Mereja መረጃ
3.36K subscribers
1.98K photos
4.09K videos
11 files
9.62K links
Information Desk
+0 000 000 0000
Download Telegram
የጨፍጫፊውና ወራሪው ዐብይ አህመድ ሰራዊትን መንገድ እየመራ በራያ ቆቦ ወረዳ ንፁኋኖችን በገፍ ሲያስገድል የነበረው ባንዳው አያሌው ጌታሁን ከነ አጃቢዎቹ ተገደለ!

ምስራቅ አማራ 102ኛ ኮር 12ኛ ክፍለ ጦር የ2ኛ ሻለቃ አባላቶች ቆቦ ከተማ ሰርገው በመግባት ዛሬ የካቲት 20/2018 ዓ.ም ጧት የፋሽስቱ አገዛዝ ብልፅግና ጋር ወግኖ የአማራ ህዝብ ላይ ዘር ማጥፋት እየፈፀመ የነበረው የራያ ቆቦ ወረዳ የታጠቀው ሃይል ዋና አስተባባሪና የገደመዩ ሊቀመንበር አቶ አያሌው ጌታሁን እና ሁለት ግብረ አበሮቹ ላይ የማያዳግም እርምጃ በመውሰድ ታላቅ ጀብድ ፈፅመዋል::

በቀድሞው ዞብል አምባ በአዲሱ አደረጃጀት በ12ኛ ክፍለ ጦር 2ኛ ሻለቃ አባላቶች ከሁለት ግብረ አበሮቹ ጋር መሃል ቆቦ ከተማ ሰኞ ገበያ ላይ የተደመሰሰው አቶ አያሌው ጌታሁን ባለፉት ሶስት አመታቶች የበርካታ ንፁሃን አማራዎችን ነፍስ የቀጠፈ ሲሆን የፋኖን ፍፁም ትግስትና የምህረት አዋጅም ጭምር ባለመቀበሉ ጊዜውን ጠብቆ በህዝብ ልጆች የማያዳግም እርምጃ ተወስዶበታል::   

