ETHIO ≈ SCHOOL
2.51K subscribers
5.02K photos
10 videos
225 files
1.97K links
ይህ ለተማሪዎች እና ለትምህርት ፈላጊዎች ተብሎ የተዘጋጀ ፈጣን የሆነ መረጃ የሚያገኙበት ቻናል ነው።
እንዲሁም በተጨማሪ መረጃወችን በመሰብሰብ በሁሉም የ ት/ት ደረጃ ተማሪን የሚመለከት መረጃ በፍጥነት እናደርሳለን።
ለCross ፦
👇👇👇

👍 @yesshsammmits
👍 @gashtiman1990

Join
👇👇👇
@merejamnch
Download Telegram
#AAU
#FacultyPromotions

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ለ16 ምሁራን የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ ሰጥቷል፡፡

የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሥራ አመራር ቦርድ የ16 ምሁራንን የሙሉ ፕሮፌሰርነት የማዕረግ ዕድገት አፅድቋል፦

1. ፕሮፌሰር አለሙ ሀይሉ አንሹ - በእንግሊዝኛ ቋንቋ ማስተማር
2. ፕሮፌሰር ዳዊት መኮንን ምህረቴ - በኤዱኬሽን
3. ፕሮፌሰር ማቴዎስ እንሰርሙ ጃለታ - በሳፕላይ ቼይን አስተዳደር
4. ፕሮፌሰር ጌታቸው አሰፋ ወ/ማርያም - በህግ
5. ፕሮፌሰር በቀለ መኮንን ንጉሱ - በፋይን አርትስ
6. ፕሮፌሰር ወንድወሰን አሞኘ ደጉ - በተላላፊ በሽታ ጥናት
7. ፕሮፌሰር ሳምሶን ገ/መድህን ገ/ስላሴ - በኅብረተሰብ ጤና ኒዩትሪሽን
8. ፕሮፌሰር ቸርነት አመንቴ ገፌ - በኮንዴንስድ ማተር ፊዚክስ
9. ፕሮፌሰር እንግዳወርቅ አሰፋ ጥላሁን - በአካባቢ ጥናት
10. ፕሮፌሰር ገረመው ሳህሉ ገብሬ - በውሃ አቅርቦት ምህንድስና
11. ፕሮፌሰር ለሙ ጎላሳ ወዬሳ - በሜዲካል ፓራሲቶሎጂ
12. ፕሮፌሰር አለምሰገድ ቤልዳዶስ አለሆ - በአርኪዮሎጂ
13. ፕሮፌሰር መርዕድ ተሰማ ገ/መድህን - በአናሊቲክ ኬሚስትሪ
14. ፕሮፌሰር እስጢፋኖስ ኤሌ ያያ - በኦርጋኒክ ኬሚስትሪ
15. ፕሮፌሰር ሚስጥረ ዎልዴ ገብሬ - በክሊኒካል ላቦራቶሪ ሳይንስ
16. ፕሮፌሰር በላይነህ መስፍን አሊ - በሶሊድ ስቴት ፊዚክስ

በዚህ ዙር የሙሉ ፕሮፌሰርነት ማዕረግ የተሰጣቸው ምሁራን በሙሉ ወንዶች ናቸው።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#FellowshipOpportunity

በቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሚሌኒየም ሜዲካል ኮሌጅ የውስጥ ደዌ ህክምና ትምህርት ክፍል ብቁ አመልካቾችን ለ2018 ዓ.ም Adult Nephrology Fellowship ፕሮግራም አወዳድሮ መቀበል ይፈልጋል።

ለዚህ ዓመት ሦስት (3) የፌሎውሺፕ ዕድሎች መኖራቸውን ኮሌጁ ገልጿል።

የማመልከቻ ጊዜ የሚያበቃው፦
ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም

የቅበላ መስፈርት፦
➫ ከታወቀ የህክምና ትምህርት ተቋም በህክምና ዲግሪ ያለው ያላት,
➫ በ Internal medicine የሬዚደንሲ ፕሮግራም ያጠናቀቀ/ች፣
➫ Internist ሆኖ/ሆና ለሁለት ዓመት ያገለገለ/ች፣
➫ የቅበላ ምልመላ ሒደት የሚያጠናቅቁ፣
➫ በኢትዮጵያ የውስጥ ደዌ ህክምና ለመስጠት ተመዝግቦ ፈቃድ ያለው/ያላት፣
➫ ጥሩ አዕምሯዊና አካላዊ ጤና ያላት/ያለው፣
➫ አጭር የፍላጎት መግለጫ ማስገባት፣

