||ማራኪ ♡ ልቦች||
160K subscribers
69 photos
35 videos
2 files
56 links
ልብን እንድታፈቅር ላደረገ ጌታ♡

♡ምስጋና የተጋባ ይሁን!!!

አሚን🙏

@Best_islamic_quote
@SIBRAT_VIBE
@Ustaz_Nuru_Turki
@Ethio_Islamic_TikTok
@muslims_couples
@Ethio_OLD_NESHIDA
@Hamza_Picture
@Ethio_Nikabi_girl
@ADIS_NASHIDA

ለአስተያየታችሁ👉 @Hamza_Official
Download Telegram
Mohamed Tarek - Eid Takb...
@MARAKI_LIBOCH
😍 ኢድ ሙባረክ 😍 ማራኪ ነሺዳ 😍
እንኳን ለ1445 የኢድ አል ፊጥር በአል በሰላም አደረሳችሁ! 🥰

#ተክቢራህ 😍 #ተክቢራህ 😍 #ተክቢራህ

Mohamed Tarek - Eid Takbeer 2023 | محمد طارق - تكبيرات العيد

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ዒድ_ሙባረክ_አዲስ_የነሺዳ_ክሊፕ_Eid_Mubarek_Nasheed_Ali_Amin_عيد_مبارك_
ከረመዷን ተማርኩኝ!

በሳምንት ሰኞና ሀሙስ መፆም ቀላል ነገር  እንደሆነ ተማርኩኝ፣

•በረመዷን ለሱህር ስነሳ ከረመዷን በፊት ለፈጅር መነሳትም ቀላል ነገር እንደሆነ ተማርኩኝ፣

•ቁርአን በወር ውስጥ አንዴ አይደለም ብዙ ጊዜ ማኽተም ቀላል እንደሆነ ተማርኩኝ፣

•ከራሴ ጋር የሚኖር ጊዜ አውዳሚ ጠላቴ ስልኬ መሆኑን አወቅኩኝ፣

•የለይል ሰላት መስገድ ብዙ ሰአት እንደ ማይፈጅ ተማርኩኝ…
ብቻ አልሐምዱ ሊላህ ብዙ ነገር ተማርኩኝ!

እናንተስ ከረመዷን ኮርስ ምን ተማራችሁ?

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
#ኒቃቧን #አወለቀች‼️

(ልብ የሚነካ አስተማሪ ታሪክ)

⇛የሃይስኩል ተማሪ እያለች ነበር ኒቃብ የለበሠችው፡፡ ያውም በአንድ ቀን ደዕዋ፡፡ ቀኑና ጊዜውን ለማስታወስ በትዝታ ወደኋላ ርቃ ሄደች፡፡ ዕለቱ ጁሙዓ ነበር፡፡ ከሶላት በኋላ ስለ ሒጃብ ደዕዋ ያደረገው ኡስታዝ ድምፁን ከፍ አድርጎ ይናገራል፤ በተለይ ሴቶች ጆሮ እንዲሠጡት ይወተውታል ‹ሴት ልጅ ዐውራ ናት፣ ፈፅሞ ፎቷ መታየት የለባትም፣ ፊት ያልተሸፈነ ምን ሊሸፈን!፣ ኒቃብ ግዴታ ነው፤ ሴቶቻችን አላህን ፍሩ፣ ኒቃብ ልበሱ፤ ወላጆችም እንድታለብሱ …› እያለ ይመክራል፡፡

⇛እዚያው እያለች ወሠነች፡፡ ወደ ቤቷ ገባች፡፡ ለወላጆቿ ነገረች፡፡ ኒቃብ መልበስ አለብኝ አለች፡፡ ከብዙ ክርክር በኋላ አሳመነቻቸው፡፡ ትምህርት ብትጨርስም ዉጤት አልመጣላትም፡፡ በግል ኮሌጅ አካውንቲንግ ተማረች፡፡ ዉጤቷ ጥሩ ነበር፡፡ ሥራ ፈለገች፡፡ ግና በኒቃቧ ምክንያት ተገፋች፡፡ ተቆጨች፣ ተናደደች ….

↳ዕድሜዋ ሲገፋ ይታወቃታል፡፡ ከአሥራ ቤት ወጥቶ ሀያ ገብቶ ወደ ሰላሳም ተጠግቷል፡፡ በዚህ በኩል የሥራ ማጣት፣ በወዲያ ከትዳር መዘግየት አስጨነቃት፡፡ ወንድ አትቀርብም፤ ወንዶችም ሊቀርቧት ይፈራሉ፡፡ የለበሠችው በልጅነት በመሆኑ ቀይ ትሁን ጥቁር፤ ቆንጆ ትሁን መልከ ጥፉ በአካል አያውቋትም፡፡ ብቻ በሩቅ ይሸሷታል፡፡ አንድም ኢማናቸውን ንቀው አሊያም ታጠብቃለች፣ አክራሪ ናት ብለው በመፍራት፡፡ ሁለት ፈተና በአንድ ጊዜ ወጥሮ ያዛት፡፡ የለፋችበት ትምህርት ቆጫት፤ የምትመኘው ትዳር ራቃት፡፡ ብዙ ጓደኞቿ ሥራ አገኙ፡፡ በዕድሜ ታናሾቿ ተራ በተራ አገቡ፡፡ ሒጃብን ለሥሙ ብቻ ጣል የሚያደርጉት ጥሩ ትዳር ያዙ፡፡

