y655y nlsmood w981w vxmere 🍓
10.5K subscribers
1.62K photos
1.41K videos
12 files
428 links
የማንያዘዋል እሸቱ ስልጠና ዘውትር እሁድ ከጠዋቱ 4:00 እስከ 6:0 0 ሰዓት ቦሌ በማንያዘዋል እሸቱ ግቢ ከሰላም ሲቲ ሞል ጀርባ ይሰጣል:: ለበለጠ መረጃ 0987209020 ይደውሉ:: ለአስተያየት @manyazewal ላይ ይጻፉ፡፡

https://linktr.ee/manyazewal
Download Telegram
የሌለህ እንዲኖርህ----ያላደረከውን አድርግ!
Audio
ከልባችሁ አድሙጡ፡፡ኮሜንት ካለ @manyazewal ላይ ጻፉ፡፡
ሰላም ትፈልጋለህ? በጎ አስብ፡፡በጎ ማሰብ ለራስ ደግ መሆን ነው፡፡አእምሮህ ውስጥ መልካም ሀሳብ ብቻ ይመላለስ፡፡ለምን ራስህን ትወቅሳለህ? ትላንት ውስጥ ያደረከው መጥፎ ነገር ከትላንት ጋር አልፏል፡፡ይህ ሌላ አዲስ ቀን ነው፡፡በአሮጌው ሀሳብ አዲሱን ቀን አታበላሻው፡፡የቱንም ያህል የወንጀለኛነት ስሜት ቢሰማህም ትላንትን አትለውጥም፡፡እስቲ ለራስህ ደግ ሁን፡፡ራስህን ይቅር በለው፡፡ነገንም አትፍራ፡፡የነገ አምላክ ካንተ ቀድሞ በዚያ አለ፡፡የሚያስፈልግህን ነገር ለሟሟላት ሽር ጉድ እያለ ነው፡፡አንተ ግን ታምነዋለህ? ሁኔታዎች ከባድ ቢሆኑም እመን፡፡የጥርጣሬ ሀሳብ ከአእምሮህ ይውጣ፡፡የእምነት ሀሳብ ወደ ልብህ ይግባ፡፡ዛሬ ጥሩ ይሆናል፡፡ነገም ጥሩ ይሆናል፡፡ለራስህ ደግ ሁን፡፡በጎ ነገር አስብ፡፡
#share!
#Comment : @manyazewal
<<ቅሩብ እግዚአብሔር ለየዋህነ ልብ!>> አሉኝ የኔታ፡፡<<ምን ማለት ነው?>> አልኳቸው፡፡<<እግዚአብሔር ልባቸው የዋህ ለሆነ ሰዎች ቅርብ ነው!>> ብለው ተረጎሙልኝ፡፡thank you የኔታ!
S I M P L E
I S
B E A U T I F U L!!!!
#Be_Beautiful!
ካሰብሽበት ባትደርሽም ከተነሳሽበት ግን አይደለሽም፡፡ከትላንት ይልቅ ዛሬ ወደ እቅድሽ ቀርበሻል፡፡<<ትንሿ ቀዳዳ መርከብ ታፈነዳ!>> ይላሉና ለውጧ ትንሽ ብትሆንም ተስፋ አትቁረጪ፡፡#ልፊ! #ደርሰሻል! #share!
የዛሬ 1$ vs የዛሬ ሀያ አመት 1000,000$
--------------------------------
ይሄ ደግሞ <<ኮርያ ልውሰድህ!>> ይለኛል? ምን ሞኝ አድርጎ ቢያስበኝ ነው ? አብሮት ያለው ደግሞ <<እኛ ከኮሪያ ደብዳቤ ጽፈን እንጋብዝሃለን፡፡ያንተ ስራ አዲስ አበባ ያለውን የኮርያ ኢምባሲ ማሳመን ብቻ ነው፡፡>> አላለኝም መሰላችሁ? ደሞ እሱም መልሶ ያግዘዋል፡
<<አንተ ጥሩ ጭንቅላት ስላለህ ኢምባሲውን ማሳመን አይከብድህም፡፡>> ይላል፡፡በዚህ ሰዓት ጥሩ ጭንቅላት ያለው ወደ ኮርያ የሚሰደደው አብዶ ነው? ተናደድኩኝ፡፡ተበሳጨው፡፡