ከዚህ ጋር ተያይዞም የራያ ቆቦ ወረዳ ሚሊሻዎች ፋኖ ወዳለበት ቀጠና ሄደው መዋጋት ስለማይችሉ ቆቦ ከተማ ሰኞ ገበያ እና ሌሎች የተለያዩ ቦታዎች ላይ ጦር መሳሪያ ያልታጠቁ ንፁሃኖችን እየረሸኑ ይገኛሉ:: በዚህም እስካሁን ሶስት ንፁሃኖች በጥይት መትተዋል::
©የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ምኒልክ ዕዝ!
ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን ዛሬ የጋራ የመከላከያ የመግባቢያ ስምምነት ሰነድ ተፈራረሙ። ኢትዮጵያ እና አዘርባጃን፣ ኢትዮጵያ በምታዘጋጀው 32ኛው የተመድ የአየር ንብረት ጉባዔ፣ በግብርና፣ በሚዲያ ልማትና ልምድ ልውውጥ፣ በኢንቨስትመንት ማስፋፊያ እና በጸረ-ሙስና ትብብር ዙሪያ ጭምር ስምምነቶችን ተፈራርመዋል። የኢትዮጵያ እና አዘርባጃን አጋርነት፣ ‎ባለፉት ጥቂት ዓመታት በአቪዬሽን ዘርፍ፣ በኢንዱስትሪ ፓርኮች እና በነጻ የንግድ ቀጠናዎች እንዲሁም በኢትዮጵያ ኢንቨስትመንት ሆልዲንግስ እና በአዘርባጃን አቻው መካከል በተደረጉ የኢኮኖሚ ትብብሮች ላይ በመመስረት በየጊዜው እያደገ መምጣቱን ጠቅላይ ሚንስትር ዐቢይ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ገልጸዋል። የትብብር ዘርፎች ለሁለትዮሽ ግንኙነቱ መጠናከር መሠረት መጣላቸውን የገለጡት ዐቢይ፣ ከአዘርባጃን ፕሬዝዳንት ኢልሃም አሊዬቭ ጋር ዛሬ ባደረጉት "ጥልቅ ውይይት" ይህንኑ ግንኙነትና ትብብር ይበልጥ ለማጠናከርና ወደ ላቀ ደረጃ ለማሳደግ መስማማታቸውን አስታውቀዋል።
የትግራይ መምህራን ማኅበር የአፈጻጸም ክስ ተቋረጠ። ማኅበሩ የ20 ወራት የመምህራን ውዝፍ ደሞዝ እንዲከፈል የክልሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሚያዚያ 3 ቀን፤ 2017 ዓ፣ም የሠጠው ትዕዛዝ ተፈፃሚ ባለመደረጉ ባለፈው ጥር 25 የአፈፃፀም አቤቱታ ማቅረቡ ይታወሳል። ከታኅሳስ 1፤ 2015 ዓ፣ም በፊት ያልተከፈለውን የ17 ወራት ውዝፍ የመምህራን ደሞዝ በሚመለከት ጊዜያዊ አስተዳደሩንም ሆነ የፌደራሉን መንግሥት መክሰስ የሚከለክለውና በጌታቸው ረዳ ይመራ የነበረው ጊዜያዊ አስተዳደር ያፀደቀውን ደንብ መሠረት በማድረግ ማኅበሩ ያቀረበው የአፈፃፀም ክስ እንዲቋረጥ የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ጠበቆች የካቲት 6 ቀን አቤቱታ አቅበው ነበር። ፍርድ ቤቱ በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አራት ኪሎ ቅርንጫፍ የተቀመጠው 18 ሚሊዮን ብር ወደ ማኅበሩ የባንክ ሂሳብ እንዲተላለፍ ጥር 25 ቀን ትዕዛዝ ሠጥቶ እንደነበር አይዘነጋም።
ዛሬ መቀሌን ጨምሮ በተለያዩ የትግራይ ከተሞች የፌደሬሽን ምክር ቤት እና ምርጫ ቦርድ ራያ አላማጣንና ሁመራን ጨምሮ በአምስት የምርጫ ክልሎች የሕዝብ ተወካዮች ምርጫ እንዲካሄድ ያሳለፉትን ውሳኔ በመቃወም ሰላማዊ ሰልፎች ተደርገዋል። ሰልፈኞቹ፣ የምርጫ ቦርድንና የፌደሬሽን ምክር ቤትን ውሳኔ የሚቃወሙ እንዲሁም የትግራይ ግዛታዊ አንድነት እንዲከበርና ሰላማዊ ትግሉ እንዲቀጥል የሚጠይቁ መፈክሮችን አስተጋብተዋል። የትግራይ ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዝዳንት ጀኔራል ታደሠ ወረደ፣ የትግራይ የግዛት አንድነት ጥያቄ በፌደሬሽን ምክር ቤት፣ በምርጫ ቦርድ ወይም በፍርድ ቤት ውሳኔ ብቻ ሊፈታ አይችልም በማለት በመቀሌው ሰልፍ ላይ ተናግረዋል። ለትግራይ የግዛት አንድነት እና የተፈናቃዮች መመለስ ጥያቄዎች መፍትሄው ሕገመንግሥታዊ እንደሆነ የጠቀሱት ጀኔራል ታደሠ፣ የፍጥጫ አካሄዶችን መከተል ውጤት አያመጣም ብለዋል። ይህን ችግር አለመፍታት በመላው ኢትዮጵያ "አለመረጋጋት ያስከትላል" በማለትም ጀኔራል ታደሠ አስጠንቅቀዋል።
የወልቃይት ጠገዴ አማራ የማንነት እና ወሠን አስመላሽ ኮሚቴ፣ የፌደራሉ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ራያ አላማጣንና ሑመራን ጨምሮ በአምስት የምርጫ ክልሎች ምርጫ እንዳይካሄድ የጣለውን ጊዜያዊ እገዳ ተከትሎ በስምረት ፓርቲ እና በቦርዱ ክርክር ሂደት ጣልቃ ገብቶ ለመከራከር እንዲፈቀድለት በጠበቃው በኩል ለፍርድ ቤቱ በጻፈው ማመልከቻ ጠየቀ። የኮሚቴው ጠበቃ፣ በክርክር ሂደቱ ኮሚቴው ተካፋይ ባልኾነበት ሁኔታ ፍርድ ቤቱ የሚሠጥ ውሳኔ በሕገመንግሥቱ አንቀጽ 38 ላይ የተደነገገውን "የመምረጥና መመረጥ መብት" እና የኮሚቴውን "ጥቅም" ይነካል በማለት አመልክተዋል። የሑመራ እና የአድረመጽ ምርጫ ክልሎች ከ2013 ዓ፣ም ጀምሮ ከትግራይ ክልል ወጥቶ በወልቃይት ጠገዴ ሰቲት ሑመራ ዞን ሥር ራሱን በራሱ ሲያስተዳድር መቆየቱን የጠቀሠው ማመልከቻው፣ የወልቃይት ጠገዴ የአማራ ማንነት አስመላሽ ኮሚቴም ለአስርት ዓመታት ለወልቃይት ጠገዴ የአማራ ሕዝብ የማንነትና ወሠን ጥያቄ መፍትሄ ለማግኘት ከሕዝብ ውክልና ይዞ በመንቀሳቀስ ላይ ይገኛል ብሏል።
ኢትዮጵያ በናይል ተፋሰስ ላይ "የተናጥል ርምጃ" ከመውሠድ እንድትቆጠብ ግብጽ እና ሱዳን በጋራ ጠየቁ። የግብጹ ጠቅላይ ሚንስትር ሙስጠፋ ማድቡሊ እና የሱዳን የሽግግር ጠቅላይ ሚንስትር ከሚል እድሪስ ትናንት ካይሮ ውስጥ ባደረጉት ውይይት፣ ኢትዮጵያ በናይል ወንዝ ላይ ለምታካሂደው ልማት ሁሉ "አስቀድሞ የማሳወቅ"፣ "የማማከር" እና በታችኞቹ ተፋሰስ አገራት ላይ "ከፍተኛ ጉዳት ያለማድረስ" መርሆዎችን እንድታከብር አሳስበዋል። ሁለቱ ወገኖች የናይል ወንዝ የሁሉም የተፋሰሱ አገራት "የትብብር" እና "የጋራ እድገት" ምንጭ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል። የ1959ኙ የናይል ወንዝ የውሃ ክፍፍል ስምምነታቸው የሠጣቸውን "የውሃ ድርሻ" እና "የማይነጣጠል የውሃ ደኅንነታቸውን" እንደሚያስጠብቁ ያረጋገጡት ሁለቱ ወገኖች፣ በምሥራቅ ናይል ተፋሰስ ላይ የሚካሄዱ የተናጥል ውሳኔዎች "ቀጠናዊ አለመረጋጋት" ይፈጥራሉ በማለት አስጠንቅቀዋል።
የኢራኑ ጠቅላይ መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኔኢ ተገደሉ!

