#የሳይኮሎጂ_5_ዋና_ጥቅሞች
ይህ ገፅ የተከፈተበት አንዱ ዓላማ የሥነ-ልቦና ሳይንስን በየቀኑ እንድንጠቀምበት ለማድረግ ነው። ምክንያቱም የሥነ-ልቦና ሳይንስ በንድፈ ሀሳብ እና በተግባር የሚሰጥ ትምህርት ስለሆነ በብዙ አይነት መንገዶች ልንጠቀመው እንችላለን፡፡ በሥነ-ልቦና ሳይንስ በርካታ ጥናቶች ስለሚጠኑ እነዚህን ተመርኩዘን ተግባራዊ በማድረግ የተሻለ ሕይወት መኖር እንድንችል ያደርገናል ከሚል እምነት ነው፡፡
እስኪ የሚከተሉትን ዋና ዋና ጥቅሞች እንመልክት፣
#1. ለመነሳሳት
አላማችን ሲጋራ ለማቆም፣ ክብደት ለመቀነስ ወይም አዲስ ቋንቋ ለመማር ሊሆን ይችላል፡፡ ይህን ለማደረግ ያለን(የሚኖረን) መነሳሳት ወሳኝ ነው። ይህንን ለማሳካት እና መነሳሳታችንን ለመጨመር የሚከተሉትን እንድንጠቀም ሥነ-ልቦና ይመክረናል፡፡
*አዲስ (ያልተለመደ) ነገር ፍላጎታችንን እንዲጨምር ያደርጋል፣
*በያዝነው የተወሰነ ዕውቀት ላይ አዲስ ነገርን ለመጨመር እና ለመማር መጣር፣
*ከምንሰራው ሥራ ጋር በቀጥታ የሚገናኝ ግብ ማስቀመጥ፣
*ለሰራንው ጥሩ ሥራ ራሳችንን መሸለም፣
#2. የመሪነት ክህሎትን ለማሻሻል
የአንድ መሥሪያ ቤት ማኔጀር ወይም የሆነ በጎ ፈቃደኛ መሆን ዋናው ቁምነገር አይደለም ነገርግን በተሰማራንበት ቦታ ጥሩ የመሪነት ክህሎት ማዳበር ያስፈልጋል፡፡ ይህም ለቀጣይ ሕይወታችን ጠቃሚ ይሆናል፡፡ ሁሉም ሰው መሪ ሆኖ ላይወለድ ይችላል ነገር ግን የሥነ-ልቦና ጥናቶች እንደሚረጋግጡት የተወሰኑ ነገሮች የመሪነት ክህሎታችንን እንድናሻሽል ያግዙናል ፡፡ ከተደረጉት ጥናቶች አንዱ 3 የመሪነት ዘዴዎች እንዳሉ የሚጠቁመን ነው፡፡
በዚህ የጥናት ግኝት መሠረት በመሪነት ቦታ ላይ ካለን
የሚከተሉትን ጥቂት ነገሮች ተግባራዊ ማድረግ ጠቃሚ ነው፡፡
*ግልጽ የሆነ አቅጣጫ መንደፍ፤ ነገር ግን የተለያዩ ሰዎች ድምጽ እንዲሰጡበት መፍቀድ፣
*ከቡድን አባላት ጋር በመሆን ለሚፈጠሩ ችግሮች የመፍትሔ ሀሳብ ማቅረብ፣
*የሚያነሳሱ ሀሳቦች ላይ ማተኮር፤ ፈጠራን ለመሸለም ፈቃደኛ መሆን
#3. የተሻለ ተግባቢ ለመሆን
ተግባቦት ከምንፅፈው እና ከምንናገረው በላይ ነው፡፡ጥናቶች እንደሚያሳዩት በድምፅ የማይገለፁ ንግግሮች ትልቁን የተግባቦት ቦታ ይይዛሉ፡፡ስለሆነም ጥሩ መልዕክት ለማስተላለፍ ራሳችንን በምልክት (በአካላዊ ቋንቋ)በሚገለፁ የመግባቢያ ችሎታዎች መግለጽ የሌላውንም ምልክት ማንበብ መቻልወሳኝ ነው፡፡
ለዚህም የሚከተሉትን ይጠቀሙ።
*ጥሩ የዓይን ለአይን ትኩረት ይኑርዎት
*ያለ ቃላት የሚገለፁእንቅስቃሴዎችን በሌሎች ላይ ልብ ብለው ለማየት ይሞክሩ።
*የሚያስተላልፉትን መልዕክት የበለጠ ለማገዝ ሲናገሩ የድምፅ ቅላፄዎን ያስተካክሉ።
#4. ሌሎችን በተሻለ ለመረዳት
ቃላትን ሳንጠቀም ተግባቦትን እንደምናደርግ ሁሉ የራስን ስሜት መረዳት እና የሌሎችንም ስሜት መረዳትለማህበራዊ ግንኙነትም ሆነ ለሙያዊ ሕይወት ጠቃሚ ነው፡፡ የስሜት ብልህነት ማለት የራሳችንን እንዲሁም የሌሎችን ስሜት የመረዳት ችሎታ ማለት ነው፡፡ የስሜት ብልህነት ከሌላው ጉብዝና የላቀ መሆኑን የሥነ ልቦና ባለሙያዎች ይስማማሉ።
ይህንን ብልህነት ለማምጣት የሚከተሉትን መንገዶች ይጠቀሙ፡፡
* የራስዎንስሜትና ለስሜትዎ የሚሰጡትን ምላሽ ይፈትሹ
*ስሜትዎንና ልምድዎን ለመገንዘብ ይሞክሩ
*ራስዎን በሌላው ቦታ አድርገው ለማየት ይሞክሩ
#5. የበለጠ ትክክኛ ውሳኔ ለመወሰን
የተለያዩ የሥነ ልቦና ሳይንስ ጥናቶች ለውሳኔ የሚያስፈልጉ መረጃዎችን ይጠቁማሉ፡፡እነዚህን መረጃዎች በመጠቀም በሕይወትዎ የሚጠቅም ውሳኔ ለመወሰን ያስችልዎታል።
ትላልቅ ውሳኔዎችን ሲወስኑ "ባለ 6 ቆብ አስተሳሰብን" መንገዶች ይጠቀሙ ፡- ይህም ማለት ሁኔታውን ከተለያየ አቅጣጫ ማለትም
(ከምክንያታዊ ፣ ከስሜታዊ ፣ ከደመነፍሳዊ ፣ ከአዎንታዊ ፣ ከፈጠራዊ እና ከአሉታዊ)
እይታዎች ይመልከቱ፣
*ውሳኔው ከሚያስከፍለው ዋጋ እና ከሚያስገኘው ትርፍ አንፃር ያመዛዝኑ፣
*ነገሮችን ከፋፍሎ ነጥብ የመስጠት ዘዴን በመጠቀም ለእያንዳንዱ ምን እንደሚያስፈልግ እና ከዛም የሚገኘውን እርካታ ያስሉ፣
Source:- ዘንድሮ Times
@melkam_enaseb

የሶቅራጠስ 3ቱ ጠቃሚ ጥያቄዎች
----------------------------------
አንድ ሠው ሶቅራጠስ ወዳረፈበት እልፍኝ ሄዶ እንዲህ አለው፡፡
‹‹ሶቅራጠስ ወዳጄ፣ እገሌ ስለተባለው ወዳጅህ ዛሬ የሠማሁት ነገር ምንም ደስ አይልም›› አለው፡፡
ሶቅራጦስ መከዳው ላይ እንደተደገፈ መልስ ሳይሰጠው ዝም አለ፡፡
ሠውየውም እንደገና ‹‹ይገርማል ከእርሱ አይጠበቅም፤ በጣም ገርሞኛል›› ሲል ተናገረ፡፡
