ETHIO ≈ SCHOOL
2.51K subscribers
5.02K photos
10 videos
225 files
1.97K links
ይህ ለተማሪዎች እና ለትምህርት ፈላጊዎች ተብሎ የተዘጋጀ ፈጣን የሆነ መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ነው።
እንዲሁም በተጨማሪ መረጃወችን በመሰብሰብ በሁሉም የ ት/ት ደረጃ ተማሪን የሚመለከት መረጃ በፍጥነት እናደርሳለን።
ለCross ፦
👇👇👇

👍 @yesshsammmits
👍 @gashtiman1990

Join
👇👇👇
@merejamnch
Download Telegram
የሙያ ፈቃድዎን ይውሰዱ!

በታህሳስ 2018 ዓ.ም የተሰጠውን የብቃት ምዘና ፈተና ወሰዳችሁ ፈተናውን ያለፋችሁ ተመዛኞች ከዛሬ ጥር 13/2018 ዓ.ም ጀምሮ በምትኖሩበት ክልል በመሔድ የሙያ ፈቃድ መውሰድ የምትችሉ መሆኑ በጤና ሚኒስቴር ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#ExitExam

በ2018 ዓ.ም አጋማሽ የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ተፈታኞች የፈተና ጊዜ ተራዝሟል፡፡


ትምህርት ሚኒስቴር ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በጻፈው ደብዳቤ የዚህ ዓመት አጋማሽ የመውጫ ፈተና ከጥር 14/2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ማስታወቁ ይታወሳል።

ነገር ግን "ከፈተና ዝግጅት ሥራዎች ጋር በተያያዘ ምክንያት" የፈተናው ቀን የተራዘመ መሆኑ ተገልጿል።

ምዝገባ ያደረጋችሁና በማድረግ ላይ የምትገኘ ተመዛኞች ፈተናው የሚሰጥበት ትክክለኛ ቀን በትምህርት ምዘናና ፈተናዎች አገልግሎት / በትምህርት ሚኒስቴር እስከሚገለጽ ድረስ በትዕግስት አንድትጠብቁ ተብሏል።

(ከላይ የተያያዘው የምስል መረጃ ከወለጋ ዩኒቨርሲቲ የተገኘ ነው።)

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
መቐለ ዩኒቨርሲቲ በአማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም ለመሰልጠን ያመለከቱና የመጀመሪያ ዙር ማጣሪያ ያለፉ አመልካቾች ተጨማሪ ማረጋገጫ ማስገባት እንደሚጠበቅባቸው አሳውቋል፡፡

በዚህም የመቐለ ዩኒቨርሲቲ ኤዱኬሽን ሳይንስ ትምህርት ቤት ያወጣው አመልካቾች ዝርዝር ላይ "to be verified" የተባላችሁ በሙሉ፣ የመጀመሪያ ዲግሪ ሰርተፊኬታችሁን እስከ ጥር 17/2018 ዓ.ም ለትምህርት ቤቱ እንድታስገቡ ተብሏል፡፡

እስከተጠቀሰው ቀን ድረስ ሰነዳቸውን የማያስገቡ አመልካቾች በሌሎች ዕጩዎች እንደሚተኩ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

የመቐለ ዩኒቨርሲቲ አመልካቾች ዝርዝር 👇🏻
https://drive.google.com/file/d/1N6_CNkRjWZeX4LQXIDQGOxRx-4P8wbc-/view

መቐለ ዩኒቨርሲቲ በአምስት የትምህርት ዘርፎች ማለትም ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ እንግሊዝኛ እና ሒሳብ መስኮች በእያንዳንዳቸው 40 አመልካቾችን እንደሚቀበል አስረድቷል፡፡

ለአንድ ዓመት የሚሰጠው ’አማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም’ በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ በኮተቤ የትምህርት ዩኒቨርሲቲ፣ በጅማ ዩኒቨርሲቲ፣ በሀዋሳ ዩኒቨርሲቲ፣ በመቐለ ዩኒቨርሲቲ እና በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ተግባራዊ እየተደረገ ይገኛል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
ተራዝሟል!

ትምህርት ሚኒስቴር ትምህርት ባስጀመረባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ባሉ ጥቂት ክፍት ቦታዎች ተጨማሪ ተማሪዎችን (አሁን 9ኛ ክፍል ገብተው እየተማሩ ካሉ ተማሪዎች መካከል በማወዳደር) ተቀብሎ ማስተማር ይፈልጋል።

የምዝገባ ጊዜው እንዲጨመር አንዳንድ ክልሎች በጠየቁት መሰረት እስከ ጥር 20/2018 ዓ.ም የተራዘመ መሆኑን ሚኒስቴሩ አሳውቋል፡፡