የማመልከቻ አማራጮች፦
ፍላጎት ያላችሁ አመለልካቾች በ Internal ህክምና ትምህርት ክፍል በአካል በመቅረብ ወይም በኢሜል አድራሻዎች ayantu17@yahoo.com / lejahamza@yahoo.com ማመልከት ይችላሉ፡፡

አመልካቾች ሊያሟሏቸው የሚገቡ፦
➫ የማመልከቻ ደብዳቤ
➫ የቅርብ ጊዜ CV
➫ የትምህርት ማስረጃዎች (ዲግሪ እና የውጤት መግለጫ)
➫ ሁለት የድጋፍ ደብዳቤዎች
➫ የስፖንሰርሺፕ ደብዳቤ (በመንግሥት ስፖንሰር ለምትደረጉ)
➫ የድኅረ ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) ውጤት

ለበለጠ መረጃ፦
➫ Dr. Ayantu Tesfaye 0911890635
➫ Dr. Leja Hamza 0917804057

የፅሑፍ እና የቃል ፈተና የሚሰጥባቸው ጊዜያት በቀጣይ ይገለጻል የተባለ ሲሆን፤ ትምህርት ታህሳስ 06/2018 ዓ.ም ይጀመራል ተብሏል፡፡

     👇
[https://t.me/allethioschool]
አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም ሁለተኛው ሴሚስተር የድኅረ-ምረቃ ትምህርት አመልካቾችን በቀን መርሐግብር በሁለተኛ እና በሦስተኛ ዲግሪ ፕሮግራሞች ለማስተማር ዝግጅት ማጠናቀቁን አሳውቋል፡፡

በዩኒቨርሲቲዉ ድረ-ገጽ (www.aau.edu.et) ላይ የተመለከቱትን መስፈርቶች በማሟላት ማመልከት እንደምትችሉ ዩኒቨርሲቲው ገልጿል፡፡

የድኅረ-ምረቃ መግቢያ ፈተና (GAT) የማመልከቻ ቀናት፦ ከህዳር 30 እስከ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም

የGAT መፈተኛ ቀናት፦
ከታህሳስ 24-27/2018 ዓ.ም

የመግቢያ ፈተና ያለፉ አመልካቾች ውጤታችሁን https://portal.aau.edu.et/Web/ApplyForAdmission/TestingStatus በማየት ከታህሳስ 28 እስከ ጥር 06/2018 ዓ.ም በ https://admission.aau.edu.et/GraduatePrograms ማመልከት ይችላላችሁ ተብሏል።

በአካል በመገኘት የትምህርት ማስረጃ ማስረከቢያ ቦታ አ.አ.ዩ. ሬጅስትራር ቢሮ ቁጥር 203 መሆኑ ተገልጿል፡፡

(ለሁለተኛ ሴሚስተር የተዘረዘሩ የድኅረ-ምረቃ ትምህርት ፕሮግራሞች ከላይ ተያይዘዋል።)

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#AAU #GAT

በአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ የሚሰጠውን የድኅረ-ምረቃ ፕሮግራሞች የመግቢያ ፈተና (GAT) ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ!

የመግቢያ ፈተናውን ለመውሰድ የማመልከቻ ቀናት ከዛሬ ህዳር 30/2018 ዓ.ም ጀምሮ እስከ ታህሳስ 22/2018 ዓ.ም እንደሚቆይ መገለፁ ይታወቃል፡፡

https://portal.aau.edu.et ይግቡ።
➫ 'Online Exams' የሚለውን ይጫኑ።
➫ Quick Links ከሚለው ስር 'Apply for GAT' የሚለውን ይጫኑ።
➫ 'Test Taker Registration' የሚለውን ቅፅ ይሙሉ።
➫ የፓስፖርት መጠን ያለው ፎቶ ያስገቡ።
➫ 'Submit' የሚለውን ይጫኑ።
➫ ሲስተሙ የሚሰጠዎን የመለያ ቁጥር ይያዙ።
➫ ቴሌብር በመጠቀም የምዝገባ ክፍያ 750 ብር ይክፈሉ።
➫ አድሚሽን ቲኬትዎን በማውረድ ፕሪንት ብለው ይያዙ።