ሶቅራጦስ፣ ይህ ሠው በቀላሉ እንደማይፋታው ስለተረዳ አንድ መደራደሪያ አቀረበለት፡፡ ‹‹ስለ ወዳጄ ልትነግረኝ የፈለግከውን እንድሠማህ ከፈለግህ ሶስት ጥያቄዎች አሉኝ፤ እነርሱን በቅድሚያ ልትመልስልኝ ይገባል! ይህ ሲሆን ብቻ ነው የምሰማህ›› አለው፡፡
ሠውየው ለወሬው ቢቸኩልም አማራጭ ስላልነበረው በሶቅራጠስ ሀሳብ ተስማማ፡፡
‹‹የመጀመሪያው ጥያቄዬ የእውነት ጥያቄ ነው" አለ ሶቅራጠስ። "ስለወዳጄ የሠማኸው መቶ በመቶ እውነት ነው ወይ?›› ሲል ጠየቀ፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹መቶ በመቶ እንኳን እርግጠኛ መሆን አልችልም›› ሲል እያመነታ መለሰለት፡፡
‹‹በጣም ጥሩ! ልትነግረኝ የፈለግከው እርግጠኛ ያልሆነ ነገር ነው ማለት ነው፡፡ እሺ ሁለተኛው ጥያቄዬ የመልካምነት ነው፡፡ የምትነግረኝ መልካም ነገር ነው ወይ?›› ሲል ሶቅራጠስ አቀረበ ጥያቄውን፡፡
ሠውየውም፡- ‹‹እርሱማ መልካም አይደለም›› አለ ቱግ ብሎ፡፡ የሶቅራጠስ ጥያቄዎች ለማውራት የቋመጠለትን ወሬ እንዳያወራ እንቅፋት መስለው ታዩት።
ሶቅራጦስም ‹‹እውነትነቱ ያልተረጋገጠና መልካም ያልሆነ ነገር ልትነግረኝ ፈልገሃል፡፡ እሺ ሶስተኛውና የመጨረሻው ጥያቄዬን ልጠይቅህ?›› አለው፡፡
ሠውየውም ጥያቄውን ለመስማት ፈጥኖ ‹‹እሺ›› አለ፡፡
ሶቅራጦስ ጠየቀ፤ ‹‹የምትነግረኝ ነገር ለእኔ የሚጠቅመኝ ነገር አለው ወይ?››
‹‹የለም! የለም! መጥቀም እንኳን አይጠቅምህም። ብቻ ብትሰማኝ...›› ብሎ ሰውዬው መቅለስለስ ጀመረ።
ይሄን ጊዜ ሶቅራጦስ ‹‹ታዲያ እንደምን አድርጌ እውነትነቱ ያልተረጋገጠ፤ መልካም ያልሆነ እና ለእኔ ምንም ጥቅም የሌለው ነገር ልንገርህ ስትለኝ እንዴት እሰማሃለሁ። ዞር በል ካጠገቤ አልሰማህም!!›› አለው ይባላል፡፡
ስንቶቻችን ነን ሰው የሚነግረንን ነገር እውነት፣ መልካምና ጠቃሚ መሆኑን አጣርተን የምንሰማው? ስንቶቻችን ነን ለሰው ቁምነገር ብለን ልንናገር ስንል ከሶስቱ አንዱን ማሟላቱን የምናረጋገጠው? እነዚህን የሶቅራጠስ 3ቱ ጥያቄዎችን እንደ ወንፊት ተጠቅመን ማጣራት ብቻ በቂ ነው፡፡
ምንጭ ከ .FB መንደር የተገኘ

#የፍቅር_አይነቶች!
ፍቅር በተለያዩ ሙያዎች አንፃር በተለያየ መንገድ ተተርጉሟል ፡፡ Social psychology (በማህበራዊ ሳይኮሎጂ ) አንዱን ትኩረቱን በዚህ ላይ በማረግ የተለያዩ የፍቅር ትርጉም ፣ አይነት ... ላይ ያተኮሩ ጥናቶችን ያበረክታል ፡፡
በአጠቃላይ ስናየው ወንዶች ከሴቶች ይልቅ ቶሎ በፍቅር ይወድቃሉ ሴቶች ደግሞ ተግባራዊ ጓደኛነትን መሰረት ባደረገ ፍቅር ይሳባሉ ፡፡ ፍቅር በብዙ መንገድ ተተርጉሟል ። ከነዚህ በጥቂቱ
*ለሰው ከዝምድና / ከቅርበት የተነሳ ያለን ጥልቅ ስሜት
*ከፆታዊ ፍላጎት ምክንያት ያለ መሳሳብ ወዘተ ......
___________________
ይህ ብዙ ትርጓሜ ያሉት ፍቅር ስድስት አይነት የፍቅር አይነቶች /ዘይቤዎች / እንዳሉት ማህበራዊ ሳይኮሎጂስቶች ይናገራሉ ፡፡ እነዚህም
1.Eros-ኤሮስ ፦ለኛ ልዩ ውበት ያለውን ሰው በማየት የሚፈቀርበት ዘይቤ ነው ።
በዚህ ዘይቤ ወንዶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ገና እንዳዩ የሚሰማ ጥልቅ የፍቅር ስሜት ነው ፡፡
2.Storge-ስቶርጄ :- ይህ ደግሞ ከጓደኛነት የተነሳ የሚፈቀርበት ዘይቤ ነው ፡፡
በዚህ ዘይቤ ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ይህ ፍቅር የሚመነጨው በመለማመድ ፣ በመቀራረብ ፣ አብሮ ጊዜ በማሳለፍ ነው ፡፡
3. Ludus-ሉደስ ፦ ፍቅርን በጨዋታ መልክ የሚገለፅበት ዘይቤ ነው ፡፡
በዚህ #ዘይቤ ወንዶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው፡፡ ይህ ፍቅር በብዛት በማማለል የሚፈጠር ሲሆን ስራዬ ተብሎ ያልተያዘ ፍቅር ነው ፡፡
4. Mania-ማኒያ ፦ እጅጉን በኔነት ስሜት የሚያፈቅሩና ፍቅራቸውን በብዙ መከራ ራሱ የማይጥሉበት የተወሰነ ጊዜ የተቆጠረበት የፍቅር ግንኙነት ነው ፡፡
በዚህ ዘይቤ #ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው።
5. Pragma- ፕራግማ ፦ ይሄ ደግሞ በምክንያት የተደገፈ ፍቅር ሲሆን በባሕሪ ፣ ባስተሳሰብ የሚመስለንን ሰው የምናፈቅርበት ዘይቤ ነው ፡፡
በዚህ ዘይቤ #ሴቶች የበለጠ አፍቃሪዎች ናቸው።
6. Agape- አጋፔ፦ይህ የፍቅር አይነት ያለአንዳች ምክንያት የምናፈቅረውን ሰው ከራሳችን በላይ የምናስቀምጥበት ነው ፡፡
ይህ የፍቅር ብዙ ጊዜ ከእምነት ጋር ይያያዛል ፡፡ እንደዚህ የሚያፈቅሩ ሰዋች ፍቅረኛዬ ከሚጎዳ እኔ ልጎዳ ፣ ከሚቸገር እኔ ልቸገር የሚሉ ናቸው ፡፡
ምንጭ ፦ አዲስ አበባ ዩኒቨርስቲ
ማስተማሪያ መሳሪያዎች

7 ነገሮችን አስታውስ!