⇨አላህ እሱን ለማይፈሩት ነው እንዴ የሚያደላው! አለች፡፡ ጥሩዎች ሲጎዱ መጥፎዎች ሲጠቀሙ አየች፡፡ ታዘበች፣ አሰበች፡፡ ኢማኗ እየደከመ መጣ፣ በራስ መተማመኗ ቀነሰ፣ ሌሎች የሚያወሩላት ወሬ ሸረሸራት፡፡ ከራሷ ጋር ታገለች፡፡ ኡስታዞችንና ዓሊሞችን ጠየቀች፡፡ ‹ልጅ ሆኜ ስለ ዲን ብዙም ሳላውቅ ነበር በችኮላ የለበስኩት፤ አሁን ማውለቅ እችላለሁ ?› አለች፡፡ አውልቂ የሚላት ጠፋ፡፡ ወደ ራሷ ተመለሰች፡፡ ከሁለት ያጣች እንደሆነች ታወቃት፡፡ ኒቃብ ከሥራም ከትዳርም እየከለከላት እንደሆነ ሸይጧን ሹክ አላት፡፡ ደስ እያላት ባለመልበሷ ምክንያት ምንም አጅር እንደማታገኝም ነገራት፡፡

ወረደች፣ ተጠራጠረች፣ ግራ ታጋባች …. በጥርጣሬ ዉስጥ ከምዋልል ለምን አላወልቀውም አለች፡፡ ከብዙ ትግል በኋላ አወለቀች፡፡ የመጀመሪያ ሰሞን እርቃኗን የሆነች ያህል ተሰማት፡፡ ግና አንድ አድርጌዋለሁ ብላ ራሷን አበረታታች፡፡ ያዩዋትና የሚያውቋት ደነገጡ፡፡ እሷ ናት ወይስ ሌላ? አሉ፡፡ እሷነቷን ሲያረጋግጡ ብዙ አወሩ፣ ተሳለቁ፡፡ በወሬያቸው ይበልጥ ባሰባት፣ እልህ ተጋባች፡፡ በዚያው ሄደች፡፡ ወደ ቀደመ ቦታዋ አልተመለሠችም፡፡ እሷ የድሮ ኒቃቧን ረሣች፡፡ እነርሱም አውርተው ሲደክሙ ዘነጓት፡፡

☞ኒቃብ የለበስሽ እህቴ ሆይ!

① ስለተነገረሽ ሳይሆን አውቀሽና አምነሸበት በዝርዝር አጥንተሸና አገናዝበሽ ልበሺ፣

②ኒቃብ ስትለብሺ ዒባዳ መሆኑን አስቢ፤ ኒቃብያሽ ቀጥ ያለና የተስተካከለ ይሁን፣

③- በአንድ ልብ ኑሪ፤ ሁለት ሀሳብ መሆን ላውልቅ አላውልቅ ምንዳ የለውም፤

④ጊዜው ቢረዝምም፣ ቀኑ ቢቆይም አላህ መልካም ባሮቹን ጥሎ አይጥልም፡፡

⑤ኒቃብ በማውለቅና ፎቶ በመለጠፍ የሚገኝ ትዳር የለም፤

⑥በአላህ መመካትሽ እንደ ወፍ ይሁን፣ ባዶ ሆዷን ወጥታ ሆዷን ሞልታ ትገባለች፣

⑦ በአላህ አምኛለሁ በይና ቀጥ በይ፣

⑧- ጥሩ መጨረሻ አላህን ለሚፈሩና ለጥንቁቆች ነው፡፡

⑨- አላህ በመልካም ነገር ላይ ፅናት ይስጠን፡፡

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
ስንት ጁዝ ሐፈዘሻል⁉️

የሸህ እገሌን ልጅ ልንድርህ ነውና ሂድ እያት አሉት ወላጆቹ፡፡ ገና ሲያያት ግንባሩ ከግንባሯ ገጠመ፡፡ ወደዳት፡፡ እናም በሌላ ቀን ፈቃደኝነቷን ሊጠይቃት ብሎ ሄደ፡፡ ስለ ሀሳባቸዉና ዓላማቸው አወሩ፡፡

#ቁርኣን #ምን #ያህል #ሐፍዘሃል?” #አለችው፡፡

“አይ ብዙ አላፈዝኩም፤ ምናልባት ካሁን በኋላ እሐፍዝ ይሆናል፡፡ ግን መልካም የአላህ ባርያ የመሆን ጉጉት አለኝ፡፡” አላት፡፡ ጉጉቱን በቀልቧ ያዘችለት፡፡ ሲቪው አማረለት ።

