MSI Ethiopia Reproductive Choices
3.09K subscribers
581 photos
34 videos
2 files
166 links
Marie Stopes Ethiopia provides high-quality family planning, maternal and child health, and HIV/AIDS service across Ethiopia.

☎️ 8044

🗨 @MariestopesContactCenter

🌐 www.mariestopes.org.et
Download Telegram
ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ለጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል የማህበረሰብ አቀፍ መድሃኒት ቤት ከመቶ ሺህ ብር በላይ የሚገመት የህክምና ቁሳቁስና የመድሃኒት ድጋፍ አደረገ።

መድሃኒት ቤቱ በዛሬ እለት ተመርቆ ለዉጪና ለሆስፒታሉ ታካሚዎች አገልግሎት መስጠት ጀምሯል።

ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በእናቶች ጤና ላይ ትኩረት በማድረግ የህክምና አገልግሎት ለሚሰጠዉ ለጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል የማህበሰብ አቀፍ መድሃኒት ቤት በእርግዝና ወቅት የሚወሰድ 300 መልቲ ቫይታሚን ብልቃጥ  (ቲን) እና 50 የእርግዝና መመርመሪያ ቁስ እንዲሁም የመድሃኒት ቤት ማስታወቂያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።

ይህም የህክምና ቁሳቁስ ድጋፍ በገንዘብ ሲተመን ከመቶ ሺህ ብር በላይ መሆኑን የማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ የሽያጭና የማስታወቂያ ባለሙያ ከሆኑት ከወ/ሪት ሶስና ተሾመ ለመረዳት ተችሏል።

መድሃኒት ቤቱን መርቀዉ ያስከፈቱት የሆስፒታሉ ዋና ሾል አስፈፃሚ ዶ/ር ታሪኩ ደሬሳ ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ በስነተዋልዶና በእናቶች ጤና አጠባበቅ ላይ ለጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል ከፍተኛ የሆነ  ድጋፍ እያደረገ መሆኑን ተናግረዋል። ለአብነት ያህልም ከዚህ ቀደም የተከታታይ የባለሙያ ማጎልበቻ ማዕከላቸዉን (ሲፒዲ) ሲያስገነቡ ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ያደረገዉን ድጋፍ አንስተዋል።

ስነተዋልዶና የእናቶች ጤና አጠባበቅ ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ እና የጋንዲ መታሰቢያ ሆስፒታል የትኩረት ማዕከሎች እንደሆኑ ይታወቃል።
የኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የተለያዩ ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎች የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ሪፕሮዳክቲቭ ቾይዝስ የአናቶችና የህፃናት ህክምና ልዩ ማዕከልን ጎበኙ፤ ከድርጅቱ የስራ ሀላፊዎች ጋርም ውጤታማ ውይይት አካሂደዋል። 

ለቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢዎቹ ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ለህብረተሰቡ እየሰጠ ያለዉን አገልግሎት ማብራሪያ የሰጡት የድርጅቱ ካንትሪ ዳሬክተር ዶ/ር አበበ ሽብሩ የአፍላ ወጣቶች የስነ ተዋልዶ ጤናና የቤተሰብ እቅድ ብሎም ሌሎች የጤና አገልግሎቶችን  ጨምሮ የእናቶችና የህፃናት ጤና ተደራሽነትን ለማስፋትና ለማዘመን ከፍተኛ የሆነ ሾል እየሰራ መሆኑን አስረድተዋል።

ዶ/ር አበበ አያይዘዉም ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ሪፕሮዳክቲቭ ቾይዝስ የሲቪክ ማህበራት የራሳቸዉን አቅም በመፍጠር ህብረተሰቡን ማገልገል እንደሚኖርባቸዉ የተቀመጠዉ የመንግስት የትኩረት አቅጣጫን እያሳካ ስለመሆኑም ገለፃ ሰተዋል።

በኢፌዴሪ የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የማህበራዊ ጉዳይ ቋሚ ኮሜቴ ሰብሳቢ  ክብርት ወርቀሰሙ ማሞ በበኩላቸው የጎተራ ማዕከልን ጨምሮ በተለያዩ የሀገሪቱ ክፍሎች ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ በስነተዋልዶና በእናቶች ጤና ዙሪያ እያከናወነ የሚገኘዉ አንኳር ተግባራትን አወድሰዋል።