1. ከሕልምህ እንጂ ከሰዎች ኋላ አትሂድ፣
2. ራስህን አፍቅርና ሌላው ይከተልሃል፣
3. የማድነቅ ስሜትህን ፍጹም አትተዉ፣
4. ከምታውቀው በላይ ትችላለህ፣
5. በሕይወት መፀፀት የለም፤ ትምህርት መውሰድ እንጂ፣
6. ብቸኛው ወሳኝ ራስህ ነህ፣
7. ሕይወት ከመቅፅበት ትጠፋለች።
ስለሆነም ሕይወትን ኑር!
@melkam_enaseb
1. ከሕልምህ እንጂ ከሰዎች ኋላ አትሂድ፣
2. ራስህን አፍቅርና ሌላው ይከተልሃል፣
3. የማድነቅ ስሜትህን ፍጹም አትተዉ፣
4. ከምታውቀው በላይ ትችላለህ፣
5. በሕይወት መፀፀት የለም፤ ትምህርት መውሰድ እንጂ፣
6. ብቸኛው ወሳኝ ራስህ ነህ፣
7. ሕይወት ከመቅፅበት ትጠፋለች።
ስለሆነም ሕይወትን ኑር!
@melkam_enaseb
10 የሕይወት መርሆዎች!
================
ታላቁ ሰው ማህተመ ጋንዲ "ነገ እንደምትሞት አድርገህ ኑር፤ ዘላለም እንደምትኖር አድርገህ ተማር" እንዳለው የሚከተሉት ለደስተኛ ሕይወት ቁልፍ የሆኑ ነገሮች ቀርበዋል፤ ያንብቧቸው። ይጠቀሙበታል። ሕይወትዎን ለመቀየር የመነሻ እርምጃ ሊሆንዎት ይችላል።
1. ራስህን ከሌላ ሰው ጋር አታፎካክር፦
ሁላችንም እንደ አሻራችን ሁሉ ባህሪያችን እና ፍላጎታችንም በጣም ይለያያል። ደስታን ከሚያጠፉ ምክንያቶች አንደኛው ራስን ከሌላ ሰው ጋር ማፎካከር ነው። አሳ ደስታዋን እንደ ወፍ በሰማይ ልፈልግ ብትል፤ ወፍ ደግሞ እንደ አሳ በውሃ ውስጥ ልፈልግ ብትል፤ ሁለቱም ሳይደሰቱ ይቀራሉ። ስለዚህ ደስታህን በራስህ መለኪያ ለካው። አንተ በሌሎች ስትቀና ሌሎችም ባንተ እንደሚቀኑ እወቅ።
2. አትኩሮትህን በሌለህ ነገር ላይ ሳይሆን ባለህ ነገር ላይ አድርገው፦
የጎደለህ ምንድን ነው? ያለህስ ምንድን ነው? ብታመዛዝነው የቱ ይበልጣል? ብዙዎቻችን ሃሳብ እና አትኩሮቶቻችን በሌለን ነገር ላይ ስለሆነ፤ ያለንን ነገር ሳንጠቀምበት እንቀራለን። ደስተኛ ለመሆን ሁሉም ነገር ሊኖርህ አይገባም። በደንብ ካስተዋልከው አሁን ያለህ ነገር ደስተኛ ለመሆን በቂ ነው። ምክንያቱም አንተ ያለህን የሚመኙ ምስኪኖች ብዙ ናቸውና።
3. ራስህን ሁን፦
በዚህ ምድር ላይ ሌላውን ለመምሰል እንደመሞከር ከባድ ነገር ምን አለ ሌላውን ለመምሰል ስትሞክር፤ የምትጣላው ከሰው ጋር ሳይሆን ከገዛ እራስህ ጋር ነው። እናም እራስህን አታስቀይመው፤ እውነተኛ ወዳጆችህ አንተን ባንተነትህ ይቀበሉሃል…..ከምንም በላይ እራስህን በመሆን ከራስህ ጋር ሰላም ፍጠር።
4. ሁሉን ለማስደሰት አትሞክር፦
አንድ ነገር ስታደርግ ሰዎች ደስ እንዲላቸው ብለህ ሳይሆን ትክክለኛ እና አንተ ያመንክበት ነገር ስለሆነ ይሁን። በዚህ ምድር ላይ ምንም አይነት ጻዲቅ ሰው ብትሆን እንኳን ሁሉንም ሰዎች ማስደሰት አትችልም። ስለዚህ የምታደርጋቸው ነገሮች ከህሊናህ ጋር እስከተስማሙ ድረስ በቂ ነው። ለሰው ሳይሆን ለህሊናህ ኑር።
5. የውሸት ደስታን አትፈልግ፦
በውሸት ደስታና በእውነተኛ ደስታ መካከል ትልቅ ልዩነት አለ። የውሸት ደስታ፤ ጊዜያዊ በሆኑና ከውጪ በምናገኛቸው ነገሮች የሚመጣ ነው። ሃዘናችንን ለጊዜው የሚጋርድ ጊዜያዊ ማስታገሻ፤ እውነተኛ ደስታ ግን ሃሳባችን፤ አላማችን፤ ምግባራችን ሲጣመር የሚፈጠር ስሜት ነው። ሃዘን እና መከራችንን ሳንደብቅ የምንጽናናበት ደስታ።
6. ማንን እንደምታገኝ አታውቅምና ለሁሉም ሰው ቅን ሁን፦
ከመንገደኛው አንስቶ እስከ ቅርብ ወዳጆቻችን ድረስ፤ ሰዎች በኛ ላይ ትልቅ አስተዋጽኦ አላቸው። በህይወትህ የምታሰፍራቸው ነጥቦች ሁሉ በኋላ ላይ ተያይዘው መስመር መስራታቸው አይቀርም። የተናቀው ድንጋይ የማዕዘን ራስ ይሆናል ተብሏልና ሰዎችን አትናቅ። በየትኛውም አጋጣሚ ለምታገኛቸው ሰዎች ትክክለኛውን ነገር አድርግ።
7. መለወጥ የማትችላቸውን ነገሮች ተቀበላቸው፦
ብዙ ሰዎች ጭንቀት ውስጥ የሚገቡት መለወጥ የማይችሏቸውን ነገሮች ለመለወጥ ስለሚጥሩ ነው። ምንም እንኳን በህይወታችን ውስጥ አብዛኛው ነገሮች ላይ ስልጣን ቢኖረንም፤ መለወጥ የማንችላቸው ነገሮች አሉ። ከአቅምህ በላይ በሆኑ ነገሮች እራስህን አታስጨንቅ። ከአቅምህ በላይ የሆነውን ነገር ለአምላክህ ስጠው። መንፈሳዊነትህን በማጠንከር አሸንፍ።
8. የራስህ እውነተኛ ወዳጅ ሁን፦
ምንም እንኳን ሰዎች በአንተ ቢያምኑብህም እና ቢመኩብህም፤ አንተ በገዛ እራስህ ካላመንክ ህይወትህ ምንም ዋጋ የለውም። ከሰዎች ፍቅር በላይ የራስህ ፍቅር ወሳኝ ነው። የሚገርመው ሰዎች እራሱ ሊወዱህ የሚችሉት አንተ በመጀመሪያ እራስህን መውደድ ስትችል ነው። ራስህን በደንብ ተንከባከበው። ሲያጠፋ ይቅር በለው፤ ሲደክም አበርታው፤ ሲሳካለት አሞካሸው። ላንተ ካንተ የቀረበ ማን አለህና?
