ አመልካቾች ዋናውን ዲግሪያችሁን ለመውሰድ ክፍያ መፈፀማችሁን ወይም በአገልግሎት መወጣታችሁን የሚያረጋግጥ ደብዳቤ እና ደረሰኝ ማቅረብ ይጠበቅባችኋል ተብሏል፡፡

ምዝገባ ለማድረግ 👇🏼
https://forms.gle/9ymN9vsQP6Df5y1y8

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#RayaUniversity

ራያ ዩኒቨርሲቲ ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀውን የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የተቋሙ ተማሪዎች መካከል 98.98 በመቶዎቹ የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ገልጿል።

ዩኒቨርሲቲው ለአገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ካስቀመጣቸው 295 እጩ ተመራቂዎች መካከል 292 ተማሪዎች ወይም 98.98% ማለፉቸውን አሳውቋል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#WolkiteUniversity

ወልቂጤ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የተቋሙ የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች መካከል 92.5% የሚሆኑት እጩ ተመራቂ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ገልጿል።

ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀውን የመውጫ ፈተና ካስፈተኑት 17 የተቋሙ ትምህርት ክፍሎች መካከል ዘጠኙ ሙሉ በሙሉ (100%) በማሳለፍ የላቀ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#UoG

የጎንደር ዩኒቨርሲቲ ሥራ አመራር ቦርድ ለስምንት የተቋሙ ምሑራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እድገት አጽድቋል።

ከተባባሪ ፕሮፌሰርነት ወደ ሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ እድገት ያደጉ ምሑራን፦

1. ዶ/ር በውቀቱ መሐሪ
2. ዶ/ር ሞላ ተፈራ
3. ዶ/ር ምሳዬ ሙላቴ
4. ዶ/ር ጌትነት ማስረሻ
5. ዶ/ር ደሴ ጥበበ
6. ዶ/ር ማስተዋል ብርሀን
7. ዶ/ር አስማማው አጥናፉ
8. ዶ/ር አስማማው ዓለሙ

​የአካዳሚክ ማዕረግ እድገቱ በትምህርት ሚኒስቴር መመሪያ መሠረት ምሑራኑ በምርምር፣ በማስተማር እና በላቀ ተቋማዊ አመራር ላበረከቱት ከፍተኛ አስተዋጽኦ የተሰጠ መሆኑን ዩኒቨርሲቲው ገልጿል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#ArsiUniversity

አርሲ ዩኒቨርሲቲ የመውጫ ፈተና ከወሰዱ የተቋሙ የመደበኛ መርሐግብር ተማሪዎች መካከል 94.14% የሚሆኑት እጩ ተመራቂ ተማሪዎች የማለፊያ ነጥብ ማምጣታቸውን ገልጿል።

ባለፈው ሳምንት የተጠናቀቀውን የመውጫ ፈተና ካስፈተኑ የትምህርት ክፍሎች መካከል ሰባቱ ሙሉ በሙሉ (100%) በማሳለፍ የላቀ ውጤት ማስመዝገባቸው ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ በተለያዩ የትምህርት መስኮች በመጀመሪያ እና በሁለተኛ ዲግሪ ያስተማራቸውን ከ2,900 በላይ ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ከተመራቂዎቹ መካከል 178ቱ በሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራም ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ተቋሙ በ2018 ዓ.ም ለመጀመሪያ ጊዜ ካስፈተናቸው የመደበኛ እና የተከታታይ ፕሮግራም ተማሪዎች መካከል 87.4 በመቶ ተማሪዎች ሀገር አቀፍ የመውጫ ፈተና ያሳለፈ መሆኑን የእንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ፕሬዝዳንት ጋርዳቸው ወርቁ (ዶ/ር) ገልፀዋል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#UoG

ጎንደር ዩኒቨርሲቲ የድንቅነሽን ቅሪተ አካል ላገኙት አሜሪካዊ ምሑር ፕሮፌሰር ዶናልድ ጆሀንሰን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በተለያዩ የትምህርት መስኮች ያሰለጠናቸውን ከ4 ሺህ በላይ ተማሪዎች አስመርቋል፡፡

ተመራቂዎቹ በመጀመሪያ፣ በሁለተኛ፣ በሦስተኛ ዲግሪ እንዲሁም በስፔሻሊቲ እና በሰብ-ስፔሻሊቲ ፕሮግራሞች ስልጠናዎች ትምህርታቸውን ተከታትለው ያጠናቀቁ ናቸው።