በእስራኤል መገናኛ ብዙኃን ላይ የወጡ ዘገባዎችን ዋቢ በማድረግ ሮይተርስ እንደዘገበው፣ የኢራን ከፍተኛው መሪ አያቶላህ አሊ ካሜኔኢ ህይወት አልፏል።

የሪፖርቱ ምንጮች እንዳመለከቱት፣ የካሜኔኢ አስከሬን መገኘቱ ተነግሯል።
አፋብን ቴወድሮስ እዝ 90 ክላሽ እና 3 ብሬን የማረከበት ውጊያ ተደረገ።

ከዳንግላ እስከ አባድራ፣ ወርቅ ሜዳ እንዲሁም ከዳንግላ እስከ ጭሮ ቢኮሎ የተዘረጋውን የጠላት ኃይል ብትንትኑ ወጧል።

የወገን ኃይል ከምስራቁ ወደ ምዕራቡ የጎጃም ክፍል የሚያደርገውን እንቅስቃሴ ለማስተጓጎል በሚል እቅድ ከዳንግላ ባህርዳር ዋናዉን አስፋልት ለወራት ይዞ የነበረውን የጠላት ጥምር ኃይል (መከላከያ፣ አድማ ብተና እና ፖሊስ) በተቀናጀ መንገድ ለመምታት በወጣው ወታደራዊ እቅድ መሰረት ታላቅ ጀብዱ ተፈፅሟል።

ከጃዊ ወደ ዳንግላ መውጫ ያሉትን ገዥ ቦታወች ካሳች፣ አፄ ዮሃንስ እና ወለቴ ላይ የሰፈረውን ጠላት ዛሬ የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም በጠዋቱ ማጥቃት በተጀመረ በደቂቃወች ውስጥ ብሬን የተማረከበትን ውጊያ በድል ቀጥሏል።

የአፋብን ቴወድሮስ እዝ 105ኛ እና 109ኛ ኮሮች በጋራ ያደረጉት ማጥቃት አድማሱን በማስፋት ከዳንግላ እና መርዓዊ መካከል ጭሮ የተባለ ቦታ ላይ የሰፈረውን አረመኔ ሰራዊት መደምሰስ ችሏል።

የወገን ኃይል ላይ ከፍተኛ መነቃቃት እና ወኔን በፈጠረው በዛሬው የውጊያ ውሎ:-
1) 90 (ዘጠና) የነፍስ ወከፍ መሳሪያወች
2) 3 (ሶስት) ብሬን መትረዬስ
3) 1(አንድ) የዲሽቃ አፈሙዝ ከነ ተተኳሹ
4) 10,000 (አስር ሺ) በላይ የክላሽ እና የብሬን ጥይት
5) በርካታ የእጅ ቦንቦች እና ሌሎች ወታደራዊ ቁሳቁሶችን የወገን ኃይል ማርኮ መታጠቅ ችሏል።

እንዲሁም 20(ሃያ) የመከላከያ አባላት ሲማረኩ ከ100 በላይ የጠላት ሰራዊት ተገድሏል።

ቴዎድሮስ ዕዝ ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ!
Mereja መረጃ
Photo
በአርሲ የ21 ኦርቶዶክሳውያን ተገደሉ፣ ቤተ ክህነቱ የኃዘን መግለጫ አወጣ
======
(የካቲት 20 ቀን 2018 ዓ.ም):- በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ በጃዊ ቀበሌ 21 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ጥቃት ሕይወታቸው መገደላቸው ከፍተኛ ቁጣ ቀስቅሷል።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ በጃዊ ቀበሌ 21 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ጥቃት መገደላቸውን በመግለፅ የመንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ቤተክህነት ከሚመለከተው የፌደራል የመንግሥት አካላት ጋር ተወያይቶ ለችግሩ ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈልግ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ የሶማሌ እና የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ጳጳስ አሳሰበዋል።

ሊቀ ጳጳሱ እያሰለሰ በቀጠለው የምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ችግር የካቲት 19 ለ20 አጥቢያ 21 ኦርቶዶክሳውያን የተገደሉ ሲሆን እነዚህም አንድ ካህን፣ ሁለት ሴቶች እና 18 ወንድ ኦርቶዶክሳውያን መሆናቸው ታውቋል።

ከተገደሉት በተጨማሪ ሁለት ክርስቲያኖች ታግተው ሲወሰዱ፣ ሌሎች ስምንት ወገኖቻችን በጎቤላ ሆስፒታል በሕክምና ላይ እንደሚገኙ በደብዳቤው ተገልጿል።