9. መልካም አስብ መልካም ተናገር፦
በመጀመሪያ ሰው ያስተሳሰቡ ውጤት መሆኑን እመን፤ አሁን የምንኖረው ህይወት የአመለካከታችን እና የአስተሳሰባችን ውጤት ነው። ይህን ካወቅህ አስተሳሰብህን በጥንቃቄ አጢነው። ደስተኛ ለመሆን የተመረጠ አስተሳሰብ ሊኖርህ ይገባል።
10. ለምን እንደምትኖር እወቅ፦
ሕይወት ማለት የተሰጠህን ኃላፊነት ለመጨረስ የተሰጠችህ ጊዜ ናት። ኃላፊነትህ ምንድን ነው? በህይወትህ ማድረግ የምፈልገው ነገር ምንድን ነው? መልሱን ካወቅክ ለሕይወት ያለህ አመለካከት ይለወጣል።

#ከቆመ_ሰዓት_ትሻላለህ!!!
“ሁል ጊዜ እንደተሳሳትኩ ነው … አንድ ቀን ትክክል ሆኜ አላውቅም … አመለካከቴ የተሳሳተ ነው … ብቃት የለኝም ... ሰዎች ወደፊት ሲገሰግሱ እኔ ግን ኋላ ቀርቻለሁ … አልቻልኩበትም … ዓላማየን አላውቀውም … እና የመሳሰሉት ስሜቶች ብዙ ሰዎችን የሚያጠቁ ስሜቶች ናቸው፡፡ እነዚህ ስሜቶች በተገቢው መንገድ ካልተያዙ ማንነትህን የማኮሰስና ወደኋላ የማስቀረት አቅም አላቸው፡፡
እንደ እውነቱ ከሆነ እነዚህ ስሜቶች ሁሉም ሰው የሚጋራቸው ስሜቶች ናቸው፡፡ ሆኖም፣ እንደ መንቂያ ደወል ከተጠቀምክባቸው መልካም ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ እነዚህን ስሜቶች ለተስፋ መቁረጥ ከተጠቀምክባቸው ወደ ኋላ ይጎትቱሃል፡፡
በብልሽት ምክንያት ልክ ከጠዋቱ 2 ሰዓት ላይ የቆመ (አናሎግ) ሰዓትን ተመልከተው፡፡ ይህ ሰዓት ምንም እንኳን የቆመና ትክክል ያልሆነ ሰዓት ቢሆንም፣ እንደ እውነቱ ከሆነ ይህ የቆመ ሰዓት በቀን ሁለት ጊዜ ትክክል ይሆናል - ከጠዋቱ ሁለት ሰዓት ላይ እና ከምሽቱ ሁለት ሰዓት ላይ፡፡ አየህ የተበላሸ ሰዓት እንኳን በቀን ሁለት ጊዜ ትክክል ይሆናል፡፡ አንተ ደግሞ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!
የቆመ ሰዓት በቀን ሁለት ጊዜ ትክክል ከሆነ፣ ምንም ያህል ስህተት የሰራህ ሰው ብትሆን፣ ምንም ያህል ወደፊት መራመድ እንዳቃተህ ብታስብ፣ ምንም ያህል የመሻሻል ነገር እንዳልታየብህ ብታምን፣ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!! የዛሬ አስር አመት፣ የዛሬ አምስት አመት፣ የዛሬ ሶስት አመት፣ የዛሬ አመት . . . የነበርክበትን አስብ፡፡ በትንሹም ቢሆን አሁን ከዚያ ትሻላለህ፡፡
ምናልባት፣ “እኔ ባለሁበት የቆምኩ ሰው ነኝ” ልትል ትችላል፡፡ ምናልባትም፣ “እኔ ባለፉት አመታት ከነበርኩበት ደረጃ የወረደ ሁኔታ ላይ ነው ያለሁት” በማለት ታስብ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ከዚህ ሁኔታ እንኳን የተማርከውን ትምህርት አስበው፡፡ ሁኔታህ አለመሻሻሉ እየሰጠህ ያለውን የመንቂያ ደውል አስታውሰው፡፡ ማሰብ፣ ራስን መገምገም፣ ያለፈውንና የወደፊቱን ማስላት የመቻልህን ብቃት አስበው፡፡
ከዚህ አመለካከት ለመውጣት ከፈለክ፣ ከተሳሳትከው፣ ከማትችለው፣ ካልተሳካውና ካልሆነው አትነሳ፡፡ ምንም እንኳን ትንሽ ነው ብለህ ብታስብም፣ ከትክክለኛነትህ፣ ከተሳካልህና ከሆነልህ ነገር ተነሳ፡፡ በዚህ ስሜት ጫና ውስጥ ሆነህ ዘንግተኸው ነው እንጂ፣ ሌሎች ማድረግ የቻሏቸው ለአንተ ግን ያቃቱህ በርካታ ነገሮች የመኖራቸውን ያህል፣ ሌሎች ሰዎች ያቃታቸው አንተ ግን ማድረግ የምትችላቸው በርካታ ነገሮች እንዳሉ አትርሳ፡፡
ያም ሆነ ይህ፣ ከቆመ ሰዓት ትሻላለህ!!!