የኦንላይን ማመልከቻችሁን ሞልታችሁ ካጠናቀቃችሁ በኋላ የትምህርት እና ሌሎች ሰነዶቻችሁን ሀርድ ኮፒ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ፣ ቅበላ ቢሮ፣ ሬጅስትራር ህንጻ ቢሮ ቁ. 203 ማስገባት ይጠበቅባችኋል፡፡

🔔 የ'GAT' ፈተና በኦንላይን የሚሰጥ ሲሆን፤ ከመስከረም 2017 ዓ.ም ጀምሮ የተወሰደ የ'GAT' ፈተና ውጤት ለዚህኛው ማመልከቻ ይሠራል ተብሏል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
2ኛው የኢትዮጵያ "አጠቃላይ" ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር ጠቅላላ ጉባኤ በወራቤ ዩኒቨርሲቲ ነገ ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ይካሔዳል፡፡

የጠቅላላ ጉባኤው ተሳታፊ የኢትዮጵያ ኮምፕርሄንሲቭ ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዝዳንቶች በወራቤ ዩኒቨርሲቲ እየተሠሩ ያሉ ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።

የኢትዮጵያ "አጠቃላይ" ዩኒቨርሲቲዎች ማኅበር በመጋቢት 2017 ዓ.ም መመስረቱ ይታወሳል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#RayaUniversity

በ2016 እና 2017 ዓ.ም የሪሚዲያል ፕሮግራም ወይም የአንደኛ ዓመት ትምህርታችሁን በተለያዩ ምክንያቶች ያቋረጣችሁና በ2018 ዓ.ም በራያ ዩኒቨርሲቲ ትምህርታችሁን መከታተል የምትፈልጉ ተማሪዎች ከረቡዕ ታህሳስ 01/2018 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት አምስት (5) ተከታታይ የሥራ ቀናት በቂ ምክንያት በመያዝ በተቋሙ ዋና ሬጅስትራር ፅ/ቤት በአካል በመቅረብ ሪፖርት ማድረግ እንድምትችሉ ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#MoE

አምስት የመንግሥት ዩኒቨርሲቲዎች ራስገዝ ለመሆን ለትምህርት ሚኒስቴር ጥያቄ አቅርበዋል፡፡

ባሕር ዳር፣ ጅማ፣ ጎንደር፣ አዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ እና አዲስ አበባ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲዎች ራስገዝ ለመሆን ጥያቄ ያቀረቡ ዩኒቨርሲቲዎች መሆናቸውን በትምህርት ሚኒስቴር የአስተዳደርና መሰረተ ልማት መሪ ሥራ አስፈፃሚ ሰለሞን አብርሃ (ዶ/ር) ለኢዜአ ተናግረዋል።

ዩኒቨርሲቲዎች በአስተዳደር፣ በፋይናንስ፣ በሰው ሃብት፣ በአካዳሚክ ጉዳዮች እና በምርምር ዘርፍ ባላቸው ቁመና እና በሚያስመዘግቡት ውጤት መሰረት ወደ ራስገዝነት እንደሚሸጋገሩ ጠቁመዋል፡፡

አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ራስገዝ መሆን የሚያስችለውን የሁለት ዓመት የሽግግር ጊዜ አጠናቆ ወደ ሙሉ ራስገዝነት በመሸጋገር ላይ እንደሚገኝም ገልፀዋል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#BongaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ትምህርት ቦንጋ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 06 እና 07/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

ትምህርት ታህሳስ 08/2018 ዓ.ም የሚጀምር መሆኑ ተገልጿል።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3x4 የሆነ 6 ፎቶግራፍ፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ እና የትራስ ልብስ፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#WachemoUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ትምህርት ዋቸሞ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 15 እና 16/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
➫ ስማችሁ ከ A-H የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ሆሳዕና ከተማ
➫ ስማችሁ ከ I-Z የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዱራሜ ካምፓስ ፣ ዱራሜ ከተማ
➫ ስማችሁ ከ A-L የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ሆሳዕና ከተማ
➫ ስማችሁ ከ M-Z የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዱራሜ ካምፓስ ፣ ዱራሜ ከተማ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ካርድ ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3x4 የሆነ 8 ፎቶግራፍ፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣
➫ ብርድ ልብስ፣ አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#ጥቆማ
#InjibaraUniversity

እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ ለህክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጁ ብቃት ያላቸው ባለሙያዎችን አወዳድሮ መቅጠር ይፈልጋል።

➤ የሥራ መደብ፦ በተለያዩ የሙያ መስኮች
➤ ተፈላጊ ባለሙያዎች ብዛት፦ 05
➤ ተፈላጊ የትምህርት ደረጃ፦ የመጀመሪያ ዲግሪና በላይ
➤ ደመወዝ፦ በከፍተኛ ት/ት ተቋማት ስኬል መሰረት
➤ የሥራ ቦታ፦ እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ

የማመልከቻ ጊዜ፦
እስከ ታህሳስ 10/2018 ዓ.ም

የምዝገባ ቦታ፦
እንጅባራ ዩኒቨርሲቲ የብቃትና የሰው ሃብት አስተዳደር ሥራ አስፈጻሚ ቢሮ ሰልክ ቁ. 0932862917

አመልካቾች ለምዝገባ በምትቀርቡበት ወቅት CV እና የትምህርት ማስረጃዎች ዋናውና ኮፒውን ከማመልከቻ ጋር ማቅረብ ይኖርባችኋል፡፡

(ዝርዝር መስፈርቶችን ከላይ ከተያያዘው የዩኒቨርሲቲው ማስታወቂያ ይመልከቱ፡፡)

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ ይመዝገቡ!

ጤና ሚኒስቴር ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ17 የጤና ሙያዎች በመጀመሪያ ዲግሪ ተመርቀው የብቃት ምዘና ፈተና ለመውሰድ በመጠባበቅ ላይ ለሚገኙ የጤና ባለሙያዎች በታህሳስ 2018 ዓ.ም የብቃት ምዘና ፈተና ለመስጠት በዝግጅት ላይ መሆኑን ገልጿል፡፡

በመሆኑም አዲስ እንዲሁም ነባር የመንግሥት እና የግል ተቋማት ተመዛኞች በኦንላይን http://hpe.moh.gov.et/hple ላይ በመግባት እንድትመዘገቡ አሳስቧል፡፡

የኦንላይን ምዝገባ ጊዜ፦
ከታህሳስ 02-12/2018 ዓ.ም

ከተጠቀሰው የምዝገባ ጊዜ በኋላ ምንም ዓይነት የምዝገባ ጥያቄ የማያስተናግድ መሆኑን የገለፀው ሚኒስቴሩ፤ በተጠቀሱት ቀናት እንድትመዘገቡና ሲስተሙ የሚሰጣችሁን የፈተና መለያ ቁጥር (Registration No) የያዘ ስሊፕ Print አድርጋችሁ መያዝ እንዳለባችሁ ገልጿል፡፡

ስትመዘገቡ በመረጣችሁት የፈተና ጣቢያ በፈተናው ወቅት እንድትገኙ እናሳስባለን፡፡

ተመዛኞች ምዝገባውን ለማካሔድ የዲጂታል መታወቂያ (ፋይዳ) ግዴታ በመሆኑ፣ የፋይዳ መለያ ልዩ ቁጥር (FIN) በትክክል እንድታስገቡ አሳስቧል፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#ArsiUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት አርሲ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
በዩኒቨርሲቲው ዋናው ግቢ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3x4 የሆነ 4 ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
የአማራ ክልል ትምህርት ቢሮ ተቋርጦ የነበረውን መደበኛ የመምህራን የሥራ ቦታ ዝውውር ሊያስጀምር ነው፡፡

ባለፉት ዓመታት በክልሉ በተፈጠረው የፀጥታ ችግር ምክንያት ተቋርጦ የቆየው የመምህራን እና ትምህርት ቤት አመራሮች ዝውውር በዚህ ዓመት ሊጀመር መሆኑን የቢሮው ምክትል ኃላፊ ደምስ እንድሪስ ገልፀዋል።

የመምህራንና የትምህርት ቤት አመራሮች የዝውውር መመሪያ መሻሻሉን የገለፁት ኃላፊው፤ ዝውውር ለማድረግ ገዳቢ የነበሩ ችግሮች በተሻሻለው መመሪያ ምላሽ ማግኘታቸውን አስረድተዋል፡፡

በአዲሱ ስርዓተ ትምህርት የታጠፉ የትምህርት ዓይነቶች ሲያስተምሩ የነበሩ መምህራን አዲስ በተመደቡበት የትምህርት ዓይነት ዝውውራቸው የሚፈፀም መሆኑ ተመላክቷል፡፡ በዘርፉ የሚታየውን የሰው ሃይል ስምሪት ምጥጥን ለማረጋገጥም ያስችላል ተብሏል፡፡