“አንቺስ ሐፍዘሻል?” አላት፡፡
“የዐምማን ጁዝ ሐፍዣለሁ፡፡” አለችው፡፡

እውነት የነገራት መሆኑን ባወቀች ጊዜ ቀልቧ ወደዳት፡፡ አሳዝኗትም ወዳዉም ጥያቄዉን ተቀበለች፡፡

“ከተጋቡ በኋላ ቁርኣን እንዲአስሐፍዛት ጠየቀችው፡፡ ችግር የለዉም እሺ እንተጋገዛለን፡፡” አላት፡፡

ከ “መርየም” ምዕራፍ አብረው ጀመሩ፡፡
ሒፍዙን ሳያቆሙ ቀጠሉ፡፡ በመጨረሻም ሁለቱም ቁርኣንን በቃል አኽትመው የሒፍዝ ሰርተፊኬት አገኙ፡፡

አላረፈችም፡፡ አሁን ደግሞ ።"ሐዲሥ ለምን አንሐፍዝም?" አለችው፡፡ ቡኻሪን አጥንተው ጨረሱ፡፡

አንድ ቀን ለዚያራ ወደ ወላጆቿ ቤት ሄዱ፡፡
ባል “አንድ ያልነገርንዎት ነገር አለ አባ፡፡ አልሐምዱሊላህ ልጅዎ ቁርኣን ሐፍዛለች፡፡” አላቸው ለአማቹ በኩራት ፡፡

አማቹ በግርምት አዩት፡፡ ወደ ጓዳ ገቡና የልጃቸዉን የተለያዩ የምስክር ወረቀቶችን አመጡ፡፡ አማች ባየው ነገር ደነገጠ፡፡ ልጅት ሳታገባው በፊት አስቀድማ ሐፊዛ ነበረች ለካ፡፡ ከቁርአን አልፋ ሱነኑ ሲታንም ጭምር የጨረሠች ስለመሆኑ ማስረጃ አላት፡፡ ባል ተገረመና ዝም አለ፡፡

ያኔ እንዲያ ያደረገችው የባሏ ሞራል እንዳይነካ ፈርታ ነበር፡፡ ዒልም የለህም፤ ቁርኣን አላፈዝክም ብላ አላጣጣለችዉም፤ በዕውቀቱ ደረጃ አልናቀችዉም፡፡ እሱ እውነቱን በነገራት ጊዜ ከልቧ አስገባችው፤ ፈቀደችዉም፡፡ እንደሷ ቁርአን እንዲሐፍዝም ስለፈለገች በዚያ መልኩ አስጀመረችው፡፡ ዐምማን ሐፍዣላሁ ያለችውም እውነቷን ነበር አልዋሸችም፡፡ ዐምማ ከ30 የቁርኣን ጁዞች አንዱ ነዉና፡፡

በዲን፣ በዕውቀት፣ በገንዘብ ይሁን በቤተሰብ የደረጃ ሁኔታ ተገማግሞ መናናቅ የትዳር ፀር ነው።
አላህ ሷሊሕ የትዳር ጓደኛ ይስጠን

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#እናቴ በጣም ምርጥ ሴት ናት🥹
ወላሂ
#እናቴ ምርጥ ሴት ናት..🥹
እና በጣም መልካም ሴት ናት.🥹
#ሂዳያ ብቻ የጎደለት ሴት ናት.💔

ስትል የህይወት ታሪክዋን ትቀጥላለች የሜምበር ቲቪ ገዜጠኛ እህት
#ሶፊያጁሀር እስኪ ተገባዙልኝ...🙏🥹

💚       ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ      💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
#መካሪዎች #ሲመክሩ

①ከዉጭሽ ይልቅ ለዉስጥሽ ዉበት ይበልጥ ተጨነቂ፣
②- ከ30 ዓመት በፊት ትዳር/ልጅ ይኑርሽ፣?
③- በስህተት ዉስጥ ትምህርት ይገኛልና መሳሳትሽን አትፍሪ ፣
④- አላህን እንጂ ሰዉን አትፍሪ፣
⑤- ለአላህ ነው የምሠራው ካልሽ ይሉኝታ አይያዝሽ፣
⑥- በኢኮኖሚ ራስሽን ቻይ፣
⑦- ጥሩ ጥሩ ጓደኞች ይኑሩሽ፣
⑧- ቀልብሽ ያልወደደዉን አታግቢ፣
⑨- ያለፈን ነገር እርሺ፣
⑩- ከወንዶች ይልቅ ሴቶች ሊቃወሙሽ ይችላሉ፣
⑪- ታውቃለች ለመባል ሳይሆን ለማወቅ እወቂ፣
⑫- ከሀሜትና ተራ ወሬ ራቂ፣
⑬- በራስሽ እጅ ታሪክሽን ፃፊ፣
⑭- ጥገኛ አትሁኚ፣
⑮- ሴትነትሽን ዉደጂ፣
⑯- ትልቅና የሚጨበጥ ዓላማ ይኑርሽ፣
⑰- ትክክል ነኝ ብለሽ ካሰብሽ ግፊበት፣…

“እስኪ እናንተ 3 ጨምሩበት እና ⑳ ሙሏት”

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
#ከተዋለዱት #የተዋደዱት!