ምንጭ: ዶ/ር ኢዮብ

#ሁለቱ_የደስታ_ገጽታዎች
“ሌሎችን ለመርዳት በሚኖረን ፈቃደኝነት ውስጥ ከግል ኃዘንና ድብርት የሚያወጣን ደስታ መለማመድ እንችላል” - Gerald Jampolsky
የሰው ዘር ሁሉ ለማግኘት ከሚጦዝላቸው ፍላጎቶቹ አንዱ ደስታን የማግኘት ፍላጎት ነው፡፡ ሆኖም፣ ብዙ ሰዎች ደስታን የሚያገናኙት ለራሳቸው ከሚያደርጉት ነገር ጋር ብቻ ነው፡፡ ስለዚህም፣ የጣፈጠውን ስለበሉ፣ ለአይን የሚያምረውን ቁሳቁስ ስለገዙ፣ ሰው ሁሉ የሚመኘውን ማሕበራዊ መሰላል ስለወጡና አንዳንዴም፣ “ካልቀመስከኝና ካላሸተትከኝ እረፍት አልሰጥህም” ያላቸውን የሱስ ጥማት ስላረኩ ብቻ ደስታ የሚያገኙ ይመስላቸዋል፡፡
ደስታ የሚገኘው የፈለግነውን ስላገኘን፣ ስለነካንና ስለቀመስን ብቻ ነው ብሎ ማሰብ የሞኞች ሃሳብ ነው፡፡ በተቃራኒ ግን ሌላውን በማገልገል፣ ያለንን በማካፈልና ከራስ አልፎ ሌላውን በመንካት ውስጥ የሚገኝ ደስታ አለ፡፡ ስለዚህም፣ አንዱ የደስታ ምንጭ ለራሳችን ከምናደርገው ነገር የሚቀዳ ሲሆን፣ ሌላኛው የደስታ ምንጭ ደግሞ ለሌሎች ከምናደርገው ነገር የሚቀዳ ነው፡፡ የመጀመሪያው ጊዜያዊ ነው፣ ሁለተኛው ማለቂያ የሌለውና ዘላቂ ነው፡፡
ለራሳችን ከምናደርጋቸው ነገሮች የሚቀዳው የደስታ ምንጭ ውስን ነው፡፡ ምክንያቱም የፈለግነውን ነገር ያላገኘን ጊዜ ደስታው ስለሚርቀንና እንዲያውም የድብርትን ተጽእኖ ይዞብን ስለሚመጣ ነው፡፡ በተቃራኒው ግን ለሰዎች ከምናደርጋቸው መልካም ነገሮች የሚቀዳው የደስታ ምንጭ ማለቂያ የለውም፡፡ ሁል ጊዜ ልንደግፋቸው የምንችላቸው ሰዎች በዙሪያችን ስላሉ ምንጩ ማለቂያ የለውም፡፡
“በዚህ ዓለም ላይ የሌላውን ሸክም ተሸክሞ ዋጋ-ቢስ ስሜት ሊሰማው የሚችል ሰው ተፈልጎ አይገኝም” ይለናል አንዱ መካሪ (Charles Dickens)፡፡
እንግዲህ የደስታ አንዱ ገጽታ ለራሳችን በምናደርገው ዙሪያ ሲሆን፣ ከዚያ የላቀው ገጽታው ግን የሌላውን ኃዘን በመካፈል ውስጥ የሚገኘውን ደስታ የማጣጣም ሁኔታ ነው፡፡ ይህንን ሁኔታ፣ “በኃዘን ውስጥ የሚገኝ ደስታ” ልንለው እንችላለን፡፡ አዎን፣ በኃዘን ውስጥ ደስታ ተሰውሮ ይገኛል፤ ለሌሎች ሰዎች በማዘን፣ የሌሎች ሰዎችን ኃዘን ከልብ በመገንዘብና አብሮ በማዘን … በዚያ ውስጥ ማለቂያ የሌለው ደስታ አለ፡፡ ይህ ምስጢር የገባቸው ግን ጠቢባን ብቻ ናቸው፡፡
ለትክክለኛ ነገር በማዘንና ከሚያዝኑ ጋር በማዘን ውስጥ ይህ ነው የማይባል ደስታ አለ፡፡ በማግኘት ደስታ የመኖሩን ያህል፣ ለሰው ጥቅም ሲባል በማጣትም ደስታ አለ፡፡ ሁለቱንም ኩላሊቱን ላጣና ለሞት ለተቃረበ ወንድሟ አንዱን ኩላሊቷን በመስጠት ውስጥ ያለውን ደስታ ያጣጣመችን እህት ማሰብ ትችላልህ፡፡ በዚህ ህብረተሰብ ውስጥ የአንተስ ድርሻ ምንድን ነው?
አንድ ነገር አትርሳ፣ ስትሰጥ ከእጅህ ባወጣኸው መጠን ሳይሆን እጅህ ላይ ባስቀረኸው መጠን ነው የምትመዘነው፡፡ አንድ ሚሊየን ብር ያለው ሰውና አስር ሺህ ብር ያለው ሰው እያንዳንዳቸው ዘጠኝ ሺህ ብር ለድሆች ቢሰጡ የትኛው ብዙ የሰጠ ይመስልሃል?
“ስጥ፣ ስትሰጥ ግን እስከሚያምህ ድረስ ስጥ” - Mother Teresa
(ዶ/ር እዮብ ማሞ)

🔹የሥነ-ልቦና ሳይንስ ትምህርት እንዴትና በማን ተጀመረ?
ሥነ-ልቦና ከሰው ልጅ ፍጥረት ጀምሮ (በ Evolution ለሚያምኑ ደግሞ አሁን ያለው የሰዉ ዘር Evolv ካረገበት ጊዜ ጀምሮ) በተለያየ የህይወት መስተጋብር ሲጠና ሲገለጥ ሲታወቅ የመጣ ሙያ ነዉ፡፡ ይሁን እንጂ ሥነ-ልቦና እራሱን እንደቻለ ትምህርት/ ሳይንስ መጠናት የጀመረው ከ 19ነኛው ክፍለ ዘመን በኀላ ነው፡፡ Wilhelm Wundt የሚባል ሰው በጀርመን ሀገር 1879 የመጀመሪያውን የሥነ ልቡና የሙከራ (ምርምር) ተቋም በ Leipzig ዩኒቨርስቲ ከፈተ፡፡ ይህ በታሪክ የመጀመሪያው የሥነልቡና ምርምር ቤተሙከራ ለመሆን በቅቷል፡፡ በዚህም ሳቢያ አቶ Wundt አብዛኛውን ጊዜ የሥነ-ልቦና አባት በመባል ሊጠራ ችሏል ለዘመናዊ ሥነ-ልቦና ጥናት መጀመርም መሰረት ሆኗል፡፡
ከዚህ በፊት የፈረንሳዩ ፈላስፋ ሬኒ ዴካርት (1596 -1650) በስነልቦና ሙያ እድገትና ሙያውን ከፍልስፍና ትምህርት ራሱን ችሎ እንዲወጣ ብዙ ሚና የተጫወተ ነው፡፡ በ Interactive dualism Theory (በበይነግንኙነታዊ ሁለትዮሽ ፅንሰ ሀሳቡ) የሰውን ልጅን አዕምሮ/ አስተሳሰብ ከ ስጋው በመነጠል ያላቸውን መስተጋብር ለማጥናት የሞከረ ፈላስፋ ነው፡፡ በ 17 ክፍለ ዘመንም ጆን ሎክ እና ቶማስ ሆብስ ለዚህ ሙያ እድገት ከፍልስፍናው ጎን ብዙ ሚና ተጫውተዋል፡፡
🔹የሥነ-ልቦና ታሪካዊ አመጣጥ፦
ሥነ-ልቦና በታሪክ ዉስጥ በፍልስፍና ስር የሚጠና ሙያ የነበረ ሲሆን ትርጓሜውም ከጊዜ ወደጊዜ እየሰፋና እየተስተካከለ እራሱን ችሎ ወቷል፡፡ የሥነ-ልቦና ትምህርት እድገት በታሪክ ውስጥ በአራት ተከፍሎ ይታያል። እነርሱም፦
1. Ancient Greekperiod/ በጥንታዊ የግሪክ ክፍለጊዜያት
2. per-modern period/ ቅድመ ዘመናዊነት ጊዜ
3. Modern Period/ በዘመናዊነት ጊዜ
4. Current Status/ አሁን ያለንበት (ድህረ ስልጣኔ እንዲሁም ተሻጋሪያዊ ስልጣኔ) ዘመን
1. በጥንታዊ የግሪክ ክፍለጊዜያት የግሪክ ፈላስፎች ለዕድገቱ ብዙ ሚና አበርክተዋል፡፡ ከነዚህም በጉልህ ተጠቃሾቹ ሶቅራጥስ፣ ፕሌቶና አርስቶትል ናቸው፡፡ በዚህ ጊዜ ሥነልቦና የሚጠናው ከነፍስ/ አዕምሮ አንፃር ብቻ ነበረ፡፡ እነዚህ ፈላስፎችም በስራቸው የሚያነሱት ስለ አዕምሮ እንጂ ስለ ባህሪ አልነበረም፡፡