<<አመሠግናለሁ ነገር ግን እኔ ኮርያ የመሄድ ፍላጎት የለኝም!>> አልኩኝ የጋበዘኝን ቡና ፉት እያልኩኝ፡፡ሰውዬውማ በመጀመሪያ ሊጋብዘኝ የፈለገው ቢራ ነበር፡፡አልጠጣም ስለው በጣም ገርሞታል፡፡የተገናኘነው አርባምንጭ ሐይሌ ሪዞርት ነው፡፡የዛን ቀን ቀኑን ሙሉ አድካሚ ስራ ስሰራ ዋልኩኝ፡፡አመሻሽ ላይ ሰውነቴን ለማሳረፍ ወደ ሐይሌ ሪዞርት አቀናሁ፡፡የሪዞርቱ መናፈሻ ላይ ቆሜ ጫካውን ስመለከት በድጋሚ ዛሬም ገነት ያለው መሠለኝ፡፡ሰውነቴ ድካሙን ረስቶ ዛሬም እንደ አዲስ በአርባምንጭ ውበት መደመሙን ቀጠለው፡፡አንድ ትልቅ ንስር እንደተዋጊ ጄት በጫካው ሰማይ ላይ ሲምዘገዘግ እያየሁ ቪዲዮ መቅረጽ ጀመርኩኝ፡፡ይሄ ኮርያዊ ከጎኔ ቆሞ እሱም በአግራሞት ይመለከት ጀመር፡፡
<<ሄሎ!>> ስለው <<ሰላም እንዴት ነህ?>> አለኝ በአማርኛ፡፡ሰላምታ ስለሆነ አልገረመኝም፡፡ነገር ግን ማውራት ስንቀጥል እኔ በኢንግሊዘኛ ለማውራት በጣርኩ ቁጥር እሱ በአማረኛ ተንደፋድፎ ይመልሳል፡፡በተገናኘን በአስራ አምስቲ ደቂቃ ውስጥ ብዙ ነገር አወራን፡፡
<<አንድ ቢራ ልጋብዝህ!>> ብሎኝ ቆመን ከምናወራበት እየመራኝ ወደ ጠረጴዛው ወሰደኝ፡፡
<<እኔ ሌላ ጓደኛ አለ!>> በማለት ሌላ ጓደኛው ጋር አስተዋወቀኝ፡፡ድንቡሽቡሽ ያለ ሌላ ኮርያዊ በታልቅ ትህትና ከተቀመጠበት ተነስቶ ጨበጠኝ፡፡ወንበር ስቤ አንድቀመጥ በከባድ ትህትና ጠቆመኝ፡፡ደስ አለኝ፡፡ወንበር ስቤ ቁጭ እንዳልኩኝ፡
<<አሽተናጋጅ ቢራ! ቢራ! ባለ ቀንዱን ዋሊያ ቢራ!>> አለ ይዞኝ የመጣው፡፡ለእኔ አልመሠለኝም፡፡አስተናጋጇ አምጥታ ግን ከፈተችው፡፡ብርጭቆ ውስጥ ቀድታ ከፊትለፊቴ ስታስቀምጥ እንደማልጠጣ ነገርኩትና ቡና አዘዝኩኝ፡፡እነሱ ቢራቸውን እኔ ደግሞ ቡናዬን እየጠጣሁ ጨዋታችን ጦፈ፡፡ከአርባንጭ ሰማይ ስር ለሶስት ትልልቅ ሀሳቦችን እያነሳን ልክ እንደ አብሮ አደጎች መጫወትና መንጫጫት ጀመርን፡፡አስተሳሴቤን ወደውታል መሰለኝ አገራቸው እንድመጣ ፈለጉ፡፡እኔ ደግሞ አልፈለኩም፡፡ኮርያ መሄድ አለመፈለጌ አስገርሟቸዋል፡፡
<<ወንድሜ ደቡብ ኮርያ እኮ አይደለም እንጋብዝህ ያልነው፡፡ሰሜን ኮርያ ነው፡፡>> አለኝ ድንቡሽቡሹ ጓደኛው፡፡
<<ለምን ሰሜን አሜሪካ አይሆንም፡፡መሄድ አልፈልግም፡፡>>
<<ለምንድን ነው የማትሄደው?>>
<<ለምን እሄዳለው?>>
<<እሱማ ለማንም ግልጽ ነው፡፡ኮርያ ከኢትዮጵያ የተሻለች አገር ነች፡፡ብትሄድ ከዚህ የተሻለ ገንዘብ ትሰራለህ፡፡ምርጥ ምርጥ ነገር ትማራለህ፡፡>>
<<አትሳሳት ኮሪያ ከኢትዮጵያ የተሻለችው ዛሬ ነው፡፡አዎ ዛሬ ኮርያ መሄድ አሪፍ ነገር ሊመስል ይችላል፡፡የዛሬ ሀያ አመት ግን በእርግጠኝነት አሪፏ አገር ኢትዮጵያ ናት፡፡>>