#አንዳንዴ ቁጭ ብለን አላህ የለገሰንን ፀጋዎች ብንቆጥር ኢስላም ብቻ ያስተሳሰረን ወንድሞችና እህቶች ጎልተው ይታዩናል፡፡ መለስ ብለን የቴሌ ግራም ጓደኞቻችንን ብንፈትሽ በአካል የምናውቃቸው ጥቂቶችን ብቻ ናቸው፡፡ ከብዙዎች ጋር ጓደኝነት የመሠረትነው መንፈሣችን ስለተጠራራ ነው፡፡ ይሄ ቴሌ ግራም ራሱ ፀጋው ትልቅ ነው፡፡ ከስንት #ቅን ወንድሞችና እህቶች ጋር አስተዋውቆናል፡፡

•ሀሰባቸው
#ጀነት፣ ዓላማቸው #የአላህ #ዉዴታ፣ አቅጣጫቸው ተመሳሳይ የሆኑ ነፍሦች ሁሌም ይሳሳባሉ፣ ይተሳሰባሉ፡፡ #ይነፋፈቃሉ፣ ይጠራራሉ፡፡ #ሩቅ ሆነዉም የተቀራረቡ ናቸው፡፡ #ከእስልምና በላይ የሚያስተሳስር ምን አለ ወዳጆቼ!፡፡ በሥም ብቻ ተዋውቀህ #ትዋደዳለህ፡፡ ድንገት በአካል የተገናኘህ ቀን ደግሞ ለረጅም ጊዜ እንደሚተዋወቅ ሰው #ትፈነድቃለህ፡፡ #እስልምና ምንኛ መልካም ነው!!
||
•የአላህ ዉዴታና ሰላም በነዚያ ሳያውቁን በወደዱን ላይ ሁሉ ይስፈን!!

•ሰላም በነዚያ ከደረጃችን በላይ ግምት ሰጥተው ላከበሩንና ለወደዱን የንፁህ ነፍስ ባለቤቶች ሁሉ ይሁን!

•ጌታችን ሆይ! የወደድናቸዉን ያንተን ባሮች ምድር ላይ የማግኘት ዕድሉ ብናጣ ነገ በመጨረሻው ዓለም ከነርሱ ጋር መገናኘትን አትንፈገን፡፡

•አምላካችን ሆይ! በሩቅ ሆነው በአካል ሳናውቃቸው ከወደድናቸዉና ከወደዱን ጋር ነገ ቀስቅሰን፣

•ስለ ክብርህና ልቅናህ ብለን ተዋደናልና በእዝነትህ ጀነትህን ለግሠን፡፡

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
⇨አሁንስ አበዛችሁት!! ደሞ ማን ነው ፂም መላጨት ሐራም ነው ያላቹህ⁉️

📛ፂምን መላጨት በአንድ ሁኔታ ላይ ብቻ ከመፈቀድም አልፎ ይወደዳል!!!
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
መላጨት ስለተፈቀደልህ ደስ አለህ አይደል?
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
ግን ፂም ማሳደግኮ የነቢዩ ሱና ነው። ስለመላጨት ሲወራ እሄን ያክል ምን ደስ አስባለህ⁉️
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
ደስታህ ቀጥሏል አይደል⁉️
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
እሺ አዳምጠኝ ልንገርህ!
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
ለማንኛውም ተረጋጋ እሄ አንተን አይመለከትም‼️
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
እና ማንን ነው የሚመለከተው
°
°
°
°
°
°
°
°
⇨የሚለከተውማ {እናትህን፣እህትህን፣አክስትህን፣ሚስትህንና በጥቅሉ ሴቶችን} ነው የሚመለከተው።
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
°
ኢማሙ ነወውይ(ረሒመሁሏህ) እንዲህ ይላሉ:-
"በሴት ላይ ፂም ከበቀለላት ለርሷ መላጨት ይፈቀድላታል"

📚ምንጭ【ሸርሁ ሶሒሂ ሙስሊም (3/149)】
°
°
°
°
°
አዎ በሸሪዓችን ፂም በሴት ላይ ከበቀለባት ብቻ ነው መላጨት የተፈቀደው
ስለዚህ ወንድ በምንም መልኩ ፂሙን መላጨት አይፈቀድለትም

°
☞እወቅ ወንድሜ ወዳጅህ ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) እና እነዚያ ጀግና ባልደረቦቻቸው እነርሱን በመልካም የተከተሉ የአሏህ ባሮች ፂማቸውን በማሳደግ ነው የሚታወቁት።
☞አንተ ማንን አርአያ አድርገህ ነው ፂምህን የምትላጨው? አርአያህ ማን እንደሆነ አስተውለሀልን?
☞አዎ ፂምህን የምትላጭ ከሆነ አርአያህ ነቢዩ (ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሳይሆኑ
እወቅ አርአያህ አይሂዶች ናቸው።


ታዲያ አስተዋይ የሆነ ሰው የሰው ልጆች ምርጥ የሆኑትን የነቢያቶች ዋና የሆኑትን የነቢዩን(ሶለሏሁ ዐለይሂ ወሰለም) ሱና ትቶ የአይሆዶችን ሱና ይከተላል⁉️
አሏሁል ሙስተአን