የክብርት ወርቀሰሙን ሀሳብ የተጋሩት የህዝብ ተወካዮች ም/ቤት ጽ/ቤት ሃላፊ ዶ/ር ምስራቅ መኮንን በበኩላቸዉ ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ በሰሜኑ የሀገራችን ክፍል በነበረዉ ጦርነት ወቅት ጭምር ለእናቶች ጤና አገልግሎቱን ሳያቋርጥ በመስጠቱ  መደሰታቸዉን ተናግረዋል።

የም/ቤቱ ቋሚ ኮሚቴ ተሰብሳቢዎች የማዕከሉን አገልግሎት ተዟዙሮ ከማየት በተጨማሪ በዛሬዉ ዕለት ለወለዱ እናቶች ስጦታዎችን አበርክተዋል።
ኤም ኤስ ኢትዮጵያ ሪፕሮዳክቲቭ ቾይዝስ አመታዊውን የኢትዮጵያ የማህፀንና ፅንስ ሃኪሞች ማህበር ጠቅላላ ጉባኤ ላይ በአጋርነት ተሳተፈ፡፡

በማህበሩ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ የተሳተፉት የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ካንትሪ ዳሬክተር ዶ/ር አበበ ሽብሩ የመሪዎች ድርሻ ለሴቶች ዉሳኔ ሰጪነት መጎልበት ከፍተኛ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት በመረዳት በዚሁ አግባብ መንቀሳቅስ ይኖርባቸዋል ሲሉ አስገንዝበዋል፡፡

በጠቅላላ ጉባኤዉ ላይ ለማህበሩ መልካም ምኞታቸውን ያስተላለፉት ዶ/ር አበበ ኢ ሶ ግ ላለፉት በርካታ አመታት ከኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ጋር በእናቶችና በህፃናት ጤና እንዲሁም በስነ ተዋልዶ እና በቤተሰብ እቅድ ዙሪያ በመስራቱ እንደ ሀገር ጉልህ የሆኑ ለዉጦች ሊታዩ ችለዋል ሲሉም አመላክተዋል።

በዚህ ውጤት ውስጥም የኢ ሶ ግ አጋርነት እጅግ ወሳኝ እንደነበረ መረዳት ይቻላል ሲሉም ተናግረዋል። ዶ/ር አበበ አያይዘዉም በብዙ ምክንያቶች መጪዉ ጊዜ ተገማች ባለመሆኑ መሪዎች ከዛሬዋ እለት ጀምሮ የሴቶችን ዉሳኔ ሰጪነት ከወትሮዉ በላቀ መልኩ በማጉላት መሬት ላይ የወረደ ስራ መስራት ይጠበቅባቸዉዋልም ብለዋል።

የማህፀንና የፅንስ ሃኪሞች ማህበር ለኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ስትራቴጂክ አጋር መሆኑንና ከዚህ ቀደምም ለማህበሩ መሰል የአጋርነት ድጋፎችን ሲያደርግ እንደነበር ያነሱት ደግሞ የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ የሶሻል ማርኬቲንግ ቴክኒካል ማናጀር ዮርዳኖስ አያሌው በበኩላቸው የኤም ኤ ስ አይ እና የ የኢትዮጵያ የማህፀንና ፅንስ ሃኪሞች ማህበር አጋርነት ለበርካታ አመታት የዘለቀ ከመሆኑ ባሻገርም እንደዚህ አይነት መድረኮችም ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ለተጠቃሚዎች የሚያቀርባቸው የቤተሰብ እቅድ አማራጮች ላይ ግንዛቤ ለመፍጠር መልካም አጋጣሚ ይሆናሉ ሲሉም አስረድተዋል፡፡
Channel name was changed to ÂŤMSI Ethiopia Reproductive ChoicesÂť
ጉግል ካርታን በመጠቀም ያግኙን: LOCATE US

MSI Ethiopia Reproductive Choices/ማሪ ስቶፕስ ኢንተርናሽናል ኢትዮጵያ ሃና ማርያም ሜዲካል ሴንተር

ለሃና ማርያም አና በዙሪያው የሚገኙ ደንበኞቻችን ተደራሽ ለማድረግ በቅርቡ አገልግሎት የምንጀምር መሆኑን ስናበስር በታላቅ ደስታ ነው፡፡ በላቀ አገልግሎት እናንተን ለማስተናገድ በዝግጅት ላይ እንገኛለን። ተጨማሪ ምቾት ይጠብቁ!!!


ለተጨማሪ መረጃ 8044 ላይ በነጻ ይደውሉልን!