<<ሃሃሃሃሃሃ እንዴት?>> አለ ወደ ጠረጴዛው ያመጣኝ በጣም ተገርሞ፡፡
<<በጣም ጥሩ፡፡የሚመጣው ጊዜ የአፍሪካ ነው፡፡ወደድክም ጠላህም የሚመጣው ዘመን የአለም የንግድ፣ የመዝናኛ፣ የባህልና የቴክኖሎጂ ማዕከል አፍሪካ ነች፡፡ኢትዮጵያ ደግሞ የአፍሪካ እምበርት ነች፡፡አሜሪካ፣ ቻይና፣ ሩሲያ፣ ራሷ ኮርያና የአውሮፓ አገራት የሚመጣው ጊዜ የአፍሪካ እንደሆነ ያምናሉ፡፡በእርዳታ እና በገንዘብ የአፍሪካን መሪዎች የሚይዙትም ለዚያ ነው፡፡የምድራችን ጉዙፍ የንግድ ድርጆት ይሄንን እውነት ተረድተው ወደ አህጉረ አፍሪካ በፍጥነት እየተስፋፉ ነው፡፡የአካዳሚክ እና የምርምር ሰዎች በመጻፍ እና በጥናቶቻቸው የሚመጣው ሀያ ሰላሳ አመት የአፍሪካ እንደሆነ በድፍረት እየተናገሩ ነው፡፡ ይሄ ዘመኑ ራሱ ለእኛ ለአፍሪካውያን ያመጣው እድል ነው፡፡ምውራባውያን ፈልገው ወይም እኛ ፈጥረነው ሳይሆን ፈጣሪና ጊዜው ራሱ ያመጣልን በረከት ነው፡፡ስለዚህ ይሄንን እውነት በአይኑ በብሮቱ እያየ ኢትዮጽያን ጥሎ ወደ ወጪ አገር የሚሰደድ ወጣት አለም ወድየት እንደሚሄድ ያልገባው ወጣት ነው፡፡ዛሬ በሚሠራው ነገር የዛሬ ሀያ አመት ላይ ስህተት እንደሆነ ይገባዋል፡፡መሰደድ ትክክል አይደለም እልኩኝ አይደለም፡፡ኢዚህ ኢትዮጵያ ውስጥም ከውጪ የላቀ መልካም አጋጣሚ አለ ለማለት ነው፡ጰ>> አልኩኝ ቅልጥፍጥፍ ብዬ፡፡
<<እንዴት?>> ፡፡
<<ከሞላ ጎደል ሌላው አለም ተገንብቷል፡፡ሁሉም ኢንፍራስትራክቸር ተሰርቶ አልቋል፡፡አፍሪካ ግን ገና አልተነካችም፡፡ኢትዮጵያ? ጥሬ ነች፡፡ሌላው ቢቀር አልተጎበኘችም፡፡ምንም በቀኝ ግዛት ሰበብ አፍሪካ ብዙ ሀብት ቢመዘበርባትም ገና ገና ሀብቷ ድንግል ነው፡፡ምዕራባውያን ምድር ላይ ያለውን ጥሬ እቃ ጨርሰወው ለፍለጋ ወደ ማርስ እና ወደሌላው ፕላኔት እየበረሩ ነው፡፡በአሁን ሰዓት የምድር ውዱ ነገር ጥሬ እቃ ነው፡፡ምድር ላይ ብዙ ጥሬ እቃ ያላቸው አገራት ያሉት ደግሞ አፍሪካ ላይ ነው፡፡በተለይ ደግሞ ኢትዮጵያ ስላልተገዛች ከሁሉም ትሻላለች፡፡ስለዚህ ይሄንን ጥሬ እቃ ፈልገው ትልልቅ አገራት እና ድርጅቶች ወደ አፍራካ ይኮበልላሉ፡፡ያኔ አፍሪካን ከእነሱ በተሻለ የምናቅ ሰዎች በላናቸው ብለው ሲመጡ እኛም ከእነሱ ቀድመን ልንበላቸው ያስፈልጋል፡፡አሁን ኮርያ ብሰደድ ስራ ብትሰጡኝ የሚያገኘው ነገር የተወሰነ ዶላር ቢሆን ነው፡፡ያ ደግሞ ህይወቴን በመሠረታዊ ደረጃ ላይለውጥ ይችላል፡፡ዶላሩ አገሬ ላይ የራሴን አሻራ እንዳኖር እድል ላይፈጥር ይችላል፡፡ለሚቀጥሉት 20 አመታት ግን ኢትዮጵያ ላይ ቁጭ ብዬ ቀስበቀስ በዘመኑ የሚፈለግ ነገር እንዴት አድርጌ መገንባት እንደምችል ራሴን ባስተምር የራሴን ብቻ ሳይሆን የብዙ ሰዎችን ህይወት የምለውጥ ሰው እሆናለው፡፡የእኔ ፍላጎት የአሁኗ አንድ ዶላር ሳትሆን የዛሬ ሀያ አመቷ አንድ ሚሊዮን ዶላር ነች፡፡>>