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
'ዱዓ አርግልኝ' አልኩት
'ምን ሆንክ?' አለኝ ።
'ምንም ካልሆንኩ ዱዓ አታደርግልኝም?' ማለት ነው ? አልኩት።
'እሺ በቃ' አለኝ ።

አዎ ምንም ሳይሆኑም ዱዓ ይደረጋል ፣ ያስፈልጋልም።

እንዲህም ሆኖ
ምንም እንኳ እንደጉዳዩ ባለቤት ጉዳዩን ለአምላኩ የሚናገር የሌለ መሆኑን ባውቅም፤ ከራሴ እጅ ይልቅ በሌሎች እጅ የሚደረግልኝን ዱዓ እመርጣለሁ ።

#እጄ #በእጅጉ #ቆሽሿል

ወንድም እህቶች ሆይ ይህን ደካማ ባርያ በዱዓችሁ አስታውሱት።

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
ድህነቱ ዐይኑ ይጥፋ!

#ከሚስቱ ጋር በድህነት ዉስጥ ይኖር የነበር አንድ ሰው ነበር አሉ፡፡ የሆነ ቀን ታዲያ ሚስቱ ለረጅም ፀጉሯ ማበጠሪያ እንዲገዛላት ጠየቀችው፡፡ ለሚስቱ ያለው ፍቅር ከፍ ያለ ነበርና ፍላጎቷን ማሟላት ባለመቻሉ ሰውዬው በሐዘን ስሜት ሚስቱን ተመለከታት፡፡

ብኖረኝማ ኖሮ ለዚህች ሰዓቴ እንኳ ማሰሪያ በገዛሁላት ነበር እኮ› አላት፡፡

ሚስቱም የባሏን ኪስ ስለምታውቅ ክፉ ቃል አልተናገረችውም፤ በስሱ ፈገግ ብላ ዝም አለች፡፡

በነጋታው ማታ ላይ ከሥራ ሲወጣ ግና ያችን ሰዓት ለመሸጥ ወደ ገበያ ወጣ፡፡ ገዢም አገኘና በርካሽ ዋጋ ሽጦ ለሚስቱ ማበጠሪያ ገዝቶላት ደስ እያለው ወደቤቱ አዘገመ፡፡

እቤት ሲደርስ ግን ያየውን ማመን አቃተው፡፡ ሚስቱ ፀጉሯን ተቆርጣ የሰዓት ማሰሪያ በእጇ ይዛ ጠበቀቸው፡፡

ተያዩና ድንገት መላቀስ ጀመሩ፡፡

ይህን ያደረጉት ያለምክንያት አልነበረም፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ስለሚዋደዱ ነበር፡፡

ስለሚዋደዱም አንዱ የሌላኛውን ፍላጎት ለማሟላት ተሸቀዳደሙ፡፡

አላህ በትዳር ሕይወታቸው ዉስጥ የሚገነዛዘቡና የሚተሳሰቡ ያድርገን፡፡

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
Audio
@MARAKI_LIBOCH
🍒:እስኪ በአላህ አንዴ ለአንድ
አፍታ ጀነት ደርሰን እንምጣ 😌
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
:13:50 ደቂቃ
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💾:3.2 MB
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
📢:
T.me/Maraki_Liboch
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
ፍቅር አላህ በሁለት ቀልቦች ዉስጥ የሚጥለው መግኒጣሳዊ ስህበት ነው፤ ስህበቱ ከሁለቱም በኩል ሲሆን እጅግ ደስ የሚል ስሜት ይሠጣል፡፡ ተዋዳጆች ድንገት ሲገናኙ  “ኦ እያሰብኩህ” ነበር ስትለው “ኦ እኔም እኮ እያሰብኩሽ ነበር” ይላታል፡፡

ጀሊሉ በዚህ መልኩ በተመሳሳይ ሰዓት አንዱ ስለሌላኛው እንዲያስብ ያደርጋል፡፡ ፍቅር “ተዓምር” ነው እንጂ ሌላ ምን ሊባል ይችላል ወዳጆቼ፡፡
የአላህ መልዕክተኛም (ሰለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም) እንዳሉት ፍቅር መድሃኒቱም፣ ፈውሱም፣ ማስተንፈሻዉም፣ ማስታገሻዉም ጋብቻ ብቻ ነው፡፡ በእውነት ያፈቀረ ልብ ላግባሽ፣ አግባኝ፣ እንጋባ … ለማለት ይሉኝታ አይዘዉም፡፡ ፍቅር ከነኚህ ሁሉ በላይ ተንሳፎ ተቀምጧልና፡፡

 ⇛በፍቅር ከማይቀልዱትና ዋጋዉን ከማያሳንሱት አንዱ ነኝ ብየ አስባለው፡፡
⇨በሌላ በኩል ደግሞ አላህ ቀልብህ/ሽ ዉስጥ ያላስቀመጠዉን ሰው ለምን አልወደድከኝም/ሽኝም ብሎ መነጫነጭ ትርፉ ድካም ነው የሚሆነው ብዬ አስባለሁ፡፡  
⇨ባይሆን ቀልብን ቀያያሪ የሆነ ጌታ የወደዱትን ሰው መልሶ እንዲወድ ያደርግ ዘንድ ዱዓ ማድረጉ የተሻለ ነው፡፡ ዱዓ የማይለዉጠው  ነገር የለምና፡፡