#በየትኛውምእድሜሽላይ #ForEveryStageOfWoman #MarieStopesEth #MSIE
የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር ዲኤታ ክብርት ፍሬህይወት አበበ የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ሪፕሮዳክቲቭ ቾይዝስ የአገልግሎት ማዕከልን ጎበኙ።

የጤና ሚኒስቴር ጤና አስተዳደርና የሃብት ግብት ዘርፍ ሚኒስትር ዲኤታ የሆኑት ክብርት ፍሬህይወት አበበ የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ሪፕሮዳክቲቭ ቾይዝስ የጎተራ የእናቶችና የህፃናት ህክምና ልዩ ማዕከልን ጎበኙ።

ክብርት ሚንስትሯ በማዕከሉ ተዘዋውረዉ በተመለከቱት ጥራት ያለዉ የአገልግሎት አሰጣጥና ተቋሙ በሀገር ደረጃ እያከናወነ ለሚገኘዉ አንኳር ተግባራት በተደረገላቸዉ ገለፃ መደሰታቸዉን ገልፀዋል።

የማዕከሉን አገልግሎት በተመለከተ ለሚኒስትር ዲኤታዋ ማብራሪያ የሰጡት የጎተራ ማዕከል ስራ አስኪያጁ አቶ አማኑኤል ታደሰ ማዕከሉ ጥራት ያለዉ የእናቶችና የህፃናት የጤና አገልግሎት በተመጣጣኝ ዋጋ እየሰጠ መሆኑን አስረድተዋል።

ከጎተራ ማዕከል ጉብኝት በኋላ በካንትሪ ዳሬክተሩ ዶ/ር አበበ ሽብሩ ለሚንስትሯ የሲቪክ ማህበረሰብ ድርጅቶች በገቢ ማስገኛ እንዲሰማሩ የሚያስችለዉን የመንግስት ህግን ተግባራዊ በማድረግ ረገድ ኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ አርያ ሊሆን የሚችል ተቋም መሆኑን ለሚንስትሯ አስረድተዋል። በዚህም ክብርት ፍሬህይወት መደሰታቸዉንና በቀጣይም የጤና ሚኒስቴር ከኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ጋር ያለዉን ጠንካራ የስራ ግንኙነት ለማስቀጠል እንደሚሰሩ ተናግረዋል።
የኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ሪፕሮዳክቲቭ ቾይዝስ የሽያጭ ክፍል አመታዊን የስራ ግምገማ አደረገ። የተሻለ አፈፃፀም ላሳዩ የሽያጭ ማዕከላትም የዕዉቅና ሰርተፍኬት አበርክቷል።

ለሁለት ቀናት በቢሾፍቱ አፍሪካ አሻም ሆቴል በተካሄደዉ መርሃ ግብር፣ ከአመታዊዉ የስራ ግምገማ በተጨማሪ ለሽያጭ ባለሙያዎች የ2 ቀናት የሙያ ማጎልበቻ ስልጠና ተሰቷል።

በስልጠናዉና በአመታዊዉ የስራ ግምገማ ላይ ከሽያጭ ባለሙያዎች በተጨማሪ የተለያዩ የአከባቢ ማናጀሮችና የዋናዉ ድጋፍ ሰጪ መ/ቤት የሚመለከታቸው የስራ ክፍል ባለሙያዎች ተሳትፈዋል።

አመታዊዉ አጠቃላይ የሽያጭ ስራን በተመለከተ ከክፍሉ ሪፖርት ቀርቦ ከተሳታፊዎች ዉይይት ተካሂዶበታል። ከተሳታፊዎች ለተነሱ ጥያቄዎችም የገቢ ማመንጫ ዘርፍ ዳሬክተርን ጨምሮ የክፍሉ ማናጀሮች ምላሽና ማብራሪያ ሰተዋል።

በሌላ በኩል፣ በሽያጭ ክፍሉ የማህበራዊ ግብይት ቴክኒካል ማናጀር የሆኑት ወ/ሮ ዮርዳኖስ አያሌዉ ስልጠናዉ የሽያጭ ባለሙያዎችን የአሻሻጥ ክህሎት ከማሳደግና የቴክኖሎጂ አጠቃቀም ክፍተትን በመሙላት ረገድ ከፍተኛ አስተዋህፆ እንደሚያበረክት አስረድተዋል።

በ2023 የተሻለ አፈፃፀም ያሳዩ የሽያጭ ማዕከላት የእውቅና የምስክር ወረቀት ከኤም ኤስ አይ ኢትዮጵያ ሪፕሮዳክቲቭ ቾይዝስ ካንትሪ ዳሬክተር ዶ/ር አበበ ሽብሩ እና ከዳሬክተሩ ዶ/ር ማኖጅ ተቀብለዋል።