<<ሃሃሃሃሃሃሃ አደገኛ ልጅ!... ስለዚህ ስደት ካልፈለክ አንተ ምን እያሰብክ ነው ወይም ምን እያደረክ ነው?>> ጠየቀ ድንቡሽቡሹ፡፡
<<ሰውነቴን አይሰደድ እንጂ አእምሮዬ ግን ሁሌም ይሰደዳል፡፡በኢንተርኔት በኩል ሹልክ ብዬ ስፈልግ ኮርያ ስፈልግ አማሪካ ስፈልግ እሳራኤል እሰደዳለው፡፡መጽሐፋቸውን አነባለው፡፡ቪዲዮ እመለከታለው፡፡በሚመጣው ዘመን ላይ ምን ባደርግ የራሴን ኢምፓየር መገንባት እንደምችል እዚህ ሆኜ እዛ ያለውን የጨዋታ ህግ ራሴን አስተምራለው፡፡እኔ ሳር ውስጥ እንደተደበቀ እባብ ነኝ፡፡እግዚአብሔር እና ዘመኑ የሚያመጡልኝን መልካም አጋጣሚዎች ለመንደፍ በንቃት እየጠበኩኝ ነው፡፡ፈረንጆች ይንቁናል፡፡ምንም የምናውቅ አይመስላቸውም፡፡ምስጋና ለኢንተርኔት ይግባውና ብዙ ነገሮችን ለአፍሪካውያን ወጣቶች እያሳወቀን ነው፡፡ፈጣሪ ከረዳን እኛም ከበረታን አገራችንን እና አህጉራችንን በሚሚጣው ዘመን ላይ እንዲያንፀባርቁ እናደርጋለን ብዬ አስባለው፡፡>> እንዳልኩኝ ፡<<ቺንኩ ቻካ ቺንክ ቹቻቾ!>> ምንም እያሉ በራሳቸው ቋንቋ ማግሮምሮም ጀመሩ፡፡ ሳፈጥባቸው፡፡
<<አደገኛ ጭንቅላት ነው ያለህ እያልን ነው!>> አሉሉኝ፡፡
<<አመሠግናለሁ!>> አልኩኝ፡፡ሂሳቡን ከፈሉና በፍቅር ሰላምታ ተሰናብተውኝ ወደ ክፍላቸው ገቡ እኔም ወደ ቤት አንሶስያት ማድረግ ጀመርኩኝ፡፡
#ሟር!
እነዚህ ደግሞ ምን እብዶች ናቸው? አሁን ከጀርመን እስከ አርባምንጭ በመኪና ይመጣል? ያውም ራሳችሁ በሰራችሁት መኪና? ምን የሚሉት አድቬንቸር ነው ይሄ ? ደግሞ እኮ የመጨረሻ <አርጅተዋል>፡፡ስልሳ ሲደመር ምናምን አመት ውስጥ ናቸው፡፡ፍቅራቸው ደግሞ ሲያስቀና፡፡የእውነቴን ነው ሚስቴን አስናፈቁኝ፡፡እንዴት አድርጎ እንዳቀፋት እዩልኝ፡፡የእሷን ፊት ደግሞ ልብ አድርጋችሁ አስተውልሉኝ፡፡ሀኒ ሙን ላይ ያሉ ካፕሎች እንጂ በትዳር ለአርባ ሁለት አመት የቆዩ ሼባዎች አይመስሉም፡፡እነዚህ ብልጥ ሰዎች ናቸው፡፡ትዳር አሰልቺ ነገር እንደሆነ ስላወቁ አስቀድመው የሆነ ነገር ዘየዱ፡፡<<አብረን ለብዙ ዘመን የምንኖር ከሆነ አብረን የምንሰራው ብዙ ነገር ሊኖረን ያስፈልጋል፡፡አለበለዚያ ትዳራችን አሰልቺ ይሆናል፡፡እንደባበራለን፡፡>> ተባባሉ፡፡ትልቅ የጋራ ጥረት በሚጠይቅ አላማም ትዳራቸውን መሠረቱ፡፡አላማቸውም አለምን ራሳቸው በሰሩት መኪና መጎብኘት ነበር፡፡ሁለቱም MAN [እኔ አይደለሁም] የተባለው የመኪና አምራች ኩባኒያ ውሰጥ በመካኒክነት ተቀጥረው መስራት ጀመሩ፡፡