2. ቅድመ ስልጣኔ ዘመን በፊት፦ ሥነልቦና ከፍልስፍና ተነጥሎ ለብቻው የወጣው በዚህ 1800ዋቹ ጊዜ ነበር። ለዚህ ትልቅ ሚና ያበረከቱት Wilhelm Wundt and William James ናቸው፡፡
3. በዘመናዊነት ጊዜ፦ በዚህ ዘመን ብዙ የስነባህሪ ተመራማሪዎች የመጡበት ጊዜ ሲሆን ሥነ ልቦናን ከአዕምሮ/ ነፍስ በተለይ ከባህሪ አንፃር ለማየት የተሞከረበት ጊዜ ነው፡፡
4. አሁን ያለንበት ጊዜ፦ ከዚህ በፊት የነበሩት የሥነ ልቦና ትርጓሜዎች ሙሉ ያልነበሩ ሲሆኑ በዚህ ጊዜ ግን ሥነ ልቦና የአዕምሮ አሰራር ሂደትንና ባህሪን አጠቃሎ የሚያጠና ሳይንስ ተብሎ ተተርጉሟል፡፡
🔹በሥነልቦና ስር ያሉ ዋና ዋና ሙያዎች (Sub fields)፦
ዘርፉ እራሱን ችሎ እንደ ሳይንስ ከወጣ ገና 140 አመት በመሆኑና በዚህ ጊዜም በጣም ብዙ በስሩ ያሉ የሙያ አይነቶች እየታወቁና እየተጠኑ በመሆናቸው ትክክለኛ ቁጥሩ አሻሚ ነው፡፡ ይሁን እንጂ በተለያዩ የሥነ ልቦና ተቋሟች ውስጥ ያሉ ሰዎች ያሉት ሙያዎች በዚህ ጊዜ ከ 100 እንደሚያልፉ ይነገራሉ፡፡ ካሉት ሙያዎች ውስጥ በጣም የሚታወቁትን ጥቂቶች እንይ፦
1. Clinical Psychology (ክሊኒካል ሳይኮሎጂ)፦ ከቀላል እስከ አስከፊ የአዕምሮ፣ የስሜትና የባህሪይ ህመሞች፣ ችግሮችን የሚያጠናና የሚያክም ነው፡፡
2. Counseling Psychology፦ የሰው ልጅ የሚገጥሙትን የቀን ተቀን ግላዊ፣ ማህበራዊ ችግሮች ለመፍታት የሚሞክር ነው፡፡ ሰዎችም ችግርን ለመቋቋምና ለመፍታት እንዲረዳቸው ያላቸውን ጥንካሬ እንዲያውቁ ይረዳል፡፡
3. Cognitive and Perceptual Psychology፦ የሰዉን የመረዳት፣ የማሰብ፣ የመገንዘብና የማስታወስ ሁኔታ የሚያጠና ነው፡፡ በዚሀሸ ስር አዕምሮአችን እንዴት ዕውነታን እንደሚረዳ? ሰዎች ነገሮችን እንዴት እንደሚማሩ? ሰዎች ቋንቋን እንዴት እንደሚረዱና እንደሚያወጡ? ሰዎች እንዴት እንደሚወስኑ፣ እንደሚፈርዱ እምክንያታዊ ሀሳብ እንደሚያመነጩ ያጠናል፡፡
4. Neuropsychologists and Behavioral Neuropsychologists፦ በአዕምሮና በባህሪይ መካከል ስላለው ግንኙነትና የአሰራር ዘዴ ያጠናል፡፡
5. Health Psychology፦ እንዴት ስነህይወት፣ ሥነልቦናና ማህበራዊ ጉዳዮች የሰው ልጅ ጤናን እንደሚያጠቁ ያጠናል፡፡
6. Developmental Psychology፦ የሰው ልጅ በሕይወት ዘመኑ የሚያሳልፋቸውን የተለያዩ የእድገት ደረጃዎች ያጠናል፡፡
7. Social Psychology፦ የሰው ልጅ እርስ በርሱ በሚያረገው ማህበራዊ ግንኙነትና መስተጋብር ያሚደርስበትን ተፅዕኖዎች ያጠናል፡፡
8. School & Educational psychology፦ ከመማር ማስተማር ጋር የተያያዙ እያንዳንዳቸው ጉዳዮች የሚጠኑበት ነው፡፡
9.Industrial- Organizational Psychology፦ በአንድ የስራ ቦታ ላይ የሚገኙ የሰዎችን ግንኙነት፣ የሥራ ተዛምዶና ባህሪይ የሚያጠና ነው፡፡

''ገበየሁ ቢሞት ተተካ ባልቻ
መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ!''
የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኀተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው።
ይህ ድል ያደረግንበት ቀን ነው።
እንኳን አደረሳችሁ!
@melkam_enaseb
መድፍ አገላባጭ ብቻ ለብቻ!''
የአድዋ ድል የኢትዮጵያ ብሔራዊ ክብር ማኀተም፤ የጥቁር ህዝቦች የነፃነት ተጋድሎ ቀንዲል ነው።
ይህ ድል ያደረግንበት ቀን ነው።
እንኳን አደረሳችሁ!
@melkam_enaseb
Psychology (ሥነ-ልቦና) ምንድነው?
ሥነ-ልቦና በታሪኩ ውስጥ የተለያየ ትርጓሜ ይዞ የመጣ ሲሆን አሁን በደረሰበት የዕድገት ደረጃ ግን አብዛኞቹ ተመራማሪዎች የሚስማሙበት ትርጉም ይህን ይመስላል፡፡
ሳይኮሎጂ ከሁለት የግሪክ ቃላት ሳይኪ እና ሎጎስ (Psyche & logos) የሚሉ ቃላቶች የተወሰደ ነው፡፡
- (Psych) ሳይኪ| Mind (ነፍስ፣ አዕምሮ፣ መንፈስ) ሲሆን
- (Logos) ሎጎስ| Disclosure (ገለፃ /ጥናት) ማለት ነዉ፡፡
በዚህም መሰረት ሥነ-ልቦና ማለት፦
ስለ ባህሪይ እና የአዕምሮ አሰራር ሂደት የሚያጠና ሳይንስ ነው፡፡
ባህሪይ ስንል ማናቸውም የምናረጋቸዉና በአይን የሚታዩ ነገሮች ሲሆኑ የአዕምሮ አሰራር ሂደት ደግሞ በአይን የማይታይ ግን በተግባር የሚገለፅ ነዉ፡፡
ሳይንስ ስንል ሳይንስ የሚያልፍባቸውን ሂደቶች ስለሚያልፍ ነዉ እነርሱም (Emperical/ በሙከራ የተረጋገጠና መመልከት የምንችለው, Objective / ከግል ስሜት ጋር ያልተያያዘና ከገሀዱ አለም ጋር የተገናኘ, Systematic/ በስርአት የተቀረፀና የሚሰራ, Replicable/ ውጤቱ ሆነ ሂደቱ በሌላ ሰው መደገም የሚችል) ናቸው፡፡
ሌላው ሥነ-ልቦና ማህበራዊ ወይስ ተፈጥሮአዊ ሳይንስ ነው የሚለው ጥያቄ ነው፡፡ ምንም እንኳን ባለንበት ሀገር ኢትዮጵያ ውስጥ በሁሉም የትምህርት ተቋም እንደማህበራዊ ሳይንስ የሚታይና የሚሰጥ ሲሆን ባብዛኞቹ ባደጉት ሀገራት ግን ከህክምና ትምህርት ክፍል ስር የሚሰጥ በተፈጥሮአዊ ሳይንስ ስር ያለ ትምህርት ነው፡፡
ሥነ-ልቦና አዕምሮን አያጠናም ይልቁንስ ስለ አዕምሮ አሰራር ሂደት እንጂ። (ስለ አዕምሮ የሚያጠኑት ኒውሮሎጂስት እና ሳይካትሪስቶች ናቸዉ፡፡)
የሥነ-ልቦና ትምህርት ዋና አላማ/ ግብ (goal) አራት ናቸው እነርሱም፦
1.ባህሪን መግለፅ (Describe)
2.ባህሪን ማብራራት (Explain)
3.ባህሪን መተንበይ (predict)
4.ባህሪን መምራት/ መቆጣጠር (control)