ይህ በእንዲህ እንዳለ በክርስቲያኖች ላይ በደረሰው ግድያ ጥልቅ ኀዘን እንደተሰማቸው የጠቅላይ ቤተ ክህነት ዋና ሥራ አስኪያጅ ብፁዕ አቡነ ሳዊሮስ ባወጡት መግለጫ ገልጸዋል። የመግለጫው ሙሉ ቃል ከዚህ በታች ሠፍሯል።
====

የኀዘን መግለጫ

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ በጃዊ ቀበሌ 21 ኦርቶዶክሳውያን በታጣቂዎች ሕይወታቸው ማለፉን ተከትሎ የተሰማቸውን ጥልቅ ኀዘን እንገልጻለን።

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ሽርካ ወረዳ በጃዊ ቀበሌ በታጣቂዎች ጥቃት የካቲት 19 ለ20 አጥቢያ አንድ ካህን፣ ሁለት ሴቶች እና 18 ወንድ ኦርቶዶክሳውያን በግፍ መገደላቸውን የሀገረ ስብከቱ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ኤልሳዕ ለጽሕፈት ቤታችን ከጻፉት ደብዳቤ ስንመለከት እጅግ በከፍተኛ ኀዘን ተሰምቶናል።

በመሆኑም በሀገረ ስብከቱ በተለያዩ ጊዜያት በኦርቶዶክሳዊያን ልጆቻችን ላይ የሚፈጸመውና የተፈጸመው ዘግናኝና እጅግ አሳዛኝ ግድያዎች የኦርቶዶክሳዊያን ልጆቻችንን በየትኛውም የአገራችን ክፍል በነጻነት የመኖርና ሃይማኖታዊ ሥርዓታቸውን የመፈጸም መብትን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥታት ጉዳዮን በልዩ ሁኔታ መከታተልና የማያዳግም መፍትሔ የሚያገኝበት መንገድ መፈለግ እንዳለባቸው እያሳሰብን የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤትም የአካባቢው ችግር በመሠረቱ እስከሚፈታ ድረስ የሚያደርገውን ጥረት አጠናክሮ እንደሚቀጥል በዚህ አጋጣሚ ለመግለጽ እንወዳለን።

በመጨረሻም በዚህ ዘግናኝና አሳዛኝ ግድያ ሕይወታቸውን ላጡ ልጆቻችን እግዚአብሔር አምላክ መንግሥተ ሰማያትን እንዲያወርስልን እና ለወዳጅ ዘመዶቻቸውም መጽናናትን እንዲሰጥልን የቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን የዘወትር ጸሎቷ መሆኑን እንገልጻለን።

አባ ሳዊሮስ
የአትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን
መንበረ ፓትርያርክ ጠቅላይ ጽሕፈት ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣
የደቡብ ምዕራብ ሸዋና የሸገር ከተማ አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ
የካቲት 21 ቀን 2018 ዓ.ም
አዲስ አበባ - ኢትዮጵያ
1
Mereja መረጃ
Video
በምሥ/አርሲ ተጨማሪ ሰባት ኦርቶዶክሳውያን ተገደሉ፤ ቀብራቸው ዛሬ ተፈጽሟል
========
⚫️ " ትክክል ነው። የተገደሉት ሰባት ሰዎች ቤተክርስቲያን ግቢ ውስጥ አስከሬናቸው ተገኝቷል። እነዚህ ትናንት ወዲያ ከተገደሉት 21 ምዕመናን ውጭ የተገደሉ ናቸው " (የአርሲ ዞን ሀገረስብከት)
+++++
ከትናንትና ወዲያ "21 ምዕመናን ሲገደሉ፣ ስምንት የደረሱበት አልታወቀም፣ ስምንት ሆስፒታል ገብተዋል፣ ሁለት ታግተዋል" በተባለበት በኦሮሚያ ክልል ምሥራቅ አርሲ ዞን ሽርካ ወረዳ ትናንት ምሽት ተጨማሪ ኦርቶዶክሳውያን ምዕመናን መገደላቸው ታውቋል።

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት፣ እንዲሁም በዞኑ የሽርካ ወረዳ ቤተ ክህነት፣ ከትናንት ወዲያ ግድያ በተፈጸመበት በሽርካ ወረዳ ጃዌ ዋጩ ቀበሌ፣ ትናንት ምሽትም ሌላ ጥቃት ተፈጽሞ ሰባት ምዕመናን በታጣቁት አካላት ተገድለዋል ሲሉ ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ተናግረዋል።

አንድ የሽርካ ወረዳ ቤተክህነት አካል ዛሬ ከሰዓት በሰጡን ቃል፣ " ትናንት ምሽትም ሰባት ሰዎች ተገድለዋል። ቀብራቸው ዛሬ ተፈጽሟል " ብለዋል። በዚህም እስካሁን ተረጋገጠው መረጃ ብቻ በሁለት ቀናት በቀበሌው የተገደሉት ምዕመናን ብዛት 28 ደርሷል።