ሴት እና ወንድ ልጆችን ወለዱ፡፡አላማቸው ልጆቻቸውን እያስተማሩ፣ በአነስተኛ የኑሮ ደረጃ እየኖሩና ለአላማቸው ገንዘብ መቆጠብ ነበር፡፡የሚኖሩበት ቤት አነስተኛ ነው፡፡የሚነዱት መኪና አነስተኛ ነው፡፡ሶፋ፣ ቲቪ፣ ብራንድ ልብስ ትርኪምርኪ አላሳደዱም፡፡እኩዮቻቸው የሰሩትን ገንዘብ ሲበትኑ እነሱ ግን ቆጠቡ፡፡አንድ ቀን የቆጠቡትን ገንዘብ በፎቶው ላይ የምትመለከቱትን መኪና ቻንሲና ሞተር ከሚሰሩበት ድርጅት ገዙ፡፡
በዙርያቸው ያሉ ሰዎች <<እብድ!>> አሏቸው፡፡እውነትም እብድ ይመስላሉ፡፡እነሱ ግን መስሚያቸውን ጥጥ አድርገው ስራቸውን ገፉበት፡፡ቀስ በቀስ መኪናውን ለጉዟቸው እንዲያመች አድርገው መገንባት ጀመሩ፡፡መካኒኮች ናቸውና ምን ማድረግ እንዳለባቸው ያውቃሉ፡፡ሳሎን፣ መኝታ ቤት፣ ሻወር፣ ሽንት ቤት፣ ኩሽና፣ የጸሎት ክፍል በራሳቸውን ዲዛይን መኪናው ላይ ቀስበቀስ ሰሩ፡፡አንድ ሺ ሊተር የተጣራ ውሃ አላቸው፡፡ኧረ ምን ጎድሏቸው፡፡መኪናቸው አንድ መሠረታዊ ቤት የሚያስፈልገውን ነገር በሙሉ እንዲኖረው አደረጉ፡፡ነገር ግን ይህን ያደረጉት በአንድ ወይም በአስር አመት አይደለም፡፡ቢያንስ ሰላሳ አመትና ከዚያ በላይ ፈጅቶባቸዋል፡፡ከብዙ ልፋት እና ጥረት በኋላ ልጆቻቸው አድገው በትምህርት ተመርቀው ራሳቸውን ቻሉ፡፡እነሱም ብዙ አመት ከሰሩት ስራ ጡረታ ወጡ፡፡በየት አድርገው የት መሄድ እንደፈለጉ ካርታቸው ላይ አሰፈሩ፡፡ጣጣቸውን ጨርሰው የዛሬ ሶስት አመት አለምን መዞር ጀመሩ፡፡በጀርመን፣ በፖላንድ፣ ዩክሬን፣ ኢራቅ፣ ዱባይ፣ ጁቡቲ አድርገው ይሄው ኢትዮጵያ አርባምንጭ ከእኔ ጋር ናቸው፡፡በዚህ ሶስት አመት ውስጥ ብዙ አገር ጎብኝተዋል፡፡አንድ አገር ላይ ለስድስት ወር ይቆያሉ፡፡ምንም ነገር አያስጨንቃቸውም፡፡ስሜታቸውን ብቻ ነው የሚከተሉት፡፡ስለነገ ምንም አያስቡም፡፡የሚኖሩት ዛሬን ብቻ ነው፡፡ምንም ፍርሃት ብሎ አልፈጠረባቸውም፡፡ለምሳሌ አርባምንጭ ጫካ ውስጥ ትልቁን መኪናቸውን ይዘው ገቡ፡፡የጫካው ዝምታ ተመቻቸው፡፡ዛፎቹ ለመንፈሳቸው ሰላምን ሲለግሱ <<እዚሁ ጪካው ውስጥ እናድራለን¡>> አሉ፡፡ጥበቃዎቹ የሆነ ነገር እንዳይሆኑ ብለው በመስጋት ቢጮሁም ሰዎቹ አሻፈረኝ አሉ፡፡በዚያ ጥቅጥቅ ጫካ ውስጥ ድቅድቁን ጨለማ አሳለፉት፡፡ህይወታቸው በጣም ያስቀናል፡፡የሚበሉት ደግሞ ራሳቸው የሰሩትን ነው፡፡ከፈለጉ አርባምንጭ ሲቀላ ገበያ ጎራ ይላሉ፡፡ፍሬሽ ፍራፍሬ በርካሽ ዋጋ ይገዛሉ፡፡ጎመን፣ ድነንች፣ ሽንኩርት፣ ቲማቲም ቃርያ...ወዘተ ይገዛሉ፡፡እዛው መኪናቸው ውስጥ ይሰራሉ፡፡ባልና ሚስቶቹ አብረው እየተጫወቱ ይበላሉ፡፡<<ፍቅር አያረጅም!