የነጻ ትምህርት ዕድሉ ጥቅሞች፦
➫ ሙሉ የትምህርት ክፍያ ሸፋን
➫ ነጻ የመኝታ እና የምግብ አገልግሎቶች
➫ ልዩ ስርዓተ ትምህርት የሚከተል ጥራት ያለው ትምህርት
➫ ምቹ የመማሪያ አካባቢ

አመልካቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ መስፈርቶች፦
➫ በ2017 ዓ.ም 8ኛ ክፍልን ያጠናቀቀ/ች፣
➫ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ያለው/ያላት፣
➫ በ8ኛ ክፍል ክልላዊ ፈተና 85% ወይም ከዚያ በላይ አማካይ ውጤት ያለው/ያላትና አሁን 9ኛ ክፍል እየተማረ ያለ/ያለች።

መስፈርቱን የምታሟሉ ተማሪዎች ምዝገባችሁን ባላችሁበት ሆናችሁ በኦንላይን https://sbs.moe.gov.et/apply መመዝገብ እና አስፈላጊ የተባሉ መረጃዎችን ማያያዝ ይጠበቅባችኋል።

የማስተማር ሥራ የተጀመረባቸው የፌዴራል ልዩ አዳሪ ትምህርት ቤቶች ጋምቤል፣ ጅግጅጋ፣ ቡኢ (ወልቂጤ)፣ ቦንጋ እና ወሊሶ ናቸው።

ለፈተና የሚቀርቡ ተማሪዎች ዝርዝር እና የፈተና ጊዜ ወደፊት ይገለጻል ተብሏል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#ጥቆማ

በሐረማያ ዩኒቨርሲቲ የኤዱኬሽን እና ባህሪ ሳይንስ ኮሌጅ በስምንት ልዩ የማስተርስ ፕሮግራሞች አመልካቾችን ይቀበላል፡፡

የአመልካቾች ምዝገባ ከዛሬ ጥር 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ እየተከናወነ ይገኛል፡፡

የ2ኛ ዲግሪ ትምህርት መስኮች፦
➫ Adult Education and Lifelong Learning
➫ Curriculum and Instruction
➫ Curriculum and Quality Assurance
➫ Special Needs and Inclusive Education
➫ Educational Psychology
➫ Educational Planning and Management
➫ Social Psychology
➫ Developmental Disability

የምዝገባ ቦታ፦
በድሬዳዋ የመምህራን ትምህርት ኮሌጅ

ለበለጠ መረጃ፦
0913502864 / 0938922477

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#JinkaUniversity

ጂንካ ዩኒቨርሲቲ የተመደቡ የ2018 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም አዲስ ገቢ ተማሪዎች ወደዩኒቨርሲቲው ከትናንት ጥር 18/2018 ዓ.ም ጀምሮ በመግባት ላይ ይገኛሉ።

ዩኒቨርሲቲው አሁን ላይ መቆጣጠር በተቻለው የማርበርገር ቫይረስ ምክንያት ለሪሚዲያል ተማሪዎች ዘግይቶ ጥሪ ማድረጉ ይታወቃል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#BahirDarUniversity

ባሕርዳር ዩኒቨርሲቲ ለአማራጭ የመምህራን ስልጠና አመልካቾች ጥሪ አድርጓል።

በተለያዩ የትምህርት ዘርፎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቃችሁ የአንድ ዓመት ስልጠና በመውሰድ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የእንግሊዝኛ መምህር ለመሆን ያመለከታችሁና ከስር በተገለፁት የትምህርት ዘርፎች ብቻ የተመረቃችሁ የትምህርት ማስረጃችሁን (Temporary Certificate of Graduation) እስከ ጥር 22/2018 ዓ.ም ድረስ በቴሌግራም አድራሻ @assefa3443 እንድትልኩ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል።

የትምህርት ዘርፎች፦

➫ English Language and Literature
➫ Journalism and Communication
➫ Ethiopian Languages and Literature
➫ Communication and Media Studies
➫ General Linguistics

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#Update

የ2018 ዓ.ም አጋማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና (Exit Exam) ከየካቲት 16-27/2018 ዓ.ም ይሰጣል።

የቅድመ ምረቃ ፕሮግራም የመውጫ ፈተና ከየካቲት 16 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ እንደሚሰጥ ትምህርት ሚኒስቴር ትናንት ጥር 19/2018 ዓ.ም ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በላከው መረጃ ገልጿል።

የፈተና መርሐግብሩን ትክክለኛነትና ለዩኒቨርሲቲዎች መድረሱን ቲክቫህ ዩኒቨርሲቲ አረጋግጧል።

በመሆኑም የ2018 ዓ.ም ግማሽ ዓመት የመውጫ ፈተና ዕጩ ተፈታኞች የጊዜ ሰሌዳውን አውቃችሁ አስፈላጊውን ዝግጅት እንድታደርጉ ተብሏል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#Update #ERMP