ዩኒቨርሲቲው “ሉሲ” ወይም “ድንቅነሽ” በመባል የምትታወቀውን የ3.2 ሚሊዮን ዓመት እድሜ ያላትን የሰው ዘር ቅሪት አካል በአፋር ክልል ላገኙት አሜሪካዊ ምሑር ፕሮፌሰር ዶናልድ ካርል ጆሀንሰን የክብር የሳይንስ ዶክትሬት ዲግሪ ሰጥቷል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#MoH

በሰኔ 2018 ዓ.ም የመውጫ ፈተና ለወስዳችሁ የጤና ሙያ ተመራቂዎች የብቃት ምዘና ፈተና #በሐምሌ ወር 2018 ዓ.ም መጨረሻ ለመስጠት መታቀዱን ጤና ሚኒስቴር አሳውቋል።

ለዚህም በቅርብ ቀን ምዝገባ እንደሚጀመር ሚኒስቴሩ ገልጿል።

በመሆኑም በሰኔ ወር የመውጫ ፈተና የወሰዳችሁ የጤና ሙያ ተመራቂዎች ለብቃት ምዘናው የሚያስፈልጉ የትምህርት ማስረጃዎችን እንድታሟሉ እና ለምዝገባው ዝግጁ እንድታደርጉ ተብሏል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#DebreBerhanUniversity

‎ደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ በቅድመ እና በድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች ያስተማራቸውን 897 ተማሪዎች በዛሬው ዕለት አስመርቋል።

35 A+ ያመጣው ተማሪ

ብሩክ ደግነት ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የፕ/ር አስራት ወልደየስ ጤና ሳይንስ ኮሌጅ የፋርማሲ ትምህርት ክፍል ተመራቂ ነው።

ብሩክ ከወሰዳቸው አጠቃላይ ኮርሶች 35 A+ በማምጣት እና 3.97 ውጤት በማስመዝገብ የሜዳልያ እና የዋንጫ አሸናፊ ሆኗል። 👏👏

ከሴቶች የከፍተኛ ውጤት ባለቤቷ

ተማሪ ትርንጎ ገዛኸኝ ከደብረ ብርሃን ዩኒቨርሲቲ የማኔጅመንት ትምህርት ክፍል በላቀ ማዕሰግ ተመርቃለች።

ከዘንድሮ ሴት ተመራቂዎች ከፍተኛ የሆነውን 3.96 አጠቃላይ ውጤት በማስመዝገብ የክብር ዋንጫ ተሸላሚ ሆናለች። 👏👏

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
በአዲስ አበባ የ8ኛ ክፍል ከተማ አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 95.85% ተማሪዎች ማለፋቸውን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ አሳውቋል።

በአዲስ አበባ የ2018 ትምህርት ዘመን የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ከተማ አቀፍ ፈተና ከወሰዱ ተማሪዎች 95.85% ተማሪዎች 50 እና ከዛ በላይ ውጤት ማስመዝገባቸውን የከተማ አስተዳደሩ ትምህርት ቢሮ ገልጿል።

በመዲናዋ የ8ኛ ክፍል ፈተና የወሰዳችሁ ውጤታችሁን ለመመልከት 👇 https://aa.ministry.et/#/result

በአዲስ አበባ ከተማ ሰኔ 11 እና 12/2018 ዓ.ም የተሰጠውን ከተማ አቀፍ የ8ኛ ክፍል ፈተና፣ ከ86 ሺህ በላይ ተማሪዎች መውሰዳቸው ይታወሳል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
ትምህርት ሚኒስቴር ላለፉት ዓመታት አቋርጦት የቆየውን የመምህራን የክረምት ትምህርት ስልጠና ዘንድሮ ሊጀምር ነው።

በኮቪድ-19፣ በጦርነት እና በተለያዩ ምክንያቶች ተቋርጦ የቆየው የመምህራን የክረምት ትምህርት ስልጠና በዚህ ዓመት ሊጀመር እንደሆነ ተሰምቷል።

የስልጠና ፕሮግራሙ በዲግሪ ፕሮግራም በስምንት የትምህርት አይነቶች በተያዘው ዓመት በድጋሚ ሊጀመር መሆኑ ታውቋል።

እንግሊዝኛ፣ ሒሳብ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ፣ ባዮሎጂ፣ ጂኦግራፊ፣ ታሪክ እና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ በክረምቱ ወራት ስልጠና የሚሠጥባቸው የትምህርት አይነቶች መሆናቸው ተገልጿል።