>> ሙዚቃ ብቻ እንዳልሆነ በህይወትም እንዳለ የሚያረጋግጡ ካፕሎች ናቸው፡፡እነሱ ጋ ለሆቴል ወይም ለሪዞርት ያልተፈለገ ወጪ ማውጣት የለም፡፡ሰው እብድ ይበላቸው እንጂ እነሱ ግን ብልጥ ናቸው፡፡ለምሳሌ መኪናቸው ያራፈው ሐይሌ ሪዞርት ነው፡፡የሚከፍሉት ለፖርኪንግ 450 ብር ብቻ ነው፡፡እዛው መኪናው ውስጥ ያድራሉ፡፡ሌላ ቱሪስት ግን ከእነሱ በብዙ እጥፍ ይቀጣል፡፡በግሌ የሰጡኝ እውቀት የከበረ ነው፡፡ለአራት ቀን ጥሩ ጎረቤታቸው ሆኜ ጥራት ያለው ጊዜ አሳልያለሁ፡፡ቁጭ ብዬ ጨዋታቸውን ሳደምጥ ብዙ ጥበብ ቃርሚያለው፡፡እሷ እንግሊዘኛ ስለማትችል ብዙ አታወራም፡፡እሱ ግን በጣም ጨዋታ ይወዳል፡፡አንድ ጊዜ ጅቢቲ የገጠማቸውን ነገር ነገሮች ስቄ ሳልጨርስ እንደገና ፖላንድ ወይም ዱባይ ስላጋጠማቸው አስተማሪ ነገር አጫውቶኝ ያስተምረኛል፡፡ለምሳሌ አንድ ጊዜ ዱባይ ውስጥ መኪናቸውን ሲያሽከረክሩ የተመለከተ የዱባይ ባለሀብት መኪናቸውን ወደደው፡፡ መኪናውን ለመግዛት 5000, 000$ [አምስት ሚሊዮን ዶላር] አቀረበላቸው፡፡
<<እና ለምን አትሸጡተም ነበር?>> አልኩኝ ተገርሜ፡፡
<<እንዴ ህልሜ እኮ ነው እንዴት እሸጣለው? አንተ ህልምልህን በስንት ብር ትሸጣለህ?>> ብሎ ጠየቀኝ፡፡
<<በምንም አልሸጥም ህይወቴ እኮ ነው!>> አልኩት፡፡
<<እኛም ያልሸጥነው ለዛ ነው፡፡ይህ ነገር ለእኔና ለሚስቴ ከምንም በላይ ነው፡፡>> አለኝ፡፡
ትዕግስት፣ ጽናት፣ አላማ፣ ድፍረት፣ እምነት ለብዙ ዘመን የሚቆይ ትዳርን መመስረት የአራት ቀን ጎረቤቶቼ ጊርድ እና ዮዳ ያስተማሩኝ ነገሮች ናቸው፡፡በተለይ በፈጣሪ ያላቸው እምነት ትልቅ ነው፡፡ምንም ቢሆን ፈጣሪ የፈቀደው ይሁን በለው የሚኖሩ ሰዎች ናቸው፡፡አንድ ቀን ተገናኝተን አውርተን ስንለያይ <<ነገም አርባምንጭ አላችሁ?>> አልኳቸው፡፡
<<ነገ ጠይቀን>> አሉኝ፡፡
<<እኛ ስለነገ አናስብም፡፡የምናስበው ስለዛሬ ብቻ ነው፡፡ጠዋት ስንነሳ ምን ማድረግ እንዳለብን እናስባለን፡፡እሱን እናደርጋለን፡፡ለምሳሌ ካንተ ጋር እንገናኛለን ብለን አላሰብንም፡፡እግዚአብሔር አገናኘን ጥሩ ጊዜ አሳለፍን፡፡ስለዚህ ሁኔታዎችን እንደ አመጣጣቸው እናስተናግዳለን፡፡በቀናችን ስሜታችንን ብቻ ነው የምንከተለው፡፡>>አሉኝ፡፡
<<ስሜታችሁን ብቻ መከተል አይጎዳችሁም? ማለት ማቀድ ማሰብ አለባችሁ? ስሜትን መከትል አንዳንድ ጊዜ አይጎዳም?>> ብዬ ጠየኩኝ፡፡
<<ድሮ ድሮ ባንተ እድሜ እያለን በጣም እናስብ እንጨነቅ ነበር፡፡የቤት ኪራይ አለብን፣ ልጆችን ማስተማር፣ ስራ መግባት፣ ማህበራዊ ህይወት ብቻ ብዙ ነገር ያስጨንቀን ነበር አሁን ግን ያንን ሁሉ ጣጣ ጨርሰን የፈለግነውን ነገር የምናደርግበት ጊዜ ላይ ነን፡፡አንተ ግን እንደኛ አትሁን፡፡ማሰብ ማቀድ መሮጥ አለብህ፡፡ወደፊት እንደኛ የምትኖርበት ዘመን ይመጣል፡፡የፈለከውን የምታደርገበት ጊዜ፡፡>> አሉኝ፡፡