ሥነ-ልቦና (Psychology ) መገለጫ ምልክት (Symbol) ያለዉ ሲሆን ምልክቱ የግሪኩ 23ኛ ካፒታል ሊተር Ψ ሳይ (Psi) ነዉ፡፡ የ ሳይ ምልክት የተገለበጠ "ሐ" ይመስላል፡፡ በዚህ ምልክት ' Ψ ' ላይ ያሉት ሶስት አምዶች አብዛኛዎቹ ጠቢባን በነዚህ ሶስት ነገሮች ይመስሏቸዋል፦
1. ነፍስን #Soul
2. ሀሳብን(አዕምሮ) #Mind
3. መንፈስን #Spirit

#የሰዎችን_ስሜት_አትካድ
ሰዎች በተለያዩ ጊዜአት ስሜትን የሚጎዳ ገጠመኞችን ይጋፈጣሉ፡፡ ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ በሚያልፉበት ጊዜ የእነሱን ልምምድና ስሜት ልክ በእነሱ ሁኔታ ሊያየው የሚችል ሌላ ሰው ተፈልጎ አይገኝም፡፡ አመጣጣቸውና አመለካከታቸው ለችግሩ የተለየ “ኬሚስትሪ” ስለሚሰጠው ማለት ነው፡፡
ሰዎች በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ሲያልፉ ከምናደርግላቸው ትልቅ ውለታ አንዱ በስሜታቸው ላይ ከመፍረድ ይልቅ ስሜታቸውን በመረዳት አብሮ መቆየትና ማገዝ ነው፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች የተሰማቸውን ስሜት የሚገነዘብላቸውና የሚያደምጣቸው እንጂ ሃሳብ የሚያዘንብላቸው ሰው አይፈልጉም፡፡ የራሱን ችግር ሳይፈታ በሌላው ሰው ሁኔታ ላይ ሃሳብ ሰጪው ብዙ ነውና፡፡
ለምሳሌ፣ አንድ ሰው በጣም አዝኖ ሲያለቅስ ብታገኘው፣ “ምን ያስለቅስሃል? ይህ ነገር አሁን የሚያስለቅስ ነገር ነው?” ከማለት ይልቅ፤ “ስለደረሰብህ ሁኔታ በጣም አዝናለሁ፣ ላግዝህ የምችለው ነገር አለኝ?” ማለት የበለጠ የስሜትና የማህበራዊ ብልህነት ነው፡፡ ይህ አይነቱ አቀራረብ የበሳሎችና በስሜት ብልህነት የመጠቁ ሰዎች አቀራረብ ነው፡፡
የማዘንም ሆነ የማልቀስ ስሜት የማንነታችን አካል የመሆኑ ምክንያት እነዚህ ስሜቶች ሲመጡ በቅጡ እንድንገልጣቸውና ከውስጣችን በማስተንፈስ እንድናወጣቸው ነው፡፡ ለዚህ ነው ሰዎች የሚያልፉበትን ስሜት ጊዜ ወስደው እንዲያልፉበት በመፍቀድ ለማገዝ ራሳችንን ማቅረብ ይገባናል የምንለው፡፡
የሰዎችን ስሜት አለመካድ ማለት . . .
• በስሜታቸው ላይ ባለመፍረድ እንዲገልጹት መፍቀድ
• በስሜታዊነታቸው መሰረት ማንነታቸው ላይ ስም አለመለጠፍ
• ስሜታቸውን ለመገንዘብና ለመጋራት መሞከር
• በስሜታዊነታቸው አቅጣጫ እኛ የመሰለንን ድጋፍ ሳይሆን እነሱ የሚፈልጉትን ድጋፍ ለመለገስ መሞከር
ምንጭ
(“የስሜት ብልህነት” ከተሰኘው የዶ/ር ኢዮብ ማሞ መጽሐፍ የተወሰደ፡፡)

#መቄዶንያ
እንደ ቢንያም በለጠ በጎ መሆን መታደል ነው!
ለገቢ ማሰባሰብያው እርዳታ ለማድረግ 8161 ላይ OK ብለው ይላኩ። ቃል ለመግባት ደግሞ 0970-707070፣ 0940-404040 ወይም 0989-898989 ላይ ይደውሉ።

#Depression_ድብርት/መደበት
ድብርት/መደበት የበሃሪ መለወጥ የጤና እክል ሲሆን ይህም ሚቆይ የሃዘን ስሜትን እና ለነገሮች ፍላጎት ማጣትን ያስከትላል።ይህም ስሜታችንን እና በባህሪያችን ላይ ለዉጥ ያስከትላል።እነዚህን በመከተል የተለያዩ በአካላችን ላይ እና በዉስጣዊ ስሜታችን ላይ ችግሮችን ያስከትላል።የቀን ተቀን ስራችን ለመከወን በራሱ ልንቸገር እንችላለን አንዳንዴም ለመኖር ያለን ጉጉት ይቀንሳል ወይም ለመኖር ብቁ አደለንም የሚል አስተሳሰብ ጭንቅላታችን ይንሰራራል።ለዚህም የጤና እክል ረዘም ላለ ጊዜ ሚወሰድ መድሀኒት ይፈልጋል አብዛኛው በድብርት የተጠቁ ሰዎች መድሀኒት ሲወስዱ ትልቅ ለዉጥ ያሳያል።
#ምልክቶች
ድብርት በህይወቶ ላይ አንዴ ብቻ አጋጥሞት ሊሆን ይችላል ነገር ግን በተለመደ አብዛኛው ሰው ላይ ተደጋጋሚ የሆነ መደበት ያጋጥመዋል/ይጠቃል።በነዚህም ወቅት የተለያዩ ምልክቶች ቀን በቀን እና በቀን ዉስጥም ለብዙ ጊዜ ይኖራሉ ከነዚህም መሀል፦
#በሀዘን ስሜት መወረር ወይም ማልቀስ/ሆደ ባሻ መሆን ፤ባዶነት መሰማት ወይም ተስፋ መቁረጥ
#በንዴት መገንፈል/ቱግ ማለት፤ቁጡ መሆን፤ በጣም በትንሽ ነገር መፍራት እና ተስፋ መቁረጥ
#ለነገሮች ፍላጎት መቀነስ ወይም ደስተኛ አለመሆን ነገር ግን እነዛ ነገሮች ከዚ በፊት ሚያስደስቱን ሊሆኑ ይችላሉ ለምሳሌ ወሲብ፤ስፖርት እና የመሳሰሉት
#የእንቅልፍ መዛባት ይህም ምንም እንቅልፍ አለመተኛት ወይም ከመጠን በላይ መተኛት
#ድክምክም ማለት እና ጉልበት ማጣት
#የምግብ ፍላጎት መቀነስ=>ክብደት መቀነስ ወይም የመግብ ፍላጎታችን መጨመር=>ዉፍረት
#በስጋት ስሜት መወረር፤የስሜት መረበሽ ወይም መቁነጥነጥ /እረፍት ማጣት
#የማሰብ ችሎታ መቀነስ ፤ሲናገሩ ቀስ ብሎ ማውራት(አብዛኛውን ጊዜ ምንሰማቸው ሲደግሙልን ወይም በጣም ተጠግተናቸው ነው) እና በዝግታ መንቀሳቀስ
#ምንም የማልረባ ነኝ ብሎ ማሰብ ወይም ባለፉ ነገሮች ላይ የጥፋተኛነት ስሜት መሰማት ወይም ከልክ ያለፈ እራስን መውቀስ
#የማሰብ ችሎታ መቀነስ ፤ጥሞና ዉስጥ ለመግባት መቸገር፤ የተዛባ ፍርድ መፍረድ/ፍርደ ገምድል መሆን እና ነገሮችን ለማስታወስ መቸገር
#ተደጋጋሚ የሆነ እራስን ስለ ማጥፋት ማሰብ ወይም መሞከር
#በምንም ነገር ሊብራራ ያልቻለ የወገብ ህመም ወይም እራስምታት
በአብዛንኛው በድብርት የተጠቁ ሰዎች ላይ እነዚህም ምልክቶች የሚታዩ እና የሚስተዋሉ የሆኑ የእለት-ተእለት እንቅስቃሴዎችን ሊያስተጓጉሉ እና ሊያሰናክሉ ይችላሉ፦ለምሳሌ ስራ፤ ትምህርት እና ከማህበረሰቡ ጋር ያለንን ግንኙነት ሊጎዱ/ሊያበላሹ ይችላሉ።

ዶ/ር ካትሪን ሀምሊን
ላለፉት 61 አመታት ኢትዮጵያ ውስጥ ባደረጉት ከፍተኛ እንቅስቃሴ 60,000 ገደማ ኢትዮጵያውያን የፊስቱላ ህክምና ተደርጎላቸዋል።
እንደ እሳቸው መልካም ሰዎችን ያብዛልን !