" ትናንት ማታም በርካታ ቤቶች ተቃጥለዋል። ሲቃጠሉም ነው ያደረሩት። አንድ ቤተክርስቲያን ተዘርፏል" ያሉን የቤተክህነቱ አካል፣ "ቤተክርስቲያን ዙሪያ ያለ ደጀሰላም እና አዳራሽ ተቃጥለዋል " ብለዋል።

"ሥጋቱ አሁንም እንዳለ ነው" ያሉም ሲሆን "ይህ ጥቃት የተሰነዘረበት ቤተ ክርስቲያን ጃዊ አቦ አቡነ ገብረመንፈስ ቅዱስ እንደሚባል ገልጸው "የተወሰነ ኃይል ብቻ ከዞን መጥቷል። ሟቾቹ እንዲቀበሩ ያደረጉት እነርሱ ናቸው። ግን ይቆዩ፣ ይሄዱ ይሆን አይታወቅም " ነው ያሉት።

የአርሲ ዞን ሀገረ ስብከት በበኩሉ "የሚያገኟትን ነገር እየተጠቀሙ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ተጠግተው ሲኖሩ የነበሩ አቃቢት እና ነዳያን በተጠቀሰው ቦታ ትናንት ምሽት በተሰነዘረ ጥቃት ተገድለዋል" ሲል ለቲክቫህ ኢትዮጵያ ገልጿል።

ይህን ያሉት አንድ የሀገረ ስብከቱ አመራር በሰጡን ቃል፣ "ትክክል ነው። የተገደሉት ሰባት ሰዎች ቤተ ክርስቲያን ግቢ ውስጥ አስከሬናቸው ተገኝቷል። እነዚህ ትናንት ወዲያ ከተገደሉት 21 ምዕመናን ውጭ የተገደሉ ናቸው" ብለዋል።

ከሟቾቹ ባሻገር "ደጀ ሰላሙ ሙሉ ለሙሉ ተቃጥሏል። የሰበካ ጉባዔው ጽሕፈት ቤት የስንዴ እህል ነበረው እሱም ወድሟል። ብዙ ቤቶችም ተቃጥለዋል" ሲሉ አክለዋል።
2
የካቲት 23 ቀን 2018 ዓ.ም

130ኛውን የአድዋ ድል አስመልክቶ ከአፋብን የተሰጠ መግለጫ

አድዋ የነፃነት፣ የአንድነት፣ የአይበገሬነት፣ የራስ በቅነት ውጤት ነው። አድዋ ከግዜያዊ ትርፍ ይልቅ የሀገር ክብር እና ነፃነትን፣ ከፍርፋሪ ይልቅ ኩራትን፣ ከአጎብዳጅነት ይልቅ የሞራል ልዕልናን ያስቀደሙ አባቶቻችን የፈፀሙት ድንቃ የታሪክ ክስተት ነው።

አድዋ ኢትዮጵያ በዓለም መድረክ ከተከሰቱ የዓለም ስልጣኔወች መካከል አንዷ መሆኗን ያስመሰከረ፣ በደረጀ የአመራር ጥበብ፣ የጋራ በሆነ ብሔራዊ አጀንዳ ኢትዮጵያዊያን በአንድነት የተሰለፉበት መድረክ ነው።

ሀገር እና ህዝብ መውደድን አውርተው ሳይሆን ሰርተው፣ ተነግሮላቸው ሳይሆን ተግብረውት ያሳዩት አፄ ምኒልክ፣ እቴጌ ጣይቱ እና ሌሎች የዘመኑ ክስተቶች በፅናታቸው፣ በአመራር ጥበባቸው፣ በአስተዋይነታቸው እና በቆራጥነታቸው እብሪተኛ ወራሪወችን በማሸነፍ ለአፍሪካ ኩራት የሆነ ድል፤ የቅኝ ገዥወችን የኃይል ሚዛን ያዛቡበት ታሪካዊ ክስተትም ነው አድዋ።

የኢትዮጵያን ብዝሃነት ከጭፍለቃ ያዳነው የአድዋ ድል ኢትዮጵያ በዓለም አቀፍ የፖለቲካ መድረክ ተሰሚነት ያላት ሀገር እንድትሆን ከማስቻሉም በላይ ለዓለም የዲፕሎማሲ ህግ የጋራ ደህንነት እና በሉዓላዊነት ጣልቃ ያለ መግባትን መርሆወች እንድታበረክት አድርጓል።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ ለመላው ኢትዮጵያዊያን እንኳን ለአድዋ ድል 130 ኛ ዓመት አደረሳችሁ ይላል። 130ኛውን የአድዋ ድል ስናከብር ኢትዮጵያን ከነታሪኳ የሚጠላው የብልፅግና አገዛዝ በአማራ ህዝብ ላይ የከፈተውን የዘር ማጥፋት ጦርነት በመመከት እና በሌሎች ኢትዮጵያዊያን ላይ የደቀነውን አደጋም ለመከላከል የሚያበቃ ተጋድሎ በማድረግ ነው።