<<አሁን እንደ እናንተ ስሜቴን ብቻ ብከተልስ?>>
<<አለም አናትህ ላይ የፈተና መዓት ይጥልብሃል፡፡ብዙ መፍታት ያለብህ ችግር አለብህ!>> አለኝ፡፡
<<እሺገልጆቻችሁ አይናፍቋችሁም?>> ሌላኛው ጥያቄዬ ነበር፡፡
<<ይናፍቁናል ነገር ግን ይጠይቁናል እኮ፡፡ጉዞ ከጀመርን ሁለት ጊዜ ተገናኝተናል፡፡ለምሳሌ ባለፈው ዱባይ እያለን ሊጠይቁን መጥተው ነበር፡፡ኢትዮጵያ ያለንን ቆይታ ጨርሰን ወደ ኬኒያ ናይሮቢ ስንሄድ ደግሞ ይመጣሉ፡፡እዛ እንገናኛለን>> ብለው መለሱልኝ ምርጦቹ ጎረቤቶቼ፡፡አራት ቀን ጥሩ ጊዜ አሳልፈን በአምስተኛው ቀንም ላገኛቸው ሰፍ ብዬ ስመጣ የሉም፡፡ጥበቃውን ጠየኩት፡ <<ከሲቀላ ገበያ ብዙ እቃ ገዝተው መጡ! አርባምንጭን ተሰናብተው ወጡ!>> አለኝ፡፡እግዚአብሔር ይከተላቸው፡፡በሄዱበት መልካሙን ይግጠማቸው፡፡
#ሟር
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የአርባ አመት ህልማቸውን እውን ያደረጉ ጥንዶች::
#share!
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ካስገረሙኝ ባልና ሚስቶች ጋር አደረኩትን አጠር ያለች ውይይቴን እንሆ! እንግሊዘኛ ነው ብላችሁ አትፍሩ፡፡እኛም በገገማው እንጂ #ፈርፌክት ሆነን አይደለም፡፡
ሞት የአቀናባሪ ኤሊያሰ መልካን ቤት ዛሬ አንኳኳ፡፡ኤሊያስ መልካ አረፈ! ያሳዝናል! ነፍሱን በአጸደ ገነት ያኑራት፡፡ሞት የሁላችንንም ቤት ደርሶ ማንኳኳቱ አይቀርም፡፡የቱንም ያህል ብንፈራውም አይቀርልንም፡፡ወደድንም ጠላንም እየመጣ ነው፡፡አንድ ቀን የእኛም ቤት ይንኳኳል፡፡ ሞት ይወስደናል፡፡ወደ አፈርም እንጨመራለን፡፡ያንጊዜ የአለም ህይወት ከንቱ እንደሆነ ይገባናል፡፡ሰዎች #እንንቃ! ከሞት በኋላ ያለውን ዘለዓለማዊ ህይወትንም እናስብ፡፡በጽድቅ እና በእውነት ጎዳና ለመራመድ እንትጋ፡፡በቀረችን የምድር ቆይታ መልካም ነገር እናድርግ፡፡ጥበብ እና ማስተዋሉን እንዲያድለን እንጸልይ! አሜን! #RIP
ቆይ ግን
ጠዋት በሰላም ከአልጋ ነቅቶ ማታ በሰላም ወደ አልጋ መመለስ ዋጋው ስንት ነው?
በምድር ከዚህ የሚበልጥ ውድ ነገር ምን አለ?
ታዲያ ይህን ውድ ነገር ያለክፍያ ላደረገ አምላክ ምስጋናውን የምትነሱት ለምንድን ነው?
እናንተ ደክሟችሁ ስታንቀላፉ እሱ አያንቀላፋም፡፡
በተኛችሁበት ከክፉ ነገር ሁሉ ይጠብቃችኋል፡፡
እና ይሄ ፈጣሪ ምስጋና አይገባውም ነው የምትሉት?
ግድ የለም #ተመስገን! በሉት
#ተመስገን!