«
አላህ በሐላሉ ያብቃቃን»

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
ሰዎችን በምክንያት መወደድም ሆነ በምክንያት መጥላት የጤነኛ ሠው ሙሉነት መገለጫ ነው ፡፡ ምክንያቱ ተገቢና ትክክለኛ መሆኑን ማረጋገጥ ደግሞ ብልህነት ነው ፡፡

አንዳንዴ , አሏህ መልካም ነገር ሊውልልህ ሲፈልግ በህይወትህ ውስጥ መወደድ የሚገባውን ሠው እንድትወደው አድርጎ ያኖርልሃል ፡፡ ይህም እያንዳንዷ እስትንፋስህ ትርጉም እንዲኖራትና ልብህም በሀሴት እንዲሞላ ያደርግልሃል ፡፡

ሊቀጣህ የፈለገም ሰዐት ደግሞ መወደድ
የማይገባውን ሠው እንድትወደው ያደርግሃል ፡፡ ይህም በእያንዳንዱ ሰከንድ ልብህ የጠቆረ የሀዘን ደም እንዲረጭና እንዲቆስል ያደርግሃል ፡፡

አሏህ ቀልባችንን መወደድ
የማይገባውን ከመውደድ ይጠብቅልን!


💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
ጁምአ

ነብዩ  ﷺ  እንዲህ አሉ

ፀሀይ ከምትወጣበት ቀን ሁሉ ምርጡ  የጁምአ ቀን ነው. አደም የተፈጠረበት, ጀነትም የገባበት ከሷም የወጣበት ቀን ነው.
#ሰአቷም(የፍርዱ ቀን) አትቆምም በጁምአ ቀን ቢሆን እንጂ.  ቲርሚዚይ 488 🤍


#ሰዓቷ በእርግጥ መጪ ናት፡፡ በእርሷ ጥርጥር የለም፡፡ ግን አብዛኞቹ ሰዎች አያምኑም፡፡  40:59

#ሰዓቷም በምትቆምበት ቀን አመጸኞች ጭጭ ይላሉ

ለእነርሱም ከሚያጋሩዋቸው (ጣዖታት) አማላጆች አይኖሯቸውም፤ በሚያጋሯቸውም (ከአላህ  ውጪ በሚያመልኩት ነገር) ከሓዲዎች    ይኾናሉ

#ሰዓቷ በምትቆምበት ቀንም በዚያ ቀን ይለያያሉ፡፡

እነዚያ ያመኑትና መልካሞችን ሥራዎች የሠሩትማ እነርሱ በገነት ጨፌ ውስጥ ይደሰታሉ

እነዚያም የካዱትማ በአንቀጾቻችንና በኋለኛይቱም ዓለም መገናኘት ያስተባበሉት እነዚያ በቅጣቱ ውስጥ የሚጣዱ ናቸው፡፡ 30:12-16

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
በኡመቶቼ ላይ አምስት ነገርን
ወደው አምስት ነገርን የሚረሱበት
ዘመን ይመጣባቸዋል


🌾ዱንያን ይወዳሉ⇨ አኺራን ይረሳሉ!     
🪴ህይወትን ይወዳሉ⇨ሞትን ይረሳሉ!          
🏢ፎቅን ይወዳሉ⇨ቀብርን ይረሳሉ!
💲 ብርን ይወዳሉ⇨ ሂሳብን{ምርመራ}ይረሳሉ!
♥️ፍጡርን ይወዳሉ⇨ፈጣሪን ይረሳሉ
                                           
🔺ዱንያ ጠፊ ናት ይላሉ ጠፊ እንደሆነችም ያውቃሉ ግን ዘላለማዊ እንደሆነች ይገነባሉ።

🔺 ሞት አይቀርም ይላሉ እንደሚሞቱም ያውቃሉ ። ነገር ግን ለሱ አይዘጋጁም 

🔺 የተፈጠርነው አላህን ለማገልገልና ባርነታችንም ለአላህ ነው ይላሉ።  ጌታ እንደሌለው ነፃ እንደሆነ ሰው ይዝናናሉ።

🔺 ርዝቅ ከአላህ ነው ይላሉ። ነገር ግን በራሳቸው ጥረት ብቻ የሚያገኙ ይመስል ይፈጋሉ።

🔺አላህ መሃሪና አዛኝ ነው ይላሉ። ግን በተውባ ወደሱ አይመለሱም።  ከሚሰሩትም ኃጢአትም አይመለሱም።

🔺የአላህ ቅጣቱ ብርቱና አያያዙም የከፋ ነው ይላሉ። ነገር ግን ቅጣቱን እንደሚፈራ ሰው እንኳን አይፈሩም። ትዕዛዛቱን ይጥሳሉ ህግጋቱንም ይዳፍራሉ።