ከአድዋ መንፈስ በተቃራኒ የተሰለፈው የአብይ አህመድ ቡድን የሀገሪቱን የመከላከያ ተቋም አመራር ለአረብ ኢምሬቶች በማስረከብ፣ ኢትዮጵያዊያንን በባዕዳን ወንበዴ ሀገራት ድሮን እና ጀት በማስጨፍጨፍ ታሪክ ይቅር የማይለው አሳፋሪ ተግባር በመፈፀም ላይ ይገኛል። ባንዳነትን እና ባዳነትን ከአረመኔነት ጋር የተላበሰውን የብልፅግና አገዛዝ በማስወገድ ሀገራችንን ካልተነገረው የአረብ ኢምሬትስ ቅኝ ግዛት ለማላቀቅ በቁርጠኝነት የምንታገል መሆኑን በዚህ አጋጣሚ እናረጋግጣለን።

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
1
ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ የተሰጠ የኃዘን መግለጫ
===========
‹‹እለ ሐሙ በእንተ ስሙ፤ ምድር ሠናይት ርስቶሙ
ስለስሙ መከራን የተቀበሉት፤ መንግሥተ ሰማያት የእነርሱ ናት››
(ማቴ 5÷51 ፤ ቅዱስ ያሬድ)

ከዚህ በፊት በአርሲ ሀገረ ስብከት በተለያዩ ወረዳዎች የበርካታ ኦርቶዶክሳውያን ወገኖቻችን ሕይወት በመጥፋቱና ከሞት የተረፉትም ከቤት ንብረታቸው ተፈናቅለው ወደ አጎራባች ከተሞች ተሰደው ለረሀብና ለእርዛት ተጋልጠው እየኖሩ መሆኑ ይታወቃል፡፡

ቀደም ሲል በተለያዩ ጊዜያት በደረሰው ሞትና ስደት ምእመናን እያዘነ ባሉበት፣ እኛም ከኃዘናችን ባልተጽናናንበት ሁኔታ ጥቃቱ በአዲስ መልኩ ቀጥሎ የ21 ንጹሐን ወገኖቻችን ሕይወት በግፍ ማለፉን፣ በሕይወት የተረፉትም በታጣቂዎቹ መታገታቸውንና የደረሱበት አለመታወቁን፣ ከ10 የሚበልጡ አባወራዎች ቤትና ንብረት እንደተቃጠለ በመግለጽ ከሀገረ ስብከቱ የቀረበውን ሪፖርት የተመለከትነው ጥልቅ በሆነ ኃዘን ነው፡፡

አገር ሰላም ብለው በሚኖሩት ከምንም ጉዳይ ጋር ንክኪ በሌላቸው ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን ላይ ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላትም ግድያውን በሃይማኖት ስም ይፈጽሙት እንጂ የሃይማኖት ሰዎች ግን አይደሉም፡፡ ዓላማቸውም በሀገራችን ለረዥም ዘመናት ተከባብረው አብረው በኖሩት የሃይማኖት ተቋማት መካከል ግጭትን መፍጠር ነውና የእስልምና ሃይማኖት ተከታዮችና ሕዝበ ክርስቲያኑ በጋራ ልናወግዛቸው ይገባል፡፡

በመሆኑም በወገኖቻችን ላይ የተፈጸመው አሰቃቂ ግድያ በሕዝበ ክርስቲያኑ ዕለታዊ ኑሮ [ላይ] አሉታዊ ተጽዕኖ የሚፈጥር፣ በቅዱሳት መጻሕፍትም ሆነ በሰው ልጅ ሰብአዊ አኗኗር ፈጽሞ ተቀባይነት የሌለው አጸያፊ ድርጊት በመሆኑ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ በጽኑ አውግዞታል፡፡

በምሥራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት በተደጋጋሚ እየተፈጸመ ያለው ሞትና መፈናቀልም ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን በየትኛውም የሀገራችን ክፍል በነጻነት ሠርተው የመኖርና ሥርዓተ አምልኮ የመፈጸም ሕገ መንግሥታዊ መብታቸውን የሚጋፋ በመሆኑ የክልሉና የፌዴራል መንግሥት ጉዳዩን በልዩ ሁኔታ ተከታትለው አፋጣኝ መፍትሔ እንዲሰጡበት ቋሚ ሲኖዶስ በጥብቅ ያሳስባል።

ፍርድን በመሻት የሚጮኸው ስለ ስሙ መከራን የተቀበሉት የንጹሐን ደም ተገቢውን ፍትሕ ይፈልጋልና ይህን አስነዋሪ ድርጊት የፈጸሙት አካላት በሕግ እንዲጠየቁ፣ ወደፊትም ክቡር የሆነው የሰው ልጅ ሕይወት እንዳይጠፋ፣ የዜጎች ሀብትና ንብረት እንዳይወድም መንግሥት የዜጎችን ደኅንነት የማስጠበቅ ተግባሩን እንዲያከናውን ቋሚ ሲኖዶስ ጥሪውን በአጽንኦት ያስተላልፋል።