ለእግር ኳስ የሚሆን ጊዜ አለህ፡፡ቢያንስ በሳምንት ለዘጠና ደቂቃ የፈረንጅ እግር ኳስ ታያለህ፡፡በሳምንት አንድ ጊዜ ቤተክርስቲያን
ለመሄድ ግን <<ጊዜ የለኝም>> ስትል ትደመጣለህ፡፡ ቀኑን ሙሉ ከፌስቡክ ጓደኞችህ የሚክላልህን ቴክስት ስታነብ አልሰለቸህም፡፡መጽሐፍ ቅዱስ ማንበብ ግን አያስደስትህም፡፡ከጓደኞችህ ጋር ተደዋውለህ ባር ወይም ካፌ በአንድነት ትዝናናለህ፡፡ልብህ እስኪወልቅ ትደሰታለህ፡፡ከጓደኞችህ ጋር በአንድነት ለመዘመር፣ ለማምለክ፣ ቅዳሳት ገዳማትን ለመጎብኘት፣ ንድህያንን ለመርዳት እና የጽድቅ ስራዎችን ለመስራት መች ታስባለህ? የምትሰራው መስርያ ቤት ደሞዙ እንዳይቆረጥብህ በጥንቃቄ ሰዓቱን
ታከብራለህ፡፡ቤተክርስቲያን ባለመሄድ ስለምታጣው ሰማያዊ ደሞዝ ግን መች ትጨነቃለህ? ለምን እግዚአብሔርን ከአለም ፍላጎቶች ሁሉ ኋላ ታስቀረዋለህ? መጽሐፍ ቅዱስ ለማንበብ፣ ለማስቀደስ፣ ለመጾም እና ለመጸለይ የሚሆን ጊዜ እንዴት ታጣለህ? እስቲ እግዚአብሔርን የሚፈራ እና በእርሱ ትዕዛዝ ብትኖር የምታጣው ነገር ምንድን ነው? ትርኪምርኪ እና ቆሻሻ ነገር ባታጣ ነው፡፡ሳይገባህ ሁሉን ነገር የሰጠህ ማን ነው? ልብህ የሚመታው፣ ሳንባህ የሚተነፍሰው፣ እግርህ የሚራመደው፣ የበላኸው ምግብ ስርዓቱን ጠብቆ የሚፈጨው፣ ደምህ የሚዘዋወረው፣ በሰላም ወጥተህ በሰላም የምትገባው እስቲ በማን ነው? ተው! ተው!የአለም ፍርፋሪን ስታሳድ ሁሉን ነገር በነጻ የሰጠህን ንጉስን አትርሳው፡፡
አለም ጋር ተጣብቀህ መንፈሳዊነትህን አትተው፡፡ምን አልባት ቤተክርስቲያን ጥንታዊ ስለሆነች ኋላቀር አድርግህ ንቀሃት ሊሆን ይችላል፡፡ምን አልባተ ፋሽን ስለማትከተል ወይም ቴክኖሎጂ ስለማትፈጥር ከስልጣኔ የራቀች መስሎህ ሊሆንም ይችላል፡፡ነገር ግን ቤተክርስቲያን አንተ ዘመናዊ ከምትለው አለም በብዙ እጥፍ
የዘመነች እና ቀድማ የተራመደች ነች፡፡ንቃ በሚያልፈው አለም አትታለል፡፡ወደ ቀደመ ቤትህ ወደ ቤተ እግዚአብሔር ተመለስ፡፡ወደ እርሷ ስትቀርብ ምን ያህል እረፍት እንደምታገኝ ታውቀዋለህ፡፡ታዲያ ለምን ደጋግመመህ እየጎበኘሃት ደስታን አታጭድም?
አትዝናና ማለት አይደለም፡፡አትጫወት፣ ሻይ ቡናም አትበል ማለትም አይደለም፡፡ሁሌ ቤተክርስቲያን ተመላለስ ማለትም አይደለም፡፡ምን አልባት በሳምንት አንድ ጊዜ ይቅርና በአመት አንድ ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን መምጣት ላይመችህ ይችላል፡፡ነገር ግን በማይመች ሁኔታ ውስጥ ለልብህ ምቾት የሚሰጠውን አምላክ አስብ ለማለት ነው፡፡ከሞት በኋላ ስላለው ህይወትም ተጨነቅ ለማለት ነው፡፡እግዚአብሔርን የሚፈራ ሰዎችን የሚያከብር መልካም ሰው ሁን ለማለት ነው፡፡ወደ ቤተክርስቲን የምንጠጋው ጥሩ፣ ታማኝ፣ ደግ፣ አገልጋይ፣ ጪ፣ ይቅር ባይ፣ ደስተኛ እና ፈጣሪን የሚፈሩ ሰዎችን ለመሆን ነው፡፡
መልካም እለተ ሰንበት!
#Share
Telegram፡ @maneshetu
Instagram፡ manyazewal eshetu
Facebook፡ Manyazewal Eshetu