ነፍስ ይማር

#ጠቃሚ_መረጃ
"""""""""""""""""""
እባኮ ፈፅሞ እዳይዋሱ
ኤርፎን የጆሮ ማዳመጫ ማዋስም ሆነ መዋስ ለጆሮ ኢንፌክሽን ሊያጋልጥ እንደሚችል ያውቃሉ?
ያዋሱት ሰው የጆሮ ኢንፌክሽን ቢኖርበትም ባይኖርበትም የሁላችንም የጆሮ ኩክ የተለያየ የባክቴሪያ አይነት ሳላለው ለሌላ ጆሮ ላይስማማ እና ኢንፌክሽን ሊያስከትል ይችላል::
ኤርፎን የጆሮ ማዳመጫ ከጆሮዋችን ስናወጣው በአይን የማይታዩ ጀርሞችን ከጆሮዋችን ይዞ ይወጣል
ከማንኛውም ሰው ኤርፎን የጆሮ ማዳመጫ ስንዋስ ማድረግ ያለብን ነገር፦ የተዋስነውን ወይም ያዋስነውን የማዳመጫ ኤርፎን በንፁህ ጨርቅ ወይም ሶፍት ፀረ ባክቴሪያ ወይም አልኮል በማድረግ ማፅዳት ይኖርብናል።
ይህ መረጃ ለሌላ ሰው እንዲጠቅም
(share) ያድርጉ።

#በኮሮና_ቫይረስ_ዙርያ_ያሉ_የተሳሳቱ_ግንዛቤዎች!
በዶ/ር መንግስቱ አሰፋ
1.ኮሮና ቫይረስ የሚያጠቃው አረጋዊያንን ብቻ ነው>> ስሕተት
የኮሮና ቫይረስ ዘርን፣ ቀለምን፣ ዕድሜን ሳይለይ ማንንም ይይዛል። ነገር ግን አረጋዊያንን ይበልጥ ለከፋ ጉዳት ያደርሳል የሚል አጠቃላይ ግምት ብቻ ነው ያለው።
በተጨማሪም የሳምባ፣ የጉበት፣ የኩላሊት፣ የልብ ሕመሞች፣ ካንሰር፣ ኤድስ፣ ስኳር በሽታ ወዘተ ያለባቸውን ሕሙማን በከፍተኛ ሁኔታ ይጎዳል። ወጣቶችም አናመልጥም፣ እንጠንቀቅ።
2. የቤት እንስሳት ኮሮናቫይረስን ያሰራጫሉ>> ስሕተት
እስካሁን ባለው ሁኔታ ከውሻ፣ ድመት ወዘተ ወደ ሰው ተላልፎ የተከሰተ የዚህ በሽታ ሪፖርት የለም። ሆኖም ግን ከነሱ ጋርም ሆነ ተቀምጠን ከተነሣንም፣ የእጃችንን ሁሉንም ክፍል በሳሙና ለ20 ሰኮንድ መታጠብ ለጥንቃቄ ያግዛል።
3. የተለያዩ ባሕላዊ መድኃኒቶች፣ ቫይታሚኖች ከቫይረሱ ያድናሉ>> ስሕተት (በጥንቃቄ)
እስካሁን በሳይንስ የተረጋገጠ መድኃኒትም፣ ክትባትም የለም። በቅርብ የምናይ ይሆናል። ቫይታሚንና የተለያዩ የሰውነት የመከላከል አቅምን የሚጨምሩ ምግቦችን መውሰድ ጥሩ ነው። ግን በሽታው እንዳይዘን አያደርጉንም።
4. መድኃኒቶች (antibiotics) ከኮሮና ቫይረስ በሽታ ያድናሉ>> ስሕተት
በኮሮና ቫይረስ በሽታ የታመሙ ሰዎች አንታይባዮቲክስ የሚወስዱት ተጨማሪ ኢንፌክሺን ሲኖራቸው ነው። አንታይባዮቲክስ ከኮረናቫይረስ እንደሚያድን ሳይንስ አላረጋገጠም።
5. Surgical Mask መጠቀም ከኮሮናቫይረስ በበቂ ሁኔታ ይከላከላል>> ስሕተት
የፊትና የአፍ ማስክ መጠቀም ያለበት በሽታው ያለበትና የጤና ባለሙያ ነው። ሌላ ሰው (N95 የሚባለውን ማስክ ጨምሮ) ባይጠቀም ይመረጣል። ምክንያት:
- disposable surgical masks በአየር የሚመጡ ጎጂ ኢንፌክሺኖችን ለመከላከል ፊትን ሙሉ በሙሉ አይሸፍኑም፣ ሰለዚህ በቀላሉ እንጠቃለን።
- በተደጋጋሚ እያወለቅን፣ እየነካካነው ለረጅም ጊዜ በተለይ ጸሐያማ ወይም ሙቀት ያለበት ቦታ ከተጠቀምነው ይበልጥ ለኢንፌክሽኑ ያጋልጡናል እንጂ አያድኑንም።
ዋናው!👇
እጃችሁን ታጠቡ፣ ማኅበራዊ መራራቅን ተግባራዊ አድርጉ፣ ሰው የተሰበሰበት ቦታ አትሂዱ፣ እጅ መታጠቢያ ቦታ ለመታጠብ አትሰለፉ፣ አትጋፉ፣ የበሽታው ምልክት ያለበት ሰው ቶሎ የሕክምና አገልግሎትን ያግኝ።
Via...Elias meseret