በደረሰው አደጋ ዙሪያ ተነጋግሮ ተገቢውን ውሳኔ ለማስተላለፍ የተሰበሰበው ቋሚ ሲኖዶስም የአካባቢው ችግር አስተማማኝ በሆነ መንገድ ተፈትቶ ዘላቂ ስላም እስኪገኝ ድረስ በቅዱስ ሲኖዶስ ምልዐተ ጉባኤ የተሰየመው የሀገር ሰላምና የቤተ ክርስቲያን አንድነት ዐቢይ ኮሚቴ ከፌደራልና ከክልሉ መንግሥት ጋር በመነጋገር ሥራውን አጠናክሮ እንዲቀጥልና የሚመለከታቸውም አካላት በየድርሻቸው አስፈላጊውን ትብብር እንዲያደርጉ ቋሚ ሲኖዶስ በክብር ያሳስባል።

የክልሉ መንግሥትና የአካባቢው መስተዳድርም ችግሩን ለመፍታት እያደረገ ያለውን ጥረት አጠናክሮ እንዲቀጥልና ወደፊትም ችግሩ እንዳይደገም ከመሠረቱ መፍታት የሚያስችል እርምጃ እንዲወስድ ቅድስት ቤተ ክርስቲያናችን ትጠይቃለች።

በመጨረሻም ስለ ስሙ በሥጋቸው መከራን በመቀበል ሕይወታቸውን በአጡት ኦርቶዶክሳውያን ልጆቻችን የተሰማንን መሪር ኃዘን እየገለጽን ልዑል እግዚአብሔር ዕረፍተ ነፍስን እንዲሰጥልን፣ ቤተሰቦቻቸውንም እንዲያጽናናልን እንጸልያለን።

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ቋሚ ሲኖዶስ
የካቲት 2018 ዓ/ም
አዲስ አበባ ኢትዮጵያ
2
ሰሞነኛውን ጥቃት ጨምሮ እስካሁን ድረስ፣ በሽርካ ወረዳ በተፈጸሙ ተከታታይ የሆኑ ጥቃቶች ከ164 በላይ ኦርቶዶክሳውያን መገደላቸውን የምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት መረጃ አመልክቷል።

ከተገደሉት በተጨማሪ የደረሱበት ያልታወቁ በርካታ ምእመናን አሉ።

ከሰሞኑን በየካቲት 19፣ 20 እና 22 በደረሰ ጥቃት ብቻ የ31 ሰዎች ሕይወት አልፏል።

ከትላንት በስቲያ በሽርካ ወረዳ ጢጆ ለቡ ቀበሌ የ70 እና 72 ዓመት ዕድሜ ያላቸው ሁለት ወንድማማች አረጋውያን በታጣቂዎች ግድያ ተፈጽሞባቸዋል።

የሁለቱ ወንድማማቾች ሥርዓተ ቀብርም ትላንትና ሰኞ በጋለማ ገብረ ክርስቶስ ቤተ ክርስቲያን ተፈጽሟል።

Via EOTCMK TV
በአርሲ ኦርቶዶክሳውያን ላይ የደረሰውን ጭፍጨፋ አስመልክቶ ከአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ የተሰጠ መግለጫ

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ምስራቅ አርሲ ሀገረ ስብከት ስር በሚገኙ ወረዳወች ነዋሪ የሆኑ የቤተ ክህነቷ ታላላቅ አባቶች፣ ካህናት እና ምዕመናን ላይ በደረሰባቸው ጭፍጨፋ ከፍተኛ ሀዘን የተሰማው መሆኑን ይገልፃል።

ከየካቲት 19 ቀን 2018 ዓ.ም ጀምሮ በተፈፀመው ጭፍጨፋ ከአርባ በላይ ንፁሃን ነፍሶች በብልፅግና አገዛዝ መር የሽብር ተግባር በጥይት ተደብድበው እና በስለት ተወግተው ህይወታቸው አልፏል። በሺወች የሚቆጠሩትም ንብረታቸው ወድሟል፤ ለዘመናት ከኖሩበት ቀያቸው ተሰደዋል።

አርሲን ጨምሮ የእምነት፣ የቋንቋ እና የማንነት ብዝሃነት ባለባቸው አካባቢወች ላይ ኢ-መደበኛ ኃይሎችን በማደራጀት በዜጎች ላይ ሽብር የሚፈፅመው የብልፅግና አገዛዝ መሰል የዘር ማጥፋት ወንጀልን በግልፅ እና በስውር ሲፈፅም ይህ የመጀመሪያዉ አይደለም። በዚህ ዓመት በምስራቅ አርሲ ዞን የሽርካ ወረዳ ብቻ ከ164 በላይ ኦርቶዶክሳውያን በተመሳሳይ መንገድ ተገድለዋል። በርካታ ምዕመናንም የደረሱበት አይታወቅም።

በመሆኑም ይህ ጉዳይ ለህዝብ ጀሮ እንዲደርስ ያደረጉ የሚዲያ አካላትን እና የተፈፀመውን የሽብር ተግባር ያወገዙ የፖለቲካ ኃይሎችን እያመሰገንን፤ ጨፍጫፊውን የብልፅግና ስርዓት ለማስወገድ እየታገላችሁ ያላችሁ የኦሮሞ የፖለቲካ ኃይሎችና ተፅዕኖ ፈጣሪ ፖለቲከኞች መሬት የወረደ ትግል በማድረግ በኦሮሚያ ክልል የሚኖረው አማራ ህዝብ ህልውናው እንዲከበር የበኩላችሁን እንድታደርጉ ወገናዊ ጥሪያችንን እናቀርባለን።