የ2018 ዓ.ም የብሔራዊ ህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (ERMP) የመግቢያ ፈተና የካቲት 09 እና 10/2018 ዓ.ም በተመረጡ የፈተና ማዕከላት እንደሚሰጥ ጤና ሚኒስቴር አረጋግጧል፡፡

ለ2018 ዓ.ም የብሔራዊ ህክምና ስፔሻሊቲ ስልጠና (ERMP) የተመረጡ ዕጩ አመልካቾችን ዝርዝር በቀጣይ ሳምንት ይፋ እንደሚያደርግ ሚኒስቴሩ ገልጿል።

የተመዘገቡ አመልካቾችን የማጣራት ሥራ ሲያከናውን የቆየው ሚኒስቴሩ፤ የመጨረሻ የተመረጡ አመልካቾችና የመፈተኛ ማዕከላትን በቀጣይ ሳምንት ይፋ እንደሚያደርግ ጠቁሟል፡፡

እስካሁን ከ3,000 በላይ አመልካቾች ምዝገባ ያደረጉ ሲሆን፤ 2,534 አመልካቾች የተረጋጠጡ እንደሆኑ ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
ማስታወቂያ
በባሕር ዳር የኒቨርሲቲ ልዩ አማራጭ መምህራን ትምህርት ስልጠና አመልካቾች በሙሉ፤

በልዩ አማራጭ መምህራን ትምህርት ስልጠና ለመሳተፍ ካመለከታችሁት ምሩቃን መካከል በአማርኛ፤ እንግሊዝኛ እና ፊዚክስ ትምህርቶች ዘርፍ የተመረጣችሁ ስልጣኞች ስማችሁን ከዚህ ጋር በተዘረዘሩት ሰንጠረዦች ማየት የምትችሉ መሆኑን እየገለፅን የምዝገባ ጊዜ የካቲት 2 እና 3፣ 2018 ዓ፣ም በፔዳ ካምፓስ መምህራን ትምህርት ትምህርት ቤት መሆኑን እናሳውቃለን፡፡
Announcement
To all applicants of Bahir Dar University Special Alternative Teacher Education Training:
We would like to inform you that, among the graduates who applied to participate in the Special Alternative Teacher Education Training in Amharic, English, and Physics, the names of the selected candidates are presented in the attached tables.
The registration period will be February 10–11, 2026, at the Teacher Education School, PEDA Campus.
ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
ጎንደር ዩኒቨርሲቲ ዲጂታል ቴክኖሎጂ ላይ ትኩረት ያደረጉ አራት አዳዲስ የትምህርት መስኮችን በመክፈት በሁለተኛ ዲግሪ ማሰልጠን ሊጀምር ነው።

በትምህርት መስኮቹ ላይ የፍላጎት ዳሰሳ ጥናት መካሔዱን የገለፁት የዩኒቨርሲቲው ፕሬዝዳንት አስራት አፀደወይን (ዶ/ር) ፤ በትምህርት ፕሮግራሞቹ ላይ የስርዓተ ትምህርት ቀረጻ እና ግምገማ መካሔዱን ገልፀዋል፡፡

አዲስ የሚጀመሩ የሁለተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች፦
➫ ሰው ሰራሽ አስተውሎት (AI)
➫ ኮምፒውተር ኔትዎርኪንግና ሴኩሪቲ
➫ ዲጂታል ማርኬቲንግና ዲጂታል አናሊሲስ
➫ ዲጂታል ትራንስፎርሜሽንና ኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ

ዩኒቨርሲቲው በዚህ ዓመት ሁለተኛ ሴሚስተር በፕሮግራሞች ተማሪዎችን ማሰልጠን እንደሚጀምር ፕሬዝዳንቱ ጠቅሰዋል። #ኢዜአ

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#MekelleUniversity

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ለአማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም አመልካቾች ጥሪ አድርጓል፡፡

ከዚህ በፊት የመቐለ ዩኒቨርሲቲ የትምህርት ሳይንስ ትምህርት ቤት ባወጣው የአመልካቾች ዝርዝር ላይ "to be verified" የተባላችሁ እንዲሁም "Last Chance" የተባላችሁ አመልካቶች፤ የመጀመርያ ዲግሪ የትምህርት ማስረጃችሁን ኮፒ እስከ ጥር 29/2018 ዓ.ም እንድታስገቡ ዩኒቨርሲቲው አሳስቧል፡፡

(የአመልካቾች ዝርዝር በዩኒቨርሲቲው የማኅበራዊ ገጾች ላይ ይገኛል፡፡)

መቐለ ዩኒቨርሲቲ ለአንድ ዓመት በሚሰጠው 'አማራጭ የመምህራን ስልጠና ፕሮግራም' በአምስት የትምህርት ዘርፎች ማለትም ባዮሎጂ፣ ፊዚክስ፣ ኬሚስትሪ፣ እንግሊዝኛ እና ሒሳብ መስኮች አመልካቾችን እንደሚቀበል መግለፁ ይታወቃል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]