ዝውውሩ ገቢራዊ ከመሆኑ በፊት በተሻሻለው መመሪያ ላይ በዘርፉ ለሚገኙ ባለሙያዎች ስልጠና የሚሰጥ መሆኑ ታውቋል፡፡

መምህራን፣ ርዕሰ መምህራን እና ሱፐርቫይዘሮች ከታህሳስ 30/2018 ዓ.ም እስከ ጥር 10/2018 ዓ.ም ድረስ ባሉት ቀናት የዝውውር ፎርም እንደሚሞሉ ተገልጿል። #አክትቢ

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#ScholarshipTip

የባሕር ዳር ዩኒቨርሲቲ ትምህርት ኮሌጅ በኖርዌይ የልማትና ትብብር ድርጅት የገንዘብ ድጋፍ ባስጀመራቸው በስነ ትምህርት የሁለተኛ ዲግሪ በሒሳብ ስነ ማስተማር (MED in Educational Sciences: Teaching of Mathematics) እና በስነ ትምህርት የሁለተኛ ዲግሪ በሳይንስ ስነ ማስተማር (MED in Educational Sciences: Teaching of Science Subjects) ፕሮግራሞች ከየካቲት 2018 ዓ.ም ጀምሮ #ነፃ የትምህርት ዕድል አመልካቾችን ተቀብሎ ለማስተማር ይፈልጋል።

አመልካቾች ልታሟሏቸው የሚገቡ፦
➫ የ2ኛ ዲግሪ ለመማር በትምህርት ሚኒስቴር የሚሰጠውን የመግቢያ ፈተና (NGAT) ማለፍ ይኖርባችኋል፡፡
➫ በባዮሎጅ፣ ኬሚስትሪ፣ ፊዚክስ እና ሂሳብ ትምህርት መስኮች የመጀመሪያ ዲግሪ ሊኖራችሁ ይገባል፡፡
➫ ከላይ በተጠቀሱት የትምህርት መስኮች የ2ኛ ዲግሪ ያላችሁ ማመልከት ትችላላችሁ፡፡
➫ የማስተማር ልምድ ያላችሁ አመልካቾች ቅድሚያ ይሰጣችኋል፡፡
➫ በፕሮግራሞቹ ተቀባይነት ለሚያገኙ አመልካቾች ነፃ የትምህርት ዕድሉ በዋናነት የሚሸፍነው ለዩኒቨርሲቲው የሚከፈለውን የትምህርት ክፍያ (Tuition Fee) እና የምርምር ገንዘብ ሲሆን፤ መጠነኛ ወርሃዊ የኪስ ገንዘብም ይታሰብላችኋል፡፡

🔔 አመልካቾች ዩኒቨርሲቲው ለ2018 ዓ.ም ሁለተኛ ሴሚስተር በሚያወጣው ማስታወቂያ የማመልከቻ ጊዜ ሰሌዳ መሰረት ማመልከቻችሁን ማስገባት ይኖርባችኋል፡፡

ለበለጠ መረጃ፦ 0929402311 / 0918766232

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#MizanTepiUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ሚዛን-ቴፒ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 25 እና 26/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
➫ በማኅበራዊ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ ሚዛን አማን ከተማ በሚገኘው ዋናው ግቢ፣
➫ በተፈጥሮ ሳይንስ መስክ የተመደባችሁ ቴፒ ከተማ በሚገኘው ቴፒ ግቢ።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 3 ኮፒ፣
➫ መጠኑ 3x4 የሆነ የቅርብ ጊዜ ዘጠኝ ፎቶግራፍ፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#WolaitaSodoUniversity

ወላይታ ሶዶ ዩኒቨርሲቲ በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ትምህርት ወደ ተቋሙ ለተመደቡ ተማሪዎች ጥሪ አድርጓል።