የሀገር ውስጥ እና ዓለም ዓቀፍ ሰብዓዊ መብት ማንነትን እና ሃይማኖትን መሰረት ያደረገውን መንግስት መር ጭፍጨፋ በዝምታ ማየታችሁ ከመተባበር ተለይቶ የማይታይ በመሆኑ የአሁኑን ጨምሮ ከዚህ በፊት የተፈፀሙት የሽብር ተግባራት ተጣርተው በአገዛዙ ላይ ዲፕሎማሲያዊ እርምጃ እንዲወሰድ ግፊት እንድታደርጉ እንጠይቃለን።

በመጨረሻም ይህንን ብሔር እና ኃይማኖትን መሰረት ያደረገ መንግስታዊ ግድያ አዳዲስ ገዳይ ዩኒቶችን በማቋቋም የሚፈፅመው እና የሚያስፈፅመውን የብልፅግና አገዛዝ በማስወገድ ሀገራችንን ከቀውስ እና ከሽብር አገዛዝ እንድናላቅቅ ለመላው ኢትዮጵያዊያን ሁሉ ጥሪ እናቀርባለን!

የአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ
1
የአገዛዙ ወታደሮች በትጉለትና ቡልጋ ግንባር የንፁኋኖችን መኖሪያ ቤት ላይ ቤንዚን በማርከፍከፍ በእሳት ማቃጠላቸው ተሰምቷል።

አረመኔው ስርዓት በትጉለትና ቡልጋ አውራጃ በባሶና ወራና ወረዳ  በመሃል-አምባ ፣ በጭራሮ ደብርና ናስ/አይዞሽ አሞራ ቀበሌዎች ላይ ያለ የሌለ ሃይሉን ሰብስቦ ለመግባት ቢሞክርም በአጼ አምደ ፅዮን ኮር 7ለ70 ክፍለጦር ሲኖ ሻለቃ እና አዲስ ከአባት አርበኞች ወደ መደበኛ አደረጃጀቱን ከፍ ያደገረው ተጉለት ንጉስ ሳህለስላሴ ክፍለጦር ባደረጉት ቅንጅታዊ አሰላለፍ ጠላት ሰብአዊ እና ቁሳዊ ኪሳራ ተከናንቦ ተመልሷል።

ይህ ሽንፈት የደረሰበት ወሮበላ እና ቅጥረኛው የዐብይ ሰራዊት የጥፋት በትሩን በንፁሃን ህይወት ፣ ሃብትና ንብረት ላይ አሳርፎ ከፍተኛ የሆነ ኪሳራ አድርሷል ።

ካደረሰው የጥፋት ተልዕኮ ውስጥም ንፁሐን በጥይት ተመተዋል ተደብድበዋል ። የግለሰብ መኖሪያ ቤት የሆነውን የአቶ ሃይሉ ጥላሁን መኖሪያ ቤትን ቤንዚን በማርከፈከፍ በእሳት አቃጥሏል ፣ የህዝብ መገልገያ ተቋማትን  በከባድ መሳሪ መቶ አቃጥሏል ፣ የህዝብ ማህበራዊ ተቋማትን ቀበሌዎችን ጨምሮ አውድሟል ፣ የግለሰቦችን የቤት እቃ፣ የሱቅ ሸቀጣሸቀጥ ቁልፍ እየሰበሩ ዘርፏል።

በአፋብን ሸዋ ጠቅላይ ግዛት ዕዝ ሚዲያና ኮሚዩኒኬሽን መምሪያ!
በአማራ ፋኖ ብሔራዊ ንቅናቄ (አፋብን) ምኒልክ ዕዝ 101ኛ ኮር የ11ኛ፣ 15ኛ እና 35ኛ ክፍለ ጦር ምስረታ ተጠናቋል።

በአፋብን ምኒልክ ዕዝ የመልሶ ማደራጀት እና የመዋቅር ማሻሻል ተግባራት መካከል አንዱ የሆነው የኮር አደረጃጀት እና የክፍለጦር መልሶ ማደራጀት ይገኝበታል ።

ስለሆነም ከዚህ በፊት የአማራ ፋኖ ብሄራዊ ንቅናቄ /አፋብን/ የምስራቅ አማራ ኮር1 በአሁኑ አደረጃጀት 101ኛ ኮር በሚል መጠሪያ የተሰየመ ሲሆን ፣በኮሩ ውስጥ የሚገኙ ክፍለጦሮች ስያሜን በተመለከተ ፣ጀግናው አሳምነው ክፍለ ጦር ወደ 11ኛ ክፍለ ጦር፣ ነበልባሎቹ ሐውጃኖ ክፍለ ጦር ወደ 15ኛ ክፍለ ጦር እንዲሁም ሽርጥ ለባሽ ኮማንዶዎቹ ወይም ባለሽርጡ ክፍለ ጦር ወደ 35ኛ ክፍለ ጦር በመሠየም የኮሩን መልሶ ማደራጀት ተግባር አጠናቀናል።
ምንጭ፦በአፋብን  ምኒልክ ዕዝ ህዝብ ግንኙነት መምሪያ!
1