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
ሱብሂ መነሳት ለምን ይከብደናል

አንዳንዶቻችን  ለመነሳት አላርም ሁሉ ሞልተን ሰአቱ  ደርሶ ሲጮህ ተነስተን ዘግተን ሁሉ ተመልሰን የምንተኛ አለን

አንዳንዱ ያለምንም አላርምና ቀስቃሽ በቀላሉ ተነስቶ ይሰግዳል  እንዴት ሊገራላቸው ቻለ⁉️

ሱብሂ ለመነሳት የቀን ውሏችን ይወስነዋል; በቀን ውሏችእ ወልካም ነገር ስንስራ ከዋል ኢማናችን ቻርጅ አድርገንዋል በቂ ሀይል ስላለው ይቀሰቅሰናል,  ሀራም ነገር ስንሰራ ከዋል ደሞ ኢማናችንን አዳክመንዋል በተቃራኒው የሰይጣናችንን ሀይል ቻርጅ አድርገናል ማለት ነው በዚህም የሱ ሀይል ከኛ ስለበለጠ  በቀላሉ  ስለሚቆጣጠረን መነሳት ይከብደናል.

ኢማናችን እንዴት ለሱብሂ ለመነሳት የሚይስችለው ሀይል ማግኘት እንችላለን ታዳ⁉️
   ከሀራም መቆጠብ
    በአላህ መንገድ መንቀሳቀስ እንደ
   ደአዋ  ማድረግ,  መማር, ኢልም ማዳመጥ
በመስጊድ(በጀመአ)  እንቅስቃሴ መሳተፍ

ይህን እንኳን    ማድረግ ባንችል  በቤት ውስጥ ልጆችን, እህት ወንድሞችን, ወላጆችን ዲናቸውን መከታተል ማስተማር , 15 -30 ደቂቃ በየቀኑ ስለዲን  መማማር  በቂ ሀይል እንድናገኘ ያደርገናል ይሞክሩት ፍቱን መዳኒት ነው.

ከመተኛታችን በፊት ቢያንስ አንድ  10 ጊዜ እስቲግፋር ማድረግ ተጨማሪ ሀይል ያስገኛል
 
🗣ካልሆነ  ግን  አንድ ሰው ከባድ በሽታ ይዞት ካልታከመው ለሞት እንደሚዳርገው ሁሉ ሱብሂ አለመስገድ ለጀሀነም ስለሚዳርግ የግድ መስተካከል አለበት

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
ከሞት በኃላ ያለ ፀፀት

የሰው ልጅ አላህ የሚለውን ባለመስማቱ ከሞት በኃላ በጅጉ ይፀፀታን;  ስራውንም ሲያ ምነው እነንትናን ጓደኛ አድርጌ  ባልሊያዝኩ; የስራ   መዝገቤብ ባልተሰጠኝ ይላል;  አፈር ሆኖ መቅረትንም ይመኛልሸ

«ወይ ጸጸቴ! በጌታዬ አንድም ባላጋራሁ» የሚል ኾነ፡፡ 18:42

ፊቶቻቸው በእሳት ውሰጥ በሚገለባበጡ ቀን «ዋ ምኞታችን! አላህን በተገዛን መልክተኛውንም በታዘዝን ኖሮ» እያሉ ይጸጸታሉ፡፡ 33:66

«ዋ ጥፋቴ! እገሌን ወዳጅ ባልያዝኩ ኖሮ እመኛለሁ፡፡ 25:28

እኛ ሰው ሁሉ እጆቹ ያስቀደሙትን በሚያይበትና ከሓዲውም ዋ ምኞቴ! ምንነው ዐፈር በኾንኩ በሚልበት ቀን ቅርብ የኾነን ቅጣት አስጠነቀቅናችሁ፡፡ 78:40

መጽሐፉንም በግራው የተሰጠማ «ዋ ጥፋቴ! ምነው መጽሐፌን ባልተሰጠሁ» ይላል፡፡ 69:25

በእሳትም ላይ በተቆሙ ጊዜ ምነው (ወደ ምድረ ዓለም) በተመለስን በጌታችንም አንቀጾች ባላስተባበልን ከምእምናንም በኾንን ዋ ምኞታችን! ባሉ ጊዜ ብታይ ኖሮ (የሚያሰደነግጥን ነገር ባየህ ነበር
)፡፡6:27

(የጀነት   ነዋሪዋች ይሏቸዋልም) «በሰቀር ሲኦል ውስጥ ምን አገባችሁ; (እነርሱም) ይላሉ « #ከሰጋጆቹ አልነበርንም
« #ለድኾችም የምናበላ አልነበርንም፡፡
« #ከዘባራቂዎቹም ጋር እንዘባርቅ ነበርን፡፡
«በፍርዱ ቀንም እናስተባብል ነበርን፡፡ 74:42-46

ፀፀት የማይጠቅምበት ቀን ከመፀፀት አላህ ያዘዘንን መታዘዝ አላህን ያመፁ ሰዋች ስራቸውን በሚያዩበት  ጊዜ ሞት ቢኖር ኖሮ ከፀፀት ብዛት ይሞቱ ነበር

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
ይህችን ብለን  ብንተኛስ

ጌታዬ ሆይ!
⊙የኔ ባልሆነ ነገር ላይ አታባክነኝ
 የኔ ያልሆነን ሰው ከጃይ አታድርገኝ
⊙አንተ በማትወደው ነገር ቀልቤ አይሰረቅ
አንተ በምትጠላው ነገር ዉስጤ አይደነቅ
⊙ህልሜ ሳይሆን መሻትህ በኔ ላይ ይፈፀም
 ይሁንታህ ይሁን ምኞቴ ለዘላለሙ ይክሰም።

ኢላሂ!