የኢትዮ ኮደርስ ስልጠና ያጠናቀቁ እና የሙያ ብቃት ምዘና ያለፉበትን የምስክር ወረቀት ማቅረብ የሚችሉ መምህራን ለክረምቱ የዲግሪ ፕሮግራም ስልጠና ማመልከት ይችላሉ ተብሏል።

አመልካቾች ከ8ኛ ክፍል ጀምሮ የትምህርት ማስረጃዎቻቸውን ማቅረብ የሚችሉ፣ ቢያንስ የሦስት ዓመት የሥራ ልምድ ያላቸው እና እድሜአቸው ከ50 ያልበለጠ እንዲሆኑ ይጠበቃል።

ትምህርት ሚኒስቴር ባለፉት ሁለት ዓመታት ልዩ የመምህራን እና የትምህርት ቤት አመራሮች የክረምት ስልጠና መስጠቱ ይታወቃል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
በአራት ዘርፎች ከ6ዐ በመቶ በላይ የሚያመጡ የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ራስ ገዝ ይሆናሉ። - ትምህርት ሚኒስቴር

የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች በአስተዳዳር፣ በፋይናንስ፣ በሰው ኃይል አደረጃጀት እና በአካዳሚክ መለኪያዎች መሠረት ተገምግመው ከ6ዐ በመቶ በላይ ውጤት ካስመዘገቡ ራስ ገዝ መሆን እንደሚችሉ የትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል፡፡

ራስ ገዝ መሆን የሚፈልግ ዩኒቨርሲቲ የራሱን ተቋማዊ ግለ ግምገማ በማድረግ ወደ ራስ ገዝነት ለመሸጋገር የሚያስችል ውጤት 6ዐ በመቶና ከዚያ በላይ ማገኘቱን ሲያረጋግጥ በዩኒቨርሲቲው ሥራ አመራር ቦርድ አፀድቆ፣ ለትምህርት ሚኒስቴር ግምገማ እንዲካሄድለት በደብዳቤ ጥያቄ ማቅረብ እንዳለበት ሰኔ 19 ቀን 2018 ዓ.ም. በትምህርት ሚኒስቴር የወጣው መመሪያ ያዛል፡፡

ሚኒስቴሩ በመመሪያው መሠረት 60 በመቶና ከዚያ በላይ ላስመዘገበ ተቋም የራስ ገዝነት ሽግግር ሒደት እንዲጀምር ፈቃድ ይሰጣል።

ሚኒስቴሩም የቀረበለትን የግምገማ ውጤቱ መሠረት በማድረግ 6ዐ በመቶና ከዚያ በላይ ያገኘ ዩኒቨርሲቲ ወደ ራስ ገዝ ዩኒቨርሲቲነት የሚያሸጋግረውን የሚፈቅድ የማቋቋሚያ ደንብ ከተቋሙ ጋር ተመካክሮ በማዘጋጀት፣ ለሚኒስትሮች ምክር ቤት እንዲፀድቅለት ጥያቄ እንደሚያቀርብ በመሪያው ሠፍሯል።

የዩኒቨርሲቲው የግምገማ ውጤት ዝቅተኛ ሆኖ ከተገኘ በታዩ ክፍተቶች ላይ የማሻሻያ መርሐግብር ተቋሙ እንዲያዘጋጅ አቅጣጫ በማስቀመጥና ውጤቱን እንዲያሻሽል ክትትል በማድረግ፣ በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ ለሁለተኛ ጊዜ ግምገማ እንዲካሄድ ሁኔታዎችን ማመቻቸትም የሚኒስቴሩ ተግባር መሆኑ ተመልክቷል፡፡ #ሪፖርተር

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
የድሬዳዋ አስተዳደር ትምህርት ቢሮ የ2018 ዓ.ም የ6ኛ ክፍል ፈተና ውጤት ይፋ አዶርጓል።

በአስተዳደሩ የ6ኛ ክፍል ፈተና የወሰዱ ተማሪዎች (ወላጆች) ከታች በተቀመጠው ሊንክ በመግባት የፈተና መለያ ቁጥራችሁን (Registration Number) በማስገባት ውጤታችሁን መመልከት ትችላላችሁ ተብሏል።



ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]