የሪሚዲያል ተማሪዎች ምዝገባ የሚከናወነው ታህሳስ 23/2018 ዓ.ም እና በቦዲቲ ካምፓስ የተመደባችሁ ተማሪዎች ጥር 01/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
➫ ስማችሁ ከ A-B የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ቦዲቲ ካምፓስ፣ ቦዲቲ ከተማ
➫ ስማችሁ ከ C-R የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ
➫ ስማችሁ ከ S-Z የሆነ የተፈጥሮ ሳይንስ ተማሪዎች ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ፣ ታርጫ ከተማ
➫ ስማችሁ ከ A-B የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ቦዲቲ ካምፓስ፣ ቦዲቲ ከተማ
➫ ስማችሁ ከ C-S የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዋናው ግቢ፣ ወላይታ ሶዶ ከተማ
➫ ስማችሁ ከ T-Z የሆነ የማኅበራዊ ሳይንስ ተማሪዎች ዳውሮ ታርጫ ካምፓስ፣ ታርጫ ከተማ

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦
➫ የ8ኛ ክፍል ሰርተፊኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ የ12ኛ ክፍል ሰርተፍኬት ዋናውና 2 ኮፒ፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣
➫ ብርድ ልብስ፣አንሶላ፣ የትራስ ልብስ እና የስፖርት ትጥቅ፡፡

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#DillaUniversity

በ2018 ዓ.ም በትምህርት ሚኒስቴር ለሪሚዲያል ፕሮግራም ትምህርት ዲላ ዩኒቨርሲቲ የተመደባችሁ ተማሪዎች የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 20 እና 21/2018 ዓ.ም መሆኑን ዩኒቨርሲቲው አሳውቋል፡፡

የምዝገባ ቦታ፦
➫ በተፈጥሮ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ አዳያኣ ግቢ፣
➫ በማኅበራዊ ሳይንስ ዘርፍ የተመደባችሁ ሀሴደላ ግቢ።

ለምዝገባ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ከ9-12ኛ ክፍል ትራንስክሪፕት ዋናውና ኮፒው፣
➫ የ8ኛ እና የ12ኛ ክፍል ሰርትፍኬት ዋናውና ኮፒው፣
➫ መጠኑ 3x4 የሆነ አራት ፎቶግራፍ፣
➫ ብሔራዊ መታወቂያ (ፋይዳ)፣
➫ አንሶላ፣ ብርድ ልብስ እና የትራስ ልብስ።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#MoE

በፌዴራል ልዩ አዳሪ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ለመማር ተወዳድራችሁ ያለፋችሁና በየትምህርት ቤቶቹ የተመደባችሁ የመግቢያ ጊዜ ታህሳስ 11 እና 12/2018 ዓ.ም መሆኑን ትምህርት ሚኒስቴር አሳውቋል።

ወደ ትምህርት ቤታችሁ ስትሔዱ ልትይዟቸው የሚገቡ፦

➫ ለ9ኛ ክፍል የሚያስፈልጉ የመማሪያ ቁሳቁሶች (ደብተር፣ እስክሪብቶ፣ ቦርሳ፣ የስፖርት ትጥቅ፣ ወዘተ)
➫ የመኝታ አልባሳት (አንሶላ እና ብርድ ልብስ)
➫ ስትማሩ ከነበረበት ትምህርት ቤት መሸኛ እና የትምህርት ውጤት

ዩኒፎርም ሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ውል ከያዘበት አቅራቢ ድርጅት በራሳችሁ ወጪ የሚሸፈን መሆኑ ተመላክቷል።

ከተጠቀሰው ቀን ቀድሞ ወይም ዘግይቶ ወደ ትምህርት ቤቶቹ መሔድ እንደማይቻል ተገልጿል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#ExitExam

በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ!

የተፈታኞች የምዝገባ ጊዜ፦
ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም

የመውጫ ፈተናውን የምትፈተኑ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባችሁን በተጠቀሱት ቀናት ማድረግ ይጠበቅባችኋል።

ትክክለኛ መረጃ የምትገኙበት የ 12ኛ

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]
#ExitExam

በጥር ወር 2018 ዓ.ም የሚሰጠውን የከፍተኛ ትምህርት መውጫ ፈተና ለመውሰድ ምዝገባ ያድርጉ!

የተፈታኞች የምዝገባ ጊዜ፦
ከታህሳስ 06-13/2018 ዓ.ም

የመውጫ ፈተናውን የምትፈተኑ የቅድመ-ምረቃ ፕሮግራም ተማሪዎች ምዝገባችሁን በተጠቀሱት ቀናት ማድረግ ይጠበቅባችኋል።

ለበለጠ መረጃ እና
አስተያየት ካለዎት
     👇👇👇
[https://t.me/allethioschool]
[https://t.me/allethioschool]