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ
“እሺ ካልኩት በኋላ ሸሸ ...

⇨እሺ ያለችው ለትዳር ነበር፡፡ ጠየቃት፤ በፊትም ታስበው ነበርና ከትንሽ ማንገራገር እሺ አለችው፡፡

ከዚያ ጠፋ፤ ሸሸ፣ ከዐይኗ ራቀ ። ምን ታድርግ? ደዉላ ምነው ጠፋህ አትለው ነገር፤ ተስማምቻለሁ እኮ ያንን ዕቃ አትወስድም ወይ አትለው ነገር …፡፡
—እሱ ሲጠፋ መልሶ አሳፈራት፤ ተሸማቀቀች፤ ደበራት፣ እንደመበሳጨትም አደረጋት፡፡ የምሩን ነው ወይስ ሊፈትነኝ ነው የጠየቀኝ ብላም ራሷኝ ጠየቀች፡፡ የሰው ዉስጡ አይታወቅ ነገር፡፡

⇄ትዳር አንዳንዴ ከንግድ ጋር ይመሳሰላል ። አንዱ ደህና ዋጋ ሰጥቶ ሲጠፋባችሁ ምን ይሰማችኋል ? ይመለስ ይሆን ብሎ በር በሩን እንደማየት። ማሰብ ፣ ተስፋ አለመቁረጥ ...

በርግጥ በወቅቱ ያኔ ትንሽ ላግደርድረው ብላም አስባ ነበር፤ ግና በዚያው ቢቀርስ ብላ ፈራች፤ ይሄ ስትናፍቀው የነበረ መልካም ጥያቄ ላይደገም ይችላል ብላ ሰጋች፡፡ መልካም አክሲዮን አይገፋም። ትዳር ሐላል አክሲዮን ። እስከ አኺራና ጀነት አብሮ የመዝለቅ እሳቤ።

እናም ተስገብግባ እሺ አለችው፡፡
ደግ አደረግሽ።
ቢሆን ባይሆን ፣ ቢመለስ ባይመለስ፣ ቢመጣ ቢቀር ...እሱ የጀሊሉ ዉሳኔ ነው። አንች ግን እንኳን ለሐላል ጓጋሽ።

–ለሐላል ነገር መስገብገብ እኮ ጥፋት አይደለም፡፡ እንደዉም የሚበረታታ ነው።

–እሺ ስላልሽው ምን አሳፈረሽ! ምንስ ያጠፋሽው ነገር አለ!፡፡ አዎ ምንም የተሳሳትሽው ነገር የለምና አትፈሪ፡፡

–እርግጥ ነው በሰው ልብ መጫወት የሚፈልጉ አንዳንድ ሰዎች አሉ። ሰዉን እንደ ገበያ ዕቃ ያያሉ፤
ካስለፈለፉ በኋላ በዉስጣቸው በሰው የሚስቁ፣ እሺ አለችኝ ብሎ ለማስወራት የሚመጡም አሉ።

—አንዳንዶች ፈሪ ናቸው። ቶሎ እሺ ስለተባሉ ብቻ ምርጫ ላይ ተሳስቼ ይሆን? ቸኩዬ ይሆን? ብለው የሚደነግጡም አሉ።
–አንዳንዶች ደግሞ ለማግባት ወስነው አይመጡም፤ እሺ ከተባሉ በኋላም አጀላቸው የተቃረበ ይመስል የሚርበተበቱም አሉ፤
እሺ አልባልም ብለው አስበው ጠይቀው እሺ ሲባሉ ድራሻቸው የሚጠፋም አሉ፤
ፍላጎት ሳይኖራቸው ከአንገት በላይ ሰዉን የሚያወሩም አሉ፡፡

↠የሁሉን ልብ የሚያውቀው ጀሊሉ ነው። ፍርዱንም ለሱ መተው ነው ። እሱ ለያንዳንዱ የንያውን ይሠጣል ።
ቁምነገሩ ቁምነገረኛ ነው ብለው ላሰቡት ሰው ልብንና እጅን መሰጠት ነው። ለትክክለኛ ጥያቄ ትክክለኛ ምላሽ መስጠት ጥፋት አይደለም፤
ሐላልን መናፈቅ አያሳፍርም፤
ለምን ታፍሪያለሽ እሱ ከመልካም አክሲዩን የቀረው ይፈር፡፡

▫️ተልቁ ችግራችን በምን ማፈር እንዳለብንና እንደሌለብን አለማወቃችን ነው ።

ሐላል ፍለጋ ላይ ማፈር ብሎ የለም።

💚 ᴊᴏɪɴ & sʜᴀʀᴇ    💚
ღ   
@Maraki_Liboch    ღ
ღ  
@Maraki_Liboch    ღ